Addis Standard Amharic – Telegram
Addis Standard Amharic
18K subscribers
4.76K photos
123 videos
3 files
3.78K links
አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሚኒስትሮች ልዑክ ቡድን በሮም፤ ጣሊያን የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ከፕሬዝዳንት ሴርጂዮ ማታሬላ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት በኢትዮጵያ እና ጣሊያን መካከል ስላለው ግንኙነት እንዲሁም በሌሎች ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። #PMOEthiopia
ዜና፡ የምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ የፀጥታ ኃላፊ እና የሚኒሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በታጣቂዎች መገደላቸውን ተገለፀ

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻከል ወረዳ የፀጥታ ኃላፊ አቶ አይናለም አላምነህ እና የወረዳው ሚኒሻ ጽህፈት ቤት ሃላፊ የነበሩት አቶ አዝመራው አማረ በታጣቂዎች መገደላቸውን የዞኑ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ አስታወቀ።

ኃላፊዎቹ በማቻከል ወረዳ ጥር 27/2015 ዓ.ም. ሌሊት ህዝብን ለማገልገል በነበሩ የጸጥታ አመራሮች ላይ ማንነታቸዉ ባልታወቁ አካላት በተተኮሰ ጥይት ህወታቸዉ መለፉ ገልጿል። https://amharic.addisstandard.com/%e1%8b%9c%e1%8a%93%e1%8d%a1-%e1%8b%a8%e1%88%9d%e1%88%b5%e1%88%ab%e1%89%85-%e1%8c%8e%e1%8c%83%e1%88%9d-%e1%8b%9e%e1%8a%95-%e1%88%9b%e1%89%bb%e1%8a%a8%e1%88%8d-%e1%8b%88%e1%88%a8%e1%8b%b3-%e1%8b%a8/
ዜና፡ ምርጫ ቦርድ አዲስ ክልል ለመመስረት ህዝበ ውሳኔ እየተካሄዳ ባለበቅ ቀን በጉራጌ ዞን ነዋሪዎች ለአራተኛ ጊዜ ስራ የማቆም አድማ እያደረጉ ነው

የጉራጌ ዞን የክልል አደረጃጀት ጥያቄን ተከትሎ በተነሱ ተቃውሞዎች ዞኑ ከህዳር 16 ቀን ጀምሮ በተደረጃ ኮማንድ ፖስት እንድትመራ አድርጓታል፡፡ ዛሬ እየተደረገ ያለው ቤት የመዋል ተግባር ኮማንድ ፖስቱ ያስተላለፈውን ክልከላ በመጣስ ነው።

የጉራጌ ዞን ዋና ከተማ የሆነችው የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ ሃይደር ሙራድ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለፀው የጉራጌ ህዝብ በምክር ቤት የጠቀውን በክልል የመደራጀት መብቱን መንግስት በፍጥነት መልስ መስጠት ባለመቻሉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በተደጋጋሚ ስራ የማቆም አድማ እየተደረገ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ዘሬ እየተደረገ ያለው ስራ የማቆም አድማም በውልቂጤ ከተማ ብቻ ሳይሆን ጉሙሬ፣ እንደብር፣ አገና፣ ጉንቹሬ፣ ሚቄ፣ ዱንኩላ፣ ቋንጤ፣ አበሽኬ እና በሌሎችም ወረዳዎችም ቤት ውስጥ የመዋል አድማ እየተከናወነ እንደሚገኝ ትግሉን ከሚመሩት አንዱ የሆኑት አንድነት አኑሎ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል፡፡ አክለውም ከነገ ጅምሮ ህዝቡ ወደ ተለመደው እንቅስቃሴ እንደሚገባ ጠቅሰው መንግስት ለጥያቄያችን መልስ እስካልሰጠ ድረስ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ትግሉ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-ምርጫ-ቦርድ-አዲስ-ክልል-ለመመስረት/?fbclid=IwAR2cCXYdY9dZ0-5eFVhDcyKVzJJhvdzcQWauQLSPGLM4Ch5NH9diQ7W-xhQ
ዜና ትንታኔ፡ ከኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ጋር በተፈጠር ግጭት በ19 የፖሊስ አባላት ላይ ጉዳት ደረሰ፤ በሻሸመኔ ከተማ በምዕመናንን እና ፖሊስ መካከል በተፈጠረው ግጭት “በርካታ ሰዎች” ሞተዋል፤ መንግስት “ህገወጥ” የተባሉትን ቡድን ከመደገፍ እንዲቆጠብ ሲኖዶሱ አሳሰበ

በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ልዩ ዞን ድንበር በተለምዶ ፊሊዶሮ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቅድስት ለደታ ቤተ ክርስቲያን የተሰበሰቡ ሰዎች “የታሰሩ ሰዎች ይፈቱ” በማለት መንገድ በመዝጋት የፀጥታ ችግር ኢንዲከሰት በማድረግ በ19 ፖሊሶች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ማድረሳቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሻሸመኔ ከተማ ቅዳሜ ጥር 27 በኦርቶዶክስ ምዕመናን እና በከተማ ፖሊስ መካካል በተነሳ ግጭት የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን የአይን እማኝ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፀ፡፡ ግጭቱ የተቀሰቀሰው በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በአዲሱ “የኦሮሚያና ብሔሮች ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ” የተሾሙ አባላት የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ላይ በነበረበት ወቅት ነው።

የሟቾቹን ትክክለኛ ቁጥር ማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም የቤተክርስቲያኗ ሚዲያዎች የማቾቹ ብዛት ከ35 በላይ እንደሚደርስ ዘግበዋል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሃፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ከአንከር ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ቁጥሩ እስከ 30 መድረሱን ተናግረዋል።

https://amharic.addisstandard.com/ዜና-ትንታኔ፡-ከኦርቶዶክስ-እምነት-ተከታ/?fbclid=IwAR2DFWX4mRuFQ1rQo0vjJpsGJv_Z0xqEC8bnfemNv_Boy5jfLxepT-WNAas
ዜና: አንድ ነጥብ አራት ቢሊየን ብር የሚፈጅ የኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ህንፃ ሊገነባ ነው

የኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ህንፃ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ ።

በመከላከያ ሠራዊት መሰረት በአንድ ነጥብ አራት ቢሊየን ብር የሚገነባው የኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ህንፃ በአራት መቶ ቀናት ዉስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን በዛሬዉ ዕለት የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ እና የስምምነት ፊርማ ተከናዉኗል፡፡ ይሁን እንጂ የሕንፃው ቦታ የት እንደሚሆን ግልጽ አይደለም፡፡

በዝግጅቱ ላይ በመገኘት የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጡት የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ፤ ህንፃው ዘመናዊና ሁለገብ ሰራዊት ለመገንባት የተጀመሩ ስራዎች አንዱ አካል የሆነ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።

https://amharic.addisstandard.com/ዜና-አንድ-ነጥብ-አራት-ቢሊየን-ብር-የሚፈጅ/?fbclid=IwAR04TjnfmXgjcvKeu9cQ1-yx1xwAa6JVM6jEETxxrfJJvcguCCkRNYuZem4
በጋምቤላ ክልል ከዛሬ ጀምሮ የስራ ሰዓት ለውጥ ተደረገ

በጋምቤላ ክልል የሙቀት መጠን እየጨመረ በመምጣቱ የመንግስት የስራ ሰዓት ከነገ ጀምሮ ለውጥ እንደሚደረግ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት አስታወቀ።

የክልሉ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፒተር ሆው እንዳሉት በክልሉ የሙቀቱ መጨመር ለስራ ምቹ ባለመሆኑ ከዛሬ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ወራት የሚቆይ የስራ ሰዓት ለውጥ ተደርጓል።

በለውጡ መሰረትም ቀደም ሲል የመደበኛው የስራ ሰዓት ከጥዋቱ አንድ ሰዓት እስከ ስድስት ሰዓት ተኩል የነበረው ከአንድ ሰዓት እስከ አምስት ሰዓት ተኩል እንደሚሆን አስታውቀዋል።

እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከዘጠኝ ሰዓት እስከ 11 ተኩል የነበረው ከአስር ሰዓት እስከ 12 ሰዓት ተኩል እንዲሆን መወሰኑን አቶ ፒተር አመልክተዋል።

የስራ ሰዓት ለውጡ በማጃንግ ዞን የመንገሽና የጎደሬ ወረዳዎችን እንደማይጨምር አስረድተዋል።

በለውጡ መሰረትም የክልሉ የመንግስት ሰራተኞች በተጠቀሰው የስራ ስዓት መስሪያ ቤታቸው በመገኘት የተለመደ ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ አቶ ፒተር አሳስበዋል።

ምንጭ- የጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት

ፎቶ- ፋና
ዜና፡ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ባቀረበችው የሶስት ወር እግድ አቤቱታ ላይ ፍርድ ቤቱ ዛሬ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ህገ ወጥ የሆነ ሹመት ሰጥተዋል በተባሉት በአቡነ ሳውሮስና በ25 ቱ ተሻሙዎች እንዲሁም ህግ የማስከበር ግዴታቸውን አልተወጡም ባለቻቸው የኦሮሚያ ክልል መንግስት፣የፌደራል ፖሊስና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽኖች ላይ ባቀረበችው የዕግድ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለዛሬ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-የኢትዮጵያ-ኦሮቶዶክስ-ተዋህዶ-ቤተ/?fbclid=IwAR3T5IIV2h7F_WZTFOZiFgLFUf0L2Q1G1WuJTZmMYVKFWwmpvWsjWkKM2Hw

ቤተ ክርስቲያኗ ጠ/ሚንስትሩን ጨምሮ የፀጥታ ሃይሎች ከድርጊቱ እንዲቆጠቡ የሚመለከተው አካል ትዕዛዝ እንዲሰጥ እንደምትፈልግ ለልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሠረታዊ መብቶች ችሎት የሕግ ባለሞያዎቿ ማስረዳታቸውን ቋሚ ኮሚቴው በሰጠው መግለጫ ገልጿል፡፡

እግድ የጠቀቃችሁት ምን አይነት ክስ ለመመስረት ነው ተብለን ለተቀየቅነው፣ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ካላት ምእመን፣ የቤተ ክርስቲያን ብዛት አንፃር በቂ ጊዜ ወስደን ሰፋ ያለ ክስ ማዘጋጀት ለማዘጃገት የሶስት ወር እግድ መጠየቅ አስፈላጊ መሆኑን አስረድተናል ሲል አንዷለም ገልፀዋል፡፡
የአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ በ #ትግራይ ክልል የተበላሹ የውሃ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ጥረቱን እንደቀጠለ አስታወቀ።

በመሆኑም #አክሱም ላይ የእጅ ፓምፖችን ወይም የውሃ መሳቢያ መሳሪያዎችን በመትከል ማህበረሰቡ አስተማማኝ እና ንፁህ ውሃ እንዲያገኝ አስችለናል ሲል ዛሬ ባወጣው መረጃ ገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ዛሬ ከሰዓት መወያየታቸውን የጠ/ሚ ፅ/ቤት አስታውቋል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይቱን ያደረጉት ከልዑካቸው ጋር በአውሮፓ ያደረጉትን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ከተመለሱ ከሰዓታት ቆይታ በኋላ ነው።
ዜና፡ ድንበር ጥሰው ወደ ክልሉ የገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ሁለት ሰዎችን ገድለው አንድ ሰው ማቁሰላቸው ተገለፀ

ከደቡብ ሱዳን በመነሳት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ወደ ጋምቤላ ክልል የገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ሁለት ሰዎችን ገድለው አንድ ሰው ማቁሰላቸውን የጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።

ድንበሩ ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በተለይም በአኙዋና በኑዌር ዞኖች ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈጸም መንግስት ከሚያደርገው ጥረት በተጓዳኝ ህብረተሰቡ በንቃት አካባቢውን እንዲጠብቅ አቶ ኡቶው አሳስበዋል።

የሙርሌ ታጣቂዎቹ ከዚህ በፊትም በተለይም በበጋው ወራት በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው በመግባት የሰው ሕይወት ሲያጠፉ፣ ሕፃናትን አፍነው ሲወስዱና ንብረት ሲዘርፉ እንደነበር ይታወቃል።

ባሳለፍነው አመት ጥር ወር አጋማሽ ላይ ከደቡብ ሱዳን በመጡ የሙርሌ ታጣቂዎች በክልሉ ኑዌር ዞን አኮቦ ወረዳ ባካንካን ቀበሌ ላይ በከፈቱት ጥቃት ስምንት ሰዎች ሲሞቱ አምስት ሰዎች ቆስለዋል።

https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-ድንበር-ጥሰው-ወደ-ክልሉ-የገቡ-የሙር/?fbclid=IwAR3jWB1QWs0-F2Gp5IznCYfasAtVoaPuVhQ9IiebghNUJllM8_HEinb7PI0
ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በመውጫ ፈተና ዙሪያ ከተማሪዎች ህብረት ተወካዮች ጋር የተወያዩ ሲሆን የመውጫ ፈተና በመጪው ሐምሌ ወር በኦንላይን ለሁሉም የመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ብቁ ለመሆንም ተማሪዎች በየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚሰጠውን የመጨረሻውን ሴሚስተር ፈተና መውሰድና ኮርሶችን ማጠናቀቅ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

