ARBAMINCH UNIVERSITY COMMUNITY PRIMARY SCHOOL GRADE 6 – Telegram
ARBAMINCH UNIVERSITY COMMUNITY PRIMARY SCHOOL GRADE 6
163 subscribers
85 photos
1 video
114 files
1 link
Download Telegram
ውድ የ2016ዓ/ም የ6ኛ ክፍል ተማሪዎቼ እንኳን ደስ አላችሁ። እንኳን ደስ አለን።
100% ወደ ቀጣዩ ክፍል አልፋችኋል።
👍6
በተጨማሪ እንኳን ለ2017ዓ/ም አድስ ዓመት በሠላም በጤና አደረሰን። አደረሳችሁ። መልካም በዓል።
👍5
365 አድስ ያልተጀመረ ገፅ ፈጣሪ ሰቶልናልና መልካም ነገሮችን የምንፅፍበት እንድሆንልን ከልብ እመኛለሁ። መልካም አድስ ዓመት ይሁንልን። አሜን
መልካም እና ፍጹም ስጦታ ሁሉ ከላይ ነው አድስ ቀን ሁሉ አድስ ጅማሬ ነው ከብዙ ነገር ጠብቆ ለዚህ ላደረሰን እግ/ር ይመስገን ባጣነው ሳይሆን ባለን የምናመሰግንበት ወደ አምላካችን የምንመለስበት የሀገራችን ሰላም አንድነት እና ፍቅር ተመልሶ የምንደሰትበት እንሆን ተመኘው።
👏3
Forwarded from Yeka Education (Α𝕕𝕦𝕘𝕟𝕒𝕨 Bamlaku🦉)
ከቅድመ 1ኛ -12ኛ ክፍል የተማሪዎችን መጽሀፍት በሚከተሉት ሊንኮች ማግኘት ትችላላቹህ

የቅድመ 1ኛ መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/dam76/3693

⭐️የቅድመ አንደኛ የእንግሊዘኛ መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/dam76/4609

የ1ኛ ክፍል መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/dam76/3716

የ2ኛ ክፍል መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/dam76/3709

የ3ኛ ክፍል  መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/dam76/3702

የ4ኛ ክፍል መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/dam76/3685

የ5ኛ ክፍል መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/dam76/3678

የ6ኛ ክፍል መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/dam76/3670

የ7ኛ ክፍል መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/dam76/3659

የ8ኛ ክፍል መጽሀፍ
👇👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/dam76/3641

Afan Oromo Grade 3-8 text books
👇👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/dam76/3099

Afan Oromo grade 6-8
👇👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/dam76/3047

📘ከ9ኛ-12ኛ ክፍል መጽሀፍ ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://news.1rj.ru/str/dam76/3720
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2👍2
ለ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ሰኞ ዕለት 6:00 ላይ የመጀመሪያ ዙር ውድድር ስለሚጀምር ከ A ክፍል 30 እና ከB ክፍል 30 በድምሩ 60 ተማሪዎች 3ኛ A ክፍል እንድንገናኝ ይሁን።
👍7
አውቶብሶችን በሙሉ ዞኑ ስለተረከበ ሐሙስ  አለ ያልነው ተሰርዘዋል ። በመሆኑም ሰኞ ዕለት ከ9_10ኛ ያሉ የዛሬን ፈተና ይፈተናሉ። ከ11-12ኛ ማክሰኞና ረቡዕ ይፈተናሉ።ፈታኝ መ/ራንን በተመለከተ ረቡዕ የተመደቡ ሰኞ ይፈትናሉ:ሐሙስ  የተመደቡ ማክሰኞ :አርብ የተመደቡ ረቡዕ ይፈትናሉ። ተምሪዎቾ ነገ እንዳይመጡ በተቻለ መጠን በየሠፈራችሁ መረጃውን አድርሱልኝ  አመሰግናለሁ ።
7
ፅኑ ስብዕና (resilient personality)

የወርቅ ንፅህና በእሳት ተፈትኖ እንደሚለየው የሰው ልጅ ፅናትም በመከራ ውስጥ ነው ፍንትው ብሎ የሚወጣው። ለምሳሌ ሁለት ነጋዴዎች በተመሳሳይ ጊዜ ሊከስሩ ይችላሉ። ማንነታቸው ግን የሚወሰነው በደረሰባቸው ኪሳራ ሳይሆን ለኪሳራው በሰጡት ምላሽ ይሆናል። አንዱ ተስፋ ቆርጦ ድባቴ ውስጥ ሊዘፈቅ ይችላል፣ ሌላው ደግሞ የተሻለ ለመስራት ሊነሳሳ ይችላል።

