ዜና፡ #የአፍሪካ ህብረት #በትግራይ የተፈጸሙ ጥሰቶችን ምርመራ ግልጽ ባልሆነ መንገድ አቆመ፤ ህብረቱ በድረገጹ በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ የሚሰጠውን ገጽ አስወግዶታል
የአፍሪካ ህብረት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ የተፈጸሙ ጥሰቶችን እንዲመርመር ያቋቋመውን ኮሚሽን ይፋዊ ባልሆነ መንገድ እንዲቆም ማድረጉ ተገለጸ። በኢትዮጵያ ለሁለት አመታት የታካሄደውን ጦርነት ተከትሎ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን ለመመርመር የተቋቋመ የመጀመሪያው ኮሚሽን መሆኑ ይታወሳል።
ምርመራው እንዲቋረጥ ከማድረጉ በተጨማሪ የህብረቱ ኮሚሽን በድረገጹ የነበረውን እና በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ የሚሰጠውን ገጽ እንዳስወገደው ታውቋል።
ህብረቱ በትግራይ ሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ምርመራ እንዲያካሂድ ያቋቋመውን ኮሚሽን ስልጣኑ እንዲያበቃ እና የሚያካሂደው ምርመራ እንዲቋረጥ ውሳኔ ያሳለፈው ከአንድ ወር በፊት መሆኑም ተጠቁሟል። ኮሚሽኑ ከተቋቋመ ጀምሮ ይፋ ያደረገው #ሪፖርት የለም። https://rb.gy/176l5

ዜና፡ #በትግራይ የሚገኙ የኦርቶዶክስ አባቶች በሳምንቱ መጨረሻ #በአክሱም ጽዮን የጳጳሳት ሹመት እንደሚያካሂዱ ገለፁ
በትግራይ ክልል የሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት አባቶች በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ.ም በአክሱም ጽዮን የአዳዲስ ጳጳሳት ሹመት እንደሚያካሂዱ ገለፁ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ እና በትግራይ ክልል በሚገኙ የእምነቱ አባቶች በመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መካከል የተፈጠረው ልዩነት ባልተፈታበት ሁኔታ የትግራይ አባቶች ሹመቱን ለማካሄድ መወሰናቸውን ለመገናኛ ብዙሃን በላኩት ደብዳቤ አስታውቀዋል። የሚዲያ ሽፋን በጠየቁበት ደብዳቤ እንደተመላከተው በእለቱ የአስር ጳጳሳት ሹመት እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።
በሳምንቱ መጀመሪያ ቀናት በትግራይ ጉብኝት ያካሄዱት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ #ማትያስ በክልሉ ጉብኝት ቢያካሂዱም በክልሉ ከሚገኙ የቤተክርስቲያኗ ብጹአን አባቶች ጋር ተገናኝተው አለመምከራቸው ይታወሳል። አቡነ ማትያስ በመቀሌው ጉብኝታቸው ከክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ግዜያዊ አስተዳደሩ በቤተክርስቲያኗ ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ አቶ #ጌታቸው ረዳ እንደገለጹላቸው በዘገባችን ተካቷል።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን የሚዳስስ ሪፖርቱን ዛሬ ረቡ ሓምሌ 5፣ 2015 ዓ.ም ይፋ አድርጓል፡፡
ኮሚሽኑ በሪፖርቱ በ #ኦሮሚያ ክልል እየተፈፀመ ያለው ግጭትና ጥቃት እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሶ በ #አማራ ክልል ያለው የፀጥታ ሁኔታም በተመሳሳይ መጠን አሳሳቢ መሆኑን ገልጧል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በአገሪቱ በርካታ የመብት ጥሰቶች መፈፀማቸውን ለሚዲያ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡
የጸጥታ ችግር ያለባቸው አካባቢዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መምጣት በኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ላይ ከፍተኛ ጫና እና ጥሰት ማስከተሉም በሪፖርቱ ተጠቅሷል።