ለፈተናው በሁሉም የትምህርት መስኮች ላይ የተመረጡ ኮርሶች የብቃት ልየታ ተደርጎላቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲያውቁት መደረጉን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው በአሁኑ ወቅት የፈተና ንድፈ ማሳያና የፈተና ዝግጅት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በመሆኑም ተማሪዎች በቀሪዎቹ አምስት ወራት ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ራሳቸውን ለፈተናው ብቁ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙ የተማሪዎች ህብረት ተወካዮችም ወደ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው ሲመለሱ ተማሪዎች ለፈተናው በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

ምንጭ -ዋልታ
ዜና፡ የሰላም ጥረቱን ተከትሎ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና ስደተኞች የሚደረገው ድጋፍ እና መፍትሔ እንዲጠናከር የተመድ የስደተኞች ኮሚሽን ጠየቀ

በኢትዮጵያ ከቀያቸው የተፈናቀሉ እና ስደተኞችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን የበለጠ እንደሚያጠናክር ሃላፊው ፍሊፖ ግራንዴ አስታወቁ። በኢትዮጵያ በድርቅ እና የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የተፈናቀሉም ሆኑ ስደተኞችን ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ ለማስቻል ኮሚሽኑ ጥረቱን እንደሚያጠናክር ገለጸዋል።

የሰላም ስምምነቱ ከተደረሰ ጥቅምት ወር ጀምሮ ከተባባሪ ድርጅቶች ጋር በመሆን በርካታ እገዛወችን ማድረጉን ያሰታወቀው ዩኤንኤችሲአር፣ የህይወት አድን እርዳታዎች በተለይም ደግሞ መድሃኒት፣ የመጠለያ ቁሳቁሶቸ፣ አልባሳት፣ የቤት ቁሳቁሶቸ እና ብርድ ልብሶችን ማድረሱን አመላክቷል።

“የአርዳታ አቅርቦቱ መሬት ላይ ወርዶ የሚታይ ሆኗል፤ ህዝቡ ድጋፍ እያገኘ ነው፤ አንዳንዶች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው” ሲሉ የገለጹት ኮሚሽነሩ በአፋር፣ አማራ እና ትግራይ የሚደረገውን የመልሶ ግንባታ እና ማቋቋም ጥረትን ይበልጥ ማገዝ ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም ኮሚሽነሩ ይህ ተግባር በፍቃዳቸው ወደ ቀያቸው የሚመለሱትን ጨምሮ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት እና ኑሯቸውን ለማሻሻል የሚያስችል ወሳኝ ተግባር ነው ሲሉ ገልጸዋል።

https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-የሰላም-ጥረቱን-ተከትሎ-በኢትዮጵያ/?fbclid=IwAR3F8viQ2T6zkUWRqsq3GrvDLzAlFKMNBv0eI1IO-uCzEFU6QaxQQplYAec
ዜና፡ መንግስት በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ እና ሃይማኖት አባቶች ላይ እየደረሰ ያለውን ማዋከቦች፣ እስሮች እና ግድያዎችን በአስቸኳይ እንዲያስቆም ኢዜማ አሰሰበ

መንግስት በኦሮሚያ ክልል በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ እና በሃይማኖት አባቶች ላይ እየደረሰ ያለው ማዋከቦች፣ እስሮች እና ግድያዎችን በአስቸኳይ ኢንዲያስቆም የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አሳሰበ።

ፓርቲው ከመንግስት ሃላፊዎች አባባሽ ንግግሮች ባሻገር የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና የጸጥታ ኃይሉ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት በተግባር ካሳዩት ወገንተኝነት እና አድሎ በከፋ መልኩ ፈፅሞ የጸጥታ ስጋት ባልሆኑ ምእመናን ላይ ጭካኔ የተሞላበት የኃይል እርምጃ በመውሰዳቸው የንጹሐን ዜጎች ሕይወት እንዲቀጠፍ እና አካል እንዲጎድል ምክንያት ሆኗል ብሏል፡፡

