TEMARI-NET – Telegram
TEMARI-NET
4.11K subscribers
910 photos
17 videos
167 files
288 links
This Channel is created to disseminate proper, timely information and news for Students
Download Telegram
#TAX
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ!

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አወዛጋቢውን የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ በይፋ አጽድቋል። ይህ ውሳኔ ከሠራተኛ ማኅበራት ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠመው ቢሆንም፣ የሀገሪቱን የደመወዝ ታክስ አወቃቀር እንደሚቀይር ይጠበቃል።

ማሻሻያው ምን ይዟል?

አዲሱ አዋጅ ከዚህ ቀደም ከ600 ብር በታች የነበረውን ከቀረጥ ነፃ ገደብ ወደ 2,000 ብር ከፍ አድርጓል። መንግሥት ይህ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች የግብር ጫና ለመቀነስ እና የግብር መሠረቱን በማስፋት የሀገር ገቢን ለመጨመር እንደሚያስችል ገልጿል።

ሆኖም ተቺዎች፣ ይህ ጭማሪ የኢትዮጵያን የኑሮ ውድነት ያላገናዘበ ነው ይላሉ። አዲሱ የግብር ተመን 15% ሲሆን፣ ቀደም ሲል የነበረው 10% የመግቢያ ተመን ተነስቷል። ከፍተኛው የ35% ግብር ደግሞ ወርሃዊ ገቢያቸው ከ14,100 ብር በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ ይሠራል።

@TEMARI_Net1
1
Forwarded from AAU MEREJA
Call_for_applications_for_admission_to_graduate_programs_PADM.pdf
879.9 KB
Call for Application!
🎓 Graduate Program Opportunities at Addis Ababa University
Department of Public Administration and Development Management (PADM)

📚 Now accepting applications for the 2025/26 academic year:

MA in Public Policy & Development Management(Regular & Extension Programs)
PhD in Public Management & Policy(Regular Program)

🗓 Important Dates:

GAT Registration:July 7 – August 17, 2025
GAT Examination Period: August 18 – 25, 2025

🌐 Apply Now:[https://portal.aau.edu.et](https://portal.aau.edu.et)

📍 Location:
Eshetu Chole Building, Offices 507 & 407, College of Business and Economics (CoBE), AAU

📞 Contact Us:
Tel: +251 111 229 602 / 0910 081 200


📄 For More Information:Please refer to the official PDF announcement.


The Department

@AAUMEREJA
1
መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ሁሉም ተማሪ ዩኒቨርስቲ የሚገባበት እለት መሆኑ ተነገረ

መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የቀጣዩ አመት የዩኒቨርስቲ ት/ት ይጀመራል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የፈተና ውጤት ጳጉሜ ላይ ይፋ ይሆናል በማለት እስከዚያም ድረስ የሚቆየው ፈተና ያልወሰዱና በመጪው ነሐሴ ወር ለፈተና የሚቀመጡ ቀሪ ተፈታኝ ተማሪዎች በመኖራቸው መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

በተለያየ ምክንያት ዘግይተው ትምህርት የጀመሩ በመኖራቸው ነው ፈተና እኩል ያልወሰዱ ተፈታኞች ያሉት በማለትም በመሆኑም ጳጉሜ ወር ላይ የ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ከታወቀ በኋላ መስከረም 8 ቀን ሁሉም ተማሪ ዩኒቨርስቲ የሚጀምርበት እለት እንደሚሆን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የትምህርት ካላንደርን በአግባቡ አክብሮ በመስራት የፈተና ጊዜያትንም ላለመሻማት ይሰራል ሲሉ ያከሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከመስከረም ጀምሮ ጥብቅ አሰራር እንደሚኖር ገልጸዋል።

እንደ ሀገር እኩል ውጤት ተናግሮ በእኩል ትምህርት ለማስጀመር ሲባል ቀሪ ያልተፈተኑ ተፈታኝ ተማሪዎችን ጠብቆ ማስጨረስ እንደሚገባ የተናገሩት የትምህርት ሚኒስትሩ በራሳቸው ፈቃድና ምክንያት አስቀድመው ፈተና ላይ ካልተቀመጡት በቀር ሌሎቹ የመመዘኛ መስፈርቱ አካል መሆናቸውን ገልጸዋል።


@TEMARI_Net1
Forwarded from #Abugida Message Board
🌍 The environment is not someone else’s problem: it’s everyone’s responsibility.
From rising temperatures to shrinking green spaces, the challenges are real and urgent.

🌱 Join the Abugida GRC 2025/26 Team!
We’re calling on passionate individuals ready to take meaningful action for a greener, healthier planet.
Together, let’s protect the only home we share.

