FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1) – Telegram
FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)
8.5K subscribers
1.3K photos
37 videos
3 files
172 links
ይህ ትክክለኛ የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የቴሌግራም ቻናል ነው
Download Telegram
የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ግልጽነት እና ተጠያቂነት ያለው ስርዓት እንዲሆን ተደርጓል፡፡

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ከዚህ ቀደም የነበረው የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር እንደነበረበት ጠቁመው አዲስ የተሻሻለው አሰራር ግልጽነት እና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን ተደርጓል ብለዋል፡፡

በዜጎች ላይ ይደርስ የነበረውን እንግልት ለማስቀረት የህግ ማእቀፍ እና ደንብ በማዘጋጀት ዜጎች ያለምንም ችግር በህጋዊ መንገድ በውጭ ሀገራት መስራት እንዲችሉ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት እንደተፈረመ አስታውሰዋል፡፡

ከተለያዩ ሀገራት ጋር የተደረጉት ስምምነቶች የዜጎችን ጥቅምና መብት ያስጠበቁ እንዲሆኑ ከተደረገ በኋላ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በተለያዩ ሀገራት ለሥራ መጓዛቸውን ጠቁመዋል፡፡

ስራ ላይ የዋለው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ቴክኖሎጂም ዜጎች ምን ዓይነት ሙያ እና ክህሎት እንዳላቸው እና የት እንደሚገኙ በቀላሉ መለየት የሚያስችል ስርዓት እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

በሚኒስቴሩ የውጭ ሀገር ሰራተኛ ስምሪት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኤርምያስ ተክሉ በአሁኑ ወቅት በዓመቱ ከ 500 ሺህ በላይ ዜጎች በህጋዊ መንገድ የውጭ ሀገራት የሥራ ዕድል እየተፈጠረላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
2👍1
በተያዘው አመት 100 የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎት ማእከላት በመላው ሀገሪቱ ለማቋቋም እየተሰራ ነው፡፡

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመንግስት ተቋማት ላይ በተደጋጋሚ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት በፌደራል፣ በሁለቱ የከተማ አስተዳሮች እና በክልሎች የተቋቋመ ሀገር በቀል የድጂታል አገልግሎት ሞዴል ነው፡፡

የፌደራል ሞሰብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ዳሬክተር አቶ አንተነህ ማሞ እንዳሉት ማዕከሉ አገልግሎት ስራ በጀመረ በ8 ወራት ውስጥ ከ95 ሺህ በላይ ደንበኞችን ተስተናግደዋል፡፡ የደንበኞች እርካታም 96.01 በመቶ መድረሱን ከተጠቃሚዎች በተሰባሰበ ግብረ-መልስ መረጋገጡን ገልጸዋል፡፡

ባለፉት 6 ወራት በተለያዩ ክልሎች 21 ቅርንጫፎች መከፈታቸውን የተናገሩት ዳይሬክተሩ በተያዘው አመት በመላው ሀገሪቱ 100 የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎት ማእከላት ለማቋቋም ስራ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሪፖርተር በፌደራል መሶብ የአንድ ማዕከል ተገኝታ ያነጋገረቻቸው ተገልጋዮች በማዕከሉ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እያገኙ መሆናቸው ተናግረዋል፡፡

በማእከሉ የሚሰጡ ሁሉም አገልግሎቶች በአንድ መስኮት ብቻ የሚጠናቀቁ በመሆናቸው ጉልበታቸውን ፣ ጊዜያቸውን እና ገንዘባቸውን እንደቆጠበላቸው ነው የተናገሩት።

የፌደራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከ8 ወራት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተመርቆ ስራ የጀመረ ሲሆን 23 ተቋማትን በመያዝ ፣ 187 የአገልግሎት አይነቶችን እየሰጠ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡
👍51
በኢትዮጵያ እና ሕንድ መካከል 8 የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈርመዋል። ከዚህ ውስጥ ደግሞ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመረጃ ማዕከል ለማቋቋም የመግባቢያ ስምምነት መፈረሙ አንዱ ነው።
4
የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብዱራህማን ሩቤ  ሥርዓተ ቀብር  ተፈፀመ
**

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት የአቶ አብዱራህማን ሩቤ ሥርዓተ ቀብር በኮልፌ የሙስሊም መካነ መቃብር ተፈፅሟል።

አቶ አብዱራህማን ሩቤ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ40 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አቶ አብዱራህማን በኢቢሲ እና በኦቢኤን ከሪፖርተርነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት ያገለገሉ ሲሆን ሕይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስም የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ ነበር፡፡

አቶ አብዱራህማን ሩቤ ባለትዳር እና የሦስት ልጆች አባት ነበሩ፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ አብዱራህማን ሩቤ ኅልፈት የተሰማውን ኀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል።

በላሉ ኢታላ
4😢3👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከሚሊዮኖች ጋር ትውውቅ የሚፈጥሩበትን ልዩ አጋጣሚ ይጠቀሙ
************

በኢቢሲ አዝናኝ የገና በዓል ዝግጅቶቻችን ላይ ምርትና አገልግሎትዎን ያስተዋውቁ።

ለበለጠ መረጃ ወደ

📲 0968979797
📲 0947959595

ይደውሉ
1
ብሪክስ ከኢኮኖሚ ጥምረት ባለፈ የራሱ “የፀጥታ ምክር ቤት” ሊኖረው ይገባል፡- ደቡብ አፍሪካዊት ምሁር
*********

ብሪክስ እስከ አሁን ሲከተለው የነበረው “ዝግ ዲፕሎማሲ” (Quiet Diplomacy) ፋይዳው እንዳከተመ ደቡብ አፍሪካዊቷ ምሁር ጊሊያን ሹት ገልፀዋል።

ምዕራባውያን ታዳጊ ሀገራትን እንደ እኩል አጋር ከማየት ይልቅ እንደ ስጋት ፈርጀው ለመቆጣጠር እየሞከሩ በመሆኑ፣ ብሪክስ ከጥንቃቄ ወጥቶ ራሱን መከላከል አለበት ይላሉ እኚህ ምሁር።

የኢኮኖሚ ማዕቀቦች፣ የሳይበር ጥቃቶች እና የመረጃ ጦርነቶች የብሪክስ አባል ሀገራትን አንድነት ለመሸርሸር ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው የሚሉት ምሁሯ የ“ዝግ ዲፕሎማሲ” አካሄድ ማብቃቱን ያመላክታሉ ነው የሚሉት።

በተለይም እንደ ደቡብ አፍሪካ እና ብራዚል ያሉ ሀገራት በውጭ በሚደገፉ ሚዲያዎችና ተቋማት አማካኝነት ለውስጥ አለመረጋጋት ተጋልጠዋል።

ይህን መሰለ ችግሮችን ለመፍታት ብሪክስ የራሱ የፀጥታው ምክር ቤት ቢኖረው፣ አባል ሀገራቱ የሚያደርጓቸው ወታደራዊ ልምምዶችና ትብብሮች በጠላቶቻቸው እንዳይጠመዘዙ ሕጋዊ ጥበቃ ይሰጣቸዋል የሚል ሃሳብ ይዘው ነው የመጡት ምሁሯ።

እንዲሁም አንዲት ሀገር ላይ የሚሰነዘርን ሁለንተናዊ ጫና ሁሉም በጋራ እንዲመክቱት የሚያስችል ዕድልንም ይፈጥራል።

ከምዕራባውያን ተጽዕኖ ነፃ የሆነ፣ በምርምርና በእውነት ላይ የተመሠረተ የብሪክስ ሚዲያና የምርምር ተቋማት (Think Tanks) መገንባት ለህልውና ወሳኝ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በሰለሞን ገዳ
2
አርሰናል እና ሊቨርፑል በ2024 እና በ2025 ከ17 ጨዋታ በኋላ
****

አርሰናል የፈረንጆቹን ገና በ39 ነጥብ ሊጉን እየመራ ተቀብሏል፡፡ የባለፈው ዓመት ሻምፒዮን ሊቨርፑል ደግሞ ከአርሰናል በ10 ነጥብ አንሶ በ29 ነጥብ ነው የእነሱን ገና የተቀበለው፡፡

ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ሰዓት ሊቨርፑል ካደረጋቸው 17 ጨዋታዎች 40 ነጥቦችን በመሰብሰብ ነበር የገናን በዓል ያከበረው፡፡ አርሰናል ደግሞ ከሊጉ መሪ ሊቨርፑል በ ስድስት ነጥብ ዝቅ ብሎ በ33 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ በመቀጥ ነው የ2024 ገናን ያሳለፈው፡፡

በዚህ ዓመት ነገሮች በብዙ ተቀይረዋል፡፡ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ባለፈው ዓመት ከ17 ጨዋታ ካገኘው 33 ነጥብ በስድስት አሻሽሎ ሊጉን እየመራ ሲሆን የመርሲሳይዱ ክለብ ደግሞ ከነበረበት 40 ነጥብ በ11 ነጥብ አሽቆልቁሎ 5ኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል፡፡

የፈረንጆች ገናን እና አዲስ ዓመትን ሊጉ እየመሩ የተረከቡ በርካታ ቡድኖች ከዋንጫ ጋር የመገናኝት ዕድላቸው ሰፊ ቢሆንም አርሰናል ግን የዚህ ዓመቱን ጨምሮ ከባለፉት አራት ዓመታት በሦስቱ በአዲስ ዓመት ሊጉን ቢመራም ዋንጫውን ማሳካት አልቻለም፡፡

በዚህ ዓመትስ ቀሪዎቹ 21 የሊግ ጨዋታዎች መልስ የሚሰጡ ይሆናል፡፡

በአንተነህ ሲሳይ
2
ከግጭት ማንም አትራፊ አይሆንም ፤ መጨረሻውም ድርድር እና ስምምነት ነው፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እና በአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል በቅርቡ የሰላም ስምምነት መደረጉ ይታወሳል፡፡ በዚህን ወቅት ከግጭት አትራፊ እንደሌለ እና ችግሮችን በውይይት መፍታት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ተናግረዋል፡፡

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ)ን ወክለው ከክልሉ መንግስት ጋር ዘላቂ ስምምነቱን የተፈራረሙት ማስረሻ ሰጤ በበኩላቸው የግጭቶች መቋጫ ውይይት መሆኑም አንስተዋል፡፡

የህዝብን ጥያቄ ለማስመለስ ወደ ትግል ብንገባም የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም የሚጎዳ እና ሉዓላዊነትን የሚዳፈር ሁኔታ ሲፈጠር ወደ ሰላም አማራጭ መጥተናል ብዋል- የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች ፡፡

ስምምነቱ በህዝቡ ዘንድ ትልቅ ደስታን ፈጥሯል፡፡ ከግጭት እና አለመግባባት ወደ ጠረንጴዛ ውይይት መምጣት እና መደራደር ሁለቱን ወገኖች ከፍ ሲልም ሀገር እና ህዝብን አትራፊ ስለሚያደርግ ተጠናክሮ ይቀጥል ብለዋል- አስተያየት ሰጪዎች፡፡

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ወደ ሰላም ውይይት እና ድርድር ያልመጡ የታጠቁ ሀይሎች እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሰላም ስምምነቱ በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን እና በምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) አማካኝነት መከናወኑ ይታወሳል፡፡
3
በገና በዓል ዝግጅቶቻችን ላይ ምርትና አገልግሎትዎን ያስተዋውቁ።

ከሚሊዮኖች ጋር ትውውቅ የሚፈጥሩበትን ልዩ አጋጣሚ ይጠቀሙ።

ለበለጠ መረጃ ወደ
0968979797
0947959595
ይደውሉ
5