ዜና፡ በ #ኦሮሚያ ክልል #ባሌ ዞን አል-ሸባብ እየተንቀሳቀሰ ነው ፤ የጸጥታ ስጋት ፈጥሯል በማሉን የአካባቢው ባለስልጣናት አስተባበሉ
የ #ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ባለ 130 ገጽ ብሔራዊ ምርመራ ሪፖርት፤ “በባሌ ዞን ደን ውስጥ፤ የውጭ ዜጎች በሆኑና በ #ኬንያ፣ #ሶማሊያ እና #ኡጋንዳ በሠለጠኑ ሰዎች የ #አል-ሸባብ የሽብር ቡድን መመስረቱ” በዞኑ የፀጥታ ስጋት መሆኑን አስታውቋል።
ነገር ግን የባሌ ዞን ፖሊስ ኃላፊ ረዳት ረዳት ኮሚሽነር ጀይላን አማን፤ በባሌ ዞን የሚንቀሳቀስ የአልሸባብ ቡድን አለመኖሩን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል። በአካባቢው በቡድኑ የተገደሉ ሲቪሎችም ሆኑ የፀጥታ ኃይል አባላት እንደሌሉ በመግለጽ ስለ ኢሰመኮ ሪፖርት እንደማያውቁም ተናግረዋል።
ነገር ግን የምስራቅ ባሌ ዞን የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ናታ ዳባ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት፤ በጥቅምት 2016 አራት የአልሸባብ አባላት ተይዘው ለመከላከያ ሰራዊት ተላልፈዋል፤ አንደኛው ደግሞ ተገድሏል።
ተጨማሪ ለማንበብ፡ https://wp.me/pfjhHd-14J

Addis standard
ዜና፡ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን አልሻባብ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን እና የጸጥታ ስጋት ፈጥሯል መባሉን ባለስልጣናት አስተባበሉ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23/2016 ዓ/ም፡- በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን አልሻባብ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን እና በርካታ የዞኑን ፖሊስ አባላትና ሚሊሻዎችን ገድሏል መባሉን የአካባቢው ባለስልጣናት አስተባበሉ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ባለ 130 ገጽ ብሔራዊ ምርመራ ሪፖርት፤ “በባሌ ዞን ደን ውስጥ፤ የውጭ ዜጎች በሆኑና በኬንያ፣ ሶማሊያ እና ኡጋንዳ…
ዜና: ለበልግ ወቅት የሚያስፈልገውን "የአፈር #ማዳበሪያ ሙሉ በሙሉ አቅርቢያለሁ" ሲል ግብርና ሚኒስቴር ገለጸ
ለበልግ እርሻ ልማት 469 ሺህ 80 ነጥብ 84 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ ታቅዶ “ሙሉ በሙሉ ማቅረብ መቻሉን” ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ለ2016/17 የምርት ዘመን 19 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እንደሚገዛና ከዚህ ውስጥ 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል ዩሪያ 11 ነጥብ 19 ሚሊየን ደግሞ ኤን ፒ ኤስ ማዳበሪያ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
የ2016/17 ምርት የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት እና ሥርጭት የእስከ አሁን አፈጻጸም ጥሩ መሆኑን ጠቁሞ በአቅርቦት ደረጃ 1 ሚሊየን 678 ሺህ 730 ቶን ግዥ ተፈጽሟል ብሏል።
ካለፈው ዓመት የከረመውን 56 ሺህ 193 ነጥብ 96 ሜትሪክ ቶን ጨምሮ ለምርት ዘመኑ ጥቅም ላይ ለማዋል በአዝመራ ወቅቶች ተለይቶ መታቀዱንም ጠቁሟል።
በዚሁ መሰረት ለበጋ መስኖ ልማት 390 ሺህ 160 ሜትሪክ ቶን ለማቅረብ ታቅዶ ሙሉ በሙሉ ማቅረብ መቻሉን እና 66 ሺህ 497 ነጥብ 65 ሜትሪክ ቶን ለተጠቃሚው መሠራጨቱን ነው የገለጸው።
እንዲሁም ለበልግ እርሻ ልማት 469 ሺህ 80 ነጥብ 84 ሜትሪክ ቶን ለማቅረብ ታቅዶ ሙሉ በሙሉ ማቅረብ መቻሉን በመግለጽ÷ 141 ሺህ 964 ነጥብ 21 ሜትሪክ ቶን ለተጠቃሚው መሠራጨቱን አመላክቷል።
እስከ መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ባለው ጊዜም 973 ሺህ 774 ነጥብ 40 ሜትሪክ ቶን ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዟል ሲል ሚኒስቴሩ መግለጹን ከፋና ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
==
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n

ዜና: አቶ #አደም ፋራህን በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ አዲስ ሹመት ተሰጠቸው
ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ አቶ አደም ፋራህን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊ አድርገው መሾማቸው ተገለጸ።
ጠ/ሚኒስትር ቢሮ በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ አቶ አደም ፋራህን ከዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊ ተደርገው ተሹመዋል ብሏል።
የቀድሞ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ የነበሩት አደም ፋራህ የገዢው ፓርቲ ብልጽግና ምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት በመሆን ሲያገለግሉ እንደነበር ይታወቃል።
በቀጥታ በጠ/ሚኒስትሩ የተሾሙት አደም ፋራህ በተሰጣቸው ሹመት መሰረት እንደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የሰብአዊ መብት ኮሚሽን መሰል የዲሞክራሲ ተቋማትን እንቅስቃሴ ይመራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek

ዜና: #ንግድ ባንክ ገንዘቤን ያለአግባብ ወስደው አልመለሱም ያላቸውን የደንበኞቹን ፎቶ ይፋ አደረገ
#የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲስተም የማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ያለአግባብ ገንዘቤን ወስደው አልመለሱልኝም ያላቸው ደንበኞቹን ፎቶ በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ይፋ አድርጓል።
ምስላቸውን ያጋራው ደንበኞቹ “ከ 305ሺ እስከ 108 ሺ ብር ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ናቸው ብሏል።
ከባንኩ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ መሠረት 10,857 የሚሆኑ ግለሰቦች ያለባቸውን ገንዘብ አጠናቀው መመለሰቻውን ጠቁሟል።
ባንኩ ገንዘቡን ለማስመለስ በተከታታይ ስለሚወስዳቸው እርምጃዎች በተደጋጋሚ ባሳወቀው መሠረት እስካሁን ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን የመጀመሪያ ዙር ፎቶግራፍ ይፋ አድርጊያለሁ ብሏል።
የገንዘብ መመለሻ ጊዜውን ለመጨረሻ ጊዜ እስከ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም አራዝሚያለሁ ሲል ከቀናት በፊት ያስታወቀው ባንኩ የተራዘመው ግዜ ሳይጠናቀቅ ገንዘብ ያልመለሱ ደንበኞቹን ምስል ለምን ይፋ እንዳደረገ የጠቀሰው ምክንያት የለም።
ባንኩ ትላንት በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ባጋራው መረጃ “ይህን የመጭረሻ እድል ተጠቅማችሁ ገንዘቡን እድትመልሱ” አሳስባለሁ፣ በተሰጠው የጊዜ ገደብ የማይመልሱትን ወደ ህግ አቀርባለሁ ሲል አስጠንቅቋል።
መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ባንኩ ባወጣው መግለጫ እስካሁን ገንዘቤን ያልመለሱ ሰዎች ብዛት 117 ብቻ ነው ሲል መግለጹ ይታወሳል፤ ትላንት አመሻሽ ላይ ፎቷቸው ይፋ የተደረገው ሰዎች ብዛት 67 ብቻ ነው።

ዜና: #የአሜሪካ መንግስት ልዑክ #ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በፕሪቶርያ ስምምነት እና በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መከረ
የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ዋና ሃላፊ ዳምያን ሙፊ የተመራ ልዑክ በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ጉብኝት እያካሄደ ይገኛል።
ልዑኩ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋናው አረጋ ጋር ተወያይቷል፤ የውይይታቸው ዋነኛ አጀንዳም #የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እና የሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የኢትዮጵያ መንግስት አሁንም በሀገሪቱ የሚስተዋሉ የፖለቲካ ልዩነቶች በውይይት እንዲፈቱ የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ሚኒስትር ዴኤታው ለሉዑካኑ እንደገለጹላቸው መረጃው አመላክቷል።
አምባሳደር ምስጋናው በተጨማሪም መንግስታቸው የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እያደረገው ስላለው ጥረት፣ በሀገሪቱ ሰላም ለማስፋን ስለሚደረጉ ጥረቶች እና ስለ ኢኮኖሚ ልማት እንቅስቃሴው ለሉዑክ ቡድኑ ገለጻ ማድረጋቸውንም ጠቁሟል።
