Addis Standard Amharic – Telegram
Addis Standard Amharic
18K subscribers
4.67K photos
121 videos
3 files
3.72K links
አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Download Telegram
ኢትዮጵያ በአንድ ቀን "500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል" መርሃ-ግብር ጀምራለች

ኢትዮጵያ የአርጓዴ አሻራ መርሓ-ግብር አካል የሆነው፣ በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የሚከናወነውን በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሃ-ግብር አስጀምራለች፡፡

ዘመቻው ከጠዋት 12፡00 የጀመረ ሲሆን እስከ አመሻሽ 12፡00 የሚከናወን ይሆናል፡፡

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሰላማዊት ካሳ ለሚዲያ በሰጡት መግለጫ “በሳተላይት ቴክኖሎጂ በመታገዝ የችግኝ ተከላ ሂደቱን ለመቆጣጣርና መረጃ ለመሰብሰብ 9ሺህ የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውን” ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትላንት “ዕቅዳችን ሪከርዳችንን መስበር ነው” ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው “አርንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያን የመጠበቅ፣ የማክበርና የማበልፀግ ነው ጉዳይ ነው፤ ታሪክ የመቀየር ጉዳይ ነው፡፡ ትውልድን የማትረፍ ጉዳይ ነው፡፡”ብለዋል፡፡ በዛሬው መርሃ-ግብር ሁሉም እንዲካፈል ጥሪም አቅርበዋል፡፡
ዜና፡ #የእስራኤል ባለስልጣናት #በጎንደር የታገተው ቤተ እስራኤላዊ የውሸት ነው የሚል እምነት ስላደረባቸው ለማስለቀቅ የሚደረገው እንቅስቃሴ እንዲቋረጥ ማድረጋቸው ተገለጸ

ከቀናት በፊት በጎንደር አቅራቢያ ታግቶ የነበረው እስራኤላዊ በሀሰት ታግቻለሁ በማለት ገንዘብ ከቤተሰቦቹ ለመውሰድ በማለም ያደረገው ተግባር ነው መባሉን የእስራኤል የዜና አገልግሎት በዘገባው አስታውቋል። በዚህም ሳቢያ ታጋቹን እስራኤላዊ ለማስለቀቅ የሚደረገው ጥረት በእስራኤል ባለስልጣናት እንዲቋረጥ መደረጉን ዘገባ አመላክቷል።

የ79 አመቱ እስራኤላዊ ፍራንሲስ #አደባባይ እገታ እንደተፈጸመበት በማስመሰል ከቤተሰቦቹ የሚገኝን ገንዘብ ለመውሰድ በማለም የፈጸመው የማጭበርበር ተግባር ነው ብሎ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ማመኑን ዘገባው አመላክቷል።

አጋቾቹ ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊየን ብር ለማስለቀቂያ መጠየቃቸውን ዘገባው አስታውቋል።
ታጋቹ #ቤተእስራኤላዊ ፍራንሲስ አደባባይ ከእስራኤል ሀገር ለሚደወልለትን ስልክ ምላሽ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ያረጋገጡት የእስራኤል ባለስልጣናት ለማስለቀቅ የሚደረገው እንቅስቃሴ እንዲቋረጥ ማድረጋቸውን ዘገባው አስታውቋል።

ቤተሰቦቹ በበኩላቸው በባለስልጣኑ ግኝት ላይ አለመስማማታቸውን እና ፍራንሲስ አደባባይ አሁንም በእገታ ላይ ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ዘገባው ጠቁሟል።
https://rb.gy/wi19t
በውሸት 'ታግቻለሁ' በማለት ቤተሰቦቹን 500 መቶ ሽ ብር የጠየቀው ግለሰብ ከወንጀል ተባባሪዎቹ ጋር በፖሊሰ ቁጥጥር ስር ዋለ።

ሀምሌ 10/2015 ዓ/ም - ሳይታገት 'ታግቻለሁ' በማለት ቤተሰቦቹን 500 መቶ ሽ ብር የጠየቀው ተጠርጣሪ ግለሰብ በፖሊሰ ቁጥጥር ስር መዋሉን የ #አማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል ።