2025/26 Theme:
_"From Local Action to Global Impact: Human Beings for Earth"_
(Aligned with SDGs 11, 13, and 17)

📌 Why Join?
*   Take action for the environment
*   Connect with passionate changemakers
*   Build local impact with global reach
*   Grow through leadership and learning

📩 Get Involved Now:
Join our group → t.me/+oCSPS4HZys01ZTQ0
Contact:
@kinde21 | 0921385604
@ananiya_sirak | +251965941486


#GRC #RacAbugida  #Rotaract #Rotary #District9212 #UniteForGood #MakeItHappen

Follow us on 👇

Facebook | Instagram | Telegram | Linkedin | TikTok | WhatsApp | X(Twitter)
1
#TECH
የቀድሞው የTwitter co-founder እና CEO የነበረው Jack Dorsey ያለምንም sim card እና internet network በBluetooth ብቻ text message መላላክ የሚያስችላችሁ አፕሊኬሽን ይፋ አድርጓል።

⚫️አፕሊኬሽኑ Bitchat ይባላል።
⚫️ከPlaystore ላይ አውርዳችሁ መጠቀም ትችላላችሁ።
https://play.google.com/store/apps/details?id=dev.hostingduty.bitchat

⚫️አፕሊኬሽኑን ለመጠቀም አካዉንት መክፈት አይጠይቅም።
⚫️ምንም አይነት Server ስለሌለው end-to-end encrypted ነው። ያ ማለት 3ኛ ወገን የምንፃፃፈውን ሊያይ አይችልም።

Bluetooth በ10 ሜትር ርቀት ስለሚሰራ text መላላክ የምንችለው በ10 ሜትር ርቀት ብቻ ነዉ ? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም።
ነገር ግን ከዛም በላይ መላላክ እንችላለን። ምክንያቱም በአካባቢያችን ብዙ ተጠቃሚዎች ካሉ የሚፈጠሩት ትንንሽ ኔትዎርኮች ሌላ ትልቅ mesh network እየፈጠሩ ሰፊ ክልል እንዲያካልሉ ያስችላሉ።

ይህ ቴክኖሎጂ በጣም ብዙ አይነት ጠቀሜታዎች አሉት።
⚫️የስልክ ኔትዎርክ በሌለባቸውና አደጋ በሚያጋጥማቸው አካባቢዎች communication እንዲኖር ያስችላል።
⚫️Security ለሚያሳስባቸው ሰዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ አለዉ።

©️bighabesha_software

@TEMARI_Net1
👍21
በምድር ላይ እስካሁን ከተገኙት የማርስ ድንጋዮች ትልቁ የሆነው ድንጋይ በ4.3 ሚሊየን ዶላር ተሸጠ።

NWA 16788 በመባል የሚታወቀው ሜትሮዪት 24.5 ኪሎ ግራም ክብደት እና 38.1 ሴንቲ ሜትር እርዝማኔ አለው ሲባል በ2023 ነበር በኒጀር የተገኘው።

ከሱ ቀጥሎ ካለው የማርስ ክፋይ በ70 በመቶ ትልቅ መሆኑ ሲነገር በምድር ላይ እስካሁን 400 የሚሆኑ የማርስ ድንጋዮች ብቻ መገኘታቸውም ይነገራል።

ድንጋዩ በጨረታ በኒው ዮርክ ሲሸጥ ከታክስ እና ሌሎች ክፍያዎች ጋር ተዳምሮ ዋጋው 5.3 ሚሊየን ዶላር አውጥቷል።

ከሽያጩ በኋላም ጉዳዩ ሚስጥር በመሆኑ የድንጋዩ የመጨረሻ መዳረሻ እና ማን እንደገዛው ለህዝብ ይፋ አልተደረገም።

የማርስ ድንጋዩ በ2023 የተገኘባት ኒጀር ከሽያጩ የገንዘብ ክፍያ ስለማግኘቷም የተባለ ነገር የለም።

Source: BBC

@TEMARI_Net1
1
#DRC
በዓመት ከ11-13 ሚሊየን ዶላር ለባርሴሎና ስፖርት ክለብ ለመክፈል የተስማማችው አፍሪካዊት ሀገር!

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ሃገሯን ለማስተዋወቅ ከስፔኑ የእግር ኳስ ክለብ ባርሴሎና ጋር የ46 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ተፈራርማለች።

በስምምነቱ መሰረትም የማልያ ላይ ስፖንሰር ሲሆን በባርሴሎና የወንዶች እና የሴቶች ቡድን የልምምድ እና የማሟቂያ ማልያ ላይም ኮንጎን ለማስተዋወቅ 'Heart of Africa' የሚል ፅሁፍ ይኖራል ተብሏል።

በተጨማሪ ይህ የዲሞክራቲክ ኮንጎ ማስታወቂያ በባርሴሎና አመታዊ ሪፖርት እና መፅሔት ላይም ይኖራል ተብሏል።

ዲሞክራቲክ ኮንጎ በየአመቱ ለመጪዎቹ አራት አመታትም ከ11-13 ሚሊየን ዶላር ለባርሴሎና ትከፍላለች።

በተጨማሪ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከፈረንሳዩ ክለብ ሞናኮ ጋር አመታዊ የ1.9 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ባለፈው ወር ስትፈራረም  ከጣሊያኑ ክለብ ኤሲ ሚላን ጋር መጠኑ ያልተገለፀ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈራርማለች።

ከዚህ በፊት ሩዋንዳ 'visit rwanda' በሚል ከአርሰናል፣ ፒ ኤስ ጂ እና ባየር ሙኒክ ጋር ተመሳሳይ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ማድረጓ ይታወሳል።

Source: TRT

@TEMARI_Net1
Forwarded from Alpha Market
💠Shop at #AlphaMarket at a discount price

Airpods Pro(USA) white color 1699 birr
Airpods pro (USA) Black color 1799 birr

Calculator (Scientific) : 800 birr
P9 headset 1599 birr
Airpods Pro 5s 1199 birr
Galaxy buds pro(New product) 1900 birr


u can check additional products @alphamarket21

contact us @ordernow21
with free delivery
1
#OPPORTUNITY
🌍 Call for Applications: Fully Virtual 2025 Africa’s Data Future Fellowship($1,500 Stipend)

🎯Are you a rising changemaker in data policy, digital rights, or technology? Ready to shape the next era of Africa’s digital transformation? The Centre for the Study of the Economies of Africa (CSEA) invites early-career professionals from across the continent to apply for the 2025 Africa’s Data Future Fellowship a fully virtual, 3-month capacity-building program empowering Africa’s next data governance leaders.

Fellowship Highlights:
Fully remote, pan-African fellowship (Aug–Nov 2025)
$1,500 stipend upon successful completion
Masterclasses and expert sessions with top minds in data & policy
Publication of your policy brief on CSEA platforms
Present your work at a pan-African workshop
Build a continental network of digital governance peers

Thematic Areas:
🔸Ethical Data Stewardship
🔸AI Governance & Responsible Innovation
🔸Data Sharing & Cross-Border Flows
🔸Digital Public Infrastructure
🔸Interoperability & APIs

Who Can Apply?
Postgraduate degree + 1 year professional experience
Background in tech, law, social sciences, policy, or digital governance
Strong written English or French (Francophone candidates encouraged!)
Committed to 2 hours/week for 3 months
Must have access to a stable internet connection

🔗 Apply: https://cseaafrica.org/postdetails/call-for-application-2025-africas-data-future-fellowship-1

📝 Deadline: 30 July 2025

"If this isn't for you, please share it with others who might be interested."🙏

Follow us👇for more opportunities
@TEMARI_Net1
1
የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በ2017ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም እና በ2018 ዓ.ም መሪ እቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄደ።


በውይይቱ የቢሮው እና የክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የመረጃ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በመርሀ ግብሩ የዘርፉ የ90 ቀን እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።



የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታዬ ወልደኪዳን ውይይቱ በዋናነት በ2017 ዓ.ም የትምህርት አመት ጥራቱን የጠበቀና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የትምህርት መረጃ ለህብተረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን በማስቀጠልም ሆነ በሂደት የተስተዋሉ ክፍተቶችን በማረም በ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት የተሻለ ስራ ለመስራት ታስቦ መካሄዱን አስታውቀዋል።


ዳይሬክተሩ አያይዘውም በትምህርት ሴክተሩ የ90 ቀን የንቅናቄ እቅድ ተዘጋጅቶ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ እንደመገኘታቸው ከመረጃ አስተዳደር እና ዝግጅት ጋር በተገናኘ በ90 ቀን እቅዱ የተቀመጡ ተግባራት አፈጻጸምን በመገምገም በቀሪ ጊዜያት ውጤታማ ስራ በመስራት እቅዱ እንዲሳካ የውይይቱ ተሳታፊዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲውጡ በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር እንዲቻል መርሀግብሩ መካሄዱን አመላክተዋል።


በመርሀ ግብሩ የቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ደስታ አብረሐም የዘርፉን የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2018 ዓ.ም መሪ እቅድ ያቀረቡ ሲሆን የአፋን ኦሮሞ አጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ አዲስ ዘገየ የዘርፉን የ90 እቅድ አፈጻጸም አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።


@TEMARI_Net1
2