ዜና፡ ጠ/ሚኒስትር #አብይ አህመድ በሱዳን ጉዳይ በሚመክረው የካይሮ ስብሰባ ለመታደም ግብጽ ይገኛሉ፤ #ከአልሲሲ ጋር በህዳሴ ግድብ ዙሪያ መምከራቸው ተገልጿል
ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ #በሱዳን ጉዳይ በሚመክረው #የካይሮ ስብሰባ ለመታደም ግብጽ ይገኛሉ፤ ትላንት ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ማምሻ ግብጽ የገቡት ዶ/ር አብይ የግብጹ ፕሬዝዳንት አልሲሲ በቤተመንግስታቸው አቀባበል እንዳደረጉላቸው የግብጽ መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል።
ከአልሲሲ ጋር በህዳሴ ግድብ ዙሪያ፣ በሁለቱ ሀገራት ሁለትዮሽ ግንኙነት መምከራቸውም ተገልጿል።
በሱዳን ሰላም ዙሪያ በሚመክረው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ የሱዳን አጎራባች ሀገራት መሪዎች ካይሮ መግባታቸውን ያመላከቱት ዘገባዎቹ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ትላንት ጠዋት ላይ ካይሮ መግባታቸውንም አውስተዋል።
ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና አልሲሲ በይፋ ሲገናኙ #ከሶስት አመታት በኋላ መሆኑን የጠቆመው አልአህራም ድረገጽ በሌሎች አለም አቀፍ ስብሰባዎች በተጓዳኝ ተገናኝተው እንደሚያውቁ አውስቷል።

ዜና፡ #በትግራይ ክልል አባቶች የሚካሄደው የጳጳሳት ሹመት እንዲቆም #የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣው መግለጫ ጠየቀ
በትግራይ ክልል ሐምሌ 9 ይደረጋል የተባለው #የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያላከበረና የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስ በመሆኑ እንዲቆም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣው መግለጫ ጠየቀ።
ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር #አቢይ አህመድ እና አቶ #ጌታቸው ረዳ የጳጳሳቱን ሹመት እንዲያስቆሙ ብሎም ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ችግሮቹ በውይይት እንዲፈቱ መንግሥታዊ እገዛ በማድረግ የውይይት መድረክ እንዲያመቻቹልን ሲል ጠይቋል።
ሹመቱ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳና በጦርነት የተጎዳውን ሀብት ንብረቱ የወደመበትን ገዳማቱና አብያተ ክርስቲያናቱ የተጎዱበትን ሕዝብ የማይጠቅም ተገቢነት የሌለው በመሆኑ እንዲቆም ሲል መወሰኑን መግለጫው አስታውቋል።
#ሲኖዶሱ በመግለጫው ካካተታቸው ውሳኔዎች መካከልም ለሰላም የሚደረገው ጥረት ዘላቂ መፍትሔ እስከሚገኝ ድረስ ግንኙነቱ የማይቋረጥ መሆኑን ያስታወቀበት ይገኛል፡፡
https://rb.gy/m2te1

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአመታዊ ሪፖርቱ ላይ -የማረሚያ ቤቶች የእስረኛ አያያዝ አስከፊ መሆን፣ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት መገደብ፣ ማህበራዊ እና ተፈጥሯዊ ችግሮች መበራከት፣ መባባስን በተመለከተ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የሰጡት መግለጫ፡፡
እስከ ታሕሳስ ወር 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደተሃድሶ ማዕከላት ለማስገባት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
እስከ ቀጣዩ ዓመት ታሕሳስ ወር ድረስ 75 ሺህ የሚደርሱ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደተሃድሶ ማዕከላት ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራን አስመልክቶ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር እየመከረ ነው፡፡
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሻንቆ ደለለኝ÷ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራ በስኬት እንዲጠናቀቅ የአጋር አካላት ድጋፍ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ኮሚሽኑ እስከ ቀጣዩ ዓመት ታሕሳስ ወር መጨረሻ ድረስ 50 ሺህ የሚሆኑ ተዋጊዎችን ከትግራይ ክልል እና ቀሪ 25 ሺህ ደግሞ ከሌሎች ክልሎች ወደማዕከላቱ ለማስገባት መታቀዱን አንስተዋል፡፡
የሚሰናበቱ የቀድሞ ተዋጊዎችን ከማህበረሰቡ ጋር በዘላቂነት እንዲቀላቀሉ እና በልማት፣ በሰላምና በዴሞክራሲ ግንባታ ውስጥ እንዲሳተፉ እንዲሁም በዘላቂነት ወደ ሰላማዊ ኑሮ እንዲመለሱ የኢፌዴሪ ብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን የሚሰራ መሆኑ ይታወቃል።
ኤፍቢሲ

ዜና፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን ታጣቂዎች በመፈፀሙት ጥቃት 8 ነዋሪዎች ሲሞቱ 16 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ኢሰመኮ አስታወቀ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ግልገል በለስ ከተማ በተለምዶ “ቻይና ካምፕ” ተብሎ በሚጠራ ሰፈር በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት፣ 3 የአካባቢውን ሚሊሻ አባላት ጨምሮ 8 ነዋሪዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ፡፡
በጥቃቱ ከሞትቱ ስምንት ሰዎች በተጨማሪ በ16 ሲቪል ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶ የሕክምና እርዳታ እያገኙ መሆኑንና በርካታ ሌሎች ነዋሪዎች ቻይና ካምፕን ለቀው ወደ ሌላ ሰፈር መሸሻቸውን ኢሰመኮ በመግለጫው አመላክቷል።
ታጣቂዎቹም ለጥቃቱ ምክንያት ያሉት “ከመንግሥት ጋር የተደረሰው የሰላም ስምምነት አልተተገበረም” የሚል መሆኑን ኮሚሽኑ ካነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ማወቅ ተችሏል።
https://rb.gy/s86fw

