ዜና፡ በ #ጋምቤላ ተጨማሪ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመከላከል በቂ የጸጥታ ኃይል በአስቸኳይ እንዲሰማራ እና ተጎጂዎች ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙ #ኢሰመኮ አሳሰበ
የ #ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጋምቤላ ክልል እየታየ ያለውን የጸጥታ መደፍረስና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በአስቸኳይ ለመግታት በቂ የጸጥታ ኃይል እንዲሰማራና ተጎጂዎች ተገቢውን ካሳ እና ህክምና እንዲያገኙ አሳሰበ።
ኮሚሽኑ ታኅሣሥ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ኡመድ ኡጁሉ መገደላቸውን ተከትሎ፣ በከተማዋና በአካባቢው ወረዳዎች የተቀሰቀሰውን ግጭትና የተኩስ ልውውጥ መከሰቱን አስታውቋል።
በተከሰተው የተኩስ ልውውጥ ሳቢያ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና የአካል ጉዳት መድረሱን፣ የሰዎችን እና የመጓጓዣ አማራጮችን እንቅስቃሴ የሚገድብ የሰዓት እላፊ በክልሉ መንግሥት መጣሉን፤ ባንኮችንና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት ማቋረጣቸውን መገንዘቡን አስታውቋል።
#አዲስ_ስታንዳርድ ታህሳስ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ያነጋገራቸው የጥቃቱ ሰለባና አንድ የሕክምና ባለሙያ በጋምቤላ ከተማ እንዳዲስ የተቀሰቀሰው ጥቃት “በጎሳ ክፍፍል" እንዲሁም "በስልጣን ሽርኩቻ” ላይ ያተኮረ መሆኑን በመጥቀስ፣ የበርካታ ንጹሐን ዜጎች ሕይወት ማለፉና የአካል ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል።
አንድ የጥቃቱ ስለባ፤ “በፖሊስ የጸጥታ አካላት በጥይት ጥታቅ እንደተፈጸመበት" ለአዲስ ስታንዳርድ አስረድተዋል። ጥቃቱ “በጎሳ ልዩነቶች” ላይ ያነጣጠረ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የጤና ባለሞያ አንዳንድ ታካሚዎች በሆስፒታሉ አካባቢ በሚሰማው የተኩስ ድምፅ በመሸበር፣ ሕክምናቸውን ሳይጨርሱ ወደ ቤታቸው መሄዳቸውን አመልክተዋል።
ዝርዝሩን ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=10171

Addis standard
በጋምቤላ ተጨማሪ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመከላከል በቂ የጸጥታ ኃይል በአስቸኳይ እንዲሰማራ እና ተጎጂዎች ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙ ኢሰመኮ አሳሰበ - Addis standard
አዲስአበባ፣ታኅሣሥ13 ቀን2018 ዓ.ም.፦ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጋምቤላ ክልል እየታየ ያለውን የጸጥታ መደፍረስና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በአስቸኳይ ለመግታት በቂ የጸጥታ ኃይል እንዲሰማራና ተጎጂዎች ተገቢውን ካሳ እና ህክምና እንዲያገኙ አሳሰበ። ኮሚሽኑ ታኅሣሥ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ኡመድ…
የ #ሰላም ሚኒስቴር ከፌዴራልና ክልል ምክር ቤቶች ጋር መከረ፤ በመድረኩ ተቋማት በዕቅዳቸው ውስጥ የሰላም ግንባታን ሊያካትቱ ይገባል ተባለ
የሰላም ሚኒስቴር ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር በመተባበር፣ የፌዴራልና የክልል ምክር ቤቶች በሕግ ማውጣት፣ በክትትልና ቁጥጥር ሥራዎቻቸው ውስጥ የሰላም ግንባታን ማካተት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ማካሄዱን አስታወቀ።
የሰላም ሚኒስትሩ አቶ መሐመድ ኢድሪስ በመድረኩ ላይ "ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ተቋማት በስትራቴጂያዊ ዕቅዶቻቸው ውስጥ የሰላም ግንባታ ተግባራትን ማካተት ይኖርባቸዋል" ብለዋል።
ሰላም ከአንድ ተቋም ብቻ የሚጠበቅ ሳይሆን በግለሰቦች፣ በተቋማትና በድርጅቶች ሁሉ ውስጥ የጋራ አጀንዳ መሆን እንዳለበት ሚኒስትሩ አፅንዖት ሰጥተዋል።
ሚኒስትሩ ሰላም የሚጀምረው እያንዳንዱ ተቋም የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ ከመወጣት ጀምሮ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የመሠረተ ልማት ግንባታና የማኅበረሰብ ግንኙነት እንዲሁም የሰላም ግንባታን ታሳቢ ያደረገ ዲዛይን ሊኖረው እንደሚገባ ጠቁመዋል።
አክለውም የተቋማት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የሰላም ሥራዎችን ሚዛን ውስጥ ያስገባ መሆን እንዳለበት መግለጻቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ እና በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ ቢቂላ ሁሪሳን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ተብሏል።
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n

ዜና፡ #ሳልሳይ_ወያነ_ትግራይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እስኪመለሱና የግዛት አንድነት እስኪረጋገጥ ድረስ ምርጫ እንዲራዘም ጠየቀ
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) በ #ትግራይ ክልል ተዓማኒ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስፈልጉ አነስተኛ የፖለቲካ እና የፀጥታ ሁኔታዎች ባለመሟላታቸው ምርጫው እንዲራዘም ጥሪ አቀረበ።
የሳወት ሊቀመንበር አቶ ክንፈ ሃዱሽ ቅዳሜ ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው እስኪመለሱና የክልሉ የግዛት አንድነት እስኪረጋገጥ ድረስ የምርጫው ጊዜ መራዘም እንዳለበት ተናግረዋል።
ክልሉ እየተባባሰ በመጣው የፖለቲካ እና የፀጥታ ቀውስ ምክንያት “ከባድ የህልውና አደጋ” ተጋርጦበታል ያሉት አቶ ክንፈ፤ ስልጣንን ለመያዝ ወይም ለማቆየት በትጥቅ ኃይል ላይ የሚደገፉ የፖለቲካ ኃይሎች ክልሉን ወደ አለመረጋጋት እየገፉት መሆኑን አስጠንቅቀዋል።
“በአሁኑ ወቅት በስልጣን ላይ ያለው በመሳሪያ የሚመራ የፖለቲካ ኃይል ነው” ያሉት ሊቀመንበሩ፣ ገዢው ኃይል ራሱ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት የመጣ መሆኑን እና ሌሎች የፖለቲካ ተዋናዮችም አለመግባባቶችን በወታደራዊ መንገድ ለመፍታት መሞከራቸው መፍትሄ እንደማያመጣ ገልጸዋል።
በተጨማሪም በወታደራዊ አዛዦች የሚመራ የመንግስት መዋቅር ለክልሉ ደህንነትም ሆነ ተዓማኒነት ላለው ምርጫ ተስፋ ከፍተኛ ስጋት እንደሚፈጥር አስጠንቅቋል። “እንዲህ ዓይነቱ መዋቅር ለነጻ እና ፍትሃዊ የምርጫ ሂደት የሚያስፈልገውን ምህዳር ያዳክማል” ብለዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፣ የትግራይ ክልልን ጨምሮ በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች መጪውን ሰባተኛ ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።
ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=10185

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እስኪመለሱና የግዛት አንድነት እስኪረጋገጥ ድረስ ምርጫ እንዲራዘም ጠየቀ - Addis standard
መቀለ፣ ታህሳስ 13/ 2018 ዓ/ም፦ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) በትግራይ ክልል ተዓማኒ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስፈልጉ አነስተኛ የፖለቲካ እና የፀጥታ ሁኔታዎች ባለመሟላታቸው ምርጫው እንዲራዘም ጥሪ አቀረበ። የሳወት ሊቀመንበር አቶ ክንፈ ሃዱሽ ቅዳሜ ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው እስኪመለሱና የክልሉ የግዛት አንድነት እስኪረጋገጥ ድረስ የምርጫው ጊዜ መራዘም እንዳለበት ተናግረዋል።…
የ #ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የንግድ ትስስርን ለማጠናከር የ #ሶማሊላንድን #በርበራ ወደብ ጎበኙ
የኢትዮጵያ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ልዑክ፣ በሶማሊላንድ የሚገኘውን የበርበራ ወደብ እና የበርበራ ነፃ የንግድ ቀጠናን መጎብኘቱን ባለሥልጣናት አስታወቁ።
ጉብኝቱ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የኢኮኖሚ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ሆርን ዲፕሎማት ዘግቧል።
ልዑኩ በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ የተመራ ሲሆን የሶማሌ ክልል የኢንቨስትመንት፣ የትራንስፖርትና የንግድ ዘርፍ ምክትል ሚኒስትሮች እና የሶማሌ፣ የትግራይ፣ የኦሮሚያ፣ የአማራ እንዲሁም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የንግድ ምክር ቤት ፕሬዝዳንቶችን ያካተተ ነው ተብሏል።
ልዑኩ ዛሬ ሰኞ ዕለት በበርበራ ወደብ ባደረገው ጉብኝት፣ የወደብ አገልግሎቶችን፣ የጉምሩክ አሰራርን እንዲሁም ቁልፍ የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ መሠረተ ልማቶችን ተመልክቷል።
የሶማሊላንድ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር ሞሐመድ ሀሰን ሳሌባን፣ የወደብ አገልግሎትንና የንግድ እንቅስቃሴን ለማቀላጠፍ የተደረጉ ማሻሻያዎችን ለልዑኩ አስረድተዋል። ሚኒስትሩ አክለውም የበርበራ ወደብና ነፃ የንግድ ቀጠናው ቀጣናዊ የንግድ ትስስርን ለማሳደግ ያላቸውን ሚናም አብራርተዋል።
ወደቡን የሚያስተዳድረው የ #ዲ.ፒ_ወርልድ ኃላፊዎች በበኩላቸው ፣ የወደቡን የሥራ አቅም ለማሳደግና ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከር እየተከናወኑ ያሉ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን ለልዑኩ አስረድተዋል። በተጨማሪም በርበራን በአፍሪካ ቀንድ ተወዳዳሪ የሎጂስቲክስ ማዕከል ለማድረግ የታለሙ ሥራዎችን አፅንዖት ሰጥተው አብራርተዋል።
https://www.facebook.com/share/1FK8zgddLq/

ትራምፕ #ግብፅ እና #ሶማሊያን ጨምሮ በ15 የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ አምባሳደሮቻቸውን ወደ ዋሽንግተን ጠሩ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግብፅ እና ሶማሊያን ጨምሮ በ15 የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ አምባሳደሮቻቸውን ወደ ሀገራቸው ጠርተዋል።
እርምጃው ያልተለመደ ነው የተባለ ሲሆን፣ ዩናይትድ ስቴትስ በውጭ ሀገራት ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ውክልና መልሳ ለማዋቀር የምታደርገው ሰፊ ጥረት አካል ነው ተብሏል።
በዲፕሎማሲያዊ ማኅበረሰብ ምንጮች እየተዘዋወረ ባለው መረጃ መሠረት፣ አሜሪካ አምባሳደሮቿን ወደ ሀገሯ የጠራችባቸው የአፍሪካ ሀገራት ዝርዝር የተለያዩ የአህጉሪቱን ቀጠናዎች ያካተተ ነው።
ዝርዝሩ በሰሜን አፍሪካ የሚገኙትን #ግብፅ እና #አልጄሪያን ጨምሮ በ #አፍሪካ_ቀንድ፣ በ #ምስራቅ፣ በ #ምዕራብ፣ በ #መካከለኛውና በ #ደቡባዊ_አፍሪካ የሚገኙ ሀገራትን ያጠቃልላል።
አምባሳደሮቹ እንዲመለሱ ስለተደረገበት ምክንያት እስካሁን የተሰጠ ይፋዊ ማብራሪያ የለም የተባለ ሲሆን፤ ክፍት የሆኑትን የሥራ መደቦች ለመተካት ግልጽ የሆነ የጊዜ ሰሌዳ አለመቀመጡም ተመላክቷል።
ውሳኔው በአፍሪካ ቀንድ በሶማሊያ የሚገኙ የአሜሪካ አምባሳደርን እንደሚመለከት የተነገረ ሲሆን ቀጠናው በዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦች መተላለፊያነቱ፣ በአሜሪካ የጦር ሰፈር መገኘት እና በፀረ-ሽብር ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጠው በመሆኑ ለዋሽንግተን ስልታዊ ፋይዳ ያለው አካባቢ መሆኑ ተጠቁሟል።
ተጨማሪ:-
https://www.facebook.com/share/1EaochTddW/

ዜና፡ በ #ትግራይ #ህጻፅ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ በርካታ ተፈናቃዮች ለከፋ ረሃብና ለሞት አደጋ መጋለጣቸው ተገለፀ
በትግራይ ክልል ህጻፅ መጠለያ ጣቢያ በሚገኙ በርካታ ተፈናቃዮች እየተባባሰ በመጣ የረሃብ ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ ተገለጸ። በከፋ የምግብ እጥረትና በውስን የህክምና አገልግሎት ምክንያት ተደጋጋሚ ሞት እየተመዘገበ መሆኑንና በርካታ ሰዎች በአስከፊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ዘገባዎች አመላክተዋል።
በክልሉ መገናኛ ብዙሃን ባወጡት ዘገባ መሠረት፣ ከሐምሌ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በምግብ እጥረት ምክንያት ቢያንስ 50 ተፈናቃዮች ህይወታቸው አልፏል። ወደ 1,700 የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ ለተመሳሳይ አደጋ ተጋልጠዋል። አረጋውያን፣ ሴቶችና ህጻናት ዋነኛ ተጎጂዎች ሲሆኑ፣ ነዋሪዎች ለቀናት የሚበሉት በማጣታቸው ምክንያት ተዳክመው እንደሚወድቁ ተገልጿል።
ከምዕራብ ትግራይ ተፈናቅለው በህጻፅ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ቤተሰቦች ለመገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት፣ የምግብና የመድኃኒት እጥረት ሰዎች እንዲሞቱ ምክንያት ሆኗል።
የሚቀርብላቸው ድጋፍ በቂ እንዳልሆነና አልፎ አልፎ የሚሰጣቸው 15 ኪሎ ግራም እህል መሰረታዊ ፍላጎታቸውን እንደማያሟላም ገልጸዋል። ተፈናቃዮቹ አክለውም፣ እህሉን ለማስፈጨትና ለሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ወጪም ለመሸፈን ግማሹን እህል ለመሸጥ እንደሚገደዱ ተናግረዋል። በተጨማሪም የሚቀርበው የእህል ዓይነት ለህጻናት፣ ለአረጋውያንና ለታመሙ ሰዎች ለመመገብ አስቸጋሪ መሆኑን ጠቁመዋል።
የምዕራብ ትግራይ አስተዳዳሪ አቶ ግደይ አዘናው ከ50 በላይ ተፈናቃዮች መሞታቸውን አረጋግጠዋል። ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ከ300 በላይ ተፈናቃዮች ህይወታቸውን ማጣታቸውን ገልጸው፣ አስቸኳይ ጣልቃ ገብነት ካልተደረገ ተጨማሪ የሰው ህይወት ሊጠፋ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የችግሩን አሳሳቢነት በመግለጽ መግለጫ አውጥተዋል፤ ለአብነትም የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ( #ኢሕአፓ) ትናንት ታህሳስ13 ቀን ባወጣው መግለጫ፤ “ከጦርነት የተረፉ ንጹሀን በረሀብ እየተገረፉ መሆኑ ትልቅ የሰብዓዊነት ልሽቀት ነው!” ሲል ገልጿል።
ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=10192

በትግራይ ህጻፅ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ በርካታ ተፈናቃዮች ለከፋ ረሃብና ለሞት አደጋ መጋለጣቸው ተገለፀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14/ 2018 ዓ/ም፦ በትግራይ ክልል ህጻፅ መጠለያ ጣቢያ በሚገኙ በርካታ ተፈናቃዮች እየተባባሰ በመጣ የረሃብ ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ ተገለጸ። በከፋ የምግብ እጥረትና በውስን የህክምና አገልግሎት ምክንያት ተደጋጋሚ ሞት እየተመዘገበ መሆኑንና በርካታ ሰዎች በአስከፊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ዘገባዎች አመላክተዋል። በክልሉ መገናኛ ብዙሃን ባወጡት ዘገባ መሠረት፣ ከሐምሌ 2017 ዓ.ም…
ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶች እገዳ ከጥር 23 ቀን ጀምሮ ተግባራዊ ሊደረግ ነው ተባለ
በአካባቢ ላይ የሚደርሰውን ብክለት ለመቀነስ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት ብቻ የሚውሉ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶችን ማምረት፣ መጠቀምና ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ከጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሕግ እንደሚያስቀጣ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ።
በባለሥልጣኑ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ዴስክ ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ዓለሙ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶችን የሚከለክለው አዋጅ ከሐምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የጸደቀ ቢሆንም ፣ ባለሥልጣኑ ለባለድርሻ አካላትና ለአምራቾች የስድስት ወራት የሽግግር ጊዜ ሰጥቶ መቆየቱን አውስተዋል።
አዋጁ በወጣበት ወቅት የወረቀትና ሌሎች አማራጭ ከረጢቶች ወደ ገበያ በመምጣታቸው የፕላስቲክ ስርጭት ቀንሶ እንደነበር ያነሱት ኃላፊው ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶች በድጋሚ በገበያው ውስጥ በስፋት መስተዋላቸዉን ገልጸዋል።
አክለውም ባለሥልጣኑ አዋጁን ሙሉ በሙሉ ለመተግበር የሚያስችሉ የዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልፀው፣ ከአምራቾችና ከተጠቃሚዎች ጋር ውይይት መደረጉንም ጠቁመዋል።
ባለሥልጣኑ አማራጭ የወረቀት ከረጢቶችን ለማምረት ለሚፈልጉ አካላት፣ የማምረቻ ማሽኖችን ከቀረጥ ነፃ ማስገባት አንዲችሉና የብድር አቅርቦት እንዲመቻች ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል።
የሽግግር ጊዜዉ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚያበቃ የገለጹት ኃላፊው ፣ ከዚህ ዕለት በኋላ ስስ የፕላስቲክ ከርጢቶችን የሚያመረቱ፣ ወደ ሀገር የሚያስገቡና ይዘው የሚገኙ ኣካላት በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ ሲሉ ማስጠንቀቃቸዉን የዘገበው ኢፕድ ነው።

ምርጫ ቦርድ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት ላይ መከረ
የ #ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳን ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም. ይፋ ማድረጉን ተከትሎ፣ ትላንት ከገዢው ፓርቲና ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ።
ምክክሩ የተካሄደው ቦርዱ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሠሌዳን ጥቅምት 10 ባስተዋወቀበት ወቅት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጥያቄዎች መነሳታቸውን ተከትሎ ነው።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በውይይቱ መክፈቻ ባደረጉት ንግግር 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊና ገለልተኛ እንዲሆን የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ገልጸዋል። ሰብሳቢዋ አክለውም፣ አስቻይ የፖለቲካ ምኅዳር መፍጠርና የውይይት መድረኮችን ቀጣይነት ማረጋገጥ ለምርጫው ስኬት ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።
ፖለቲካ ፓርቲዎቹ የዕጩ ድጋፍ ፊርማ ማቅረብ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መታገድን አስመልክቶ ለቦርዱ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል ሲል የቦርዱ መረጃ አመላክቷል።
በተጨማሪም ምርጫውን አስመልክቶ መሟላት አሉባቸው ያሏቸውን ሁነቶች፣ አስቻይ ሁኔታና የውይይቱ ቀጣይነትን ጨምሮ በርካታ ጉዳዮች ላይ ተሣታፊ ፖለቲካ ፓርቲዎቹ ያሏቸውን አስተያየቶችና ጥያቄዎች አጋርተዋል።
ሜላትወርቅ በውይይቱ ፓርቲዎቹ ለሰጡት አስተያየትና ላቀረቡት ጥያቄዎች አመስግነው፤ የፀጥታ አስቻይ ሁኔታን በተመለከተና ሌሎች ምርጫውን የተመለከቱ ጉዳዮችን አስመልክቶ የሚኖሩ የምክክርና የውይይት መድረኮች ቀጣይነት ያላቸው እንደሚሆኑ ተናግረዋል።
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid02gJaEANYHwTprhZsHjNbCy8JJDP9QRWTcjG5D49wuvwfrBFHuhv9HoixMu9uiMGVql

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከ #ኬንያው ፕሬዝደንት ዊልያም ሩቶ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መከሩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት #አዲስ_አበባ የገቡትን የኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶን ተቀብለው ማነጋገራቸውን አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬዝደንቱን ጉብኝት አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ዛሬ የኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ተቀብያለሁ። ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊ እና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው“ ብለዋል።
ጠ/ሚንስትሩ አክለውም ከዊሊያም ጋር ባደረጉት ውይይት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ሃሳብ መለዋወጣቸውን ገልጸዋል።
“ይኽም በሰላም እና መረጋጋት፣ ንግግር ብሎም በአፍሪካ መር መፍትሔዎች ላይ ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያሳይ ነበር” ሲሉ አክለው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr

ዜና: ተመድ የሱዳን ጦርነት ወደ ኢትዮጵያ ሊዛመት እንደሚችል በመግለፅ ሰፊ የቀጣናዊ ግጭት ስጋት መጋረጡን አስጠነቀቀ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት፤ በሱዳን እየተባባሰና ከጊዜ ወደ ጊዜ ዓለም አቀፋዊ መልክ እየያዘ የመጣው ግጭት ወደ ጎረቤት አገራት በተለይም ወደ ኢትዮጵያ ሊዛመት እንደሚችል አስጠነቀቀ።
ይህም ሊሆን የሚችለው ውጊያው እየበረታ፣ የጦር መሣሪያዎች ስርጭት እየጨመረ እና ታጣቂ ቡድኖች ባልተጠበቁ ድንበሮች በኩል እየተንቀሳቀሱ በመሆናቸው ነው ብሏል።
ለጸጥታው ምክር ቤት ገለጻ ያደረጉት የፖለቲካና ሰላም ግንባታ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሐፊ ኻሊድ ኺያሪ፤ ጦርነቱ በቅርቡ ወደ ሱዳን የኮርዶፋን ግዛት አቅጣጫ መዞሩን ገልጸዋል።
በዚሁ መሠረት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል የባባኑሳን ከተማ በጎርጎሮሳውያኑ ታኅሣሥ 1 ቀን፣ የሄግሊግ የነዳጅ ማውጫን ደግሞ በታኅሣሥ 8 ቀን መቆጣጠሩን እና በደቡብ ኮርዶፋን የሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች አሁንም በከበባ ውስጥ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
አክለውም በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን መካከል እየታየ እንዳለው ሁሉ ታጣቂ ቡድኖች ድንበር ተሻግረው የሚያደርጉት እንቅስቃሴ፣ ለቀጣናው መረጋጋትን ሊያሳጣ የሚችል ተጽዕኖ እንዳለው አስጠንቅቀዋል።
ተጨማሪ ይመልከቱ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=10202&=1

ተመድ የሱዳን ጦርነት ወደ ኢትዮጵያ ሊዛመት እንደሚችል በመግለፅ ሰፊ የቀጣናዊ ግጭት ስጋት መጋረጡን አስጠነቀቀ - Addis standard
አዲስ አበብ፣ ታህሳስ 14/ 2018 ዓ.ም.፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት፤ በሱዳን እየተባባሰና ከጊዜ ወደ ጊዜ ዓለም አቀፋዊ መልክ እየያዘ የመጣው ግጭት ወደ ጎረቤት አገራት በተለይም ወደ ኢትዮጵያ ሊዛመት እንደሚችል አስጠነቀቀ። ይህም ሊሆን የሚችለው ውጊያው እየበረታ፣ የጦር መሣሪያዎች ስርጭት እየጨመረ እና ታጣቂ ቡድኖች ባልተጠበቁ ድንበሮች በኩል እየተንቀሳቀሱ በመሆናቸው ነው…
ዜና፡ የፈንታሌ ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ፋኑኤል ክንፉ "ማንነታቸው ካልታወቁ ሰዎች" ለማምለጥ ሲሞክር ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ገለፀ
የፈንታሌ ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ፋኑኤል ክንፉ “ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች” በአዲስ አበባ ከተማ “ሊፈፀምብኝ ነበር” ካለው ጥቃት ለማምለጥ ሲሞክር ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፀ።
ጋዜጠኛ ፋኑኤል በደረሰበት ጉዳት ሳቢያም ለመራመድ ከሶስት እስከ ስድስት ወር ሊፈጅበት እንደሚችል በህክምና ባለሞያተኞች እንደተገለጸለት ተናግሯል። ጋዜጠኛው ስለደረሰበት ጉዳት ለአዲስ ስታንዳርድ ሲያብራራ፣ ከወር በፊት ማለትም ህዳር 10/2018 ዓ.ም ስምንት ሰዓት አከባቢ “ሲቪል የለበሱ ሰዎች እንደሚፈልጉኝ” ከቤተሰብ ሰማሁ ሲል ይጀምራል።
በወቅቱ “የቅርብ ጓደኛው ጋር በመሄድ ጉዳዩን እንደነገረው እና ገስት ሀውስ ብታርፍ ይሻላል ብሎኝ ወደዚያው በማቅናትት እዛው ክፍል አግኝቼ ገባው” ሲል ጋዜጠኛው ገልጿል።
ሆኖም የቅርብ ጓደኛው ከሄደ ከ50 ደቂቃ በኋላ ያረፈበት ክፍል በሩ በጣም ይደበደብ እንደጀመረ ጠቅሶ፣ በወቅቱ “ክፈት የሚል እና ሀይለቃል የተሞላበት ቃል እሰማ ነበር” ብሏል።
“በሩን በጣም እየገፉት ሲመጡ ክፍሏ ከጎን የበረንዳ ኮሪደር ያላት በመሆኑ ኮሪደሩ ጋር ሆኜ ተዘጋጀሁ” ያለው ጋዜጠኛው፣ “በወቅቱ ደብድበው ሞቶ ተገኘ ልባል እችላለሁ የሚል ስጋት አደረብኝ በዚህም አራት ሜትር አከባቢ ከሚረዝም ሁለተኛ ፎቅ ላይ ዘለልኩ” ሲሉ ተናግሯል።
አክሎም “ዘልዬ ከወደኩኝ በኋላ ልነሳ ስል ራሴን ሳትኩ ጭልም አለብኝ” ሲሉ ገልጾ፣ “ቀና ስል አጥንቴ ተሰብሯል። በአከባቢዬ ሲቪል የለበሱ ሰዎች ነበሩ። "ይሄን እድል ደግመህ አታገኝም" ብለውኝ ሄዱ ከዛም ሰዎች ወደ ሆስፒታል ወሰዱኝ ብሏል።
“ከዛ በኋላ ለ20 ምናምን ቀናት ለማንም ጉዳዩን አልተናገርኩም ነበር” ያለው ጋዜጠኛ ፋኑኤል፣ ነገር ግን ጉዳዩ “ከሚዲያ ስራው ጋር የተገናኘ ነው” ብሎ እንደሚያምን ተናግሯል።
ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=10205

የፈንታሌ ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ፋኑኤል ክንፉ "ማንነታቸው ካልታወቁ ሰዎች" ለማምለጥ ሲሞክር ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ገለፀ - Addis standard
አዲስአበባ፣ ታህሳስ 14/ 2018 ዓ/ም፦ የፈንታሌ ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ፋኑኤል ክንፉ “ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች” በአዲስ አበባ ከተማ “ሊፈፀምብኝ ነበር” ካለው ጥቃት ለማምለጥ ሲሞክር ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፀ። ጋዜጠኛው በደረሰበት ጉዳት ሳቢያም ለመራመድ ከሶስት እስከ ስድስት ወር ሊፈጅበት እንደሚችል በባለሞያተኞች እንደተገለጸለት ተናግሯል። ጋዜጠኛ ፋኑኤል ስለደረሰበት…
በ #አዲስ_አበባ ከተማ በአጥር የተዘጉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በግብረ ኃይል የማስከፈት ስራ ተጀመረ
በአዲስ አበባ በከተማ ተለያዩ አካባቢዎች በአጥር የተዘጉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በግብረ ኃይል የማስከፈት ስራ በትናንትናው ዕለት መጀመሩን የከተማዋ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ።
ባለስልጣኑ ይህን እርምጃ መውሰድ የጀመረው፣ ከሳምንታት በፊት በከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን አጥረው የዘጉ ግለሰቦች መንገዶቹን ከታኅሣሥ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት ሰባት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ክፍት እንዲያደርጉ የሰጠው ማስጠንቀቂያ ተግባራዊ ባለመሆኑ ነው።
ባለስልጣኑ ትናንት ባጋራው መረጃ፣ የደቡብ አዲስ አበባ መንገድ ኔትዎርክ ማኔጅመንት ቡድን መሪ ኢንጅነር ቢሊሱማ በዬቻ፤ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በግለሰቦች በአጥር መዝጋታቸው፤ የህብረተሰቡን በመንገድ መሰረተ ልማት የመጠቀም መብት የሚጋፋና ለትራፊክ ፍሰት መስተጓጎል መንስኤ እየሆነ እንደሚገኝ ገልፀዋል ብሏል፡፡
በመሆኑም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቃሊቲ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ጀርባ፤ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በአጥር የዘጉ አካላት፣ አጥሩን እንዲያነሱ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ቢሆንም፤ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ባለመነሳቱ ከወረዳው የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በግብር ኃይል እንዲነሳ መደረጉን ገልጸዋል።
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0K763TCGodEANKMS2Ca5DFSMcWnBgU7U3uPXE2hQX8GfvsjPhUJKzGG8uwEp68VxDl

ዜና: ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የጤና ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ፤ የአገር ውስጥ የፋይናንስ አቅምን ለማሳደግም ቃል ገብተዋል
ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ለኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ በጋራ 1.466 ቢሊዮን ዶላር ለመመደብ የሚያስችል የአምስት ዓመት የጤና ትብብር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
በስምምነቱ መሠረት አሜሪካ እስከ 1.016 ቢሊዮን ዶላር የምትመድብ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ደግሞ ከአገር ውስጥ ሀብት 450 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሸፍን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ገልጸዋል። የመግባቢያ ስምምነቱ ከጎርጎሮሳውያኑ 2026 እስከ 2030 ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ይሆናል ተብሏል።
የአሜሪካ መንግሥት በተጨማሪም በሥራ አፈፃፀም ላይ የተመሠረተ 150 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ የገንዘብ ሚኒስቴር አመልክቷል። ድጋፉ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ከሆነ የአሜሪካ አጠቃላይ የገንዘብ ድጋፍ ወደ 1.166 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ይላል የተባለ ሲሆን፤ ይህም ኢትዮጵያ ከምትሸፍነው ጋር ተደምሮ የአምስት ዓመቱን የጤና ትብብር ጥቅል ማዕቀፍ 1.616 ቢሊዮን ዶላር ያደርሰዋል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ስምምነቱ “አሜሪካ ለኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ የሚያረጋግጥ ነው” ያሉ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ የአገር ውስጥ የጤና ኢንቨስትመንቷን ለማስፋፋት የወሰደችውን ውሳኔም አድንቀዋል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በበኩላቸው የመግባቢያ ስምምነቱን በሁለቱ መንግሥታት መካከል ያለውን መተማመን የሚያሳይ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ምልክት መሆኑን ገልጸዋል።
ተጨማሪ ይመልከቱ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=10213&=1

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የጤና ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ፤ የአገር ውስጥ የፋይናንስ አቅምን ለማሳደግም ቃል ገብተዋል - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15/ 2018 ዓ/ም፦ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ለኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ በጋራ 1.466 ቢሊዮን ዶላር ለመመደብ የሚያስችል የአምስት ዓመት የጤና ትብብር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ። በስምምነቱ መሠረት አሜሪካ እስከ 1.016 ቢሊዮን ዶላር የምትመድብ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ደግሞ ከአገር ውስጥ ሀብት 450 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሸፍን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ…