የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ቻይናን ከአውሮፓ ጋር በማገናኘት ዕውቅና አገኘ
***
የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በቻይና እና አውሮፓ መካከል በሚደረገው የሎጂስቲክስ ግንኙነት ግንባታ ቁልፍ የሎጂስቲክስ አጋር በመባል ሽልማትን አገኘ።
አየር መንገዱ የቤልጂየም መንግሥት ከቻይና ሎጅስቲክስ ማኅበር ጋር በመሆን በቻይና ጓንዡ ባዘጋጀው ሥነ-ስርዓት ላይ ሽልማቱን ተቀብሏል።
አየር መንገዱ ዕውቅናውን ያገኘው፤ የተለያዩ ዕቃዎችን ከቻይና ወደ አውሮፓ በቤልጂየም በኩል በማጓጓዝ እንደ አገናኝ ድልድይ ሆኖ እየሰጠ ላለው ጠንካራ የካርጎ አገልግሎት ነው ተብሏል፡፡
በላሉ ኢታላ ነው

ለሰላም ሲባል ዩክሬን የኔቶ አባልነት ጥያቄዋን ትተዋለች፡- ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ
***
በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ለዓመታት የዘለቀውን ጦርነት ለማስቆም "ለሰላም ሲባል ዩክሬን የኔቶ አባልነት ጥያቄዋን ትተዋለች" ሲሉ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ አስታወቁ፡፡
ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ በአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ከተመራው ልዑክ እና ከአውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በጀርመኗ ከተማ በርሊን እየመከሩ ነው፡፡
ውይይቱ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን ለማስቆም ያለመ ሲሆን ይህን ለማድረግ ያስችላል ተብሎ በተዘጋጀው የሰላም ስምምነት ላይ ያተኮረ ነው፡፡
በፕሬዚዳንቷ ተወክላ ውይይት እያደረገች ያለችው ዩክሬን ለዘላቂ ሰላም መስፈን ቁርጠኛ መሆኗን አስታውቃለች፡፡
በዚህም ለጦርነቱ መባባስ አንዱ ምክንያት የነበረው የኔቶ አባልነት ጥያቄዋን በጊዜያዊነት መሰረዟን አስታውቃለች፡፡
በምላሹም ደህንነቷ እና ስምምነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ማድረግ ላይ ሀገራቱ ከጎኗ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርባለች፡፡
በተጨማሪም ከይዞታ ጋር የተያያዙ አለመስማማቶች ላይ ንግግሩ እንደሚካሄድ ነው የተጠቆመው፡፡
በአሜሪካ አስተባባሪነት እና በአውሮፓ ሀገራት ተሳትፎ የተዘጋጀው የሰላም ስምምነቱ ተኩስ አቁምን የመጀመሪያው ርምጃ በማድረግ የይዞታ ጥያቄዎችን፣ የደህንነት ዋስትና እንዲሁም የተጣሉ ማዕቀቦችን የሚዳስስ መሆኑን የሮይተርስ ዘገባ አስነብቧል፡፡
ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ከሩሲያ የተነሳ ሃሳብ ባይኖርም፣ በአውሮፓ ሀገራት በሚቃኝ ድርድር ላይ ሩሲያ የመገኘት ፍላጎት እንደሌላት ማስታወቋ የሚታወስ ነው፡፡
በአፎሚያ ክበበው

