Advanced Freshman – Telegram
Advanced Freshman
27.4K subscribers
650 photos
9 videos
59 files
206 links
🔔ይህ ቻናል freshman ለሚማሩ ተማሪዎች የተዘጋጀ እና በዉስጡ የተለያዩ የዩንቨርስቲ መረጃዎችን, አጋዥ መፅሐፍቶች, ቲቶሪያል, mid እና final ፈተናዎችን ሚያዘጋጅ እና ተማሪዎች ወደ ሚፈልጉበት ዲፓርትመንት እንዲገቡ ሚያግዝ ነው ::

📩Owner:- @Bekijum
Download Telegram
🎓ግቢ ውስጥ አዲስ ሊሆኑባቹህ የሚችሉ የግቢ ቃላቶች ውስጥ ጥቂቶቹን እንመልከት!

🍰 ካፌ-  ብዙሃኑ ተማሪ የሚጠቀምበት  የግቢው መመገቢያ ቦታ

🍔 ላውንጅ - ግቢ ውስጥ የሚገኝ ተማሪን ባመከለ መልኩ ክፍያ የሚያስፈልግ ካፌ ነገር ነው  ፤ ምግብና መጠጦቹ(ለስላሳ ፣ ትኩስ ነገር ምናምን) ጥራት ያላቸው እና በዋጋም በጣም ቅናሽ ናቸው።

🧑‍🎓 ችከላ- ጥናት

😭 ቴንሽን- ጭለላ ፣ ውጥረት፣ መረበሽ፣ መጨናነቅ

🥖 11  - ግማሽ እንጀራ በዳቦ ( የካፌ ምግብ ነው በተለይ እራት ላይ)

🍔 Non-cafe - የግቢውን ካፌ የማይጠቀሙ ተማሪዎች

🚀Space - ባዶ ክፍል ብዙውን ጊዜ መማሪያ ክፍሎችን ለንባብ ስንጠቀምባቸው ስፔስ ይባላሉ

🥩Therefore- የካፌ ስጋ  ( ስጋ ሲባል ግን ሰፍ እንዳትሉ ! እንደስሙ ነው ማለት ትንሽ ስጋ ጣል ጣል የተደረገበት ገራሚ መረቅ )


💵Cost -ካፌ ለማይጠቀሙ ተማሪዎች የሚሰጥ ወርሃዊ ክፍያ ፤ የሁሉም ማለት በሚቻል መልኩ ክፍያው ተመሳሳይ ነው።

📤Add and drop - በትምህርት ሂደት ውስጥ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ነገሮች ናቸው ፤ ይሰውራቹህና የሆነ ኮርስ ከፈላ(F) add and drop process ግድ ይሆናል

🪑ድድ ማስጫ- አላፊ አግዳሚውን ለማየት አመቺ የሆነ ቦታ ወይም መቀመጫ 

👮‍♂️ዛፓ - ጥበቃ ሰራተኞች

🎓 GC- ተመራቂ ተማሪዎች

🐒 Fresh፣ጦጣ ምናምን  - አዲስ ገቢ ተማሪዎች ( ግቢ ስትገቡ ፍሬሽ ምናምን እያሉ አዛ የሚያደርጓቹህ ብዙውን ጊዜ ሁለተኛ አመቶች ናቸው ሁሉም ሁለተኛ አመቶች ሳይሆኑ ፍሬሽነታቸውን ያልጨረሱት ወይም ገራሚ ፉገራ የተፎገሩት ናቸው

🍃በርጮሎጂስት- የፍየልን መኖ የሚጋፉ ጫት ቃሚዎች ማለት ነው

🍺ኦቨር- መጠጥ ቤት መሄድና ሰክሮ መምጣት

🫰ሻታ - ይቅርባቹህ እንዳያስመልሳቹህ ብዬ ነው


🧦 ጥፊ- የዶርምን ላይፍ እንዳይረሳ ከሚደርግ ግሩም ጠረኖች ውስጥ አንዱ ነው፤ በተለይ በተለይ ወንዶች ጋር የተለመደ የካልሲ ጭስ ነው ( ወንዶችዬ ተዉ ግን አታሰደቡን? )