በዛሬ እለት እንኳን በወሊሶ መስመር በወለቴ፣ አለምገና እና ሰበታ ቀውሱ ተባብሶ ቀጥሏል ያለው የድርጅቱ መግለጫ ግልፅ በሆነ መንገድ ጣልቃ እየገባ ያለው መንግሥት ለሀገር ሰላምና ደህንነት ስጋት እየፈጠረ መሆኑን ተገንዝቦ ኃላፊነቱ “ህግን አክብሮ ማስከበር” መሆኑን በመረዳት እንዲንቀሳቀስ አሳስቧል

https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-መንግስት-በኦርቶዶክስ-እምነት-ተከ/?fbclid=IwAR3EwPL_RS3iOY7q24Nq1ZRzFBPb3K-FpujKcIAzf7NPQ-SuF8wKOYHJZVM
ዜና፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትግራይ በርካታ ቅርንጫፎቹ የተሟላ የባንክ አገልግሎት ጀመረ፤ በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል የከፈቱ የሂሳብ ደብተሮች መጠቀም ይቻላል ተባለ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትግራይ ክልል በሽሬ፤ አክሱም፤ ዓድዋ፤ ሰለኽለኻ፤ ማይ ፀብሪ፤ እንዳባጉና፤ ውቕሮማራይ፤ ዓዲግራት፣ ውቕሮ፣ ፍረወይኒ፣ ሓውዜን፣ ዓዲጉዶም፣ ሒዋነ፣ ዓዲሽሁ፣ መኾኒ፣ ማይጨውና አካባቢው በሚገኙ በርካታ ቅርንጫፎች የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ባንኩ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት እደገለጸው፥ አገልግሎት መስጠት በጀመረባቸው ቅርንጫፎች ለደንበኞች የተሟላ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ “የባንኩ ደንበኛ የሆነ ማንኛውም ሰው በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል የከፈተውን የሂሳብ ደብተር ይዞ በመቅረብ አገልግሎት ማግኘት ይችላል” ሲልም ጨምሮ ገልጿል፡፡

https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-የኢትዮጵያ-ንግድ-ባንክ-በትግራይ-በ/?fbclid=IwAR0TMb29k98SRVSkOgvVuF7r6hr13_or7rvFFIz8zMEVAm79shWHULAHg44
በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ዝግ ተደረጉ

በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው እለት በትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደት እየተከናወነ አለመሆኑን አዲስ ስታነንዳርድ አረጋግጣለች፡፡

አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገረቻቸው መምህር በስብሰባ ምክኒያት በዛሬው እለት ትምህርት ቤት ዝግ መደረጋቸውን ገልፀውልናል፡፡

ዝግ የተደረጉት ትምህርት ቤቶች የመንግስት ብቻ ሳይሆኑ የግል ትምህርት ቤቶች ጭምር መሆኑን አዲስ ስታነዳርድ ማረጋገጥ ችላለች፡፡

ትላንት አመሻሽ ላይ ትምህርት ቤቶች በዛሬው እለት ትምህርት አለመኖሩን የሚገልፅ አጭር መልዕክት ለወላጆች የተላከ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ስብሰባ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ትምህርት ዝግ የተደረገበት ምክኒያት የሰራተኞችና የኮሚቴ ስብሰባ ለማድረግ ነው በሚል መሆኑን ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ምንጫችን ገልፀዋል፡፡

ፎቶ- የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
ዜና፡ በመንግስትና በቅዱስ ሲኖደስ መካከል የቃላት ጦርነት ተባብሶ ቀጥሏል፤ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ–ኃይል ሰልፍ እናዳይካሄድ ቢያስጠነቅቅም ሲኖዶሱ ሰላማዊ ሰልፉ ተፈጻሚ እንደሚሆን ገልጧል

በመንግሥትና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እየተባባሰ በሄደበት ወቅት ሁለቱም ተቋማት ትላንት ከስዓት በኋላ የራሳቸውን አቋም የሚያንጸባርቅ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ መንግስት በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የተፈጠረውን አለመግባባት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው "መንግስትን በትጥቅ ሃይል ለመነቅነቅ" እየሰሩ ያሉ እና “ለዚህ አላማ ወጣቶችን የሚመለምሉ” አካላት መኖራቸውን መረጃ ማግኘቱን አስታውቋል።

ቅዱስ ሲኖዶሱ ትላንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ–ኃይል የተፈቀደ ሰልፍ የለም በማለት መግለጫ ቢሰጥም ፣ ሰላማዊ ሰልፉ በሀገራ አቀፍ ደረጃ በተያዘለት መርሃ-ግብር እንደሚከናወን ቅዱስ ሲኖዶሱ አስታውቋል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ አክሎም የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ–ኃይል የተሰጠው የሰልፍ ክልከላ መግለጫ መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን “በጽኑ እንድናምን” አድርጎናል ብሏል፡፡

https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-በመንግስትና-በቅዱስ-ሲኖደስ-መካከ/?fbclid=IwAR0U8at9Bs-HPvrvlY10uUYpCCZvpfmd9uX87Op-MlyKQioczGmBVL8_3zc