ዜና፡ #አሜሪካ #የኢትዮጵያ፣ #የኤርትራ እና #የአማራ ሃይሎች በትግራዩ ጦርነት “በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል” መፈፀማቸውን ገለፀች፤ ሁሉም ሀይሎች ደግሞ “የጦር ወንጀል” ፈፅመዋል ብላለች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12/ 2015 ዓ.ም፡– አሜሪካ የ2022 አመት በአለም ላይ የታዩ የሰብአዊ መብት ጉዳዮቹን በተመለከተ በትላንትናው ዕለት ይፋ በተደረገችበት ሪፖርት የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የአማራ ሃይሎች #በትግራዩ ጦርነት “በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል” መፈፀማቸውን አስታወቀች፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በትግራይ ተጀምሮ ለሁለት አመት በዘለቀው እና ወደ አማራ እና #አፋር በተስፋፋው ጦርነት የትግራይ ሀይሎችን ጨምሮ ሁሉም ሀይሎች “የጦር ወንጀል” ፈጽመዋል ስትል ገልፃለች።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን ሪፖርቱን ይፋ ሲያደርጉ “ከነዚህ ወነጀሎች ውስጥ አብዛኛዎቹ ድንገት ወይም በጦርነት የተከሰቱ ብቻ ሳይሆኑ ታስቦ እና ሆን ተብሎ የተፈፀሙ ናቸው” ብለዋል፡፡
መስራቤታቸው ህጎችን እና እውነታውን በጥንቃቄ ካስተዋለ በኋላ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሃይሎች፣ የኤርትራ መከላከያ ሃይሎች፣ የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ሃይሎች እና የአማራ ሃይሎች በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በነበረው ጦርነት የጦር ወንጀሎችን መፈጸሙን በተመለከተ ድምዳሜ ላይ ደርሰናል ሲሉ አስታውቀዋል።
https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-አሜሪካ-የኢትዮጵያ፣-የኤርትራ-እና/?fbclid=IwAR1LwZhGPHPe2HytwPwS-W6xEzn5A4gykwUmejQEAmZd_OpndLWC-xgSHJ0

Addis Standard
ዜና፡ አሜሪካ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የአማራ ሃይሎች በትግራዩ ጦርነት “በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል” መፈፀማቸውን ገለፀች፤ ሁሉም ተፋላሚ ሀይሎች “የጦር ወንጀል” ፈፅመዋል ብላለች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12/ 2015 ዓ.ም፡– አሜሪካ የ2022 አመት በአለም ላይ የታዩ የሰብአዊ መብት ጉዳዮቹን በተመለከተ በትላንትናው ዕለት ይፋ በተደረገችበት ሪፖርት የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የአማራ ሃይሎች በትግራዩ ጦርነት “በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል” መፈፀማቸውን አስታወቀች፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በትግራይ ተጀምሮ ለሁለት አመት በዘለቀው እና ወደ አማራ እና […]
ዜና፡ ኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግስት ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ያወጣውን መግለጫ እንደማትቀበለው አስታወቀች፤ ግዜውን ያልጠበቀ፣ አባባሽ እና አግላይ ሲል ኮንኗል
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል በትግራይ ተጀምሮ ወደ አማራ እና አፋር ክልል የተዛመተውን ጦርነት አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት እንደማይቀበለው አስታወቀ።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በጦርነቱ ከፍተኛ ወንጀል ተፈጽሟል ማለቱን እንደማይቀበለው ያስታወቀው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ግዜውን ያልጠበቀ፣ አባባሽ እና አግላይ ሲል ኮንኗል። ሪፖርቱ አንድን ወገን ላይ በማነጣጠር አላግባብ የወነጀለ ነው ሲል ተችቷል።
አስገድዶ መድፈር፣ ጾታዊ ጥቃት መሰል ወንጀሎች ተፈጽመው እያለ ግልጽነት በሌለው ምክንያት የአሜሪካን መንግስት መግለጫ አንድን ወገን በተለዩ ወንጀሎች ላይ ተጠያቂ ላለማድረግ ያለመ ነው ሲል ገልጿል።