❤1
የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ያበለፀጋቸውን አዳዲስ ዲጂታል ፕላትፎርሞች ይፋ አደረገ
***
የአዲስ አበባ ከተማ ቱሪዝም ኮሚሽን ያዘጋጀው 1ኛው የቱሪዝም ፎረም እየተካሄደ ነው።
ፎረሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር በይፋ ሲከፍቱ፤ መዲናዋ የዓለም የቱሪዝም መናገሻና መዳረሻ ትሆን ዘንድ የመደመር መንግሥት በቀጣይም በስፋት ሥራዎችን እንደሚያከናውን አመላክተዋል።
የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሁንዴ ከበደ፤ ኮሚሽኑ ከተቋቋመ ጥቂት ጊዜ ቢሆነውም ስብሰባዎችን እና ኮንፈረንሶችን መሠረት ካደረገውን የማይስ (MICE) ቱሪዝም በተጨማሪ የ10 ዓመት ፍኖተ ካርታ ቀርጾ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
አክለውም ኮሚሽኑ የቱሪዝም ዘርፉን ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችሉ የተለያዩ ዲጂታል ፕላትፎርሞችን ከዛሬ ጀምሮ ሥራ ማስጀመሩን ገልጸዋል።
በመርሀ-ግብሩ ላይ የቱሪዝም ንግድ አውደ ርዕይ እና የፎቶ ኤግዚቢሽን የቀረቡ ሲሆን፤ ኮሚሽኑ ከተማዋን ለማስተዋወቅ ያበለፀጋቸው ዲጂታል ፕላትፎርሞችም ይፋ ተደርገዋል።
ይፋ ከተደረጉትም ዲጂታል ፕላትፎርሞች መካከል 'ቪዝት አዲስ አበባ' የተሰኘው ፕላትፎርም በመዲናዋ የሚገኙ መዳረሻ ቦታዎችን ለጎብኚዎች የሚጠቁም እንዲሁም ሆቴል ያረፉ እንግዶችን ይበልጥ ለማገልገል የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።
ፕላትፎርሞቹ በከተማዋ የተሰሩ መሰረተ ልማቶችንና መዳረሻዎችን ለማስተዋወቅ እና የስፖርት ቱሪዝምን ለማጎልበት የሚያግዙ መሆናቸውንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።
በአዲስ አበባ አራዳ ፓርክ እየተካሄደ የሚገኘው ፎረሙ ነገ እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።
በሜሮን ምትኩ

❤2
የሁሉም የስፖርት ውርርድ ድርጅቶች ፈቃድ ተሰረዘ
******
በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሲሰሩ የቆዩ የሁሉም የስፖርት ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ ከዛሬ ጀምሮ መሰረዙን አስታወቀ፡፡
የፈቃድ ስረዛው በውርርድ እና በፋይናንስ ዘርፉ ላይ በተካሄደ ሀገር አቀፍ ጥልቅ ግምገማ ላይ ተመስርቶ የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር የተወሰደ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ውሳኔው በሥራ ላይ ባሉትና ቀደም ሲል በይፋ በታገዱት በሁሉም የውርርድ ድርጅቶች በእኩልነት ተፈጻሚ የሚሆን ነው፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሂደት ላይ ያለው ምርመራ በዘርፉ ውስጥ የተንሰራፋ ሕገ ወጥ አሰራር፣ የፈቃድ ውል ጥሰት እና ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት የሚሆኑ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውሮች እንዳሉ በግልጽ አመላክቷል።
አገልግሎቱ ለሚመለከታቸው አካላት መመሪያ አስተለልፏል፡፡ በዚህም መሰረት፡-
1. ለስፖርት ውርርድ ድርጅቶች እና ሲስተም ኦፕሬተሮች/አቅራቢዎች
ከታሕሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአካል፣ በዲጂታል ወይም በሌላ መንገድ የሚካሄድ ማንኛውንም የውርርድ ሥራ ወዲያውኑ ማቋረጥ ይጠበቅባቸዋል። ሁሉም የሰርቨር መረጃዎችን፣ የፋይናንስ መዝገቦችን እና የተጠቃሚ መረጃዎችን በጥብቅ ጠብቀው የማቆየት ግዴታ አለባቸው።
2. ለፋይናንስ ተቋማት (ባንኮች፣ ፔይመንት ኢንስቱርመንት ኢሹወርስ እና ፔይመንት ሲስተም ኦፕሬተሮች)
ከታሕሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ፣ የሁሉም የውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ በመሰረዙ፣ በተቋማቱ በኩል የውርርድ ድርጅቶቹ የሽያጭ እንቅስቃሴ እንዳያከናውኑ እንዲያደርጉ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ይህን ውሳኔ ከሁሉም የመንግሥት ተቋማት ጋር በመተባበር በጥብቅ የሚከታተል መሆኑን አስታውቆ፣ መመሪያውን የሚጥስ ማንኛውም አካል በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆን ገልጿል።

