Addis Standard Amharic – Telegram
Addis Standard Amharic
18K subscribers
4.66K photos
121 videos
3 files
3.71K links
አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Download Telegram
ዜና፡ #ለሱዳን ቀውስ እልባት ለማስገኘት #በአዲስ አበባ የኢጋድ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ይገኛል፤ #ኤርትራ እንደማትሳተፍ ተገልጿል፤ ተመሳሳይ ጉባኤ #ካይሮ በተናጠል አዘጋጅታለች

በሱዳን የተከሰተውን ቀውስ በዲፕሎማሲ ለመፍታት በአዲስ አበባ የኢጋድ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በጉባኤው ላይ ኤርትራ እንደማትሳተፍ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ገልጸውልኛል ሲሉ የሱዳን ላዕለዋይ ምክር ቤት ምክትል ማሊክ #አጋር መናገራቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ድረገጽ ዘግቧል። የሱዳንን ግጭት ለመፍታት በአለም አቀፍም ይሁን በቀጠናው ሀገራት በኩል የሚቀርቡ ጥረቶች የፖለቲካ #ባዛሮች በመሆናቸው ኤርትራ በባዛሩ የመሳተፍ ፍላጎት የላትም ሲሉ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ነግረውኛል ሲሉ ማሊክ አጋር መናገራቸውን ዘገባው አመላክቷል።

በሌላ ዜና በሳምንቱ አጋማሽ ተመሳሳይ ጉባኤ #ካይሮ በተናጠል ማዘጋጀቷን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል።
https://rb.gy/8i8zk
ዜና፡ #በትግራይ ጉብኝት እያካሄዱ የሚገኙት አቡነ #ማትያስ ከክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ጋር ተገናኙ፤ ግዜያዊ አስተዳደሩ በቤተክርስቲያኗ ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ አቶ #ጌታቸው ገልጸዋል

በትግራይ ጉብኝት እያካሄዱ የሚገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ተገለጸ።

ግዜያዊ አስተዳደሩ በቤተክርስቲያኗ ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ አቶ ጌታቸው ረዳ እንደገለጹላቸው ከትግራይ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በትግራይ ክልል የሚገኙ አባቶች በምን ምክንያት በውይይቱ እንዳልተገኙ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸው የሆነ ሁኖ ግን መወያየት ጥሩ ነበረ፤ በመወያየት ሀሳብን መግለጽ ይቻላል፣ የደረሰውን ችግር መግለጹ ማስረዳቱ አንድ ቁምነገር ነው፤ ይሁንም አይሁንም ለማለት ውይይት ጥሩ ነበረ፤ የሆነ ሁኖ ከብጹአን አባቶች ጋር አልተገናኘንም ሲሉ ተደምጠዋል። ለወደፊቱ ለመገናኘት ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

በትግራይ ከሚገኙ የቤተክርስቲያን አባቶች ጋር መወያየታቸውን በመድረኩ ላይ ያስታወቁት አቶ ጌታቸው እነሱን የማስገደድ ሃላፊነትም ስለጣንም ፍላጎቱም የለኝም ሲሉ ገልጸዋል።

https://rb.gy/sxh54
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚቀጥሉት 6 ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ እንዲሁም ተከራይ ማስወጣት የማይቻል መሆኑን አሳውቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የኑሮ ውድነቱ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ የቤት ኪራይ ጭማሪ እንዳይደረግ በተለያዩ ተከታታይ ጊዜያት ውሳኔ ማሳለፉን አስተዳደሩ አስታውሷል፡፡

በቀጣይም በግል ከሚደረግ ስምምነት ውጪ ማንኛውም አከራይ ለሚቀጥሉት 6 ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ እንዲሁም ተከራይ ማስወጣት የማይቻል መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ገልጿል።
ዜና፡ የሱዳን ተቀናቃኝ ሀይሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈርሙ ኢጋድ ጠየቀ፤ የአባል ሀገራቱ ወታደሮችን በሱዳን ለማስፈርም ታስቧል

አዲስ አበባ በተካሄደው ስለሱዳን ጉዳይ በመከረው የኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ የሱዳን ተቀናቃኝ ሀይሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈርሙ ተጠየቀ። ኢጋድ ትላንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ሁለቱም ሀይሎች ውጊያቸውን እንዲያቆሙና ባፋጣኝ የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲፈጽሙ ጠይቋል።

