ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 14/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ የኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት መቀበላቸውን ገልጸዋል።
ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊ እና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል።
በውይይቱ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ መለዋወጣቸውን አመልክተዋል።
ይኽም በሰላም እና መረጋጋት፣ ብሎም በአፍሪካ መር መፍትሔዎች ላይ ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያሳይ ነበር ሲሉ ገልጸዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

👍3
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር በመሆን በሳይንስ ሙዚየም እና በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ያደረጉት ጉብኝት (በምስል)
❤1👍1