BeWide Technologies – Telegram
BeWide Technologies
292 subscribers
78 photos
18 links
Pioneering AI-powered software development, IT solutions, and branding for transformative growth. From intelligent web design and custom systems to dynamic mobile apps

Elevate your digital presence with us

Be wide—Be wise

Contact us through @BeWideTech
Download Telegram
BeWide Technologies
Photo
ቢዋይድ ቴክኖሎጂ ከሀሩን ሚዲያ እና መወዳ ትምህርት ቤት  ጋር በመተባበር ለ6 ሳምንታት በዌብና አፕ ዲቨሎፕመንት እንዲሁም ኢስላማዊ የማንነት እነጻ ሲያስተምራቸው የቆዩ ተማሪዎችን በትላንታ ዕለት በቢላሉል ሀበሺ አዳራሽ አስመርቋል።

ተመራቂ ተማሪዎቹ በዌብና አፕ ዲቨሎፕመንት (Web and App Development) ፣ ኢስላማዊ ማንነት( Understanding Islam and Islamic History)፣  ልምድ ማጋራት (Mentorship)፣ ማንነት እነፃ (Personal Development) ላይ ያተኮረ ልዩ የክረምት ስልጠና በአዲስ አበባ ካራ ቆሬ በሚገኘው መወዳ ትምህርት ቤት ውስጥ ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ሲሆን በዛሬው ዕለት የመወዳ ት/ቤት አመራሮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተመራቂ ተማሪ ቤተሰቦችና ተማሪዎች በተገኙበት ተመርቀዋል።

ተመራቂ ተማሪዎች በክረምቱ ኮርስ ከወሰዱባቸው የዌብሳይት እና አፕሊኬሽን ማበልፀግ የተግባር ስራ በማከናወን ለታዳሚው አቅርበዋል። በዝግጅቱ ማጠቃለያ የክረምት ስልጠና ለወሰዱ ተማሪዎች ሰርቲፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

ቢዋይድ ቴክኖሎጂ መሠል ፕሮግራሞችን የሚቀጥል መሆኑን ፣ ለቴክኖሎጂ እድገትና ለማህበረሰብ ግንባታ ከባለ ድርሻ  አካላት ጋር የበኩሉን ድርሻ ይበልጥ እንደሚወጣ ለማሳወቅ ይወዳል። 

BeWide Technologies
#bewide_bewise

@BeWide_Tech
7
Wishing you a beautiful day

Bewide Technologies
Be Wide - Be Wise
For more info check out our website today.
https://bewidetech.com/
@BeWide_Tech
5👍1
Innovation is the outcome of a habit not a random act.


Bewide Technologies
Be Wide - Be Wise
For more info check out our website today.
https://bewidetech.com/
@BeWide_Tech
4👍1
We're looking for a highly motivated and passionate Application Development Intern to join our dynamic team. This is a hands-on opportunity for an aspiring developer to move beyond theory and gain practical experience in building and maintaining mobile applications.

Apply here

Application deadline: Nov 03, 2025
3👍1
We're looking for a highly motivated and passionate Telegram Bot & UI/UX Design Interns to join our dynamic team. This is a hands-on opportunity for an aspiring developer and designer to move beyond theory and gain practical experience in building engaging Telegram conversational applications and designing intuitive user experiences. 

Apply here

Application deadline: Nov 20, 2025
🔥3
BeWide Technologies
Photo
የኡምራ ጉዞን በተሻለ መልኩ ለማከናወን የሚረዳ "ኡምራ ጎ" የተሰኘ ፕላትፎርም ይፋ ሆነ!

- ሀሩን ሚዲያ፥ ሕዳር 20/2018

በቢ ዋይድ ቴክኖሎጂስ ያዘጋጀው የኡምራ ጉዞን በተሻለ መልኩ ለማከናወን የሚረዳ "ኡምራ ጎ" የተሰኘ ፕላት ፎርም በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ኢንተር ሌግዤሪ ሆቴል ይፋ ሆኗል።

በፕላትርሙ ላይ በሀገራችን ከኡምራ ጋር የተያያዙ ስራዎችን የሚሰሩ ኤጀንሲዎች አጠቃላይ የሚሰጡትን አገልግሎት በግልጽ እንደሚይዝ እና የእያንዳንዱን ኤጀንሲ አጠቃላይ አገልግሎት ይገልፃሉ ተብሏል።

በተጨማሪም በፕላትሮርሙ ላይ ቁርአን ከእነ ተፍሲሩ መቅራት ያስችላል የተባለ ሲሆን፤ የሰላት ሰአት የሚጠቁም፣ የቁርአን ቲላዋ ማድመጥ የሚያስችል፣ ማስታወሻ መያዝ የሚያስችል፣ የካላንደር መቁጠሪያ ጨምሮ ሌሎችም አገልግሎቶች የተካተቱበት መሆኑን የቢ ዋይድ ቴክኖሎጂ ዋና ስራ አስፈፃሚ መኪን ሙሀመድ ገልጿል።

በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው በዚሁ መርኅ ግብር ታላላቅ ኡለማኦች፣ የተለያዩ ኤጀንሲ ባለቤቶች የሚዲያ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመርኀ ግብሩ ላይ የተገኙት ሸይኽ ሙሀመድ ሐሚዲን (ዶ/ር) ኡምራ እስልምና ውስጥ ካሉ ኢባዳዎች ከዋናዎቹ ነው። ይህንን ትልቅ ኢባዳ በተቀላጠፈ መንገድ ለማከናወን የሚረዳ ቴክኖሎጂ ጅማሬው በራሱ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

"ኡምራ ጎ" የተሰኘው ፕላትፎርም በአማርኛ፣አፋን ኦሮሞ፣በአፍ ሶማሌ እንግሊዝኛ እና አረብኛ በአጠቃላይ በአምስት ቋንቋቸው አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከጥቂት ቀናት በኋላ በፕሌይ ስቶር እና አፕ ስቶር ላይ ማግኘት ይቻላል የተባለ ሲሆን አሁን ላይ "ኡምራ ጎ ዶት ኢት" ላይ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።

© ሀሩን ሚዲያ

@BeWide_Tech
🔥8👍21