ከደቡብ #ወሎ ዞን መካነ ሰላም ወረዳ ወደ #ደሴ በመምጣት ደሴ ከተማ ቧንቧ ውሀ ክፍለ ከተማ በካራ ጉቱ ከሚባለው አካባቢ ጫካ ውስጥ በመግባት ከጓደኛው ጋር በመመካከር ጓደኛው የታገተ በማስመሰል እራሱን በገመድ ከዛፍ ጋር በማሰር ፎቶውን ለቤተሰቦቹ በመላክና ቤተሰቦቹን በስልክ 500 መቶ ሽ ብር ላኩልኝ ብሎ ሲጠይቅ የነበረው ተጠርጣሪ ከወንጀል ተባባሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የገለፀው።

ቤተሰቦቹ ጉዳዩን ለፖሊስ አመልክተው እንደነበርና ፖሊስም የደረሰውን ጥቆማ ልዩ ትኩረት በመስጠት ባደረገው ክትትል ታግቻለሁ እያለ "ቤተሰቦቹን እና የአካባቢውን ሰው ያስጨነቀው ተጠርጣሪ ከሌሊቱ 07:00 ስዓት በህብረተሰቡ ጥቆማ መነሀሪያ አካባቢ አልጋ ቤት ውስጥ ከወንጀል ተባባሪዎቹ ጋር" በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል።
ዜና፡ የኢትዮጵያ መንግስት ላለፉር አራት ወራት ጥሎት የነበረውን የኢንተርኔት ገደብ አንስቷል

ጥር ወር መገባደጃ በመንግስት እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርትቲያን መካከል የተፈጠረውን እሰጥ አገባ ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በተወሰቡ ማህበራዊ መገናኝ ዘዴዎች ላይ ጥሎት የነበረውን ገደብ ከአራት ወር በኋላ አንስቷል፡፡

መንግስት ፌስቡክ፣ ቴልግራም፣ ቲክቶክን ጨምሮ በሌሎች ማህበራዊ መገናኛ መተግበሪያዎች ላይ ገደብ መጣሉን ተከትሉ ተጠቃሚው በቪፒኤን መተግበሪያን በመጠቀም ገደብ የተጣለባቸውን ማህበራዊ መገናኝ ዘዴዎች ሲጠቀም መቆየቱ ይታወሳል፡፡ በትላንትናው እለትም ይህ ገደብ መነሳቱ ተመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በኢንተርኔት ላይ የጣለውን ደገብ እንዲያነሳ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ተቋማት ሲጠይቁ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

የጋዜጠኞች ተቆርቋሪ ተቋም የሆነው ሲፒጄን ጨምሮ 47 የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች መንግስት ኢንተርኔት በመዝጋት የሚያደርገውን አፈና ያቁም ሲሉ ለጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ መጠየቃቸውም ይታወሳል።
https://rb.gy/yblpu
ዜና፡ የኢትዮ ቴሌኮም 2015 በጀት ዓመት 75.8 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

የኢትዮ ቴሌኮም 2015 በጀት ዓመት 75.8 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት የእቅዱን 101% ማሳካቱን አስታወቀ፡፡

የተገኘው ገቢ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ23.5% ብልጫ አለው ያለው ሪፖርቱ የተገኘው ገቢ በአገልግሎት አይነት ሲታይ የድምጽ አገልግሎት 43.7% ድርሻ ሲኖረው ዳታና ኢንተርኔት 26.6%፣ ዓለም አቀፍ ገቢ 9%፣ እሴት የሚጨምሩ አገልግሎቶች 6.9%፣ የቴሌኮም መጠቀሚያ መሣሪያዎች (ቀፎ፣ ዶንግል፣ ሞደም) 4.7% እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች 7.2% ድርሻ አላቸው ብሏል፡፡

የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ አገልግሎቶች አጠቃላይ 164.1 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማግኘት የተቻለ ሲሆን አፈጻጸሙም 107.8% መሆኑ በሪፖርቱ ተገልጧል፡፡
ኢትዮ ቴልኮም ዓለም ላይ ካሉ 774 ኦፕሬተሮች መካከል በሞባይል ደንበኛ ቁጥር በአፍሪካ 2ኛ ደረጃ ፣ በዓለም ደግሞ 21ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

https://rb.gy/gjwjv
የአዲስ አበባ ዪንቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በአቪዬሽን ዘርፍ ከቦይንግ ኩባንያ ጋር በትብብር መስራት የሚያስችለውን አጋርነት መመስረቱ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና ከዩኒቨርሲቲው ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎች ለኢትዮጵያ አየር መንገድ እድገት መሰረት መሆናቸውን ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከቦይንግ ኩባንያ ጋር የጀመረው አጋርነት በአፍሪካ ያለው የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ በመላው ዓለም ተወዳዳሪ እንዲሆን የሚረዳ ብቁ ባለሙያ ለማፍራት እንደሚያስችል ተናግረዋል።

የቦይንግ ኩባንያ በሚያደርገው ድጋፍ የሚገነባው የንፋስ ዋሻ የሙከራ መለማመጃ ተማሪዎች በምድር ላይ የሚገጠሙ የተለያዩ ዲዛይኖችንና ሞዴሎችን ለማወቅ ይረዳቸዋል ብለዋል። በተጨማሪም ተማሪዎች የፈጠራ ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበት፣ የአቪዬሽንና 'ኤሮስፔስ' የምርምር ላቦራቶሪ አቅም የሚገነባበት መሆኑን ኢዜኣ ዘግቧል።

የአዲስ አበባ ዪንቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቢቂላ ተክሉ፤ በቦይንግ ኩባንያና በኢንስቲትዩቱ መካከል የተመሠረተው አጋርነት በአቪዬሽንና በ 'ኤሮስፔስ' ኢንዱስትሪው የአቅም ግንባታ ስራ ማከናወን የሚያስችላቸው ነው ብለዋል።
የተደረገው ድጋፍ ተማሪዎች የፈጠራ ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበት፣ የአቪዬሽንና 'ኤሮስፔስ' የምርምር ላቦራቶሪ አቅም የሚገነባበት መሆኑን ገልጸዋል።
ዜና፡ ዶ/ር ወንደወሰን አሰፋና መስከረም አበራን ጨምሮ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ 24 ተከሻሾች የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ተደርጎ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ተሰጠ

በሽብር ወንጀል የተከሰሱትን ዶ/ር ወንደወሰን አሰፋ፣ መስከረም አበራ፣ ሲሳይ አውግቸው (ረ/ፕ) እና ጎበዜ ሲሳይን ጨምሮ 24 ተከሳሾች የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ።

ፍርድ ቤቱ የተከሻሾቹን የዋስትና መብት ጥያቄ ውድቅ ያደረገው ተከሳሶቹ የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ/ለ/፣ 35 እና 38 እና የሽብር ወንጀልን ለመቆጣጠር እና ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1176/ 2012 አንቀፅ 3 ንዑስ ቁጥር 2 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ የህግ ክልከላ አለበት በሚል መሆኑን ፋና ዘግቧል።
https://rb.gy/q5ncb
ዜና፡ "ከአጎራባች ክልሎች ጋር ያለውን እህትማማችነት እና ወንድማማችነት የበለጠ ለማጎልበት አጠናክረን እንቀጥላለን" - ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ "ከሁሉም አጎራባች ክልሎች ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ እህትማማችነትና ወንድማማችነትን የበለጠ ለማጎልበት አጠናክረን እንቀጥላለን" ሲሉ ገለፁ፡፡

ርእሰ መሥተዳድሩ በአንድ በኩል ልማታችን እንዳይስተጓጎል፣ በሌላ በኩል ደግሞ የሰላም እጦት የፈጠረውን ተግዳሮት ለመቋቋም ጥረት ሲደረግ ቆይቷል በማለት ገልፀው "በአስቸጋሪ ኹኔታዎች ውስጥ ኾነንም የተሻለ የልማት እና የኢኮኖሚ ለውጥ አስመዝግበናል" ሲሉም ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ "የክልሉ ሕዝብ የመጀመሪያ ጥያቄ ልማት እና የሕግ የበላይነት መከበር ነው" ሲሉ ገልጸዋል። መንግሥት የመሪነቱን ተግባር በትክክል በመወጣት የሕዝቡን ጥያቄ ፈጥኖ መመለስ አለበት ሲሉም ተናግረዋል። በተለይም ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት በመኾኑ መላ የክልሉ ሕዝብ ከመንግሥት ጎን በመቆም ሰላሙን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

https://rb.gy/mukvt
ለአርቲስት #እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ተሰጣት

#እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት #እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎችባስመረቀበት ወቅት ነው ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት የሰጠው፡፡

በመርሐ ግብሩ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር)÷አርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የሀገሯን ሙዚቃና እና ባህል እንዲሁም የተወለደችበትን የአገው ህዝብ ባህልና ቋንቋ ለዓለም ህዝብ በማስተዋወቋ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስቷ የክብር ዶክትሬት ሲሰጣት ታላቅ ክብር ይሰማዋል ብለዋል፡፡

ጂጂን ማክበር ጥበብን ማክበር ነው ያሉት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር)÷ጂጂን ማክበር የኢትዮጵያን ታሪክና ጀግኖችን እንዲሁም ፍቅርንና አንድነትን ማክበር ነውም ብለዋል፡፡

ተቋሙ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲውን በታሪክ ሊያስታውስ የሚችል የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ለድንቋ ድምጻዊትና ለጥበብ ንግስት ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) በሚሰጥበት እለት መሆኑ መርሐ ግብሩን ለየት ያደርገዋል ብለዋል፡፡

ፋና
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቢኒያም በለጠ እና ለአጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ የክብር ዶክትሬት ሰጠ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራችና ስራ አስኪያጅ ቢኒያም በለጠ እና ለአጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

ዩኒቨርሲቲው የክብር ዶክተሬቱን የሰጠው በዛሬው እለት ተማሪዎችን በሚሊኒየም አዳራሽ እያስመረቀ ባለበት መርሃ-ግብር ነው።

በስነ ስርዓቱ ላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራችና ስራ አስኪያጅ ቢኒያም በለጠ የክብር ዶክትሬት አበርክቶላቸዋል።

የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ከ7500 በላይ አረጋዊያንን እና የአምዕሮ ህሙማንን ከወደቁበት በማንሳት "ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው"በሚል እያደረጉት ባለው ሰብዓዊ አገልግሎት ዩኒቨርስቲው የክብር ዶክትሬት ሰጥቷቸዋል።

በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ለአርቲስት ደበበ እሸቱ በኪነጥበብ መስክ ላበረከተው አስተዋጽኦ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

አርቲስት ደበበ እሸቱ በአገር ፍቅርና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ (የአሁኑ ብሔራዊ ቴአትር) መድረክ ላይ ለረዥም ዓመታት በተዋናይነትና በአዘጋጅነት ሰርቷል።

በተለያዩ ፊልሞች ላይ በመሪ ተዋናይነት የተሳተፈ ሲሆን ሆሊውድ በተሰራው 'ሻፍት ኢን አፍሪካ' በተሰኘው ፊልም ላይ በመሳተፍም ስሙን በደማቁ ፅፏል።

ከጋዜጠኛነት በተጨማሪ በሬድዮና በቴሌቪዥን ስራዎችም ላይ ተሳትፏል። 'ያላቻ ጋብቻ'፣ 'ሮሚዎና ዡልየት' እና 'ዳንዴው ጨቡዴ' ከተወነባቸው ስራዎች መካከል ይጠቀሳሉ።


https://www.facebook.com/100076048904470/posts/pfbid02eFoNwM6s3zBNodmo56fNTJKTwzVufJdLdnmbwGXwwRTZZhzUmpx9yBNaC7vVYA6al/?app=fbl