ለችግሩ እጅ የሰጠው የመጀመሪያው ሰው ደካማ የፅናት ስብዕና ያላቸው ሰዎች ምሳሌ ሲሆን፣ በችግሩ ያልተበገረው ሁለተኛው ሰው ግን የፅኑ ሰብዕና አይነተኛ ምሳሌ ተደርጎ ሊወሳ የሚችል ነው።

በዚህች አጭር ፅሁፍ የፅኑ ሰብዕና ምንነትና ጥቅሞች እንመለከታለን።

ፅኑ ስብዕና ምንድን ነው?

ፅኑ ስብዕና ማለት በተለያዩ የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ተፈትኖ ማለፍ፣ ወድቆ የመነሳትና ችግሮችን ወደ ዕድል የመለወጥ ማንነት ነው። ለመሆኑ፣ የሰብዕናችን የፅናት ደረጃ ከፍ ያለ ወይ ዝቅ ያለ መሆኑን እንዴት እንለያያለን? ቀጥሎ 6 ነጥቦችን እንይ፦

ሀ) ቀና አመለካከት (Optimism)

ለነገሮች ያላቸው አመለካከት ቀና ነው። ሁሌም ችግሮች ጊዜአዊ እንደሆኑና "ሁሉ ነገር ለበጎ ነው" የሚል አስተሳሰብ አላቸው።

ለ) ተጣጣፊነት (flexibility)

በታላቅ አውሎነፋስ ውስጥ ብዙ ዛፎች ተገንድሰው ሲወድቁ የዘንባባ ዛፍ 🌴ግን ያንን አውሎ ንፋስ ዝቅ ብሎ ያሳልፍና መልሶ ቀና ይላል። ፅኑ ስብዕና ያላቸው ሰዎችም ልክ እንደ ዘንባባ ለተለያዩ ችግሮች የተለያዩ ምላሾች በመስጠት ያልፉታል፤ መናገር ሲገባቸው ይናገራሉ፣ ዝም ማለት ሲኖርባቸው አያወሩም፣ አንድን ችግር ችክ ብለው በተመሳሳይ መንገድ ለመፍታት አይዳክሩም።

ሐ) አለማስመሰል (Genuine)

ፅኑ ሰዎች ያልሆኑትን መስለው መታየት አይፈልጉም፤ ደካማ ጎናቸውን ለመሸፋፈን አይሯሯጡም። የሌላቸውን "አለኝ" ለማለት ለታይታ ሲሉ የተለያዩ ጭምብሎችን በማጥለቅና በማውለቅ አሳራቸውን አይበሉም።

መ) ተማሪነት

ለመንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ስኬትም ውድቀትም፣ ማጣትም ማግኘትም፣ ከፍታም ዝቅታም አንዳች ትምህርት ጥሎ ከማለፍ ውጪ አንዳች ጠባሳ አይተውባቸውም።

ረ) በሚቆጣጠሯቸው ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ

የፀና ሰብዕና ያላቸው ሰዎች ማድረግ በሚችሉት ጉዳይ ላይ እንጂ ከእነርሱ ቁጥጥር ውጭ ባለ ነገር ላይ አቅማቸውን አይጨርሱም።

ሰ) ጠንካራ ማሕበራዊ ቁርኝት

ፅኑ ሰብዕና ያላቸው ሰዎች ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት ያላቸው እንጂ ብቸኞች አይደሉም።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፅኑ ሰብእና ያላቸው ሰዎች ከሌላቸው አንፃር ሲታዩ ሲበዛ ስኬታማና የተሻለ የአዕምሮና የአካል ጤንነት ያላቸው ናቸው።

ስለዚህ፣ ሁላችንም አይናችንን ከሚገጥሙን ተግዳሮቶች ላይ አንስተን የመውጫ መንገዶችን ብንመለከት፣ ከማለቃቀስ ይልቅ የማንቀይረውን ብንቀበልና በሁሉ ብንደሰት የስኬት መንገድ ላይ መሆናችን አያጠያይቅም።
(ሳይኮሎጂ 101)
👍3😁1