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አማራጮችን ለመለየት ብሔራዊ ምክክር ለመጀመር በተዘጋጀችበት ወቅት ላይ የወጣ በመሆኑም መግለጫው ወቅቱን ያልጠበቀ ነው ሲል ኮንኗል።
https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-ኢትዮጵያ-የአሜሪካ-መንግስት-ውጭ-ጉ/?fbclid=IwAR0oy1OuggeRt4uUS3NbPTpcYPAm5yHUozPt09sV5-zlojred3ktEaaOXRs

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12/ 2015 ዓ.ም፡– የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል በትግራይ ተጀምሮ ወደ አማራ እና አፋር ክልል የተዛመተውን ጦርነት አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት እንደማይቀበለው አስታወቀ። የአሜሪካ ውጭጉዳይ መስሪያ ቤት በጦርነቱ ከፍተኛ ወንጀል ተፈጽሟል ማለቱን እንደማይቀበለው ያስታወቀው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር […]
ሰሞኑን በሞግዚቷ የተሰረቀችው የ2 ዓመት ሕጻን ሶሊያና ዳንኤል በ #ሱሉልታ መገኘቷን ፖሊስ ገለጸ
ከቀናት በፊት በሞግዚቷ ተሰርቃ የተወሰደችው የ2 ዓመቷ ሕጻን ሶሊያና ዳንኤል ከብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር በተደረገ ክትትል በሱሉልታ ክፍለ ከተማ መገኘቷን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ሕጻን ሶሊያና ሳሪስ አዲስ ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሐሙስ መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ.ም ረፋድ ላይ ቤዛ በቀለ በተባለችው የቤት ሰራተኛቸው ተሰርቃ ስለመወሰዷ በተለያዩ ማሕበራዊ ትስስር ገፆች መረጃው ሲሰራጭ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ በሕጻኗ ወላጆች የቀረበለትን አቤቱታ ተቀብሎ ከብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀትና ወደተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞችና አካባቢዎች በመሄድ ጭምር አስፈላጊ መረጃዎችን በማሰባሰብ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል፡፡
በዚህም ቤዛ በቀለ ዛሬ ሱሉልታ ክፍለ ከተማ ወሰርቢ ወረዳ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ሕጻን ሶሊያና ዳንኤልን ደብቃ በተቀመጠችበት በቁጥጥር ስር መዋሏን ነው ፖሊስ ያሳወቀው፡፡
ተጠርጣሪዋ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላ፥ 40 ሺህ ብር ይከፈልሻል ብለው ሰዎች ስላግባቧት ህፃኗን ሰርቃ መሰወሯን ተናራለች፡፡
በወንጀሉ ላይ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ምርመራው መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ገልጿል፡፡
ኤፍ ቢ ሲ

ዜና፡ #የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ብፁዕ አቡነ #አረጋዊ (ዶ/ር) ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13/ 2015 ዓ.ም - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ #ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋ እና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተገለጸ። ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ ዕድ ከሾሙት ጳጳሳት 14 ኤጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ እንደነበሩ ተጠቁሟል።
ብፁዕነታቸው ለረጅም ጊዜ ከሀገር ውጪና በሀገር ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቢቆዩም ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለይተዋል ሲሉ #የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል።