ዜና፡ #በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘው ቀይ ቀበሮ የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠበት ተገለጸ፤ የማዳን ስራ እየተሰራ መሆኑ ተጠቁሟል
በኢትዮጵያ የሚገኙ የተኩላ እንስሳ ዝርያዎች ገዳይ በሆነ #ቫይረስ ሳቢያ እና መኖሪያቸው እየጠበበ በመምጣቱ የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠባቸው ተገለጸ። ሁኔታውን ለመቀልበስ የማዳን ስራ እየተሰራ መሆኑን ዲስከቨሪ ዋይልድ ላይፍ ድረገጽ ባወጣው ዘገባ አስታውቋል።
#በባሌ ተራሮች ላይ የሚገኙት የቀይ ቀበሮ የተኩላ ዝርያዎች ካኒን ዲስቴምፐር (Canine Distemper Virus) የተሰኘ ገዳይ ቫይረስ በመጠቃታቸው ህልውናቸው አደጋ ላይ መሆኑን ድረገጹ ጠቁሟል።
ቫይረሱን ለመከላከል እየተሰጣቸው ያለው ክትባት በህይወት ለመቆየት እና ከምድረገጽ እንዳይጠፉ ለማስቻል ሁለተኛ እድል እየሰጣቸው እንደሚገኝ ዘገባው አመላክቷል። የኢትዮጵያ ቀበሮ ወይንም አቢሲኒያ ቀበሮ በመባል የሚታወቀው ቀይ ቀበሮ በአፍሪካ ከሚገኙ የተኩላ ዝርያዎች እጅጉን አደጋ ላይ የሚገኝ መሆኑን ዘገባው አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት ከ500 በታች የሚሆኑ ቀይ ቀበሮዎች ብቻ በህይወት እንደሚገኙ በዘገባው ተጠቁሟል።
ቀይ ቀበሮዎቹ የሚኖሩበት አከባቢ የሚገኙ ሰዎች እየተስፋፉ እና በዚያው አከባቢ መኖር በመጀመራቸው ቀያቸው አደጋ ላይ እንደሚገኝን የድረገጹ ዘገባ ጠቁሟል።
https://rb.gy/u5d6o

ዜና፡ አቡነ #ማትያስ እና ሉዑካቸው #በመቀሌ አቀባበል ያልተደረገላቸው ምንም አይነት የተጻፈልን ደብዳቤም ይሁን የተያዘ መርሃ ግብር ስላልነበረ ነው ስትል የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስታወቀች
#የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ቤተ ክህነት ጸሐፊ መጋቤ ብርሃናት #ተስፋየ ሀደራ ለትግራይ ቴሌቪዥን እንደገለጹት ለቤተክህነቱ ስለ ጉብኝቱ ያሳወቀው አካል የለም ሲሉ ተናግረዋል።
በቀጥታ ለመንበረ ሰላማ የተጻፈ ደብዳቤ አልነበረም፤ የተያዘ መርሃ ግብርም አልነበረም፤ እሽታችን እና እምቢታችን ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ነው እንግዶቹ ወደ መቀሌ የመጡት ሲሉ ተደመጠዋል።
ቅዱስ አባታችን እዚህ ስለመጡ ወይንም ስላልመጡ ሳይሆን ባሉበት ሁነው እሳት በሚነድበት ወቅት ስለኢትዮጵያ ህዝብ ያለቀሱ፣ የተናገሩ፣ ድምጻቸውን ያሰሙ አባት ናቸው፤ ለዚህም ትልቅ ክብር አለን ያሉት ጸሐፊው ብጹዕነታቸውም ይህን ያውቃሉ፣ እነሱም እሳቸውን የላኳቸው ሆን ብለው ለመፈተን ነው፣ የትግራይ ተወላጅ ስለሆኑ ሊቀበሏቸው ይችላሉ በሚል የተሳሳተ ግምት ነው ብለዋል።
ብፁእ ወ ቅዱስ አቡነ ማትያስን ሽፋን አድርጎ የህዝቡን ቅሬታ እና ሐዘን ለማድበስበስ ያለመ ነው ሲሉ መግለጻቸውን ዘገባው አካቷል።
በሌላ ዜና #ከአውስትራሊያ ወደ መቀሌ ሲያቀኑ የነበሩት ቆሞስ ኣባ #ሰረቀብርሃን ወልደሳሙኤል በአዲስ አበባ ኤርፖርት እንዳየወጡ መደረጋቸውን ይታወቃል ዛሬ የወጡ ዘገባዎች እንደሚያመላክቱት ቆሞስ ኣባ ሰረቀብርሃን ወልደሳሙኤል በኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች አስገዳጅነተ ወደ ሀንድ እንዲጓዙ ተደርገዋል ተብሏል።