🍔 Meal Card- የግቢው ካፌ ውስጥ ለመመገብ በግቢው የሚሰጣችሁ የመመገቢያ ካርድ።


"... የማናውቃቸው ድብቅ ስሞች ካሉ Comment'ቱ ክፍት ነው 😅

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍817😱3🔥2👏2❤‍🔥1🙏1
#MekelleUniversity

ለሁሉም በ2017 ዓ/ም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የኣንደኛ ዓመት (Freshman) ተማሪዎች

ወደ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት የምታደርጉበት ቀን ሕዳር 19 እና 20/2017 ዓ/ም መሆኑን እያሳወቅን፤ ወደ ዩኒቨርሲቲ ከመምጣታችሁ በፊት የመቐለ ዩኒቨርሲt: e-student website www.mu.edu.et ከሕዳር 13/2017ዓ/ም ጀምሮ ለምዝገባ ክፍት ስለሚሆን ባላችሁበት ሆናቹሁ በዌብሳይቱ ገብታችሁ እንድትመዘገቡ እያሳሰብን በምዝገባ ወቅት የሚከተሉት ኣስፈላጊ ዶክመንቶች ስካን በማድረግ እንድትጭኑ (Upload) እንድታድርጉ እናሳውቃለን።

ማሳሰብያ

1. በ2016 ዓ/ም በዩኒቨርስትያችን በረሜድያል ፕሮግራም ስትማሩ የቆያችሁና የማለፍያ ነጥብ ያገኛችሁ እላይ ለኣንደኛ ዓመት ተማሪዎች የተጠቀሰው መሰረት በበየነ መረብ (Online) ተምዝግባችሁ ሕዳር 19 እና 20 2017 ዓ/ም በኣካል ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን።

2. በ2017 ዓ/ም በሪሜዲያል ፕሮግራም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች በቀጣይ ጥሪ ስለምናደርግ እንድትክታተሉ እያሳወቅን፡ በሪሜድያል ፕሮግራም የምድብ ዩኒቨርሲትያችሁ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ያልሆነ ነገር ግን በግላችሁ ከፍላችሁ መማር የምትፈልጉ ምዝገባ ስለጀምርን በዋና ግቢ ሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት በኣካል ቀርባችሁ መመዝገብ እንደምትችሉ እናሳውታለን።

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍34🥰129🙈4🎉1
"ዘንድሮ ፍሬሽማን እና Remedial ምትማሩ ተማሪዎች ስለ እኔ ምን ትላላችሁ🥸"

@Advanced_Freshman
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🤮237🥰116👍39😡34🤨2322👎22🔥14👌138😍5
🎓 ዩንቨርስቲ የገባችሁ Freshman ተማሪዎች ግብያቹን እንዴት አገኛችሁት? Challenge ያረጋቹስ ነገር ምንድነው?

@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍29💔11🙈5🔥4🥰2
ፍሬሽ ማን ላይ የተሻለ ውጤት📈 የሚያመጡ  ተማሪዎች ልዩ የሚያደርጓቸው 13 ወሳኝ  የአጠናን ልምዶች🫴


1️⃣ ጥናት ከመጀመራቸው በፊት ለምን ዓላማ እንደሚያጠኑ ቀድመው ዓላማ ያስቀምጣሉ።ይህ ማለት ምን ለማወቅ እንደሚያጠኑ ቀድመው ያቅዳሉ።በተለይም ደግሞ ፍሬሽ ማን ላይ ውጤት ካለው ጉልህ ሚና አንጻር ምን ቢያጠኑ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ያውቃሉ፡፡ ወደፊት ሊገቡበት የሚጓጉለትን ሙያ በተመለከተ የሚያስፈልጋቸውን እውቀትም ጎን ለጎን  ያካብታሉ፡፡

