Code Biruh© – Telegram
Code Biruh©
4.36K subscribers
117 photos
55 links
Welcome 🤗

➢ For #TechEnthusiasts, #Programmers & #Learners
Discover insights on coding, projects, and networks.

💻 Need a custom software solution? Let’s build something powerful together!

Empowering Minds

📩 Contact us: @CodebiruhVents
Download Telegram
🧶 In today’s fast-paced world, the pressure to earn money, secure a job, and help families can feel overwhelming.


One day, you dream of becoming a web developer. next, you’re drawn to app development. Then cyber-security catches your interest. But somehow, you haven’t started yet—or maybe you did, but struggled to stay consistent.


🔥 Guess what? Every expert you admire today was once in your shoes. Every master was once a beginner.


⚡️ That’s why Code Biruh is here. As a senior tech team, we understand the challenges of learning and growing in the industry.

🥰 This channel is your space to 
explore your strengths,
➢ stay updated with global trends, and
➢ build your tech journey with the right mindset
.


Your journey starts now—let’s make it happen!😊

Are you ready💪

Show us👍,

@codebiruh

#Ethiopian_programmers #ethiocoders #hackathon #ALX
👍9🔥2💯1
ከተናቁ ጅማሮዎች እስከ ዓለም ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ ግኝቶች።

➢ Mark Zuckerberg, Elon Musk, እና Steve Jobs ስለሚባሉ ሰዎች መቼም ሰምታችኋል።

➻ አሁን meta የሚባል ግዙፍ ኩባንያ ባለቤት የሆነው Zuckerberg, መጀመሪያ ከትምህርት ቤት ጓደኞቹ ጋር የሚነጋገርበት application ነበር የሰራ። በኋላ ግን በቢሊየኖች ተጠቃሚነት ያተረፈው Facebook ሊሆን ችሏል።

➻ የወቅቱ የዓለም ቁጥር 1 ባለሃብት musk, ከህጻንነቱ ጀምሮ code ያደርግ ነበር፣ በችግር ህይወት እንደተሰቃየም ይነገርለታል። ነገር ግን PayPal-ን በጋራ ከመመስረት እስከ Tesla,Space-X...የሚባሉ ድርጅቶች ባለቤት እስከመሆን በቅቷል።

➻ Steve Jobs ደግሞ ጋራጅ ውስጥ የጀመረው ስራ ነው apple የሚባለውን ስልክ እስከመስራት እንዲደርስ ያደረገው።


➻ ሌሎቹም እንደ Bill Gates, Jeff Bezos, Sundar Pichai የመሳሰሉት ከተናቀ ትንሽ እስከ ዓለምን ያስገረመ ውጤት መድረስ የቻሉ ነበሩ።

❤️ success isn't about where you start—it's about persistence, innovation, and the belief that you can change the world.
No dream is too big if you're willing to work for it!

start small but keep going💪
@codebiruh

Empowering Minds

#ethiocoders #codingethio #ethiopiancoders #codebiruh #ALX
8👍4🥰1
Code Biruh©
Photo
❤️ Programming Language ምንድን ነው?

በተደጋጋሚ Programming language ሲባል እንሰማለን 👂
ነገር ግን አንዳንዶች ብቻ የሚረዱት የሆነ ምስጢር የሚመስል ነገር አለ።

ከምር ግን ይሄን ያክል ውስብስብ ነው?
👨‍💻👩‍💻well, it's not😊

A programming language is a formal set of instructions that can be used to produce various kinds of output, such as software applications, noscripts, or algorithms.  blah blah ከሚል definition እንውጣ እስኪ ለዛሬ😊

በመጀመሪያ program ማለት ምን ማለት ነው። ይሄ ቀጠሮ መያዝ እንዳይመስላችሁ😊 program ማለት developer-ኡ ወይም እናንተ ስራውን የምትሰሩት ሰዎች የምትጽፏቸው code-ኦች ናቸው። ስለዚህ እነዚህን code-ኦች በመጠቀም computer-ኣችሁ የተለያዩ ስራዎች እንዲሰራ ማዘዝ ማለት ነው።

ለምሳሌ movie 📽️ ማየት ብትፈልጉ computer-ኣችሁ ላይ ሄዳችሁ የplay ምልክት ትነካላችሁ አይደል፤ ያ ማለት movie-ውን ጀምርልኝ እያላችሁ እያዘዛችሁት ነው።

ቀጣይ Language ማለትስ? መቼም Language ቋንቋ መሆኑ ይጠፋችኋል ብለን አይደለም የጠየቅናችሁ😊
እንስሳቶች እና የሰው ልጆች የሚግባቡበት የራሳቸው ቋንቋ እንዳላቸው ሁሉ፤ developer-ኦች ወይም እናንተ ከcomputer-ኣችሁ ጋር የምትነጋገሩበት ቋንቋ አላችሁ።

ይህ ቋንቋ ነው እንግዲህ programming language የሚባለው።

የሰው ልጆች የተለያዩ ቋንቋዎች እንዳሏቸው ሁሉ (English,Amharic,Arabic, Spanish,Swahili...)
ለcomputer-ኦችም የተለያዩ ቋንቋዎችን መጠቀም ይቻላል። ለዛ ነው programming languag"es" የሚባል።

ከprogramming languages መካከል Python, Java, JavaScript, C++, C#, Ruby, Swift, Dart የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል።

ስለዚህ Programming Language ማለት ከcomputer-ኣችሁ ጋ የምታወሩበት፣ የምታዙበት፣ የምትግባቡበት ቋንቋ ነው።

ጽሑፉን ከወደዳችሁት 👍 አይረሳ😊

ከላይ ከተጠቀሱት ውጭ እስኪ እናንተም የምታውቋቸውን programming languages comment ላይ ጻፉልን።


@𝙘𝙤𝙙𝙚𝙗𝙞𝙧𝙪𝙝

#ethiopiancoders #hackathon #ethiocoder #A2SV #ALX #Upwork
👍107🔥1
Database ምንድን ነው?

እንደዚህ በሰለጠነው በዚህ ዓለም ፤ በጣም ብዙ የሚባሉ መረጃወችን በየቀኑ እናገኛለን፣ እንጠቀማለን።

ለምሳሌ online ስንገበያይ፣ social media ስንጠቀም፣ live ስንገባ፣ ከነዚህ ሁሉ ነገሮች ጀርባ አንድ አስደናቂ technology አለ 👉 Database.

A database is an organized collection of data that allows users to store, retrieve, manage, and manipulate information efficiently. ከሚለው የተለመደ definition እንውጣ😄

database የሁለት ቃላት ጥምረት ሲሆን data እና base ናቸው። data እንደሚታወቀው ማንኛውም ያልተጣራ፣ ያልተስተካከለ፣ አጠቃላይ መረጃ ነው። base ደግሞ የሆነ መሰረት፣ ማጠራቀሚያ፣ ሊሆን ይችላል።

ስለዚህ database ባጭሩ የመረጃዎች ማህደር ወይም መያዣ፣ ማጠራቀሚያ ሊሆን ይችላል።

ለምሳሌ social media ስትጠቀሙ የእናንተ መረጃ profile-ኣችሁ፣ ስማችሁ ወዘተ ወይም ከሰው ጋር chat የምታደርጉት፣ የምታስቀምጧቸው photos እና videos በሙሉ የሚቀመጡት database ላይ ነው።

ምን አለፋችሁ database ገመና ከታች በሉት😊

የተለያዩ የdatabase አይነቶች ሲኖሩ relational, non relational, cloud ወዘተ በመባል ይታወቃሉ።

ጽሑፉን ከወደዳችሁት 👍,  አይረሳ።😊

📌 እስኪ እናንተ ደግሞ ለdatabase ከሚያገለግሉ programming languages ውስጥ የምታውቁትን comment ላይ ጻፉልን።

@codebiruh

#ethiocoders #ethiopiancoders #coding #programming #ALXETHIOPIA #Africancoders
👍98😍2❤‍🔥1
Code Biruh©
Photo
Full Stack Developer ምንድን ነው?

ፈገግ የሚያደርግ ነገር በመንገር እንጀምር😊 google translate-ን "Full stack developer" እንዲተረጉምልን ጠየቅነው ምን ቢል ጥሩ ነው "ሙሉ ቁልል ገንቢ"😂

DeepSeek ደግሞ "ሙሉ ስቴክ ገንቢ" ብሎ ተርጉሞታል የዚህ ይሻላል። ቁልል... ሆ😀

ለማንኛውም Full Stack Developer👩‍💻👨‍💻 የሁለት ሙያወች ጥምር ነው።
Full Stack Developer 👩‍💻👨‍💻  = Front End Developer  👩‍💻 + Back End Developer 👨‍💻

Front End ማለት ይሄ በአይናችን የምናየው፣ ፊት ለፊት የምናገኘው ክፍል ነው። ለምሳሌ website ከሆነ login የሚለው የተለያዩ ቀለሞች የሚታዩን ጽሑፎች፣ የተለያዩ ማስታወቂያዎች ወ.ዘ.ተ  ብቻ ማናቸውም screen-ኡ 🖥️ ላይ የምናያቸው ነገሮች በሙሉ Front End Developer-ኡ የሚሰራቸው ናቸው።