ሁለቱ ሀገራት የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያደርጉትን ውይይት ለማስቀጠል መስማማታቸውንም ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ የፌስቡክ ገጹ ያጋራው መረጃ ያሳያል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ዋና ሃላፊ ዳምያን ሙፊ የተመራ ልዑክ በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ጉብኝት እያካሄደ ይገኛል።
ልዑኩ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋናው አረጋ ጋር ተወያይቷል፤ የውይይታቸው ዋነኛ አጀንዳም #የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እና የሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የኢትዮጵያ መንግስት አሁንም በሀገሪቱ የሚስተዋሉ የፖለቲካ ልዩነቶች በውይይት እንዲፈቱ የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ሚኒስትር ዴኤታው ለሉዑካኑ እንደገለጹላቸው መረጃው አመላክቷል።
አምባሳደር ምስጋናው በተጨማሪም መንግስታቸው የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እያደረገው ስላለው ጥረት፣ በሀገሪቱ ሰላም ለማስፋን ስለሚደረጉ ጥረቶች እና ስለ ኢኮኖሚ ልማት እንቅስቃሴው ለሉዑክ ቡድኑ ገለጻ ማድረጋቸውንም ጠቁሟል።
ሁለቱ ሀገራት የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያደርጉትን ውይይት ለማስቀጠል መስማማታቸውንም ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ የፌስቡክ ገጹ ያጋራው መረጃ ያሳያል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
ዜና: “ግድቡ እንደ #ላሊበላ፣ #አክሱም እና #ፋሲል የሀገር ኩራት የሚኾን ሃብት ነው” ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
#የህዳሴ ግድብ የመሠረተ ድንጋይ የተጣለበት 13ኛ ዓመት በተለያየ መንገድ እየተከበረ ይገኛል።
በታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አዘጋጅነት በዓሉ “በኅብረት ችለናል" በሚል መሪ መልእክት በአዲስ አበባ በፓናል ውይይት እና በፎቶ አውደ ርዕይ እየተከበረ ነው፡፡
የበዓሉ የክብር እንግዳ ምክትል ጠ/ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብት የታደለች ሀገር ብትኾንም ሃብቶቿን በተገቢው ልክ እየተጠቀመች አለመኾኗን ገልጸው “የህዳሴ ግድቡ ግንባታ ሲጠናቀቅ ኩራታችን የሚኾን ሃብት ነው” ብለዋል።
“ግድቡ እንደ ላሊበላ፣ አክሱም እና ፋሲል የሀገር ኩራት የሚኾን ሃብት ነው” ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የግንባታው ሥራ ሳይቋረጥ እዚህ የመድረሱ ሚስጥር የኅብረት ሥራው ተጠናክሮ በመቀጠሉ ነው ማለታቸውን ከአሚኮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

“መንግሥት አሳሳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መነጋገር አይፈልግም” ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ከተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ትላንት ሰኞ መጋቢት 23/2016 ዓ.ም. ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ የአስራ አንድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት አባላት ግን በውይይቱ ሳይሳተፉ ቀርተዋል።
የጥምረቱ አባላት በውይይቱ ላለመገኘት የወሰኑት “መንግሥት አሳሳቢ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መነጋገር ስለማይፈልግ” መሆኑን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ፕሮፌሰር መረራ እንዳሉት ውይይቱ “ዝም ብሎ የለበጣ እና ከፎቶ ባለፈ ምንም ቁም ነገር እንደማያመጣ ሰለተረዳን እና ተቃዋሚዎችን አናገርኩ የሚል የይምሰል በመሆኑ” ላለመሳተፋቸው ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ባለፉት ስድስት ዓመታት በአገር ውስጥ እንዲሁም ኔዘርላንድ እና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በውጭ አገራት ከእሳቸውም እንዲሁም ከተወካዮቻቸው ጋር ድርድር ቢደረግም ፍሬ አላፈራም ብለዋል ፕሮፌሰሩ።
ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎችን ጨምሮ በአገሪቱ ለበርካታ ሰዎች እልቂት እየሆኑ ያሉትን ግጭቶች እና ጦርነቶችን በሰላማዊ መንገድ እንዴት ይቋጩ? በሚለው ጉዳይ ላይ “መንግሥት መነጋገርም ሆነ ወደ መደራደር አይሄድም” ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cp044lg3593o

ዜና: የተፈጠረው #የነዳጅ እረጥት እስከ ነገ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት ድረስ ይቀረፋል ሲል #የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ገለጸ
ከሰሞኑ አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች ከወትሮው በተለየ ረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች ማስተዋል የተለመደ ሆኗል።
ይሄንንም ተከትሎ የረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች ምክንያት ምን እንደሆነ የተጠየቀው የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የነዳጅ እጥረት የተፈጠረው ጅቡቲ ላይ የዘነበውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ድልድይ በመሰበሩ ነው ብሏል።
በተጨማሪም ነዳጅ የጫነ አንድ የነዳጅ ቦቴ ተገልብጦ መንገድ መዘጋጋት በማስከተሉ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ይስማ አለም ምህረቱ ለኢቲቪ አስረድተዋል፡፡
ችግሩን ለመቅረፍ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በድሬደዋ በኩል እንዲገቡ ተደርጓል ያሉት ስራ አስፈጻሚው ይሄንኑ ተከትሎ ትናንት መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰአት ጀምሮ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች መግባት መጀመራቸውን አረጋግጠዋል፡፡
አክለውም ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም እና ነገ ነዳጅ የጫኑ ተጨማሪ ቦቴዎች እንደሚገቡ እና ችግሩ እስከ ነገ ጠዋት ድረስ እንደሚቀረፍ ገልጸዋል፡፡
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
ከሰሞኑ አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች ከወትሮው በተለየ ረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች ማስተዋል የተለመደ ሆኗል።
ይሄንንም ተከትሎ የረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች ምክንያት ምን እንደሆነ የተጠየቀው የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የነዳጅ እጥረት የተፈጠረው ጅቡቲ ላይ የዘነበውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ድልድይ በመሰበሩ ነው ብሏል።
በተጨማሪም ነዳጅ የጫነ አንድ የነዳጅ ቦቴ ተገልብጦ መንገድ መዘጋጋት በማስከተሉ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ይስማ አለም ምህረቱ ለኢቲቪ አስረድተዋል፡፡
ችግሩን ለመቅረፍ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በድሬደዋ በኩል እንዲገቡ ተደርጓል ያሉት ስራ አስፈጻሚው ይሄንኑ ተከትሎ ትናንት መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰአት ጀምሮ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች መግባት መጀመራቸውን አረጋግጠዋል፡፡
አክለውም ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም እና ነገ ነዳጅ የጫኑ ተጨማሪ ቦቴዎች እንደሚገቡ እና ችግሩ እስከ ነገ ጠዋት ድረስ እንደሚቀረፍ ገልጸዋል፡፡
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
አቶ #አደም_ፋራህ በፌደራል መንግስት እና በ #ህወሃት መካከል ሳይደረግ የዘገየውን የፖለቲካ ውይይት ለማስጀመር ወደ #መቀለ አመሩ
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊ ተደርገው የተሾሙት አቶ አደም ፋራህ፤ በፌደራል መንግስት እና በህወሃት መካከል የተዘገየውን የፖለቲካ ውይይት ለማስጀመር ወደ መቀለ አምርተዋል።
ህወኃት ባሰራጨው መረጃ መሰረት፤ አቶ አደም ፋራህ በ #ፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ለሁለት አመታት የተካሄደውን ደም አፋሳሽ ጦርነት መሰረታዊ ምክንያት ላይ የፖለቲካ ውይይት ለማስጀመር መቐለ ሲገቡ በህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካዔል አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን ከሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋርም ተገናኝተዋል።
የገዥው ብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ ከመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ እና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜን ጨምሮ ከሌሎች የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመሆን ነው ወደ መቀሌ ያመሩት።
በትግራይ በኩል በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በስብሰባው ላይ ተሳትፈዋል።
እንደ ህወሓት መረጃ መሰረት፤ በውይይቱ ወቅት ሁለቱም ወገኖች በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል የፖለቲካ ውይይት ቀደም ብሎ መጀመር እንዳለበት ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ሁለቱም ወገኖች ከዚህ በኋላ መደበኛ ውይይቶችን ለመጀመር ተስማምተዋል።

ዜና: አንድ #ተከራይ ቤት ተከራይቶ ውል ከፈፀመ በኋላ ለሁለት ዓመት የቤት ኪራይ መጨመር እና ቤት ማስለቀቅ የሚከለክል አዋጅ ጸደቀ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው 19ኛ መደበኛ ስብሰባው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅን መርምሮ አፅድቋል፡፡
በአዋጁ መሠረት አንድ ተከራይ ቤት ተከራይቶ ውል ከፈፀመ በኋላ ለሁለት ዓመት የቤት ኪራይ መጨመር እና ቤት ማስለቀቅ አይቻልም ተብሏል፤ ተከራይ ቤቱን ከጎዳ እና ሌሎች አዋኪ ተግባራትን ከፈፀመ ግን በአዋጁ አንቀፅ 16 መሠረት ቤቱን ለመልቀቅ እንደሚገደድም ተደንግጓል።
ወደፊት ለሚደረግ ጭማሪ አሁን ላይ ያለው የኪራይ ዋጋ መሠረት ተደረጎ በመንግሥት የሚሰላ እንደሚሆንም በአዋጁ ተገልጿል።
ለቤት ኪራይ የሚሆን አዲስ ቤት የገነቡ አካላት እንደማበረታቻ ለ4 ዓመት ያህል በድርድር ዋጋ ማስቀመጥ የሚችሉ ሲሆን፤ ከዛ በኋላ ግን አዋጁ ተፈፃሚ እንደሚሆንባቸው ተገልጿል።
ለዚህ አዋጅ ተፈፃሚነት ምዝገባው በቀጣይ ባሉት 3 ወራት ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መስራታቸውም ተገልጿል።
ውል አለማስመዝገብ አስተዳደራዊ ቅጣት የሚያስከትል መሆኑ ተገልፆ፤ እስከ 3 ወር የሚደርስ የቤት ኪራዩን ዋጋ ያስቀጣልም ተብሏል።
አዋጁ በርካታ አዳዲስ አሰራሮችን ያካተተ ሲሆን ያከራይንም ሆነ የተከራይን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ በመሆኑ ህብረተሰቡ መብቱን እና ግዴታውን በማወቅ ለተፈፃሚነቱ እንዲተባበር ጥሪ መቅረቡን ከኢቲቪ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
======
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው 19ኛ መደበኛ ስብሰባው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅን መርምሮ አፅድቋል፡፡
በአዋጁ መሠረት አንድ ተከራይ ቤት ተከራይቶ ውል ከፈፀመ በኋላ ለሁለት ዓመት የቤት ኪራይ መጨመር እና ቤት ማስለቀቅ አይቻልም ተብሏል፤ ተከራይ ቤቱን ከጎዳ እና ሌሎች አዋኪ ተግባራትን ከፈፀመ ግን በአዋጁ አንቀፅ 16 መሠረት ቤቱን ለመልቀቅ እንደሚገደድም ተደንግጓል።
ወደፊት ለሚደረግ ጭማሪ አሁን ላይ ያለው የኪራይ ዋጋ መሠረት ተደረጎ በመንግሥት የሚሰላ እንደሚሆንም በአዋጁ ተገልጿል።
ለቤት ኪራይ የሚሆን አዲስ ቤት የገነቡ አካላት እንደማበረታቻ ለ4 ዓመት ያህል በድርድር ዋጋ ማስቀመጥ የሚችሉ ሲሆን፤ ከዛ በኋላ ግን አዋጁ ተፈፃሚ እንደሚሆንባቸው ተገልጿል።
ለዚህ አዋጅ ተፈፃሚነት ምዝገባው በቀጣይ ባሉት 3 ወራት ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መስራታቸውም ተገልጿል።
ውል አለማስመዝገብ አስተዳደራዊ ቅጣት የሚያስከትል መሆኑ ተገልፆ፤ እስከ 3 ወር የሚደርስ የቤት ኪራዩን ዋጋ ያስቀጣልም ተብሏል።
አዋጁ በርካታ አዳዲስ አሰራሮችን ያካተተ ሲሆን ያከራይንም ሆነ የተከራይን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ በመሆኑ ህብረተሰቡ መብቱን እና ግዴታውን በማወቅ ለተፈፃሚነቱ እንዲተባበር ጥሪ መቅረቡን ከኢቲቪ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
======
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዜና: #የህዳሴ ግድብ ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 50 ቢሊየን ብር ያስፈልጋል ተባለ
የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አጠቃላይ የፋይናንስ ወጪ 191 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መድረሱን እና ቀሪ የግድቡን የግንባታ ሥራዎች ለማጠናቀቅም 50 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ አስታወቁ።
የኮንትራት ማሻሻያ መደረጉ፣ የተጣበበ የፕሮጀክት ጊዜ ሰሌዳና በግንባታ ወቅት በግድቡ መሠረት ላይ ያጋጠመ ልል ድንጋይ መኖሩ እንዲሁም የልምድ ማነስ እና የጥራትና ልኬት በሚፈለገው ደረጃ አለመሆን በፕሮጀክቱ ግንባታ ላይ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንደነበሩ ጠቅሰዋል።
ከ10 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሌት ውስጥ የ10 ነጥብ 65 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ሙሌት ተጠናቋል ሲሉ የተናገሩት ስራ አስኪያጁ በአሁኑ ወቅት የግድቡ የሲቪል ሥራዎች 99 ነጥብ 2 በመቶ እንዲሁም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች አፈፃፀም 79 በመቶ መድረሱንም ጠቁመዋል።
https://wp.me/pfjhHd-14X

የህዳሴ ግድብ ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 50 ቢሊየን ብር ያስፈልጋል ተባለ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25/2016 ዓ.ም፡- የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አጠቃላይ የፋይናንስ ወጪ 191 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መድረሱን እና ቀሪ የግድቡን የግንባታ ሥራዎች ለማጠናቀቅም 50 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ አስታወቁ። ስራ አስኪያጁ ይህንን ያስታወቁት “በህብረት ችለናል” በሚል መሪ ቃል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ…
ዜና: አይ ኤም ኤፍ እና #ኢትዮጵያ ሳይስማሙ ቀሩ
ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ሲደራደር የቆየው የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (#አይኤምኤፍ) የልዑካን ቡድን ከስምምነት ላይ ሳይደርስ ጉብኝቱን ማጠናቀቁን ሮይተርስ አስታወቀ።
#የፓሪስ ክለብ በመባል የሚታወቀው የአበዳሪ አገራት ቡድን እስከ መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ከአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ጋር ስምምነት ላይ የማትደርስ ከሆነ ብድር ለመክፈል የጠየቀችው የእፎይታ ግዜ ተቀባይነት እንደማያገኝ መግለጹ ይታወሳል።
በዚህም ሳቢያ ከአለም አቀፍ አበዳሪ ሀገራት ለኢትዮጵያ እንሰጠዋለን ያሉትን እስከ ሚቀጥለው የፈረንጆቹ አመት 2025 የሚቆይ የብድር መክፈያ የእፎይታ ግዜ ይሰርዙት ወይንም ተግባራዊ ያድርጉት የታወቀ ነገር አለመኖሩን የዜና አውታሩ በዘገባው አመላክቷል።
የአይኤምኤፍ ልዑክ ቡድን የሀገሪቱ ባለስለጣናት ያቀረቡትን የኢኮኖሚ ፕሮግራም ማገዝ በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ባካሄደው ውይይት ጥሩ መሻሻሎች ተስተውለዋል ሲል ተቋሙ መግለጹን ሮይተር በዘገባው አስታውቋል።
በአይኤምኤፍ እና በኢትዮጵያ መካከል የሚካሄደው ውይይት በሚያዚያ ወር መጨረሻ አከባቢ በዋሽንግተን እንደሚቀጥል የዜና አውታሩ በዘገባው ጠቁሟል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ሲደራደር የቆየው የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (#አይኤምኤፍ) የልዑካን ቡድን ከስምምነት ላይ ሳይደርስ ጉብኝቱን ማጠናቀቁን ሮይተርስ አስታወቀ።
#የፓሪስ ክለብ በመባል የሚታወቀው የአበዳሪ አገራት ቡድን እስከ መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ከአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ጋር ስምምነት ላይ የማትደርስ ከሆነ ብድር ለመክፈል የጠየቀችው የእፎይታ ግዜ ተቀባይነት እንደማያገኝ መግለጹ ይታወሳል።
በዚህም ሳቢያ ከአለም አቀፍ አበዳሪ ሀገራት ለኢትዮጵያ እንሰጠዋለን ያሉትን እስከ ሚቀጥለው የፈረንጆቹ አመት 2025 የሚቆይ የብድር መክፈያ የእፎይታ ግዜ ይሰርዙት ወይንም ተግባራዊ ያድርጉት የታወቀ ነገር አለመኖሩን የዜና አውታሩ በዘገባው አመላክቷል።
የአይኤምኤፍ ልዑክ ቡድን የሀገሪቱ ባለስለጣናት ያቀረቡትን የኢኮኖሚ ፕሮግራም ማገዝ በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ባካሄደው ውይይት ጥሩ መሻሻሎች ተስተውለዋል ሲል ተቋሙ መግለጹን ሮይተር በዘገባው አስታውቋል።
በአይኤምኤፍ እና በኢትዮጵያ መካከል የሚካሄደው ውይይት በሚያዚያ ወር መጨረሻ አከባቢ በዋሽንግተን እንደሚቀጥል የዜና አውታሩ በዘገባው ጠቁሟል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
ዜና: ከመርከብ የሚነሳ እሳት መከላከል የሚያስችል ስልጠና የወሰዱ #የኢትዮጵያ ባህር ሃይል አባላት በባቦጋያ ማሪታይም አካዳሚ ሰልጥነው ተመረቁ
#ከመርከብ የሚነሳ እሳት እንዴት መከላከል እና የእሳት አደጋ ከተነሳም በፍጥነት መቆጣጠር የሚያስችል ስልጠና የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ማሪታይም ባቦጋያ አካዳሚ ለኢትዮጵያ ባህር ሃይል አባላት መስጠቱ ተገለጸ።
በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ለተመራቂዎች የሥራ መመሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ዋና አዛዥ ተወካይ ሬር አዲሚራል ናስር አባድጋ የባህር ሃይል ሠልጣኝ ተመራቂዎች የኢትዮጵያ ባህር ሃይል የጀርባ አጥንት በመሆናችሁ የሚጠበቅባችሁን ሁሉ መወጣት አለባችሁ ብለዋል።
አዛዡ አክለውም የባህር ሃይል አባል መሆንና መርከብ ላይ ግዳጅን መወጣት ጥሩ ሥነ-ምግባር፤ ወታደራዊ ዲሲፒሊን፤ ጠንካራ ግዳጅ አፈፃፀምና የህይወት መስዋዕትነትን ጭምር የሚጠይቅ ሙያ በመሆኑ እናንተ ተመራቂ የመርከብ ሙያተኞች በስልጠና ያገኛችሁትን አቅም ወደ ተግባር በመለወጥ ሙያዊ ሃላፊነታችሁን ልትወጡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ባቦጋያ አካዳሚ ዲን ቺፍ ቴድሮስ ሚሊዮን ተመራቂ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል አባላት በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር የተደገፈ ሥልጠና በአግባቡ መከታተላቸውን ገልፀዋል።
ከተመራቂ አባላቱ መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት መርከብ ላይ ስንወጣ በርካታ ውጣ ውረዶች የበዛበት በመሆኑ በመርከብ ላይ የሚነሳ የእሳት አደጋን በቀላሉ ለማጥፋት የሚያስችል ሙያዊ ስልጠና ወስደናል ብለዋል።
=========

ዜና: #የጃፓን መንግስት ከ1875 ጀምሮ ለውጭ ሃገር ዜጎች የሚሰጠውን አንጋፋና ክብር ያለዉ ሽልማት #ለደራርቱ ቱሉ አበረከተ
#የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት የተበረከተላቸውን የወርቅ ጨረር ያለውን ኒሻን ሽልማታቸውን ተረከቡ።
ይህ እውቅናና ሽልማት እኤአ ከ1875 ጀምሮ ለውጭ ሃገር ዜጎች በጃፓን መንግስት የሚሰጥ አንጋፋና ክብር ያለዉ መሆኑን ከፌደሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ከኢትዮጵያ የወርቅ ጨረር ያለው ኒሻን ሽልማት ከጃፓን መንግስት ሲሰጥ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የመጀመሪያዋ መሆኑም ተጠቁሟል።
በጃፓን እና በኢትዮጵያ መካከል በስፖርት ዲፕሎማሲ እና ልውውጥ ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅዖ፣ በሌሎች ሀገራት እና አካባቢዎች መካከል ያለውን ወዳጅነት ለማሳደግ፣ ለአትሌቲክስ እድገት፣ ለአገር ሰላም ላበረከቱት አስተዋፅኦ እውቅና በመስጠት በዓለም አቀፍ መስኮች የላቀ ስኬት ምክንያት ሽልማቱን አግኝተዋል በተብሏል።
ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ሽልማታቸውን በኢትዮጵያ ከጃፓን አምባሳደር ሚስተር ሺባታ ሂሮኖሪ እጅ መረከባቸዉን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያጋራው መረጃ ያሳያል።