በተመሳሳይ ኢጋድ በሱዳን የአባል ሀገራቱ ወታደሮች ወደ ሱዳን እንዲገቡ እና ንጹሃንን እንዲታደጉ ለማድረግ ሃሳብ ማቅረቡን ዘገባዎች አመላክተዋል። የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል ወደ ሱዳን እንዲገባ እና የሰብአዊ አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ እንዲቻል የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ተሰብስበው እንዲወስኑ ለማድረግ በአዲስ አበባ በተካሄደው ጉባኤ ላይ ከስምምነት መደረሱን ዘገባዎቹ አስታውቀዋል።

የሱዳን ወታደራዊ ሀይሎች በጉባኤው ላይ ባለመሳተፋቸው የተሰማውን ቅሬታ ኢጋድ በትላንትና መግለጫው አመላክቷል።

በሌላ ዜና የሱዳኑ ዳባንጋ ሬዲዮ ባሰራጨው ዘገባ ከኢጋዱ የአዲስ አበባ ጉባኤ ቀደም ብሎ ባሳለፍነው ሳምንት መገባደጃ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሱዳን የሲቪል ፖለቲካ ሀይሎች ልዑካንን ተቀብለው ማነጋገራቸውን አስታውቋል።

https://rb.gy/qo2oi
በ2015 በጀት ዓመት 100 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 107 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡

ከንቲባዋ በተሰበሰበው በገት በርካታ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ገንብተናል ብለዋል፡፡

በ2016 በጀት ዓመት 140.29 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅደናል ያሉት ከንቲባዋ ይሄንን እቅድ ለማሳካት ግብር ከፋዮቻችንን ማበረታታት ተገቢ በመሆኑም ዛሬ የ2016 በጀት ዓመት ገቢ የማሰባሰብ ንቅናቄን አስጀምረናል ሲሉ ገልፀዋል።

የሰበሰብነውን ገንዘብ መልሰን ለዘላቂ ልማት፣ ለስራ ዕድል ፈጠራ፣ የከተማዋን ገጽታ ለመቀየር እንዲሁም የንግድ እንቅስቃሴውን በማነቃቃት የላቀ ሚና ለሚጫወቱ ፕሮጀክቶች በማዋልና የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል በታማኝነት እንሰራለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
ዜና፡ አንድ እስራኤላዊ በጎንደር መታገቱን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5/2015 ዓ.ም፡- በዜግነት እስራኤላዊ የሆነ አንድ ግለሰብ በሰሜን ኢትዮጵያ በአማራ ክልል በጎንደር ታግቶብኛል ሲል የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቀ። እስራኤላዊው የታገተው ማስለቀቂያ ገንዘብ በፈለጉ ሀይሎች መሆኑም ተጠቁሟል።

ታጋቹን እስራኤላዊ ለማስለቀቅ ዲፕሎማቶች ከአከባቢው የጸጥታ ሀይሎች እና ከኢንተርፖል ጋር በመቀናጀት እየሰሩ እንደሚገኙ መስሪያ ቤቱ ገልጿል። ታጋቹ እስራኤላዊ እድሜ በ70ዎቹ መሆኑን የጠቀሙት ዘገባዎች ወደ ጎንደር ያቀናው ከቀናት በፊት መሆኑን አስታውቀዋል።

ከአጋቾቹ ጋር ኢንተርፖል እና የአከባቢው የጸጥታ ሀይሎች ግንኙነት ለማድረግ መሞከራቸውን እና በወቅቱም ማስለቀቂያ ገንዘብ መጠየቃቸውነ ዘገባዎቹ ጠቁመዋል። ለማስለቀቅ የተጠየቀው ገንዘብ በመጀመሪያ በሚሊዮኖች እንደነበረ አና ቆየት ብሎ በተደረገ ውይይት ወደ ሺዎች መውረዱን የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች አመላክተዋል። ታጋቹ እስራኤላዊ በድምጽ ለቤተሰቦቹ በላከው መልዕክት እርዱኝ፣ በጫካ መሃል ላይ እገኛለሁ ማለቱን ያስነበቡት ዘገባዎቹ ዝናብ እየዘነበብኝ ነው እርዱኝ፤ እሁድ ዕለት መምጣት ነበረብኝ ግን መቆየቴ አይቀርም ይመስላል፤ ልጆቼ እርዱኝ፣ አሁን ያለሁበት ሁኔታን ለጠላቶቼም አልመኘውም ሲሉ እንደሚደመጡ አስታውቀዋል።

https://rb.gy/q2vgi
የጎፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ በ99 የፖሊስ አመራርና አባላት ላይ ከቀላል እስከ ከባድ የዲሲፕሊን እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ

በደቡብ ክልል የጎፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ በፖሊስ አመራር እና አባላት ላይ ሲያካሂድ በነበረው የግምገማ መድረክ፣ ከ96 በላይ የፖሊስ ማኔጅመንት እና አባላት ላይ ከቀላል እስከ ከባድ የዲሲፕሊን እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

በፖሊስ አመራር እና አባላት ዘንድ የሚታዩ የአመለካከት፣ የአሰራር፣ የአመራር እና የሥነ-ምግባር ግድፈቶችን በማረም ለህብረተሰቡ ወቅቱን የሚመጥን አገልግሎት ማበርከት የሚያስችል የግምገማ ሰነድ በማዘጋጀት ወደ ግምገማ ሂደት እንደተገባ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኢንስፔክተር ታረቀኝ አጥናፉ ተናግረዋል።

በመሆኑም የጎፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ በዞኑ ስር በሚገኙ በሁሉም ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደር የፖሊስ መዋቅር ሲያከናውን የነበረውን ዞናዊ የግምገማ መድረክ ሲያጠቃልል 70 የፖሊስ አባላት የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ፤ 20 የፖሊስ አባላት ደግሞ ከኃላፊነታቸዉ እንዲነሱ የተወሰነ ሲሆን 6 የፖሊስ አባላት በዲስፕሊን እንዲጠየቁና 3 የፖሊስ አባላት ደግሞ ከሥራ ታግደው በህግ መጠየቅ አለባቸው እንዳለባቸው መባሉን ከደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ሐረር ከተማ የዓለም የቅርስ ከተሞች አባል ሆነች

ሐረር ከተማ ከሰሃራ በታች ካሉ ከተሞች የመጀመሪያዋ የዓለም ቅርስ ከተሞች ድርጅት አባል ከተማ ሆና ተመዘገበች፡፡

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መተዳድር ኦርዲን በድሪ በካናዳ ኩቢክ ከተማ ሐረር የዓለም የቅርስ ከተሞች አባል ሆና የተመዘገበችበትን ፊርማ አኑረዋል።

ሐረር ከተማ 115 ሀገራትን በአባልነት በያዘው የቅርስ ከተሞች ድርጅት ውስጥ የተመዘገበችው ከፈረንጆቹ ሰኔ ወር 2023 ጀምሮ ነው።

ሐረር ከቅርስ ከተሞች መካከል አንዷ ሆና መመዝገቧ በተማዋ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶችን ለማልማት እና ለቱሪዝም ዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡

የቅርስ ከተሞች በጋራ ጉዳዮቻቸው ተመካክረው አቅጣጫ በማስቀመጥ ተግዳሮቶችን ለመሻገርና እድሎችን ለማስፋት ይጠቅማል መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

ሐረር ከተማ የጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስን ጨምሮ በተባበሩት መንግስት የሳይንስ፣ የትምህርትና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) የተመዘገቡ ዓለም አቀፍ ቅርሶች መገኛ ከተማ መሆኗ ይታወቃል፡፡

በተጨማሪም ከተማዋ ዜጎች በሰላም፣ በመቻቻልና በአብሮነት የሚኖሩባት ከተማ በሚል ዩኔስኮ እውቅና እንደተሰጣት ይታወሳል።

ኤፍቢሲ
ዜና፡ #የአፍሪካ ህብረት #በትግራይ የተፈጸሙ ጥሰቶችን ምርመራ ግልጽ ባልሆነ መንገድ አቆመ፤ ህብረቱ በድረገጹ በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ የሚሰጠውን ገጽ አስወግዶታል

የአፍሪካ ህብረት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ የተፈጸሙ ጥሰቶችን እንዲመርመር ያቋቋመውን ኮሚሽን ይፋዊ ባልሆነ መንገድ እንዲቆም ማድረጉ ተገለጸ። በኢትዮጵያ ለሁለት አመታት የታካሄደውን ጦርነት ተከትሎ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን ለመመርመር የተቋቋመ የመጀመሪያው ኮሚሽን መሆኑ ይታወሳል።

ምርመራው እንዲቋረጥ ከማድረጉ በተጨማሪ የህብረቱ ኮሚሽን በድረገጹ የነበረውን እና በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ የሚሰጠውን ገጽ እንዳስወገደው ታውቋል።

ህብረቱ በትግራይ ሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ምርመራ እንዲያካሂድ ያቋቋመውን ኮሚሽን ስልጣኑ እንዲያበቃ እና የሚያካሂደው ምርመራ እንዲቋረጥ ውሳኔ ያሳለፈው ከአንድ ወር በፊት መሆኑም ተጠቁሟል። ኮሚሽኑ ከተቋቋመ ጀምሮ ይፋ ያደረገው #ሪፖርት የለም። https://rb.gy/176l5
ዜና፡ #በትግራይ የሚገኙ የኦርቶዶክስ አባቶች በሳምንቱ መጨረሻ #በአክሱም ጽዮን የጳጳሳት ሹመት እንደሚያካሂዱ ገለፁ

በትግራይ ክልል የሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት አባቶች በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ.ም በአክሱም ጽዮን የአዳዲስ ጳጳሳት ሹመት እንደሚያካሂዱ ገለፁ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ እና በትግራይ ክልል በሚገኙ የእምነቱ አባቶች በመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መካከል የተፈጠረው ልዩነት ባልተፈታበት ሁኔታ የትግራይ አባቶች ሹመቱን ለማካሄድ መወሰናቸውን ለመገናኛ ብዙሃን በላኩት ደብዳቤ አስታውቀዋል። የሚዲያ ሽፋን በጠየቁበት ደብዳቤ እንደተመላከተው በእለቱ የአስር ጳጳሳት ሹመት እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።

በሳምንቱ መጀመሪያ ቀናት በትግራይ ጉብኝት ያካሄዱት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ #ማትያስ በክልሉ ጉብኝት ቢያካሂዱም በክልሉ ከሚገኙ የቤተክርስቲያኗ ብጹአን አባቶች ጋር ተገናኝተው አለመምከራቸው ይታወሳል። አቡነ ማትያስ በመቀሌው ጉብኝታቸው ከክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ግዜያዊ አስተዳደሩ በቤተክርስቲያኗ ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ አቶ #ጌታቸው ረዳ እንደገለጹላቸው በዘገባችን ተካቷል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን የሚዳስስ ሪፖርቱን ዛሬ ረቡ ሓምሌ 5፣ 2015 ዓ.ም ይፋ አድርጓል፡፡

ኮሚሽኑ በሪፖርቱ በ #ኦሮሚያ ክልል እየተፈፀመ ያለው ግጭትና ጥቃት እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሶ በ #አማራ ክልል ያለው የፀጥታ ሁኔታም በተመሳሳይ መጠን አሳሳቢ መሆኑን ገልጧል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በአገሪቱ በርካታ የመብት ጥሰቶች መፈፀማቸውን ለሚዲያ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

የጸጥታ ችግር ያለባቸው አካባቢዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መምጣት በኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ላይ ከፍተኛ ጫና እና ጥሰት ማስከተሉም በሪፖርቱ ተጠቅሷል።
ዜና፡ ጠ/ሚኒስትር #አብይ አህመድ በሱዳን ጉዳይ በሚመክረው የካይሮ ስብሰባ ለመታደም ግብጽ ይገኛሉ፤ #ከአልሲሲ ጋር በህዳሴ ግድብ ዙሪያ መምከራቸው ተገልጿል

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ #በሱዳን ጉዳይ በሚመክረው #የካይሮ ስብሰባ ለመታደም ግብጽ ይገኛሉ፤ ትላንት ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ማምሻ ግብጽ የገቡት ዶ/ር አብይ የግብጹ ፕሬዝዳንት አልሲሲ በቤተመንግስታቸው አቀባበል እንዳደረጉላቸው የግብጽ መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል።
ከአልሲሲ ጋር በህዳሴ ግድብ ዙሪያ፣ በሁለቱ ሀገራት ሁለትዮሽ ግንኙነት መምከራቸውም ተገልጿል።

በሱዳን ሰላም ዙሪያ በሚመክረው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ የሱዳን አጎራባች ሀገራት መሪዎች ካይሮ መግባታቸውን ያመላከቱት ዘገባዎቹ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ትላንት ጠዋት ላይ ካይሮ መግባታቸውንም አውስተዋል።

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና አልሲሲ በይፋ ሲገናኙ #ከሶስት አመታት በኋላ መሆኑን የጠቆመው አልአህራም ድረገጽ በሌሎች አለም አቀፍ ስብሰባዎች በተጓዳኝ ተገናኝተው እንደሚያውቁ አውስቷል።
ዜና፡ #በትግራይ ክልል አባቶች የሚካሄደው የጳጳሳት ሹመት እንዲቆም #የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣው መግለጫ ጠየቀ