በአንጻሩ Back End ደግሞ ራሱ Developer-ኡ ብቻ የሚያያቸው የተሰሩትን Website-ኦች ወይም Application-ኦች የሚጠቀሙት user-ኦች ግን የማያዩት ክፍል ነው። አስማቱ ክፍል እንለዋለን።😀

በቀላሉ መኪና🚐 እና ነዳጅን አስቡት። መኪናው በአይን የሚታዩ ፍሬን፣ ማርሽ፣ መሪ የመሳሰሉ አካላት አሉት። እነዚህን ነገሮች መኪናው ሳይነሳ (ሞተሩ እንደጠፋ) ብንጠቀማቸው ምንም አይሰሩም። ለምሳሌ ማርሽ ብትቀያይሩ መሪውን ብታዞሩ ፍሬን ብትይዙ ምንም አታመጡም። ነገር ግን ነዳጅ ሞልታችሁ፤ ቁልፉን አስነስታችሁ ብትነዱት መኪናው ይንቀሳቀሳል። ይሄው ነው Front End ማለትም website-ኡ ወይም Application-ኡ ላይ የሚገኙ login like የመሳሰሉ ነገሮችን ብትነኳቸው ምንም አታመጡም😊 ለዚህም ነው BackEnd የሚያስፈልገው። ስለዚህ ከጀርባ ሁኖ እንደ ነዳጅ ስራውን ይሰራል ማለት ነው። so ነዳጁ Back End ሲጨመር ሙሉ ወይም የተሟላ Software ይባላል።

ይሄን የሚሰሩ ሰዎች ናቸው እንግዲህ Full Stack Developer የሚባሉ።

➣ ብዙ ሰዎች በtech field ያሉም ሳይቀር Full Stack ሲባል web development ብቻ የሚሰሩ ሰዎችን ይመስላቸዋል። ነገር ግን ማንኛውም software የሚሰሩ፣ application የሚሰሩ even Game developers ራሱ Full Stack Developers ይባላሉ።

ሌላው Full Stack Developer ከ front end እና back end በተጨማሪ ስለ Data Base, DevOps, Security & Maintenance, Performance Optimization እና የመሳሰሉትን እንዲያውቅ ይጠበቃል።


Senior FullStack Developer 👩‍💻👨‍💻 ከሆናችሁ ከ120 ሺህ እስከ 160 ሺህ የአሜሪካን ዶላር አመታዊ ክፍያ አለው።😋 ወደ ኢትዮጵያ ብር ስንቀይረው ደግሞ ወደ 16.8 ሚሊዮን ብር አካባቢ ነው።🙉 (according to ZipRecruiter.com)

እንግዲህ ሙሉ "ቁልል"😂 ገንቢ መሆን የምትፈልጉ Code Biruh ትክክለኛ ምርጫችሁ ነው።🤗

ከFrontEnd, BackEnd, FullStack ከዚህ በፊት ስለየትኛው ሰምታችሁ ታውቃላችሁ። እስኪ comment ላይ ጻፉልን።

@codeBiruh

#Coding #ethiocoders #hackathon #ALX #ALXETHIOPIA #codersAfrica
3👍2
🔴 ማየት ማመን ነው🤩

C++ (Computer Programming-ን)
➊ በተብራራ ኖት ና አዝናኝ በሆነ መልኩ
➋ Mid እና Final ፈተናዎች ከነመልሳቸው
❸ ሙሉ የማጠቃለያ ጥያቄዎች ከነማብራሪያቸው
❹ የአጠናን ዘዴዎች እና tip-ኦችን ያገኙበታል።

👨‍🏫👩‍🏫 Sample-ኦቹን ለማየት👇
@codebiruh_sample

👨‍🚀👩‍🚀ለመመዝገብ 👇
@codeBiruhTutor_bot

🙇‍♂️🙇‍♀️ቻናሉን ለመቀላቀል
@codeBiruh

⚡️በተለይ Fresh-Man 2nd Semister ለሆናችሁ የቀረበ ወርቃማ እድል።

Thank You🙏
🌼Code Biruh🌼
Empowering Minds, Brewing Solutions.
🙏3👍2
🔴 first of all we would like to appreciate your Eagerness to learn and improve your self.

🎉 C++ Tutorial ምዝገባ ላይ መሆናችን ይታወቃል።

🎊 ብዙወቻችሁ ግን እንዴት እንደምትመዘገቡ እየጠየቃችