Advanced Freshman – Telegram
Advanced Freshman
27.4K subscribers
650 photos
9 videos
59 files
206 links
🔔ይህ ቻናል freshman ለሚማሩ ተማሪዎች የተዘጋጀ እና በዉስጡ የተለያዩ የዩንቨርስቲ መረጃዎችን, አጋዥ መፅሐፍቶች, ቲቶሪያል, mid እና final ፈተናዎችን ሚያዘጋጅ እና ተማሪዎች ወደ ሚፈልጉበት ዲፓርትመንት እንዲገቡ ሚያግዝ ነው ::

📩Owner:- @Bekijum
Download Telegram
#Remedial_Exam_Result

❗️❗️ብዙ ቻናሎች ላይ እንዲህ የሚሉ መረጃዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ::ነገር ግን ትምህርት ሚኒስቴር ምንም ዓይነት መረጃ እስካሁን አልሰጠም!! ስለሆነም ትክክለኛ መረጃ Officially እስክለቀቅ በተሳሳተ መረጃ አትረበሹ🙏

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
👍27🙏158🤓4
በርካታ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች በሳምንቱ መጨረሻ ያስመርቃሉ።

15 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ቅዳሜ ሰኔ 14/2017 ዓ.ም የሚያከናውኑ ሲሆን፤ የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች እሑድ ሰኔ 15/2017 ዓ.ም ያካሒዳሉ።

🎓 ጅማ ዩኒቨርሲቲ
🎓 አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 አምቦ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ራያ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ወልድያ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 አክሱም ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 መቱ ዩኒቨርሲቲ እና
🎓 የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በሳምንቱ መጨረሻ ተማሪዎቻቸውን ከሚያስመርቁ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ይጠቀሳሉ።

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
👍1312🥰1
ፍሬሽማን ተማሪዎች አመቱን ስንት GPA በማምጣት ወደ 2ኛ አመት አለፋችሁ?
Anonymous Poll
12%
4 😎
16%
Above 3.8 😇
17%
Above 3.5 ☺️
10%
Above 3.3 🥲
11%
Above 3 🥹
11%
Below 3 🤪
23%
I'm Remedial🙂
🔥176💔6👍1
Advanced Freshman
ፍሬሽማን ተማሪዎች አመቱን ስንት GPA በማምጣት ወደ 2ኛ አመት አለፋችሁ?
ሀገራችን ተስፋ አላት🥹🥹
😁72❤‍🔥5💔5🔥3🫡2😍1😎1
Advanced Freshman
ሀገራችን ተስፋ አላት🥹🥹
አረ አረጋጉት guys እንዲው ነው ያልኩት እንጂ GPA መስቀል matter አያረግም!!ያው ዕድል ያሰፋል እንጂ :: ዉጤት ከፍ አለ or ዝቅ አለ ማለት የናንተን ትክክለኛ potential አያሳይም!! ያው ታቁታላችሁ ግቢ ላይ ብዙ fair ያልሆነ ነገር አለ:ጎበዝ ሆናችሁ ዉጤት ሚበላሽበት ጊዜ አለ በተለያዩ ምክንያቶች....::እንደዛው ሁሉ ተኮራርጀው ወይም ፈተና አግኝተው 4 ሚያመጡ አሉ::

Anyways 4 ስላመጣችሁ ብዙም ደስ አይበላችሁ ዉጤት ዝቅ ስላለም አትዘኑ🙌በቻላችሁ አቅም ከትምህርታቹ ጎን ለጎን skill ለመማር ሞክሩ ✌️ አንዳንድ ሃሳቦችን እና ጠቃሚ ነገሮችን በዚህ ክረምት እናወራበታለን😊
🥰6922💯12🙏9👍8🤗1
Class of 2025 Commencement!

በርካታ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች እያስመረቁ ነው።

ከ25 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች በዛሬው ዕለት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ፡፡

ተመራቂዎቹ በተለያዩ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁና የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም የድኅረ-ምረቃ እና የስፔሻሊቲ ፕሮግራም ሰልጣኞች ናቸው፡፡

እንኳን ደስ አላችሁ!

ምስል፦ ጅማ፣ ባህርዳር፣ ደምቢ ዶሎ እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
👏97🙏1🤗1
ሰላም ቤተሰብ👋🏻በዚህ ክረምት ምን ለማድረግ ወይም በምን ለማሳለፍ አስባቿል ? እስቲ ሃሳባችሁን commment ላይ አስቀምጡ ✍️ እኛም ጠቃሚ ነው ምንላቸዉን እና የተለያዩ ሃሳቦችን እንነግራቿለን😊
15🥰4
"ጀግናው 💪

የዛሬው ምስል ነው!

ጀግናው ልጇ ለትምህርቱ ከሰል ሸጣ ለለፋችለት እናቱ ያሳየው ክብርና ምስጋና ድንቅ ነው።

ይሄ ነው እውነተኛ ፍቅር! በክሰል ሽያጭ ልጇን አስተምራ ለዚህ ያበቃች እናት፣ በምርቃቱ ቀን ደግሞ ከሰል በመሸከም የእናቱን ውለታ በአደባባይ ያመሰገነ ምርጥ ልጅ!

እንኳን ደስ አላችሁ!
እናትህን እንዲህ በክብር እንድታኖር ያደረገህ
ፈጣሪ ይመስገን!

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
🥰17229👏21🏆17🔥8❤‍🔥3👍3
ከዚህ በታች ያለው ግለሰብ ከሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ቦኃላ በከፍተኛ ዉጤት ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል😊🙈እየገባችሁ አበረታቱት☺️

የተማሪው/ዋ Username👉 Student X

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
145😁81🍾7👍6🤝6💯5😎43🔥3😱2🥰1
ዉድ የAdvanced Freshman ቤተሰቦች ደህና ናችሁ አ😊😃እስቲ ዛሬ የሆነ ሃሳብ ላካፍላቹ 👐

✳️ ያው እንደሚታወቀው ከዚህ ቦኃላ ቢያንስ 3ወር የእረፍት ጊዜ ይኖራቿል::ፍሬሽማን የነበራችሁ 2nd year ተማሪ Remedial የነበራችሁ እና ኢንትራንስ ያለፋችሁ ደግሞ ፍሬሽማን ምትገቡ ሲሆን እስካሁን ካለፋችሁበት የሕይወት መንገድ ለየት እና ከበድ እያለ ሚመጣበት ነው::

💥Next ዲፓርትመንት ምትገቡ እና Remedial የነበራችሁ ተማሪዎች life እንደ ፍሬሽማን ላይሆን ይችላል::ፍሬሽማን እያላችሁ more focus ምታደርጉት የነበረው ትምህርታቹ ብቻ ላይ ነበር እንደገና ደግሞ ቤተሰብም ፍሬሽ እንደመሆናችሁ መጠን እንክብካቤው ነበር ማለትም በላክ ጠጣክ ምን ጎደለ ብር ልላክልክ ምናምን ትባሉ ነበር😋 ያልተባላችሁ ካላችሁም Nop😁.... ነገር ግን ዲፓርትመንት ከገባችሁ ቦኃላ እንደ ፍሬሽማኑ ይንከባከቡኛል ብላችሁ እንዳታስቡ 🤨በየቀኑ ይደዉሉ የነበሩት ሁላ በወር ምናምን ወይም ላያስታዉሷቹ ወላ ይችላሉ😸.... በአጭሩ ግን ምን ልላችሁ ፈልጌ መሰላችሁ ለ1 ዓመት የግቢ life ምን እንደሚመስል በደምብ አይታቿላ🙌 እናም በዚህ በእረፍት ጊዜያችሁ ለቀጣዩ ዓመት ብሎም ከግቢ ስቶጡ ሚጠቅማችሁን ነገር አድርጉ :: ለምሳሌ ግቢ ላይ ትልቁ ችግር መላ(ብር) ነው::ምንም ያህል family ሃብታም ቢሆኑ ግቢ ላይ እስካለክ/ሽ ድረስ ገንዘብ ምታጣበት ጊዜ አለ:: ኪስክ ባዶ ሲሆን ደግሞ ሚሰማክ ስሜት damn😑...ብቻ በዚች 3 ወር ስራ ስሩ, skill ተማሩ ብር save አርጉ :: ስራ ሲባል online ላይ ሞልቷል ::ግን እኔ more ምመክራችሁ የሆነ skill ሊኖራችሁ ይገባል ::ለምሳሌ Graphics, Designing, Video editing, Photography,Forex/Crypto Trading,Freelancing, content Writing, social media managing,Digital Marketing.... ብቻ ብዙ አሉ.. እና ከነዚህ ዉስጥ የራሳችሁን ፍላጎት አይታችሁ ቅጥቅጥ አርጋችሁ ብትማሩ የምር ሳላጋንን ግቢ ከምትማሩት ዲፓርትመንት በላይ ስኬታማ ልቶኑባቸው ትችላላችሁ🤌በሂደት ደግሞ የተወሰኑትን detail suggest አረጋቿለው✌️እንዲሁም ገንዘብ ልሰሩባቸው የምትችሉበትን አንዳንድ ስራዎችን ጠቁማቿለው👋🏻፡፡

🙌እናም እነዚህን skill ብትማሩ እና ቀልጠፍ ካላችሁ የምን ከካፌ ምግብ ጋር መዳረቅ😏ምንም ሳትቸገሩ ቤተሰብንም ገንዘብ ሳታስልኩ ራሳችሁን ችላችሁ መማር ትችላላችሁ::እስቲ አስቡት የምር ቤተሰቦቻችን ምን ያህል ታታሪ እንደሆኑ ለዛዉም በዚህ ኑሮ:: ከKG ጀምረው አስተማሯቹ(ግማሹ የግል እየከፈለ), ግቢ ገብታቹም ብር እየላኩላችሁ ሌላም ብዙ ነገር...እና እንዲህ ሚለፉባችሁ እኮ ዝምብለው አይደለም ራሳችሁን ችላችሁ እናንተ በተራችሁ እንድትጦሯቸው እና ትልቅ ቦታ እንድትደርሱላቸው በናንተ በመተማመን ነው🧔👱::ስለዚህ አሁን የናንተ ተራ እየደረሰ ነው ከቤተሰብ ሸክም ወረድ ብላችሁ መጀመርያ ራሳችሁን ቻሉ then በሂደት ለቤተሰቦቻቹ እና ለሌሎችም ትተርፋላችሁ☺️

💥ስለዚህ ለተወሰኑ ቀናት አስቡበት እና ወደ ተግባር ለመግባት ሞክሩ ምንም ቀጠሮ አትያዙ ጊዜው ከሆነ እንዴት እንደሚሮጥ አይታቿል🤯ስለሆነም ስላለፈው ዉጤት or ሌላም አይምሯችሁን ሚሰርቅ ነገር ማሰብ ትታቹ ራሳችሁ ላይ Focus አርጉ::ሕይወታችሁ ላይ ምትወስኑት እናንተው እራሳችሁ ናችሁ::ስለዚህ ይሄን ክረምት እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ክረምቶች እንዳታሳልፉ😤 ከናንተ ሚጠበቀዉ ማድረግ አለባችሁ!!ፈጣሪም ደሞ ጥሎ አይጥላችሁም🙏

💬ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ comment ላይ ፃፉልን✍️እኛም በምን ዓይነት መንገድ እንድንረዳችሁ እንደምትፈልጉ ::አስፈላጊ ከሆነ ለየት ያለ ከAcademic ትምህርት ዉጪ ለሆኑ ነገሮች ምንወያይበትን group ነገር ከፍተን እንተጋገዛለን🤙

ይቀጥላል.... ግን በሃሳቤ ደስተኛ የሆናችሁ እስቲ ❤️ 👍

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
❤‍🔥13191🫡21👍18🙏85😘5🔥4
#Remedial_Result

🎯የ2017 ሪሜዲያል ውጤት ባለፋት ሁለት አመታት ተማሪዎች በተፈተኑ ሁለት ሳምንት ሳይሞላ ይለቀቅ ነበር ሆኖም በ2017 ዓ.ም ሁለት ሳምንት አልፎ ስለ ውጤት ከ ትምህርት ሚኒስትር ምንም የተባለ ነገር የለም ። በመሆኑም እራሳችሁን አረጋግታችሁ እስከ ሚለቀቅበት ቀን ድረስ ተረጋግታችሁ እንድትጠብቁ ።

በርግጥ አምና Announce ሳያደርጉ ብዙ ተማሪዎች ዉጤታቸዉን ካዩ ቦኃላ ነው officially የተነገረው::ስለሆነም ምናልባትም ከተለቀቀ ቶሎ announce ላያደርጉ ስለሚችሉ እየቆያቹ ገባ ብላችሁ check ማድረግ ትችላላችሁ::

አምና ዉጤት ሲታይበት የነበረው በዚህ link ነው👇👇

https://result.ethernet.edu.et

አዲስ መረጃ ካለ ቶሎ እናሳውቃችኋለን 🙏

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
39👍10🙏6👏5
Dilla University የሚማሩ አንዳንድ ተማሪዎች ዉጤታቸውን እያዩ ይገኛሉ::ነገር ግን የሌሎች ዩንቨርስቲዎች እስካሁን ምንም አያሳይም::ምናልባትም የሁሉም ግቢዎች ሲለቀቅ አንድ ላይ officially ሊገለፅ ተፈልጎ ይሆናል ::የሰራላቸው ተማሪዎች ዉጤት እንደ ከዚህ ቀደሙ 30%(university ) እና 70%(MoE) መሆኑን ለማየት ችለናል:: በየ ዓመቱ እንዲህ ዓይነት ነገር ስለሚያጋጥም ተረጋግታችሁ በሰራላችሁ ሰዓት ማየት ትችላላቹ ::

Link👇
https://result.ethernet.edu.et

አዲስ መረጃ ካለ ቶሎ እናሳውቃችኋለን 🙏

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
60🙏21👍8
ጠዋታችሁን በፈገግታ ጀምሩት 😇

ጥዋት ላይ የምናደርጋቸው ትናንሽ ልምዶቻችንና ተግባሮቻችን ቀናችንን እንደሚቆጣጠሩት

ሰምታችኋል ብዬ አስባለው።
►ስለዚህ ቀናችሁን ማስዋብ በእናንተው እጅ ነው ያለው ማለት ነው። እናም ቀናችሁን ውብ አድርጉት።😍
መልካም ቀን ይሁንላችሁ።

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
58🥰11🤗5🔥4😁1
ከRemedial Result ጋር በተያያዘ 🤚

ለምን የተወሰኑ ተማሪዎች(Dilla University students ) ያለ Official announcement ዉጤታቸዉን ማየት ቻሉ

የእኔ ምክንያታዊ ግምት

🗯 Result Officially Announce ከመደረጉ በፊት በትክክል መሥራቱን Test ይደረጋል። ታዲያ ይሄ የ Testing process መካሄድ የነበረበት በ Private Testing Mechanism እንጂ በዩንቨርስቲዎች portal አልነበረም። Dilla ግን ዋናውን የማሰራጫ መንገድ ለሙከራ ተጠቅሞታል።

እና ደግሞ ዝምብለው ከመሬት ተነስተው የተማሪዎችን ዉጤት portal ላይ ያስገባሉ የሚል እምነት የለንም ስለዚህ ምናልባትም የተቀየረ ነገር ሊኖር ስለሚችል እራሳቸው officially እስኪያረጉ መጠበቅ መልካም ነው::

🗯 ከዚህ ቀደም ትምህርት ሚኒስቴር ዉጤት ሙሉ በሙሉ (100%) ከMoE መሆኑን አሳዉቀው ነበር ::ነገር ግን ትላንት dilla university የሚማሩ ተማሪዎች ዉጤታቸው 30% 70% ተደርጎ ሲሆን ይህ ለብዙ ተማሪዎች ብዥታ እየፈጠረ ይገኛል::ያው የሀገራችንን ነገር ታዉቁት የለህ ሁሉ ነገር አልጋ በአልጋ አይደለም ትንሽ ማወሳሰብም ነገር ስላለ እናንተ በትግዕስት ጠብቁ ::

ተጨማሪ መረጃ ካለ በፍጥነት ምናደርሳችሁ ይሆናል🙏

#Personal_view👤

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
🙏4942🫡8👍4👏4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጋዜጠኛ ብርሽ

ብሬ ከባድ final exam ሳይገጥመው አይቀርም🤠

ጋዜጠኛው ግን 👌

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
👏180😁2616👌9🔥8😎7🫡5🥰32