ዜና፡ #ቤተክርስቲያኗ የዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሰጠች፤ #በትግራይ አባ ሰረቀብርሃንን ጨምሮ አስር አባቶች ለኤጲስ ቆጶስነት መመረጣቸው ተገለጸ
#የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን #በኦሮምያ እና #በደቡብ ክልል ለሚገኙ ሀገረ ስብከቶች የሚመደቡ የዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት መስጠቷ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ #ማቲያስ ለዘጠኙ ኤፒስ ቆጶሳት ሹመቱን የሰጡት በመንበረ ፓትሪያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም መሆኑም ታውቋል። ብጹዕነታቸው የኤጲስ ቆጶሳቱ ሹመት በሰጡበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት “ቤተክርስቲያኒቷ ውስጥ ባልተጠበቀ እና ባልተለመደ ሁኔታ ብቅ ብቅ ሲሉ የሚታዩት ራስን በራስ የመሾም አባዜ መገታት አለባቸው፤ ማንኛውም ችግር በውይይት፣ በምክክር እና የተበደለውንም በመካስ መፈታት ይገባዋል ብለዋል።”
በሌላ ዜና የትግራይ የቤተክርስቲያኗ አባቶች በቀጣይ በትግራይ ክልል እና በሌሎች ሀገራት በሚገኙ ቤተክርስትያናት እንዲያገለግሉ በሚል ዘጠኝ አባቶችን የኤጲስ ቆጶሳቱ ሹመት ለመስጠት በትላንትናው እለት ምርጫ አካሂደዋል።
#መንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን በሚል ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አደረጃጀት እራሳቸውን በማግለል ያቋቋሙት የትግራይ የቤተክርስቲያኗ አባቶች ምርጫውን ያካሄዱት #በአክሱም ከተማ መሆኑን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል።
በውጭ ሀገራት ቤተክርስቲያኗን እንዲያገለግሉ አምስት አባቶች የተመረጡ ሲሆን ከነዚህም መካከል ከአውስትራሊያ ወደ መቀሌ ሲያቀኑ በቦሌ ኤርፖርት እንዳይንቀሳቀሱ ተደርገው የነበሩት ቆሞስ አባ #ሰረቀብርሃን ወልደ ሳሙኤል ይገኙበታል።
https://rb.gy/y7fd9

ኢትዮጵያ በአንድ ቀን "500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል" መርሃ-ግብር ጀምራለች
ኢትዮጵያ የአርጓዴ አሻራ መርሓ-ግብር አካል የሆነው፣ በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የሚከናወነውን በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሃ-ግብር አስጀምራለች፡፡
ዘመቻው ከጠዋት 12፡00 የጀመረ ሲሆን እስከ አመሻሽ 12፡00 የሚከናወን ይሆናል፡፡
የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሰላማዊት ካሳ ለሚዲያ በሰጡት መግለጫ “በሳተላይት ቴክኖሎጂ በመታገዝ የችግኝ ተከላ ሂደቱን ለመቆጣጣርና መረጃ ለመሰብሰብ 9ሺህ የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውን” ገልፀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትላንት “ዕቅዳችን ሪከርዳችንን መስበር ነው” ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው “አርንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያን የመጠበቅ፣ የማክበርና የማበልፀግ ነው ጉዳይ ነው፤ ታሪክ የመቀየር ጉዳይ ነው፡፡ ትውልድን የማትረፍ ጉዳይ ነው፡፡”ብለዋል፡፡ በዛሬው መርሃ-ግብር ሁሉም እንዲካፈል ጥሪም አቅርበዋል፡፡

ዜና፡ #የእስራኤል ባለስልጣናት #በጎንደር የታገተው ቤተ እስራኤላዊ የውሸት ነው የሚል እምነት ስላደረባቸው ለማስለቀቅ የሚደረገው እንቅስቃሴ እንዲቋረጥ ማድረጋቸው ተገለጸ
ከቀናት በፊት በጎንደር አቅራቢያ ታግቶ የነበረው እስራኤላዊ በሀሰት ታግቻለሁ በማለት ገንዘብ ከቤተሰቦቹ ለመውሰድ በማለም ያደረገው ተግባር ነው መባሉን የእስራኤል የዜና አገልግሎት በዘገባው አስታውቋል። በዚህም ሳቢያ ታጋቹን እስራኤላዊ ለማስለቀቅ የሚደረገው ጥረት በእስራኤል ባለስልጣናት እንዲቋረጥ መደረጉን ዘገባ አመላክቷል።
የ79 አመቱ እስራኤላዊ ፍራንሲስ #አደባባይ እገታ እንደተፈጸመበት በማስመሰል ከቤተሰቦቹ የሚገኝን ገንዘብ ለመውሰድ በማለም የፈጸመው የማጭበርበር ተግባር ነው ብሎ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ማመኑን ዘገባው አመላክቷል።
አጋቾቹ ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊየን ብር ለማስለቀቂያ መጠየቃቸውን ዘገባው አስታውቋል።
ታጋቹ #ቤተእስራኤላዊ ፍራንሲስ አደባባይ ከእስራኤል ሀገር ለሚደወልለትን ስልክ ምላሽ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ያረጋገጡት የእስራኤል ባለስልጣናት ለማስለቀቅ የሚደረገው እንቅስቃሴ እንዲቋረጥ ማድረጋቸውን ዘገባው አስታውቋል።
ቤተሰቦቹ በበኩላቸው በባለስልጣኑ ግኝት ላይ አለመስማማታቸውን እና ፍራንሲስ አደባባይ አሁንም በእገታ ላይ ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ዘገባው ጠቁሟል።
https://rb.gy/wi19t

Addis Standard
ዜና፡ የእስራኤል ባለስልጣናት በጎንደር የታገተው ቤተ እስራኤላዊ የውሸት ነው የሚል እምነት ስላደረባቸው ለማስለቀቅ የሚደረገው እንቅስቃሴ እንዲቋረጥ ማድረጋቸው ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም፡- ከቀናት በፊት በጎንደር አቅራቢያ ታግቶ የነበረው እስራኤላዊ በሀሰት ታግቻለሁ በማለት ገንዘብ ከቤተሰቦቹ ለመውሰድ በማለም ያደረገው ተግባር ነው መባሉን የእስራኤል የዜና አገልግሎት በዘገባው አስታውቋል። በዚህም ሳቢያ ታጋቹን እስራኤላዊ ለማስለቀቅ የሚደረገው ጥረት በእስራኤል ባለስልጣናት እንዲቋረጥ መደረጉን ዘገባ አመላክቷል። የ79 አመቱ እስራኤላዊ ፍራንሲስ…
በውሸት 'ታግቻለሁ' በማለት ቤተሰቦቹን 500 መቶ ሽ ብር የጠየቀው ግለሰብ ከወንጀል ተባባሪዎቹ ጋር በፖሊሰ ቁጥጥር ስር ዋለ።
ሀምሌ 10/2015 ዓ/ም - ሳይታገት 'ታግቻለሁ' በማለት ቤተሰቦቹን 500 መቶ ሽ ብር የጠየቀው ተጠርጣሪ ግለሰብ በፖሊሰ ቁጥጥር ስር መዋሉን የ #አማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል ።
ከደቡብ #ወሎ ዞን መካነ ሰላም ወረዳ ወደ #ደሴ በመምጣት ደሴ ከተማ ቧንቧ ውሀ ክፍለ ከተማ በካራ ጉቱ ከሚባለው አካባቢ ጫካ ውስጥ በመግባት ከጓደኛው ጋር በመመካከር ጓደኛው የታገተ በማስመሰል እራሱን በገመድ ከዛፍ ጋር በማሰር ፎቶውን ለቤተሰቦቹ በመላክና ቤተሰቦቹን በስልክ 500 መቶ ሽ ብር ላኩልኝ ብሎ ሲጠይቅ የነበረው ተጠርጣሪ ከወንጀል ተባባሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የገለፀው።
ቤተሰቦቹ ጉዳዩን ለፖሊስ አመልክተው እንደነበርና ፖሊስም የደረሰውን ጥቆማ ልዩ ትኩረት በመስጠት ባደረገው ክትትል ታግቻለሁ እያለ "ቤተሰቦቹን እና የአካባቢውን ሰው ያስጨነቀው ተጠርጣሪ ከሌሊቱ 07:00 ስዓት በህብረተሰቡ ጥቆማ መነሀሪያ አካባቢ አልጋ ቤት ውስጥ ከወንጀል ተባባሪዎቹ ጋር" በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል።