ዜና: ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በጥቅምት ወር #የደመወዝ ጭማሪ ተፈጻሚ ሆኗል ቢልም በርካታ የመንግሥት ሠራተኞች ማስተካከያው እንዳልደረሳቸው አስታወቁ
ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የመንግስት ሰራተኞች በጥቅምት ወር አዲሱን የደመወዝ ጭማሪ ማግኘታቸውን ቢገልጽም፣ በርካታ የፌደራል መሥሪያ ቤት ሰራተኞች እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች ግን ማስተካከያው እስካሁን እንዳልደረሳቸው ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።
ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ መርማሪ የሆኑ ግለሰብ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት “የደመወዝ ማስተካከያው በጥቅምት ወር ይጀመራል ብለን ብንጠብቅም እስካሁን አልተከፈለንም” ብለዋል።
በተመሳሳይ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ #በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት በበኩላቸው እርሳቸውም ሆኑ ባልደረቦቻቸው ቃል የተገባውን ጭማሪ እንዳላገኙ አረጋግጠው ተግባራዊ ስለመሆኑ በይፋ ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ያገኙት መረጃ አለመኖሩን ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም በማህበራዊ ትስስር የፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ እንዳስታወቁት የገንዘብ ሚኒስቴር የተጨማሪ ክፍያ በጀቱን ለሚመለከታቸው ተቋማት መፍቀዱን ገልጸው፣ "በእኛ መስሪያ ቤትም በኩል የተስተካከለውን የጥቅምት ወር ደመወዝ ተከፍሏል" ብለዋል። ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጠቀሙ
https://addisstandard.com/Amharic/?p=5934

Addis standard
ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በጥቅምት ወር የደመወዝ ጭማሪ ተፈጻሚ ሆኗል ቢልም በርካታ የመንግሥት ሠራተኞች ማስተካከያው እንዳልደረሳቸው አስታወቁ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ህዳር 2/2017 ዓ.ም፡- ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የመንግስት ሰራተኞች በጥቅምት ወር አዲሱን የደመወዝ ጭማሪ ማግኘታቸውን ቢገልጽም፣ በርካታ የፌደራል መሥሪያ ቤት ሰራተኞች እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች ግን ማስተካከያው እስካሁን እንዳልደረሳቸው ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል። ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ መርማሪ የሆኑ ግለሰብ…
ዜና: ግንባታው ሙሉ በሙሉ ያልተጠናቀቀው #የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ 80 ሜጋ ዋት ማምረት ጀምሯል ተባለ
የግንባታ አፈጻጸሙ 82 በመቶ መድረሱ የተገለጸው የአይሻ የንፋስ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ስምንት የንፋስ ተርባይኖች ተከላ ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አሁን ላይ 80 ሜጋ ዋት ኃይል ወደ ብሄራዊ የኃይል ቋት የማስገባቱ ሥራ መጀመሩ ተገለጸ።
120 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታው አፈጻጸም 82 በመቶ መድረሱን #የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡
የግንባታ ሥራው ደረጃ በደረጃ እየተሠራ መሆኑን እና በዚህም ስምንት ክላስተር ያላቸው 80 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት የሚያስችሉ የንፋስ ተርባይኖች ተከላ ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አሁን ላይ 80 ሜጋ ዋት ኃይል ወደ ብሄራዊ የኃይል ቋት የማስገባቱ ሥራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን አስታውቀዋል።
የተቀረውን 40 ሜጋ ዋት ኃይል ወደ ቋት ለማስገባት የሚያስችሉ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ ቢሆንም ተርባይኖችን የመትከል ሥራው በፋይናንስ አቅርቦት ምክንያት ለሁለት ዓመታት ባለበት እንዲቆም ተደርጎ እንደነበር አውስተዋል፡፡
አሁን ላይ ግን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አበዳሪዎችን ሳይጠብቅ በራሱ ፋይናንስ ግንባታውን ለማካሄድ ወስኖ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ሃላፊው መናገራቸውን ከኢፕድ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የአይሻ ፕሮጀክት እየተገነባበት ያለው አካባቢው ከባህር ለሚነሳ ንፋስ ቅርብ በመሆኑ ተርባይን የማንቀሳቀስ አቅማቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም ከሌሎቹ በአንጻራዊነት ሲታይ ፕሮጀክቱ የተሻለ ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ዜና: #በትግራይ ሰላም እና ጸጥታ እንዲሰፍን ድጋፍ እናደርጋለን ሲሉ ክልሉን የጎበኙ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ የእንግሊዝ፣ ጀርመን እና ኔዘርላንድ አምባሳደሮች አስታወቁ
በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር የሆኑት ሶፊ ፎም ኤመስ በርገርን ጨምሮ #የጀርመን፣ #እንግሊዝ እና #የኔዘርላንድ አምባሳደሮች ትላንት ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም በትግራይ ክልል ጉብኝት ማካሄዳቸው ተገለጸ።
አምባሳደሮቹ በጉብኝታቸው በክልሉ ደጉዓ ተምቤን ወረዳ በመገኘት በመልሶ ግንባታው እና በመልሶ ማቋቋም የተከናወኑ ስራዎች ምን እንደሚመስሉ ማየታቸውን ከትግራይ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
አምባሳደሮቹ በክልሉ ያለው ሁኔታ ምን እንደሚመስል በደጉአ ተምቤን ወረዳ ተገኝተው መታዘባቸው እንዳስደሰታቸው በመግለጽ በትግራይ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን አስታውቋል።
አምባሳደሮቹ ከትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን የጠቆመው መረጃው ለአምባሳደሮቹ የአውሮፓ ህብረትና ሌሎች ሀገራት ለትግራይ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ መጠየቃቸውን አመላክቷል።
የአውሮፓ ህብረትና ሀገራቱ በተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት (ዩኤንዲፒ) አማካኝነት ለትግራይ ለሚያደርጉት ድጋፍ ፕረዝደንቱ ምስጋና ማቅረባቸውን ያስታወቀው የትግራይ ቴሌቪዥን ዘገባ ጦርነቱ ያስከተለው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ድጋፋቸውን አጠናክሮ እንዲቀጥሉ ማሳሰባቸውን አካቷል።
አምባሳደሮቹ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጋር በነበራቸው ውይይት በክልሉ ከሚካሄደው የመልሶ ግንባታ እና መልሶ ማቋቋም ስራዎች በተጨማሪ በትግራይ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው መመለስ በሚቻልባቸው እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይም መነጋገራቸውን መረጃው አካቷል

ዜና: #በኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት በእጅጉ እያሽቆለቆለ መጥቷል ሲል ሲፒጄ አስታወቀ
አለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ተቋም የሆነው #ሲፒጄ ከአምስተ አመት በፊት ካካሄድኩት ግምገማ በኋላ ባሉት አመታት የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት እጅጉን አሽቆልቁሏል ሲል ገለጸ።
የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ (ሲፒጄ) ይህንን የገለጸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ዛሬ ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከሚያካሂደው 47ኛ ጉባኤ በፊት የኢትዮጵያን የአምስት አመታት የፕሬስ ነጻነት ግምገማውን አስመልክቶ ባቀረበው ሪፖርት ነው።
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች እየደረሰባቸው ያለውን የዘፈቀደ እስራት፣ አካላዊ ጥቃት፣ እንግልት እና ከፍተኛ የህግ ገደቦችን በዝርዝር አቅርቧል።
"ባለፉት አምስት አመታት በሀገሪቱ ማሻሻያዎች ቢደረጉም የኢትዮጵያ የመገናኛ በዙሃን እና የፀረ ሽብር ህጎች አሁንም ተቃዋሚዎችን ለማሳደድ፣ የሚዲያ ተቋማትን ለመዝጋት፣ እንዲሁም የውጭ ጋዜጠኞችን ከሀገር ለማባረር አገልግሎት ላይ እየዋሉ” መሆኑን ሪፖርቱ አመላክቷል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=5937

ዜና: በኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት በእጅጉ እያሽቆለቆለ መጥቷል ሲል ሲፒጄ አስታወቀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ህዳር 3/2017 ዓ.ም፡- አለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ተቋም የሆነው ሲፕጄ ከአምስተ አመት በፊት ካካሄድኩት ግምገማ በኋላ ባሉት አመታት የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት በእጅጉን አሽቆልቁሏል ሲል ገለጸ። የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ (ሲፒጄ) ይህንን የገለጸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ዛሬ ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከሚያካሂደው 47ኛ ጉባኤ በፊት…
ዜና: #የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ነፃ ንግድ ቀጠናነት አድጎ በሙሉ አቅሙ ወደ ተሟላ ትግበራ ገብቷል ተባለ
የድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና በሙሉ አቅሙ ወደ ተሟላ ትግበራ መግባቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያሰተዳድራቸው ፓርኮች ውስጥ ወደ ነጻ ንግድ ቀጠናነት በማደግ የመጀመሪያው መሆኑም ተገልጿል።
በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች ምርታቸውን ለገበያ በማቅረብ ላይ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን በንግድ፣ ሎጅስቲክስ፣ በሆቴል እና ተያያዥ ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎቱ እና አቅሙ ያላቸው ኩባንያዎች በነጻ ንግድ ቀጠው ውስጥ ገብተው ስራ ለመጀመር የሚያስችላቸውን የተለያዩ ስራዎች በመከወን ላይ መሆናቸው ተጠቁሟል።
ነጻ ንግድ ቀጠናውን ወደ ተሟላ ትግበራ ለማስገባት የሚያስችሉ ተግባራት ባለፉት ሶስት ወራት በባለድርሻ አካላት በልዩ ትኩረት ሲሰሩ መቆየታቸውን ኮርፖሬሽኑ ገልጿል፡፡
በመንግስት ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ ሀገር አቀፍ የነፃ ንግድ ቀጠና ትግበራ ኮሚቴ መመስረቱን እና የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠናን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴን በመገምገም ነጻ ንግድ ቀጠናው በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንዲገባ ተገቢውን ርብርብ ሲያደርግ መቆየቱን ከኮርፔሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
የድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና በሙሉ አቅሙ ወደ ተሟላ ትግበራ ገብቷል ሲሉ ዋና ስራ አስፈጻሚው የገለጹት በነጻ ንግድ ቀጠናው ስራ ለመጀመር ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኢንቨስትመንት ፍቃድ በማውጣት ሂደት ላይ ያሉ ባለሀብቶች ነጻ ንግድ ቀጠናው እየሰጠ ያለውን የተለያዩ አገልግሎቶች ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት መሆኑም ተጠቁሟል።

ዜና: #በሀዋሳ ከተማ በቤንዚን እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሷል፣ በጥቁር ገበያ የቤንዚል ሽያጭ ተስፋፍቷል ሲሉ አስሸርካሪዎች አማረሩ
በሲዳማ ክልል ርዕሰ ከተማ በሆነችው ሀዋሳ የቤንዚን እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እየተባባሰ እንደሚገኝ እና ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ መሆናቸውን አሽከርካሪዎች አስታወቁ፣ ዋነኛ መንስኤው በከተማዋ ተስፋፍቶ የሚገኘው የነዳጅ ጥቁር ገበያ ሽያጭ መሆኑንም አሽከርካሪዎቹ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።
ለደህንነታቸው ሲሉ ሥማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በሀዋሳ ከተማ የታክሲ ሹፌር “አሁን ላይ በከተማዋ ነዳጅ በጥቁር ገበያ በሊትር እስከ 160 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ” ገልጸው: "ነዳጅ የሱቅ ሸቀጥ ሆኗል" ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።
"ነዳጅ ከማደያዎች ይልቅ በየፌርማታው ነው እየተቸበቸበ የሚገኘው፤ ይሄን ደግሞ የጸጥታ አካላት ይቅርና ማንኛውም ነዋሪ የሚያውቀው ነገር ነው" ብለዋል።
ህገ-ወጥነትን በተመለከተም የክልሉ ንግድ ቢሮ ከሃዋሳ ከተማ አስተዳደር እና ከሚመለከታቸው የፖሊስ ኮሚሽን አካላት ጋር በመቀናጀት ግብረ-ሃይል ተቋቁሞ ቤንዚን በማታ እንዳይሸጥ መከልከሉ ተገልጿል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=5940

በ #ጋምቤላ በተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ ተፈናቅለው ከነበሩ መካከል ከ20ሺ በላይ ሰዎች ወደ ቀዬያቸው ተመለሱ
በጋምቤላ ክልል ኑዌር ብሔረሰብ ዞን ጂካዎ ወረዳ በክረምት ወንዝ ሙላት እና ጎርፍ ምክንያት ተፈናቅሎ ከነበሩት ዜጎች መካከል ከ20ሺ በላይ ሰዎች ወደ ቀዬአቸው መመለሳቸውን የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል፡፡
በክልሉ ባሳለፍነው ክረምት በአምስት ወረዳዎች የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የባሮ ወንዝ ከመጠን በላይ ሞልቶ ወደ ውጪ በመፍሰሱ በተከሰተ የጎርፍ መጥለቅለቅ ከ 41 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ይታወሳል።
በኑዌር ዞን ጂካዎች ወረዳ ከተፈናቀሉት 26ሺ 836 ሰዎች መካከል አብዛኛቹ ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አንዲሪው ቱት ለዶቸ ቬለ ተናግረዋል፡፡ ከተፈናቀሉት ሰዎች መካከል የተወሰኑት ጎርፍ በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ጉዳት በማድረሱና ባለመድረቁ አለመመሳቸውንም ጠቁመዋል፡፡
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm

ዜና: #ኢትስዊች ከአንድ ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ
#የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ ሁሉም ባንኮች ባለአክሲዮኖች የሆኑበት ኢትስዊች ኩባንያ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ካፒታሉን ከ2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረሱንና ከአንድ ቢሊዮን 55 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ።
በተለያዩ የኤቲኤም ማሽኖች ገንዘብ የማውጣትን ጨምሮ ከባንክ ወደ ባንክ ገንዘብ የማስተላለፍ (P2P transfer) አገልግሎቶችን በማስተሳሰር የሚሰራው ኩባንያው የትርፍ መጠኑ መጨመሩን ተከትሎ የአንድ ባለ አንድ ሺህ ብር አክሲዮን የትርፍ ድርሻ ወደ 73 ነጥብ 7 በመቶ አድጓል ሲሉ ሊቀመንበሩ አቶ ሰለሞን ደስታ ጠቅሰዋል።
የመንግሥት ለዲጂታል ዘርፉ የተሰጠው ትኩረት ከፍተኛ በመሆኑ የሀገሪቱ የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓት ከፍተኛ እመርታ አሳይቷል ሲሉ ሊቀመንበሩ ትላንት ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደው የኢትስዊች አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት አስታውቀዋል።
የኦፕሬሽን ሥራዎችን በተመለከተ በሒሳብ ዓመቱ በአጠቃላይ የብር መጠኑ 399 ነጥብ 63 ቢሊዮን እንዲሁም ብዛቱ 146 ሚሊዮን 407 ሺህ 829 የሆነ የኤቲኤም እና የፖስ አገልግሎት መስጠቱን ጠቁመዋል።
ከዚህም ውስጥ የብር መጠኑ 270 ነጥብ 7 ቢሊዮን እንዲሁም ብዛቱ 49 ነጥብ 69 ሚሊዮን የሆነ በሞባይል ከፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ወደ ሌላ የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ገንዘብ የማስተላለፍ (PP2P transfer) አገልግሎት መከናወኑን ተናግረዋል።
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0XmJD2fvnLfEva3afxQMjodL5dMen27PfGcZCc4dL1nqgKxrTvqym6zZL2akfk5Yzl

#ኤርትራውያን ከ #ኢትዮጵያ ለመውጣት እስከ 4ሺህ ዶላር የሚደርስ የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ ገለጹ
በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራውያን ወደ ሌሎች ሀገራት ለመሄድ ሲፈልጉ የመውጫ ቪዛ ለማስመታት እስከ 4ሺህ ዶላር የሚደርስ የተጋነነ ክፍያ እየተጠየቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የክፍያው ምክንያት ግልፅ እንዳልኾነና ወጥነትም እንደሌለው የተናገሩት ኤርትራውያኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የክፍያውን መጠን ዳግም እንዲመለከተው መጠየቃቸውን የአሜሪካ ድምጽ ዘግቧል።
የኢሚግሬሽና ዜግነት አገልግሎት በበኩሉ፣ እየተጠየቀ ያለው ክፍያ፣ ለመውጫ ቪዛ ሳይሆን፣ በሕገወጥ መንገድ ለቆዩበት ጊዜ የሚወሰን ቅጣት ነው ማለቱን ዘገባው አመላክቷል፡፡ ክፍያው በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ሃገራት ዜጎች ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን የተቋሙ የውጭ ዜጎች ምዝገባና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ አዳነ ደበበ ገልጸዋል።
አክለውም ክፍያው የውጭ አገር ዜጎቹ በኢትዮጵያ የሚቆዩበት ጊዜ በጨመረ ቁጥር ክፍያውም እንደሚጨምር ጠቅሰው፤ በህገወጥ መንገድ፣ በሀገሪቱ ውስጥ እየኖሩ ያሉ የውጭ ሀገራት ዜጎች፣ በተቋሙ ተመዝግበው ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ እንዲይዙም አሳስበዋል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራውያን ወደ ሌሎች ሀገራት ለመሄድ ሲፈልጉ የመውጫ ቪዛ ለማስመታት እስከ 4ሺህ ዶላር የሚደርስ የተጋነነ ክፍያ እየተጠየቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የክፍያው ምክንያት ግልፅ እንዳልኾነና ወጥነትም እንደሌለው የተናገሩት ኤርትራውያኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የክፍያውን መጠን ዳግም እንዲመለከተው መጠየቃቸውን የአሜሪካ ድምጽ ዘግቧል።
የኢሚግሬሽና ዜግነት አገልግሎት በበኩሉ፣ እየተጠየቀ ያለው ክፍያ፣ ለመውጫ ቪዛ ሳይሆን፣ በሕገወጥ መንገድ ለቆዩበት ጊዜ የሚወሰን ቅጣት ነው ማለቱን ዘገባው አመላክቷል፡፡ ክፍያው በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ሃገራት ዜጎች ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን የተቋሙ የውጭ ዜጎች ምዝገባና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ አዳነ ደበበ ገልጸዋል።
አክለውም ክፍያው የውጭ አገር ዜጎቹ በኢትዮጵያ የሚቆዩበት ጊዜ በጨመረ ቁጥር ክፍያውም እንደሚጨምር ጠቅሰው፤ በህገወጥ መንገድ፣ በሀገሪቱ ውስጥ እየኖሩ ያሉ የውጭ ሀገራት ዜጎች፣ በተቋሙ ተመዝግበው ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ እንዲይዙም አሳስበዋል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና: #የመገናኛ ብዙኃን ማሻሻያ አዋጁ የባለሥልጣኑን ገለልተኝነትና ነፃነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው በሚል ትችት ቀረበበት
ለተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ የመገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣንን ገለልተኝነትና ነፃነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው በሚል በ14 የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ትችት ቀረበበት።
በአዲሱ ማሻሻያ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሹመት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መሰጠቱ፤ እንዲሁም በነባሩ አዋጅ ለቦርዱ ተሰጥተው የነበሩት የፈቃድ ወይም የምዝገባ ምስክር ወረቀት አለማደስ፣ ማገድ፣ መሰረዝ፣ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት የመሳሰሉት ኃላፊነቶች አሁን ለባለሥልጣኑ መሰጠታቸውን ተችተዋል።
ሥልጣንን ጠቅልሎ ለአንድ አካል ከመስጠትና በሒደትም ላልተገባ ተፅዕኖ በር ከመክፈቱ በተጨማሪ የባለሥልጣኑን ገለልተኝነትና ነፃነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ረቂቅ አዋጅ ያደርገዋል ሲሉ ገልጸዋል።
የአዋጁ ማሻሻያ አስፈላጊነት ላይ ገለልተኛ ጥናት ባልተደረገበት፣ በቂ የባለድርሻ አካላት ውይይትም ባልተካሔደበት ሁኔታ ረቂቁ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ መቅረቡ አግባብነት የለውም ሲሉ ማህበራቱ እና ድርጅቶቹ በጋራ ባወጡት መግለጫቸው ተችተዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=5943

ራስ ገዟ #ሶማሊላንድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እያካሄደች ነው
ረስ ገዟ ሶማሊላንድ ለቀጣይ አምስት አመታት የሚመራትን ፕሬዝዳንት የምትመርጥበትን የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በዛሬው ዕለት እያካሄደች ነው።
በፕሬዚዳንታዊ ውድድሩ በወቅቱ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ከኩልሚዬ ፓርቲ፣ አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ "ሲሮ" ከዋዳኒ ፓርቲ እና ፋይሰል አሊ ዋራቤ ከዩሲአይዲ ፓርቲ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ከፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ጎን ለጎን በአምስቱ የሶማሊላንድ ክልሎች 20 በመቶ ድምጽ ለማግኘት 10 የፖለቲካ ድርጅቶች እየተወዳደሩ ነው። ይህን ድምጽ ማግኘታቸው ለቀጣይ ምርጫዎች በይፋ የፓርቲነት ስያሜን ይሰጣቸዋል። መራጮች ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እና ለፖለቲካ ድርጅቶች ምርጫ የሚሆን ሁለት የምርጫ ወረቀቶች ይሰጣቸዋል።
አብዲራህማን ኪሮ በተለይ በመጨረሻው ቀን የምርጫ ቅስቃሳ ላይ ከምክትል ፕሬዝዳንት አብዲራህማን አብዱላሂ እስማኤል "ሳይሊሲ" ድጋፍ ማግኘታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ አግኝተዋል ሲል የፑትላንዱ ጋሮዌ ዘግቧል። ይህም ድጋፍ ለአምስት ዓመታት የሶማሊላንድ መሪ ሆነው ያገለገሉትን ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂን የሚፈትን ነው ተብሎ ይታሰባል።
የምርጫው የመጀመሪያ ውጤቶች ዛሬ ማታ ይታወቃል ተብሎ ይጠበቃል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ረስ ገዟ ሶማሊላንድ ለቀጣይ አምስት አመታት የሚመራትን ፕሬዝዳንት የምትመርጥበትን የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በዛሬው ዕለት እያካሄደች ነው።
በፕሬዚዳንታዊ ውድድሩ በወቅቱ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ከኩልሚዬ ፓርቲ፣ አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ "ሲሮ" ከዋዳኒ ፓርቲ እና ፋይሰል አሊ ዋራቤ ከዩሲአይዲ ፓርቲ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ከፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ጎን ለጎን በአምስቱ የሶማሊላንድ ክልሎች 20 በመቶ ድምጽ ለማግኘት 10 የፖለቲካ ድርጅቶች እየተወዳደሩ ነው። ይህን ድምጽ ማግኘታቸው ለቀጣይ ምርጫዎች በይፋ የፓርቲነት ስያሜን ይሰጣቸዋል። መራጮች ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እና ለፖለቲካ ድርጅቶች ምርጫ የሚሆን ሁለት የምርጫ ወረቀቶች ይሰጣቸዋል።
አብዲራህማን ኪሮ በተለይ በመጨረሻው ቀን የምርጫ ቅስቃሳ ላይ ከምክትል ፕሬዝዳንት አብዲራህማን አብዱላሂ እስማኤል "ሳይሊሲ" ድጋፍ ማግኘታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ አግኝተዋል ሲል የፑትላንዱ ጋሮዌ ዘግቧል። ይህም ድጋፍ ለአምስት ዓመታት የሶማሊላንድ መሪ ሆነው ያገለገሉትን ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂን የሚፈትን ነው ተብሎ ይታሰባል።
የምርጫው የመጀመሪያ ውጤቶች ዛሬ ማታ ይታወቃል ተብሎ ይጠበቃል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና: ባሳለፍነው የጥቅምት ወር ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ከተፈጽመባቸው ሀገራት #ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ ናት ተባለ
በርካታ #የአፍሪካ ሀገራት ባሳለፍነው የጥቅምት ወር ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት የተፈጸመባቸው ቢሆን የኢትዮጵያን ያክል ግን አይደለም ተብሏል።
በአለም አቀፍ ደረጃ የተፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶችን በመተንተን ደረጃ የሚያወጣው ቼክ ፖይንት ሶፍትዌር ቴክኖሎጂዎች ይፋ ባደረገው የ2024 እ.አ.አ የጥቅምት ወር ሪፖርት መሰረት ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ከተፈጽመባቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ ሆናለች።
በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሳይበር ስጋት በጨመረበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የስጋት መጠን 96 ነጥብ 8 በማስመዝገብ ኢትዮጵያ አንደኛ ደረጃ እንድትይዝ አድርጓታል፤ በአፍሪካ ደረጃ ከኢትዮጵያ በመቀጠል ተጋላጭ የሆነችው አንጎላ ስትሆን ያስመዘገበችውም 74 መሆኑን ሪፖርቱ አመላክቷል። ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጠቀሙ https://addisstandard.com/Amharic/?p=5946

ባሳለፍነው የጥቅምት ወር ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ከተፈጽመባቸው ሀገራት ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ ናት ተባለ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ህዳር 4/2017 ዓ.ም፡- በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ባሳለፍነው የጥቅምት ወር ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት የተፈጸመባቸው ቢሆን የኢትዮጵያን ያክል ግን አይደለም ተብሏል። በአለም አቀፍ ደረጃ የተፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶችን በመተንተን ደረጃ የሚያወጣው ቼክ ፖይንት ሶፍትዌር ቴክኖሎጂዎች ይፋ ባደረገው እ.አ.አ 2024 የጥቅምት ወር ሪፖርት መሰረት ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ከተፈጽመባቸው ሀገራት መካከል…
ዜና፡ በ #አምባሰል ወረዳ ባሳለፍነው ቅዳሜ በተካሄደ ውጊያ ንጹሃን ሰዎች መቁሰላቸውና በመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ተናገሩ
በ #አማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን አምባሳል ወረዳ ሮቢት በተሰኘች ስፍራ እና አከባቢዋ ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደ ውጊያ ንጹሃን ሰዎች መቁሰላቸውንና በመኖሪያ ቤቶችና ከፍተኛ ውድመት መድረሱን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳንጠቅስ የጠየቁ የአከባቢው ነዋሪ፤ ከሮቢት ከፍ ብሎ ወደ ቋዲት በሚወስደው መንገድ መካከል በምትገኘው ፍልፈል በተሰኘች ስፍራም በተደረገ ውጊያም “አከባቢው በከባድ መሣሪያ መደብደቡን” ገልጸዋል።
"ፍልፈል ላይ የከባድ መሣሪያ ድብደባ ነበረ። ህዝቡም በዕለቱ ገበያ ነበር። ከገበያ መልስ ብዙ ሰው ቤቱ ሲደርስ በከባድ መሣርያ ጋይቶ ጠበቀው።" ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ያስረዱት ነዋሪው ሁለት ሰዎች እጅ እና እግራቸው ላይ ተመተው መቁሰላቸውን ጠቁመዋል።
ተጨማሪ ይመልከቱ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=5952

በአምባሰል ወረዳ ባሳለፍነው ቅዳሜ በተካሄደ ውጊያ ንጹሃን ሰዎች መቁሰላቸውና በመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ተናገሩ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ህዳር 04/ 2017 ዓ/ም፦ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን አምባሳል ወረዳ ሮቢት በተሰኘች ስፍራ እና አከባቢዋ ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደ ውጊያ ንጹሃን ሰዎች መቁሰላቸውንና በመኖሪያ ቤቶችና ከፍተኛ ውድመት መድረሱን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ። ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳንጠቅስ የጠየቁ የአከባቢው ነዋሪ፤ በዕለቱ በመንግስት ጸጥታ…
ዜና፡ በ ማዕድን ሚኒስቴር ለናሙና ወደ ውጪ የሚላኩ ማዕድናት ወደ ሀገር ቤት አለመመለሳቸውን ቋሚ ኮሚቴው ገለጸ
ለናሙና ወደ ውጪ የሚላኩ ማዕድናት ወደ ሀገር ቤት አለመመለሳቸውን የማዕድን ሚኒስቴር የክዋኔ አዲት ሪፖርት ማሳየቱን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ።
የመንግስት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር የሺመቤት ደምሴ፤ በማዕድን ሚኒስቴር በኩል የተሰጠው ምላሽ አጥጋቢ አለመሆኑን እና ለሀብት ብክነት የሚዳርግ በመሆኑ ማዕድናቱ የሚመለሱበትን ስርአት መዘርጋት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
በተጨማሪም ከማዕድን ዘርፉ እና ከማዕድን አምራቾች በቂ ገቢ እየተሰበሰበ አለመሆኑን ጠቁመው፤ በማዕድን ጥራት እና አለማቀፍ ተወዳዳሪ በመሆን ረገድ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማረምም የአሰራር ስርአት መዘርጋት እንዳለበትም ሰብሳቢዋ አስገንዝበዋል።
ሰብሳቢዋ አክለውም፤ የማዕድን ሚኒስቴር በክዋኔ ኦዲት ግኝት የታዩበትን ክፍተቶች ትኩረት ሰጥቶ እንዲያርምና እንዲያስተካክል አሳስበዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=5955

በማዕድን ሚኒስቴር ለናሙና ወደ ውጪ የሚላኩ ማዕድናት ወደ ሀገር ቤት አለመመለሳቸውን ቋሚ ኮሚቴው ገለጸ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ህዳር 5/ 2017 ዓ/ም፦ ለናሙና ወደ ውጪ የሚላኩ ማዕድናት ወደ ሀገር ቤት አለመመለሳቸውን የማዕድን ሚኒስቴር የክዋኔ አዲት ሪፖርት ማሳየቱን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ። ቋሚ ኮሚቴው ይህን ያለው በ2015/16 በጀት አመት በማዕድን ሚኒስቴር ከማዕድን የሚገኝ ገቢን ማሳደጉን እና መሰብሰቡን በተመለከተ የተከናወነ የክዋኔ…
በ #ኦሮሚያ ክልል #ጅማ ዞን የወባ ወረርሽኝ በአስጊ ደረጃ እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ
በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የተከስተውን የወባ ወረርሽኝ ለመከላከል በተደረገው ርብርብ የሰዎች ሞት ቢቀንስም፤ ወረርሽኙ በአስጊ ደረጃ እየጨመረ ስለመምጣቱ ቋሚ ኮሚቴው ገልጿል።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህል እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በጅማ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የወረርሽኙን ሁኔታ አስመልክቶ የመስክ ጉብኝት አድርጓል።
ቋሚ ኮሚቴው በጅማ ዞን በሰቃ ጨቆርሳ፣ በጌራ እና ጎማ ወረዳዎች በተመረጡ ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች እና ጤና ኬላዎች ባደረገው ምልከታ የወባ ወረርሽኙ በፍጥነት እያደገ መምጣቱን አረጋግጧል ተብሏል።
የቋሚ ኮሚቴው አባልና የቡድኑ አስተባባሪ ወ/ሮ አሚራ መሀመድ በሦስቱም ወረዳዎች የወባ ወረርሽኙን ለመከላከል የተደረገው ሁለንተናዊ ጥረት የተሻለ ቢሆንም፤ በአንጻሩ የበሽታው ስርጭት እየከፋ መምጣቱን አስረድተዋል። ወረርሽኙን ለመግታት የሚደረጉ ጥረቶች የበለጠ ሊጠናከሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የሰቃ ጨቆርሳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ሣቢት ጀማል ወረርሽኙን ለመከላከል የደም እና የመድኃኒት አቅርቦቶች ሊሟሉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ተብሏል።
የዓለም ጤና ድርጅት በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ከታህሳስ 23፣ 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከ7.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መጠቃታቸውን እና ከእነዚህም መካከል 1,157 ሰዎች መሞታቸውን ገልጿል።

ዜና: ብሔራዊ ባንክ ላኪዎች ካመነጩት የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶውን በመሸጥ ቀሪውን ላልተወሰነ ጊዜ በአካውንታቸው እንዲያስቀምጡ ፈቀደ
#የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ላኪዎች ያመነጩትን የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶ ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውን 50 በመቶ ላልተወሰነ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለ አካውንታቸው ማስቀመጥ የሚችሉበት አሰራር ከዛሬ ህዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ እንዳሉት፣ ላኪዎች ካመነጩት የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶውን ለባንኮች ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውንም በአንድ ወር ውስጥ መሸጥ ይገደዱ ነበር።
በወቅቱ አሰራሩ በጊዜያዊነት ተግባራዊ ሲደረግ የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬ ፍሰት እንዲኖር ከመፈለግ እንደነበር አቶ ማሞ አስታውሰዋል።
ከዛሬ ህዳር 5 ቀን ጀምሮ ግን ላኪዎች ያመነጩትን የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶ ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውን 50 በመቶ ላልተወሰነ ጊዜ በአካውንታቸው ማስቀመጥ ይችላሉ ሲሉ መግለጻቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ይህም ማለት ያመነጩትን የውጭ ምንዛሬ በአንድ ወር ውስጥ እንዲሸጡ አይገደዱም ማለት መሆኑን አመላክተዋል።
በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በፊት ከነበረበት 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር በአሁኑ ወቅት 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የባንኩ ገዥ ማሞ ምህረቱ ገለጸዋል።
የግል ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ሀብት መጨመሩን ጠቅሰው፤ ከሪፎርሙ በፊት ከነበረባቸው 518 ሚሊዮን ዶላር አሁን ላይ ከእዳ ነፃ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ዜና: #ለአልሸባብ የሽብር ቡድን መረጃ በማቀበል ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ
ለአል ሸባብ የሽብር ቡድን መረጃ በማቀበል ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ 5 ተከሳሾች በጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ድሬዳዋ ምድብ 4ኛ #ጅግጅጋ ተዘዋዋሪ ወንጀል ችሎት ወሰነ።
ተከሳሾቹ ሻለቃ ሀለኔ ኑርዬ ኡመር፣ መሀመድ ጉሀድ አደም እና ኑር ሀሬ (በሌላ ስሙ ኑር መህመድ)፣ አብዲ አህመድ አብዱላሂ እና ኡመር የሱፍ ሀሰን በመከላከያ ሰራዊትና በሶማሌ ክልል የፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መርማሪዎች ከክልሉ መርማሪ ፖሊስ ጋር በመሆን ምርመራ ሲያከናውን እንደነበር ይታወሳል።
በፍትህ ሚኒስቴር የድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት የተደራጁ እና ድንበር ተሻጋሪ የወንጀል ጉዳይ ዐቃቤ ሕግ የምርመራ መዝገቡን ከፖሊስ ተረክቦ ተከሳሾቹ መቀመጫውን በሶማሊያ ሀገር ላደረገው ለአል ሸባብ የሽብር ቡድን ድጋፍ ሲያደርጉ መያዛቸውን ጠቅሶ በታህሳስ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በየተሳትፎ ደረጃቸው ዝርዝር ክስ አቅርቦባቸው ነበር።
ተከሳሾቹ የቀረበባቸው ክስ ዝርዝር በችሎት ከደረሳቸውና በንባብ ከተሰማ በኋላ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊቱን ክደው የዕምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ለወንጀሉ መፈጸም የሚያስረዱ የሰው ምስክሮችንና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦ አሰምቷል።
ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ ተከሳሾቹ እንዲከላከሉ ብይን የሰጠ ቢሆንም የቀረበባቸውን ማስረጃ በተገቢው ማስተባበል ባለመቻላቸው የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል።
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0GZKNNPy6WEoTrcJNcgXRXsEguouSekARv4kMknBa5jnEpmKYuSX5KwMXYiHHt5cEl

ዜና: በ #ኦሮሚያ ክልል ከ130 በላይ ሰዎች “ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ጋር ዝምድና አላችሁ” በሚል ለወራት ታስረው እንደሚገኙ ተገለጸ
በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ኦቦራ በተሰኘ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ከ130 በላይ ሰላማዊ ሰዎች “ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አባላት ጋር ቤተሰባዊ ግንኙነት አላችሁ” በሚል ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ከሰባት ወራት በላይ ታስረው እንደሚገኙ የታሳሪ ቤተሰቦች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
አቶ ደበላ ተስፋዬ የተባሉ የአከባቢው ነዋሪ፤ ወላጅ አባታቸው አቶ ተስፋዬ በያና እና እናታቸው ዶሳ ቶሌራ በናፉሮ አከባቢ በኦሮሚያ ክልል ሚኒሻዎች ተለይተው መታሰራቸውን ተናግረዋል።
አቶ ደረጀ ቶሎሳ የተባሉ ሌላኛው ነዋሪ በበኩላቸው ወላጅ አባታቸው የሆኑት ቶሎሳ ሶሪ “ልጃቸው ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላት ውስጥ አንዱ ነው” በሚል ሚያዝያ 8 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊሻዎች ተይዘው መወሰዳቸውን ጠቁመዋል።
አክለውም ወላጅ አባታቸው ወደ ኦቦራ ፖሊስ ጣቢያ ሲወሰዱ እየተደበደቡ እንደነበረ ጠቅሰው በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ለሰባት ወራት ያህል እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን ገልጸዋል።
ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ሊንኩን ይጨቀሙ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=5961

በኦሮሚያ ክልል ከ130 በላይ ሰዎች "ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ጋር ዝምድና አላችሁ" በሚል ለወራት ታስረው እንደሚገኙ ተገለጸ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ህዳር 05/ 2017 ዓ/ም፦ በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ኦቦራ በተሰኘ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ከ130 በላይ ሰላማዊ ሰዎች “ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አባላት ጋር ቤተሰባዊ ግንኙነት አላች”ሁ በሚል ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ከሰባት ወራት በላይ ታስረው እንደሚገኙ የታሳሪ ቤተሰቦች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ። አቶ ደበላ ተስፋዬ የተባሉ የአከባቢው ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት…
ዜና: “በየትኛውም ሁኔታ #አልሽባብን የማዳከም ሥራ የሚቀጥል ይሆናል” - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
#ኢትዮጵያ “በየትኛው ሁኔታ አልሽባብን የማዳከም ሥራ” ትቀጥላለች ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው አስታወቁ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በወቅታዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ ህዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አለሸባብ “በአሁኑ ወቅትም ለብሔራዊ ደኀንነታችን ሥጋት እንዳይሆንና የተገኙ ድሎች እንዳይቀለበሱ በየትኛውም ሁኔታ የማዳከም ሥራ የሚቀጥል ይሆናል” ብለዋል።
“ኢትዮጵያ አሸባሪው አልሽባብን በየትኛውም ሁኔታ ለቀጣናው አደጋ ሊሆን የማይችልበት ደረጃ በማድረስ ረገድ የተጫወተችው ቁልፍ ሚና በዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ በሚገባ የሚታወቅ ና ተገቢው ግንዛቤ የተያዘበት” ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የማይነጣጠሉ ጎረቤት አገሮች እንደመሆናቸው ኢትዮጵያ ግንኙነቱን በረጅም ጊዜ ዕይታ ቀጣናዊ ትስስርን በሚያጎለብት መልኩ ስትራቴጂክ ዕይታዎችን በቀጣይም እንደሚትተገብር ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ እና ሱዳንን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ታሪካዊ እና በጠንካራ ወንድማማችነት ላይ የተመሠረተ መሆኑን በማንሳት በቀጣይም የጋራ ተጠቃሚነትን ማዕከል ባደረገ መልኩ ተቀራርበን መሥራታችን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ “በሶቺ ሩስያ በተካሄደው የመጀመሪያው የሩስያ- አፍሪካ አጋርነት ፎረም የሚኒስትሮች ስብሰባ ተሳትፎ እና የጎንዮሽ ውይይቶች ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስጠቡቁ ውጤታማ ተሳትፎ” አድርገዋል ማለታቸውንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የ #አፋር ፌዴራላዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ ታጣቂዎች ‘ለክልሉ ሰላምና ልማት በጋራ ለመስራት’ መስማማታቸው ተገለጸ
የአፋር ፌደራላዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ ታጣቂዎች ‘ትጥቃቸውን ለአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስረክበው ለክልሉ ሰላምና ልማት በጋራ ለመስራት’ መስማማታቸውን የ #ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ገለጸ።
በአፋር ክልል አብአላ ከተማ ላይ በተካሄደው ስነስርዓት ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ፣ ሰላም የሁሉም ነገር መሠረት መሆኑን ገልጸው፤ ታጣቂዎቹ የሠላምን መንገድ መምረጣቸው ለክልሉ ሠላም ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባሻገር ለሀገራዊ ሠላምና አንድነት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም በክልሉ ሠላምና ልማት ላይ በንቃት መሣተፍ እንዲችሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ይደረጋል ሲሉ ገለጸው የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ ስምምነቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
እንደ መከላከያ ሠራዊት መረጃ፤ የአፋር ፌደራላዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ ታጣቂዎች ሊቀመንበር ሀጂ ስዩም አወል በበኩላቸው ከግጭትና ጦርነት የሚገኝ ትርፍ እንደሌለ ገለጸው፤ “ከአሁን በኋላ ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን አክብረን በሠላማዊ መንገድ ህዝባችንን ለማገልገል በወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን” ብለዋል።
ብርጋዲየር ጄኔራል ጀማል ሻሌ ከአፋር ፌደራላዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ ታጣቂዎች በተጨማሪ ራሱን የአፋር ነፃ አዉጪ ግንባር እያለ ከሚጠራዉ ታጣቂ ሀይል ጋርም በተሠራው ዉጤታማ ስራ ወደ ሠላማዊ መንገድ ማምጣት እንደተቻለ ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅት በአፋር ክልል “በህገ ወጥ መንገድ ትጥቅ ይዞ የሚንቀሳቀስ የተደራጀ ሃይል እንደሌለ” አስታውቀው፣ ለሀገር አንድነትና ሠላም ከሚበጅ በጎ ተግባር ሌሎች ክልሎችም ትምህርት ሊወስዱ ይገባል ብለዋል።