በዚህ ዓመት የዋጋ ንረትን ወደ ነጠላ አሀዝ ለማውረድ እየተሰራ ነው - እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)
****
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ማዕከላዊ ባንኩ እያከናወናቸው ያሉ የሪፎርም ስራዎች፣ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ማሻሻያ እና አጠቃላይ የባንኩ ዘርፍ ያለበትን ቁመና በተመለከተ ከኢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ዋጋን ማረጋጋት ከብሔራዊ ባንክ ቁልፍ ተግባራት አንዱ መሆኑን የገለፁት እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)፤ ባንኩ የተገበረው ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ ከ30 በመቶ በላይ ደርሶ የነበረውን የዋጋ ንረት በከፍተኛ መጠን ማውረድ መቻሉን ተናግረዋል።
በ2018 ህዳር ወር አጠቃላይ የዋጋ ንረት 10.9 በመቶ መውረዱንም ነው ያነሱት።
የዋጋ ንረትን በዚህ አመት ወደ ነጠላ አሀዝ ለማውረድ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካትም ባንኩ የሚተገብረውን ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
ብሔራዊ ባንክ የወለድ ምጣኔን በማስቀመጥ ኢኮኖሚው ውስጥ ያለው ገንዘብ በዚህ የሚመራበትን አዲስ አሰራር በሪፎርሙ ተግባራዊ ማድረጉንም አንስተዋል።
በካፒታል ገበያ ስርዓት በባንኮች መካከል የገንዘብ ግብይት ከተጀመረ ወዲህ 1.1 ትሪሊዮን ብር ከገበያ ውስጥ መሰብሰብ መቻሉንም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሌሎች ሀገራት አቻ ተቋማት ጋር ተወዳዳሪ የሚያደርጉትን አዳዲስ አሰራሮችን በሪፎርሙ ተግባራዊ ስለማድረጉም ነው የገለፁት።
በቀጣይም ብሔራዊ ባንክ ቁልፍ ተግባሩ የሆነውን ዋጋ ማረጋጋት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
በጌታቸው ባልቻ

❤3
ድህነትን ፣ ተረጂነትን እና ኑሮ ውድነትን ለመቀነስ…..
ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እቅሟን ሊያሳድጉ የሚችሉ ሰፊ የተፈጥሮ ሀብትና የልማት ጸጋዎች ቢኖሯትም ያላደገ የስራ ባህል ስር ለሰደደ ድህነት እና ተረጂነት ዳርጓት ቆይቷል፡፡ በተፈጥሮ ሀብት፣ በሰው ኃይል፣ በታሪክ፣ በቱሪዝምና ማዕድናት ባለፀጋ ለሆነች ሀገር ተረጂነት ያለመስራት ውጤት ነው፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በኢትዮጵያ የመስኖ ልማት የሰው ልጆችን አሁናዊ የምግብና የኢንዱስትሪ ግብዓት ፍላጎት ከ40 እስከ 50 በመቶ ድረስ የሚሸፍን መሆኑን ጥናቶች ያመለክታሉ። በኢትዮጵያም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመስኖ ስንዴ ልማት የአንበሳውን ድርሻ እየወሰደ ሲሆን በምግብ ሰብል ራስን ለመቻል በሚደረገው ጉዞም የጎላ ሥፍራ አለው።
ኢትዮጵያም ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የምታደርገው ጉዞ ቀጥሏል፡፡ ሀገሪቱ ያላትን የገፀ ምድር እና የከርሰ ምድር ውሃን በመጠቀም የምርት እና ምርታማነት አቅምን ለማሳደግ እየሰራች ትገኛለች፡፡ በበጋ እና በመስኖ ልማት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችም ድህነትን ፣ ተረጂነትን እና ኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ይገኛል፡፡

👍3❤1
የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ግልጽነት እና ተጠያቂነት ያለው ስርዓት እንዲሆን ተደርጓል፡፡
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ከዚህ ቀደም የነበረው የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር እንደነበረበት ጠቁመው አዲስ የተሻሻለው አሰራር ግልጽነት እና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን ተደርጓል ብለዋል፡፡
በዜጎች ላይ ይደርስ የነበረውን እንግልት ለማስቀረት የህግ ማእቀፍ እና ደንብ በማዘጋጀት ዜጎች ያለምንም ችግር በህጋዊ መንገድ በውጭ ሀገራት መስራት እንዲችሉ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት እንደተፈረመ አስታውሰዋል፡፡
ከተለያዩ ሀገራት ጋር የተደረጉት ስምምነቶች የዜጎችን ጥቅምና መብት ያስጠበቁ እንዲሆኑ ከተደረገ በኋላ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በተለያዩ ሀገራት ለሥራ መጓዛቸውን ጠቁመዋል፡፡
ስራ ላይ የዋለው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ቴክኖሎጂም ዜጎች ምን ዓይነት ሙያ እና ክህሎት እንዳላቸው እና የት እንደሚገኙ በቀላሉ መለየት የሚያስችል ስርዓት እንደሆነ አብራርተዋል፡፡
በሚኒስቴሩ የውጭ ሀገር ሰራተኛ ስምሪት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኤርምያስ ተክሉ በአሁኑ ወቅት በዓመቱ ከ 500 ሺህ በላይ ዜጎች በህጋዊ መንገድ የውጭ ሀገራት የሥራ ዕድል እየተፈጠረላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

❤2👍1
በተያዘው አመት 100 የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎት ማእከላት በመላው ሀገሪቱ ለማቋቋም እየተሰራ ነው፡፡
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመንግስት ተቋማት ላይ በተደጋጋሚ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት በፌደራል፣ በሁለቱ የከተማ አስተዳሮች እና በክልሎች የተቋቋመ ሀገር በቀል የድጂታል አገልግሎት ሞዴል ነው፡፡
የፌደራል ሞሰብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ዳሬክተር አቶ አንተነህ ማሞ እንዳሉት ማዕከሉ አገልግሎት ስራ በጀመረ በ8 ወራት ውስጥ ከ95 ሺህ በላይ ደንበኞችን ተስተናግደዋል፡፡ የደንበኞች እርካታም 96.01 በመቶ መድረሱን ከተጠቃሚዎች በተሰባሰበ ግብረ-መልስ መረጋገጡን ገልጸዋል፡፡
ባለፉት 6 ወራት በተለያዩ ክልሎች 21 ቅርንጫፎች መከፈታቸውን የተናገሩት ዳይሬክተሩ በተያዘው አመት በመላው ሀገሪቱ 100 የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎት ማእከላት ለማቋቋም ስራ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሪፖርተር በፌደራል መሶብ የአንድ ማዕከል ተገኝታ ያነጋገረቻቸው ተገልጋዮች በማዕከሉ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እያገኙ መሆናቸው ተናግረዋል፡፡
በማእከሉ የሚሰጡ ሁሉም አገልግሎቶች በአንድ መስኮት ብቻ የሚጠናቀቁ በመሆናቸው ጉልበታቸውን ፣ ጊዜያቸውን እና ገንዘባቸውን እንደቆጠበላቸው ነው የተናገሩት።
የፌደራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከ8 ወራት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተመርቆ ስራ የጀመረ ሲሆን 23 ተቋማትን በመያዝ ፣ 187 የአገልግሎት አይነቶችን እየሰጠ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡

👍5❤1