ዜና፡ #የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት #ህወሓትን ከሽብርተኝነት ዝርዝር አነሳ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13/ 2015 ዓ.ም - የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአብላጫ ድምጽ ህወሓትን ከሽብርተኝነት ዝርዝር ማንሳቱ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ #የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሓትን #ከኦነግ ሽኔ (የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ የሚገኘውን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን መንግስት የሰጠው ስያሜ) ጋር በሽብርተኝነት የፈረጃቸው ከሁለት አመታት በፊት ሚያዚያ ወር ላይ ነበር።
በተመሳሳይ በፓርቲው ሊቀመንበር ስም በሚጠራ መዝገብ አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የፌደራል አቃቤ ህግ 62 የሚሆኑ የቀድሞ እና በስልጣን ላይ ያሉ የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የሽብር ክስ መመስረቱ ይታወሳል። ህወሓት ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲነሳ የተደረገው የሰላም ስምምነቱ ይበልጥ መተማመን እንዲፈጥር ለማስቻል መሆኑ ተጠቁሟል።
አለማቀፉ ማህበረሰብ በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ለማስቻል በሚል ህወሓት ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲያነሳ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ እንደነበር ይታወሳል።
https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-የኢትዮጵያ-ህዝብ-ተወካዮች-ምክር-ቤ/?fbclid=IwAR2evKu-O3uUW-sz7-gBZ6AxEnv5-E3ttBM_iPeTAwpO0zqEZsfQUPss4ZM

ዜና፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሓትን ከሽብርተኝነት ዝርዝር አነሳ
ፎቶ ከፋይል አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13/ 2015 ዓ.ም - የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአብላጫ ድምጽ ህወሓትን ከሽብርተኝነት ዝርዝር ማንሳቱ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሓትን ከኦነግ ሽኔ (የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ የሚገኘውን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን መንግስት የሰጠው ስያሜ) ጋር በሽብርተኝነት […]
ዜና፡ #የትግራይ የጦር ጉዳተኞች #በመቀሌ በሰላማዊ ሰልፍ ያቀረቡት ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር ዕጩ ፕሬዝዳንት አቶ #ጌታቸው ረዳ ቃል መግባታቸው ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13/ 2015 ዓ.ም – አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር ዕጩ #ፕሬዝዳንት የትግራይ ሰራዊት የጦር ጉዳተኞች የጠየቁት ጥያቄ አግባብነት ያለው የመብት ጥያቄ በመሆኑ ትኩረት እንደሚሰጠው አስታወቁ።
በትላንትናው እለት መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ የትግራይ የጦር ጉዳተኞች ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸው ይታወቃል። የክልሉ ህዝብ ባለፉት ሁለት አመታት #ከፌደራል መንግስቱ ጋር ባካሄደው ጦርነት ለአካል ጉዳት የተዳረጉ እና የቆሰሉ ተዋጊዎች በመቀለ ከተማ ባካሄዱት ሰልፍ ተርበናል የሚል መፎክሮችን ሲያሰሙ ተደምጠዋል። ምግብ እና መድሃኒት እንዲቀርብላቸውም ጠይቀዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ የሰጡት አቶ ጌታቸው ረዳ አካል ጉዳተኞቹ የጠየቁት ወሳኝ ጥያቄ #የምግብ፣ #ንጽህና እና #የህክምና አቅርቦት መሆናቸውን አስታውቀው ጉዳዩ ሊመረመር እና አትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በመቀለ ከተማ ኩይሃ መለስ ካምፓስ እና ደጀን ሆስፒታል የሰሜን እዝ ካምፕ በሚባሉ ሁለት ወታደራዊ ሰፈሮች ተጠልለው የሚገኙት የጦር ጉዳተኞቹ በተጨማሪም በጦርነቱ ህይወታቸውን ለገበሩ ታጋይ ቤተሰቦች ካሳ እንዲከፈላቸው እና ክብር እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-የትግራይ-የጦር-ጉዳተኞች-በመቀሌ-በ/?fbclid=IwAR2aIt9CDUpnOnV5ne_PDJ4ZznHXLD1hz-x818_Y2gCQK4hY6d5nY7FbcFg

ዜና፡ የትግራይ የጦር ጉዳተኞች በመቀሌ በሰላማዊ ሰልፍ ያቀረቡት ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር ዕጩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ቃል መግባታቸው ተገለጸ
foto from social media አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13/ 2015 ዓ.ም - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር ዕጩ ፕሬዝዳንት የትግራይ ሰራዊት የጦር ጉዳተኞች የጠየቁት ጥያቄ አግባብነት ያለው የመብት ጥያቄ በመሆኑ ትኩረት እንደሚሰጠው አስታወቁ። በትላንትናው እለት መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ የትግራይ የጦር ጉዳተኞች […]
ዜና፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አድረገው ሾሙ
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቶ ጌታቸው ረዳን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳደር አድርገው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት አስታወቀ፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት መጋቢት 9 ቀን 2015 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ “የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር ደንብን ማጽደቁ ተመላክቷል ያለው መግለጫው በዚሁ ደንብ አንቀጽ 3(2) መሰረት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቶ ጌታቸው ረዳን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳደር አድርገው መሾማቸውን አስታውቋል፡፡
ርዕሰ መስተዳደሩ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ሃይሎችን ውክልና የሚያረጋገጥ እና አካታች የሆነ አስተዳደር በማዋቀር የክልሉን አስፈጻሚ አካል የመምራት እና የማስተባበር ሃላፊነት እንደተጣለባቸውም መግለጫው አክሎ ገልጧል።
https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-ጠቅላይ-ሚኒስትር-ዐቢይ-አህመድ-አቶ/?fbclid=IwAR0Ic3mJITxuFI3NYC9CUC14XgLkzDDN8Iwi9LsQPuS8bFReZnw52km-ECo

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2015 ዓ.ም፡- የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቶ ጌታቸው ረዳን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳደር አድርገው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት አስታወቀ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ የኢፌዴሪ የፌዴሬሸን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62 (9) እና በአዋጅ […]
ዜና፡ #የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት #ህወሓትን ከሽብርተኝነት በመሰረዙ ለጊዜያዊ አስተዳደር ፈጥኖ መመስረትና ስራውን ማከናወን ወሳኝ ነው: ዶ/ር #ደብረፂዮን ገብረሚካኤል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14/ 2015 ዓ.ም – የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሓትን ከሽብርተኝነት መሰረዝ ጊዜያዊ አስተዳደር ፈጥኖ ስራውን ማከናው እንዲችል ወሳኝ መሆኑ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ገለጹ።
ሊቀመንበሩ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን ትናንት በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በደቡብ አፍሪካ #ፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት ህወሓት ከሽብርተኝነት ከተነሳ በኋላ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ጊዜያዊ አስተዳደር እንደሚቋቋም ተደንግጓል በዚህም ሠሰረት ዛሬ ድርጅታችን ህወሓት ከሽብርተኝነት ዝርዝር በመሰረዙ ግዜያዊ አስተዳደራችን ስራ የሚጀምርበት፣ ሁኔታዎች ተሟልቷል ብለዋል።
በፌደራል መንግስቱ እና በጊዜያዊ አስተዳደሩ መካከል በጀት በማዘጋጀት፣ የወንጀል ክሶች መነሳት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እና ግንኙነት መጀመሩንም ዶ/ር ደብረጺዮን ተናግረዋል።
በአቶ #ጌታቸው ረዳ የሚመራ ጊዜያዊ አስተዳደራችን የተለማቸው ግቦቹ እንዲሳኩ በእኛ ወገን ሁሉንም አቅማችንን በማስተሳሰር እንረባረባለን ያሉት ዶ/ር ደብረፂዮን ሁሉም የትግራይ አቅም ጊዜያዊ አስተዳደሩን ለመደገፍ እንዲነሳ ጥሪ አቅርበዋል።
የጊዜያዊ አስተዳደሩን አወቃቀር በተመለከተም ከሰራዊቱ እና ከሙሁራን በተጨማሪ አሁን ባለው ሁኔታ በግዜያዊ አስተዳደሩ የተካተቱ ፓርቲዎች ህወሓት እና ባይቶና መሆናቸውን አስታውቀዋል።
https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-የሕዝብ-ተወካዮች-ምክር-ቤት-ህወሓት/?fbclid=IwAR0O43jLfmcRM8cJwfIaFImXKELogb-Qemi1Vx9cBzTTvwK36VAyEQ8V3Po

ዜና፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሓትን ከሽብርተኝነት በመሰረዙ ለጊዜያዊ አስተዳደር ፈጥኖ መመስረትና ስራውን ማከናወን ወሳኝ ነው: ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል
ፎቶ ከፋይል አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14/ 2015 ዓ.ም - የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሓትን ከሽብርተኝነት መሰረዝ ጊዜያዊ አስተዳደር ፈጥኖ ስራውን ማከናው እንዲችል ወሳኝ መሆኑ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ገለጹ። ሊቀመንበሩ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን ትናንት በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶርያ […]
ከአንዲት ግብር ከፋይ ግለሰብ 70 ሺህ ብር ጉቦ የተቀበለ የገቢዎች ባለሙያ እጅ ከፍንጅ ተያዘ
ሐሰተኛ ሰነድ አቅርበሻል በማለት ከአንዲት ግብር ከፋይ ግለሰብ 70 ሺህ ብር ጉቦ የተቀበለ የገቢዎች ባለሙያ እጅ ከፍንጅ ተያዘ፡፡
ሐሰተኛ ሰነድ አቅርበሻል በማለት ከአንዲት ግብር ከፋይ ግለሰብ 70 ሺህ ብር ጉቦ የተቀበለ የገቢዎች ባለሙያን እጅ ከፍንጅ መያዙን እና በወንጀሉ ተባባሪ የሆነ አንድ ባለሙያን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
በ #ቂርቆስ ክ/ከተማ የአነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርጫፍ ጽ/ቤት የአወሳሰን ባለሙያ የሆነው አንድ ሠራተኛ የቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር ከፋይ የሆኑ ግለሰብን ካቀረብሽው 10 ደረሰኞች መካከል 8ቱ የተበላሹ በመሆኑ ወደ አጣሪ ኮሚቴ መላኩን እና ሁለቱ ደግሞ እጄ ላይ ይገኛሉ በማለት ጉዳዩን ለማዳፈን ግን 100 ሺህ ብር ጉቦ እንዲሰጠው ይጠይቃል።
የግል ተበዳይ ያቀረቧቸው ሰነዶች ትክክለኛ እንደሆኑ ለማስረዳት ቢሞክሩም ባለሙያው ሳይቀበላቸው ይቀራል።
የአወሳሰን ባለሙያ የሆነው ይህው ግለሰብ በቢሮ ስልክ ደጋግሞ በመደወል የግል ተበዳይን በማስጨነቅ በሕግ እንደሚጠየቁ በማስፈራራት 70 ሺህ ብር ለመቀበል ይስማማል።
የግል ተበዳይ ጉዳዩን ለተቋሙ ኃላፊዎች በማሳወቅ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የደንበል አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ባደረገው ክትትል በቅርጫፍ ፅ/ቤቱ የአወሳሳን ባለሙያ የሆነው ሙያተኛ 22 አካባቢ ከሚገኘው መስቲ ሬስቶራንት አካባቢ መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ገንዘቡን ሲቀበል እጅ ከፍንጅ መያዙን እና ...
https://www.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid02tPFECFCriyAnZkf3aJvvCmEKXDzTFJtfizAPJmkqy4rvASWUBuDavgzzbkA7ct92l

ቃለ-ምልልስ፡ “መንግስት ለውይይት በሩን መክፈት፣የሰራተኞችን ጥያቄ መመለስ እንደዚሁም የስራ ታክስን መቀነስ አለበት”- አቶ ካሳሁን ፎሎ የኢሰማኮ ፕሬዚዳንት
ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ገፅታ እየተቀየረ መምጣቲ ያደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ብዙ የኢንዱስትሪዎች እና የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች በመስፋፋታቸው ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሰዎች የስራ እድል ተጠቃሚ ቢሆኑም በሰራተኞች አያያዝና መብት ዙሪያ የሚነሱ በርካታ ችግሮች መኖራቸው ግን እሙን ነው፡፡ ሠራተኞቹ በርካታ ቅሬታዎችን ያነሳሉ። በዋናነት በአሀሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ለሁለት ዓመታት የተካሄደው ደም አፋሳሽ ጦርነት ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልል የሚገኙ ሰራተኞች የከፋ ችግር ላይ ወድቀዋል። በኤጄንሲዎች አማክኝነት በተለያዩ ተቋማት የሚቀጠሩ ሰራተኞችም የጉልበት ብዝበዛ ሰለባ ሆነዋል፡፡ ለሚሰሩት ስራ ተመጣጣኝ ክፊያ እያገኙ እንዳልሆነ ይናገራሉ፡፡
የአዲስ ስታንዳርዱ ሞላ ምትኩ እነዚህን እና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችን በመያዝ ከአቶ ካሳሁን ፎሎ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ጋር ቆይታ አድረጓል፡፡ ሙሉ ቃለምልልሱን እንዲያነቡት ጋበዝን፡፡
https://amharic.addisstandard.com/ቃለ-ምልልስ፡-መንግስት-ለውይይት-በሩን-መ/?fbclid=IwAR1lacLsdtSjhND07wfRSHHsEo43uK4y-dr9yzc0Zh6RPUyJIracf9NsSpQ

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ ፎቶ_ ከክምችት በሞላ ምትኩ @MollaAyenew ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ገፅታ እየተቀየረ መምጣቲ ያደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ብዙ የኢንዱስትሪዎች እና የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች በመስፋፋታቸው ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሰዎች የስራ እድል ተጠቃሚ ቢሆኑም በሰራተኞች አያያዝና መብት ዙሪያ የሚነሱ…
የ #ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከዶንኪ ቲዮብ ኢንተርቴይመንት ጋር በመተባበር ለ #ቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች እያሰባሰበ ባለው ልገሳ ወደ 8 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ልገሣ ያሰባሰበ መሆኑን ገለፀ
ማህበሩ ያሰባሰበውን ብር 8,756,679.00 የሚያወጣ 1,000 ኩንታል ዱቄት እና 6,665 ሊትር ዘይት በ3 ወረዳዎች ለተጎዱ ወገኖች አጓጉዟል፡፡
የኢትዮጲያ ቀይ መስቀል ማህበር ሰራተኞችም በቦታው በመገኘት በ #አሬሮ ወረዳ ለሚገኙ 453 አባወራዎች 340 ኩንታል ዱቄትና 2260 ሊትር ዘይት አከፋፍለዋል፡፡
#ኢልዋዩ ወረዳ ላሉ 440 አባወራዎችም 330 ዱቄትና 2200 ሊትር ዘይት የተከፋፈለ ሲሆን ቀሪው ለዋቺሌ ወረዳ እየተጓጓዘ መገኘቱን የኢትዮጲያ ቀይ መስቀል ማህበር የሀብት ማሰባሰብ ክፍል ሀላፊ አቶ አህመድ ይማም በላኩት የፁሁፍ መልእክት ገልጸዋል።

ጥልቅ-ትንታኔ፡ የኢትዮጵያ መንግስት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት መርማሪ ቡድን እሰጣገባ፤ ፍራቻ የተላበሰ የፖለቲካ ውሳኔ ወይስ ሉአላዊነት ?
በሚሊዮን በየነ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ያቋቋመው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መርማሪ ኮሚሽን በምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ሪፖርት አቅርቧል። በቀረበው ሪፖርት ላይ ተመርኩዘው አባል ሀገራቱ የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል። ምክር ቤቱ መርማሪ ኮሚሽኑን ካቋቋመበት ግዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው እና ምንም አይነት ድጋፍ እንደማታደርግለት ስትገልጽ ቆይታለች፤ ለፖለቲካዊ ጥቅም ሲባል የተቋቋመ ነው በሚል ተችታዋለች።
የህግ ባለሞያ እና የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ኃላፊ አቶ ያሬድ ኃ/ማሪያም አለም አቀፍ መርማሪ ቡድን የተፈጸሙ ወንጀሎችን እንዲመረምር መፍቀድ አጥፊዎች በመንግስት በኩልም ይሁን ማንም በየትኛውም የአለም ክፍል በተለይም በከፍተኛ የፍርድ ሂደቶች የመታየት እድሉን ከፍ ስለሚያደርገው ይመስለኛል እንዲመረምር የኢትዮጵያ መንግስት ፍላጎት የሌለው ሲሉ አስተያየታቸውን አጋርተውናል።
መንግስት በሚከተለው የሽግግር ፍትህ ዙሪያ የጠየቅናቸው አቶ የማነ ዘርአይ ፍትህ ሲባል #ተጠያቂነት ብቻ ተደርጎ መወሰድ የለበትም ሲሉ አመላክተው የፍትህ የመጀመሪያ ደረጃው "#ሃቅን መለየት ነው፤ ቀጥሎ #ይቅርታ ነው፣ ቀጥሎ #እርቅ ነው፣ ቀጥሎ #ካሳ ነው" ሲሉ አብራርተዋል። የሽግግር ፍትህ በጣም ያስፈልገናል ያሉት አቶ የማነ የሽግግር ፍትህን ለማምጣት ግን ዋነኛው ተግባር እውነቱን ማውጣት ነው፤ እውነት እንዲወጣ ደግሞ ገለልተኛ ምርምራ ያስፈልጋል ሲሉ ጠቁመዋል። እውነቱ እንዲወጣ እራሳችን እንደምንጥረው ሁሉ ሌሎች ሲመጡ ደግሞ ይግቡ ያግዙን ከማለት ይልቅ መከልከል አይገባም ብለዋል።
የተፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት ከፍተኛ በመሆኑ አጣሪ ኮሚሽኑ ያስፈልጋል የሚል ሙሉ እምነት አለኝ የሚሉት አቶ ያሬድ መንግስት ከዚህ በፊት ለመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በፈቀደበት መንገድ ማለትም በጋራ ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጋር እንዲሰራ መፍቀድ የተሻለ ይሆናል ነው ሲሉ እንደአማራጭ አቅርበዋል። ከፍተኛ ልምድ ያለው በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቅ መርማሪ የተፈጸሙትን ወንጀሎች ቢያጣራ እንደ ሀገርም ጠቀሜታው ትልቅ ነው ብለዋል። ተባባሪ ፕሮፌሰር የማነ ዘርአይ በዚህ አይስማሙም፡፡
https://amharic.addisstandard.com/ጥልቅ-ትንታኔ፡-የኢትዮጵያ-መንግስት-እና/?fbclid=IwAR0SO5gzM_lBCvk0wGI26J9kVaNFLdH2uvhmw5ss2HIiryryblZABLpUJTI

በሚሊዮን በየነ @MillionBeyene አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15/ 2015 ዓ.ም፡- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ያቋቋመው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መርማሪ ኮሚሽን በምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ሪፖርት አቅርቧል። በቀረበው ሪፖርት ላይ ተመርኩዘው አባል ሀገራቱ የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል። ምክር ቤቱ መርማሪ ኮሚሽኑን ካቋቋመበት ግዜ […]
በሽሮና በርበሬ ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ ደብቆ ወደ ወደ #እንግሊዝ ለመላክ የሞከረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የ #አዲስአበባ ፖሊስ ገለፀ
ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው በ #አዲስ_ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው #መርካቶ #ጣና የገበያ ማዕከል አካባቢ በሚገኝ ፖስታ ቤት ውስጥ ነው።
የአዲስ አበባ ፖሊስ እንደዘገበው ከሆነ፣ ተጠርጣሪው ማንም ሰው በማይገምትበት ሁኔታ ካናቢስ የተባለውን አደንዛዥ ዕፅ በሽሮና በርበሬ ውስጥ ደብቆ በካርቶንና በፌስታል በማሸግ ወደ #እንግሊዝ #ለንደን በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ለመላክ ሙከራ ሲያደርግ በፖስታ አገልግሎት ቅርንጫፍ ሰራተኞቹ የተጠናከረ ፍተሻ ሊታወቅ መቻሉንና ፖሊስ በፍጥነት ወደ ስፍራው በመሄድ ግለሰቡን ከነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ መጀመሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
የፖስታ ቤቱ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ጠንካራ ፍተሻ ማድረጋቸው እንዲሁም መረጃውን በፍጥነት ለፖሊስ መስጠታቸው አበረታች ተግባር መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል፡፡
"አደንዛዥ ዕፅን ማዘዋወር በሰዎች ላይ ከሚያሳድረው ጉዳት ባሻገር በተለይ ዕፅን ወደ ውጪ ሀገር የመላክ ህገ-ወጥ ተግባር በሀገር ገፅታ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድር በመሆኑ ወንጀሉን ለመከላከል እየተከናወነ ያለው ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል" የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