2️⃣ ሲያጠኑ ያገኙትን አንኳር ነጥብ አጠር አድርገው ማስታወሻቸው ላይ ያሰፍራሉ።በፈተና ወቅትም ሰፊ ጊዜ የሚፈልጉ መጽሀፍትን  በማገላበጥ ጊዜ ከማባከን ይልቅ በቀላሉ ለማስታወስ ያዘጋጇቸውን ማስታዎሻዎች ይጠቀማሉ፡፡

3️⃣ አንብበው ለ መረዳት ያስቸገራቸውን ነጥብ /ሀሳብ/ ሳይሰለቹ  ደጋግመው ያነባሉ....ያለመታከት የተለያዩ መጽሀፍትን ያጣቅሳሉ፡፡

4️⃣ጥናት ከ መጀመራቸው በፊት ማጥናት ስለ ፈለጉት ርእሰ ጉዳይ ከ አስተማሪዎቻቸው ካዳመጡት፤ስለ ርዕሱ ቀድመው ከሚያውቁት ተነስተው ምን ማወቅ እንዳለባቸው  ጥያቄዎች ይፋጥራሉ። መፅፍ ገልጠው ጥናት ከጀመሩ በኋላ ለጥያቄዎቻቸው መልስ ይፈልጋሉ እንጂ ሁሉም ነገር በ ማንበብ ጊዜያቼውን አያጠፉም።በተለይም ደግሞ ፍሬሽ ማን ላይ ካለው የጊዜ ጥበት አንጻር አብዛኞቹ ስኬታማ ተማሪዎች የአለፉ ዓመታት ፈተናዎችን በማሰስ ፈተና የሚያተኩርባቸው እና ውጤት ለመስራት የሚያግዟቸውን ር ዕሶች እና መጽሀፍት ላይ ልዩ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡

5️⃣ ሲያነቡ ያገኙትን አዲስ ሀሳብ ወይም መረጃ ከ አሁን በፊት ከሚያወቁት ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችል መሆኑን እና አለመሆኑን ይመረምራሉ::የተለየ ሀሳብ ሲያጋጥማቸው፤ልዩ ልዩ መጽሀፍትን ለማገላበጥ፤ሲኔር እና መምህሮቻቸውን በድፍረት ጠይቆ ለመረዳት በ እጅጉ ዝግጁዎች ናቸው፡፡


6️⃣ በ አንድ ጊዜ ብዙ ነገር ለ ማጥናት አይሞክሩም፡፡ በ አንድ ጊዜ ብዙ ነገር ለ ማጥናት መሞከር ትርፉ ድካም መሆኑን ተረድተውታል፡፡

ይቀጥላል...☺️

📚JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍656🥰3🙏3
ከሀብት ሁሉ በላጩ ጤና ነውና ፈጣሪ ጤና ይስጠን !

💚💛❤️መልካም ሳምንት💚💛❤️

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🙏246🥰43👍17🤗3😘32🤩1
#BongaUniversity

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ወደ አንደኛ ዓመት (Freshman) ያለፋችሁ እና በ2017 የትምህርት ዘመን ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ ከ9-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍39👏52
#AdigratUniversity

በ2017 የትምህርት ዘመን ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታቹን ተከታትላችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣቹ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 26 እና 27/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

በ2017 ዓ.ም ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ ለተመደባቹ ተማሪዎች ወደፊት ጥሪ ደረጋል ተብሏል፡፡

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍209🥰2
ጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡለትን የቅድመ-ምረቃ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
34👍18👏9🔥6
#UniversityOfKabriDahar

በ2017 ዓ.ም ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የሪሚዳል ፕሮግራም ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 26 እና 27/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዝቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ውጤት ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የቅርብ ጊዜ ስድስት 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ የለሊት አልባሳት

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN ⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍534🔥4🥰3
#ArbaMinchUniversity

በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጥሪ ማስታወቂያ

በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች ቅበላ ረቡዕ ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ምዝገባ ሐሙስና ዓርብ ታህሳስ 3 እና 4 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀመረው ሰኞ ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡

በዚህ መሠረት የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው አባያ ካምፓስ፣

የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A እስከ R የሆናችሁ የማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው ጫሞ ካምፓስ፣

እንዲሁም የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ S እስከ Z የሆናችሁ የማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ ሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች በአካል እየቀረባችሁ በተጠቀሰው ቀን ሪፖርት እንድታደርጉ፣ ምዝገባ እንድትፈጽሙ እና ትምህርት እንድትጀምሩ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-
1ኛ) ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕትና የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ኦርጂናልና የማይመለስ ሁለት ኮፒ እንዲሁም አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ በመያዝ መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

2ኛ) ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡፡

[የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት]

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍81👏104🔥4🙈4🥰3😱3
#AKSUMUNIVERSITY

በ2017 ዓ.ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመማር የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ታህሳስ 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ8ኛ፣ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- የቅርብ ጊዜ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ፣ ብርድ ልብስ፡፡

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍2217👏7😱3
#FakeNews❗️

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2017 አዲስ ለተመደቡ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም።

"በ2017 ዓ.ም ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ህዳር 30 እና ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም እንደሆነ" የሚገልፅ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የሚዘዋወረው መረጃ #ሐሰተኛ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በ2017 ዓ.ም አዲስ የተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜን ወደፊት የሚያሳውቅ መሆኑን የገለፀው ዩኒቨርሲቲው፤ ጥሪ እስከሚደረግ ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል።

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍23💔8🙏32
#ArsiUniversity

አርሲ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

የ12ኛን ክፍል ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ዉጤት በማምጣት ወደ አርሲ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ድግሪ መደበኛ መረሃ ግብር ተማሪዎች የመመዝገቢያ ቀናት ታህሳስ 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን እየገለጽን ስትመጡ ከዚህ በታች የተገለፁትን ማለትም፤

👉 የ8ኛ ክፍል ማትሪክ ዉጤት ኦሪጅናልና ኮፒ፣

👉 19-12 ክፍል ትራንስክሪፕት አሪጅናልና ኮፒ፣

👉 12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት ኦሪጅናልና ኮፒ

👉 3 በ 4 ስድስት (6) ጉርድ ፎቶ

👉 አንሶላ፣ብርድልብስና የትራስ ጨርቅ እና

👉 የእስፖርት ትጥቅ በመያዝ የሶሻል ሣይንስ ተማሪዎች በቦቆጂ ካምፓስ እድትገኙ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ግብርና ኮሌጅ ካምፓስ ሪፖርት እንድታርጉ እያሳወቅን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መሻሻያ ትምህርት (ሪሜዲያል ኮርስ) ለመዉሰድ አርሲ ዪኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ ወደ ፊት የምናሳዉቃችሁ መሆኑን ከወዲሁ እንገልፃለን፡፡

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍26🔥97😱7🥰3💔2🫡2
እንዴት ናችሁ ቤተሰብ🥰

ፍሬሽማንነት እንዴት ይዞአቿል😅የfamily ናፍቆት... የቤት ምግብ😁.......

እና ደሞ ከዚህ በፊት ያልነገርናችሁ ነገር ግቢ ላይ ሚሰጣችሁን ID በጥንቃቄ ያዙ😳 ከጠፋባችሁ በየ ቦታው መንከራተታችሁ ነዉ😐serious አርጉት የምር ብዙ ተማሪዎች በዚህ ጉዳይ ስለሚቸገሩ ጠንቀቅ በሉ🙌


JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍81💔20🥰116🫡5🔥21😱1🙏1