ሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል አከባባር በፎቶ
የ #ኦሮሞ ህዝብ የምስጋና ቀን የሆነው የ #ሆረ_ፊንፊኔ_ኢሬቻ በዓል በባህላዊ አልባሳት ያሸበረቁ ተሳታፊዎች በተገኙበት በ #አዲስ_አበባ እየተከበረ ይገኛል።
ልክ እንደ ሆረ ፊንፊኔ የኦሮሞ ህዝብ ተሰባሰቦ 'ከክረምት ወራት ወደ ብራ ላሸጋገረው' ፈጣሪው (ዋቃ) ምስጋና የሚያቀርብበት የ #ሆረ_አርሰዴ_ኢሬቻ በዓልም በነገው ዕለት በ #ቢሾፍቱ በድምቅት ተከብሮ ይውላል።
ፎቶ: አዲስ ስታንደርድ

የ #ሆረ_ፊንፊኔ_ኢሬቻ በዓል በሰላም ተጠናቅቋል- የ #ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብና አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ ከተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እና ከጎረቤት ሀገራት የመጡ እንግዶች እንዲሁም የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች የታደሙበት የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቋል።
ፎቶ: አዲስ ስታንዳርድ

ዜና: #በአማራ ክልል “ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ የዘፈቀደ እስር ተፈጽሟል” ሲል ኢሰመኮ ኮነነ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (#ኢሰመኮ) በአማራ ክልል ከመስከረም ወር አጋማሽ 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በርካታ ሰዎች ለሕግ አግባብ ውጭ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዛ ለእስር ተዳርገዋል ሲል አስታወቀ፤ በማናቸውም ወቅት ቢሆን የሚፈጸም እስር ተገቢውን የሕግ እና የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች ሊከተል ይገባል ሲልም አሳስቧል።
የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎችን እና መርሖችን ያልተከተሉ እስሮች በአፋጣኝ ሊቆሙ ይገባል ሲል ጠይቋል።
ኢሰመኮ ትላንት መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል ጎንደር እና ባሕር ዳር ከተሞችን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የተፈጸሙት እስሮች “በሕግ አግባብ በፍርድ ቤት ትእዛዝ ያልተፈጸሙ፣ ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ መሆናቸው አመላክቷል።
የመንግሥት ሠራተኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ የሚዲያ እና የሲቪክ ማኅበረሰብ አባላትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ወደ ጊዜያዊ ማቆያዎች እየተወሰዱ መሆኑን የጠቆመው ኢሰመኮ ከመካከላቸው ቋሚ የሕክምና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሰዎች መኖራቸውን ገልጿል።
https://wp.me/pfjhHd-1sW

Addis standard
በአማራ ክልል “ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ የዘፈቀደ እስር ተፈጽሟል” ሲል ኢሰመኮ ኮነነ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27/2017 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል ከመስከረም ወር አጋማሽ 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በርካታ ሰዎች ለሕግ አግባብ ውጭ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዛ ለእስር ተዳርገዋል ሲል አስታወቀ፤ በማናቸውም ወቅት ቢሆን የሚፈጸም እስር ተገቢውን የሕግ እና የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች ሊከተል ይገባል ሲልም አሳስቧል። የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎችን እና መርሖችን…
ዜና: #በአማራ እና #አፋር ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ለሚገኙ ህጻናት ከዛሬ መስከረም 27 ጀምሮ ለአራት ቀናት የፖሊዮ ክትባት እንደሚሰጥ ተገለጸ
በአማራና በአፋር ክልል እንዲሁም #በአዲስ አበባ ከዛሬ መስከረም 27 ቀን 2017 ጀምሮ የፖሊዮ ክትባት እንደሚሰጥ ተገለጸ፡፡
ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ከ5 አመት በታች የሆኑ ህፃናትን ከዚህ በፊት ቢከተቡም ባይከተቡም በማስከተብ የልጆቻቸውን ጤንነት እንዲጠብቁ ጥሪ ተላልፏል፡፡
የአማራ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በላይ በዛብህ እንዳስታወቁት ፖሊዮ (የልጅነት ልምሻ) በሽታ በተበከለ ምግብና ውሃ አማካኝነት የሚመጣ ተላላፊ በሽታ እንደሆነ ጠቅሰው፤ በሽታው ዘላቂ ለሆነ የአካል ጉዳትና አልፎም ለሞት የሚዳርግ እንደሆነ ገልፀዋል።
በአማራ ክልል ክትባቱን ከ4 ሚሊየን ለሚበልጡ ህፃናት ለመስጠት መታቀዱን እና ከዛሬ መስከረም 27 ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ የአማራ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በላይ በዛብህ ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በአፋር ክልል የህብረተሰብ ጤናና ምርምር ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አሕመዱ አህመድ በበኩላቸው በክልሉ 6 ዞኖችና 50 ወረዳዎች እንዲሁም በከተማ አስተዳደሮች ለሚገኙ ከ364 ሺህ በላይ ህፃናት ክትባቱ ይሰጣል ብለዋል።
በክልል ደረጃ 364 ሺህ 629 ህፃናት የሚከተቡ መሆኑን አስታውቀው ክትባቱም ከዛሬ መስከረም 27 ጀምሮ ለአራት ቀናት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በበኩሉ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት ከዛሬ መስከረም 27 ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት ቤት ለቤት፣ በትምህርት ቤት ፣ በማቆያ፣ በማሳደጊያ ቦታዎች እና በሌሎች ህጻናት በሚገኙበት ሁሉ በአፍ በጠብታ ክትባቱ እንደሚሰጥ መገለጹን ከዋልታ ያገኘነው መረጃ ያሳያል

ዜና: ትላንት ምሽት ላይ #በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ ቤቶች መፍረሳቸውና መሬት መሰንጠቁ ተጠቆመ
ንዝረቱ #አዲስ አበባ ድረስ የተሰማው እና በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ትላንት መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ ቤቶችን እንዳፈረሰ፣ መሬት እንደሰነጠቀ የሰመራ ዩኒቨርስቲ አስታወቀ።
ዩኒቨርስቲው በማህበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከሁለት ሳምንታት በላይ እንደሆነው አመላክቷል።
ባሳለፍነው ሳምንት የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የጂኦሎጂ ጥናት ቡድን በአዋሽ ፋንታሌ ወረዳ የመስክ ምልከታ ማድረጉን የጠቆመው የዩኒቨርስቲው መረጃ የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተበትን በተለይም ሳቡሬ ቀበሌ ተገኝቶ መረጃ የመሰብሰብ እና ለማህበረሰቡ ጥንቃቄ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መስራቱንም አስታውቋል።
የዩኒቨርሲቲው ጂኦሎጂስቶች የአካባቢውን ነዋሪዎች ባነጋገሩበት ወቅት ከፈንታሌ ኮረብታማ ቦታ እና ከከሰም ግድብ ርቀው እንዲቆዩ ማሳሰባቸውን ገልጿል።
ትናንት መስከረም 26 ቀን ምሽት 2 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ገደማ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበበት እስከ አዲስ አበባ ድረስ ንዝረቱ የተሰማ መሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን በርካታ አለም አቀፍ ተቋማት አስታውቀዋል።
የአሜሪካው ጂዮሎጂካል ሰርቬይ: የጀርመን እና ሌሎች አለም አቀፍ ጂዮሎጂካል ሰርቬይ የምርምር ተቋማት በአዋሽ ዙሪያ በተከታታይ የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ የትናንቱን ጨምሮ በድረ-ገጻቸው ላይ አስፍረውታል።
የሰሞኑ የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ከፍተኛ ስጋትን መፍጠሩንም ዩኒቨርስቲው አመላክቷል።