በትግራይ ክልል ሐምሌ 9 ይደረጋል የተባለው #የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያላከበረና የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስ በመሆኑ እንዲቆም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣው መግለጫ ጠየቀ።

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር #አቢይ አህመድ እና አቶ #ጌታቸው ረዳ የጳጳሳቱን ሹመት እንዲያስቆሙ ብሎም ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ችግሮቹ በውይይት እንዲፈቱ መንግሥታዊ እገዛ በማድረግ የውይይት መድረክ እንዲያመቻቹልን ሲል ጠይቋል።

ሹመቱ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳና በጦርነት የተጎዳውን ሀብት ንብረቱ የወደመበትን ገዳማቱና አብያተ ክርስቲያናቱ የተጎዱበትን ሕዝብ የማይጠቅም ተገቢነት የሌለው በመሆኑ እንዲቆም ሲል መወሰኑን መግለጫው አስታውቋል።

#ሲኖዶሱ በመግለጫው ካካተታቸው ውሳኔዎች መካከልም ለሰላም የሚደረገው ጥረት ዘላቂ መፍትሔ እስከሚገኝ ድረስ ግንኙነቱ የማይቋረጥ መሆኑን ያስታወቀበት ይገኛል፡፡
https://rb.gy/m2te1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአመታዊ ሪፖርቱ ላይ -የማረሚያ ቤቶች የእስረኛ አያያዝ አስከፊ መሆን፣ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት መገደብ፣ ማህበራዊ እና ተፈጥሯዊ ችግሮች መበራከት፣ መባባስን በተመለከተ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የሰጡት መግለጫ፡፡
እስከ ታሕሳስ ወር 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደተሃድሶ ማዕከላት ለማስገባት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

እስከ ቀጣዩ ዓመት ታሕሳስ ወር ድረስ 75 ሺህ የሚደርሱ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደተሃድሶ ማዕከላት ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራን አስመልክቶ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር እየመከረ ነው፡፡

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሻንቆ ደለለኝ÷ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራ በስኬት እንዲጠናቀቅ የአጋር አካላት ድጋፍ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ኮሚሽኑ እስከ ቀጣዩ ዓመት ታሕሳስ ወር መጨረሻ ድረስ 50 ሺህ የሚሆኑ ተዋጊዎችን ከትግራይ ክልል እና ቀሪ 25 ሺህ ደግሞ ከሌሎች ክልሎች ወደማዕከላቱ ለማስገባት መታቀዱን አንስተዋል፡፡

የሚሰናበቱ የቀድሞ ተዋጊዎችን ከማህበረሰቡ ጋር በዘላቂነት እንዲቀላቀሉ እና በልማት፣ በሰላምና በዴሞክራሲ ግንባታ ውስጥ እንዲሳተፉ እንዲሁም በዘላቂነት ወደ ሰላማዊ ኑሮ እንዲመለሱ የኢፌዴሪ ብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን የሚሰራ መሆኑ ይታወቃል።

ኤፍቢሲ
ዜና፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን ታጣቂዎች በመፈፀሙት ጥቃት 8 ነዋሪዎች ሲሞቱ 16 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ኢሰመኮ አስታወቀ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ግልገል በለስ ከተማ በተለምዶ “ቻይና ካምፕ” ተብሎ በሚጠራ ሰፈር በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት፣ 3 የአካባቢውን ሚሊሻ አባላት ጨምሮ 8 ነዋሪዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ፡፡

በጥቃቱ ከሞትቱ ስምንት ሰዎች በተጨማሪ በ16 ሲቪል ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶ የሕክምና እርዳታ እያገኙ መሆኑንና በርካታ ሌሎች ነዋሪዎች ቻይና ካምፕን ለቀው ወደ ሌላ ሰፈር መሸሻቸውን ኢሰመኮ በመግለጫው አመላክቷል።

ታጣቂዎቹም ለጥቃቱ ምክንያት ያሉት “ከመንግሥት ጋር የተደረሰው የሰላም ስምምነት አልተተገበረም” የሚል መሆኑን ኮሚሽኑ ካነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ማወቅ ተችሏል።

https://rb.gy/s86fw
ዜና፡ #በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘው ቀይ ቀበሮ የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠበት ተገለጸ፤ የማዳን ስራ እየተሰራ መሆኑ ተጠቁሟል

በኢትዮጵያ የሚገኙ የተኩላ እንስሳ ዝርያዎች ገዳይ በሆነ #ቫይረስ ሳቢያ እና መኖሪያቸው እየጠበበ በመምጣቱ የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠባቸው ተገለጸ። ሁኔታውን ለመቀልበስ የማዳን ስራ እየተሰራ መሆኑን ዲስከቨሪ ዋይልድ ላይፍ ድረገጽ ባወጣው ዘገባ አስታውቋል።
#በባሌ ተራሮች ላይ የሚገኙት የቀይ ቀበሮ የተኩላ ዝርያዎች ካኒን ዲስቴምፐር (Canine Distemper Virus) የተሰኘ ገዳይ ቫይረስ በመጠቃታቸው ህልውናቸው አደጋ ላይ መሆኑን ድረገጹ ጠቁሟል።
ቫይረሱን ለመከላከል እየተሰጣቸው ያለው ክትባት በህይወት ለመቆየት እና ከምድረገጽ እንዳይጠፉ ለማስቻል ሁለተኛ እድል እየሰጣቸው እንደሚገኝ ዘገባው አመላክቷል። የኢትዮጵያ ቀበሮ ወይንም አቢሲኒያ ቀበሮ በመባል የሚታወቀው ቀይ ቀበሮ በአፍሪካ ከሚገኙ የተኩላ ዝርያዎች እጅጉን አደጋ ላይ የሚገኝ መሆኑን ዘገባው አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት ከ500 በታች የሚሆኑ ቀይ ቀበሮዎች ብቻ በህይወት እንደሚገኙ በዘገባው ተጠቁሟል።
ቀይ ቀበሮዎቹ የሚኖሩበት አከባቢ የሚገኙ ሰዎች እየተስፋፉ እና በዚያው አከባቢ መኖር በመጀመራቸው ቀያቸው አደጋ ላይ እንደሚገኝን የድረገጹ ዘገባ ጠቁሟል።
https://rb.gy/u5d6o
ዜና፡ አቡነ #ማትያስ እና ሉዑካቸው #በመቀሌ አቀባበል ያልተደረገላቸው ምንም አይነት የተጻፈልን ደብዳቤም ይሁን የተያዘ መርሃ ግብር ስላልነበረ ነው ስትል የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስታወቀች

#የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ቤተ ክህነት ጸሐፊ መጋቤ ብርሃናት #ተስፋየ ሀደራ ለትግራይ ቴሌቪዥን እንደገለጹት ለቤተክህነቱ ስለ ጉብኝቱ ያሳወቀው አካል የለም ሲሉ ተናግረዋል።

በቀጥታ ለመንበረ ሰላማ የተጻፈ ደብዳቤ አልነበረም፤ የተያዘ መርሃ ግብርም አልነበረም፤ እሽታችን እና እምቢታችን ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ነው እንግዶቹ ወደ መቀሌ የመጡት ሲሉ ተደመጠዋል።

ቅዱስ አባታችን እዚህ ስለመጡ ወይንም ስላልመጡ ሳይሆን ባሉበት ሁነው እሳት በሚነድበት ወቅት ስለኢትዮጵያ ህዝብ ያለቀሱ፣ የተናገሩ፣ ድምጻቸውን ያሰሙ አባት ናቸው፤ ለዚህም ትልቅ ክብር አለን ያሉት ጸሐፊው ብጹዕነታቸውም ይህን ያውቃሉ፣ እነሱም እሳቸውን የላኳቸው ሆን ብለው ለመፈተን ነው፣ የትግራይ ተወላጅ ስለሆኑ ሊቀበሏቸው ይችላሉ በሚል የተሳሳተ ግምት ነው ብለዋል።
ብፁእ ወ ቅዱስ አቡነ ማትያስን ሽፋን አድርጎ የህዝቡን ቅሬታ እና ሐዘን ለማድበስበስ ያለመ ነው ሲሉ መግለጻቸውን ዘገባው አካቷል።

በሌላ ዜና #ከአውስትራሊያ ወደ መቀሌ ሲያቀኑ የነበሩት ቆሞስ ኣባ #ሰረቀብርሃን ወልደሳሙኤል በአዲስ አበባ ኤርፖርት እንዳየወጡ መደረጋቸውን ይታወቃል ዛሬ የወጡ ዘገባዎች እንደሚያመላክቱት ቆሞስ ኣባ ሰረቀብርሃን ወልደሳሙኤል በኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች አስገዳጅነተ ወደ ሀንድ እንዲጓዙ ተደርገዋል ተብሏል።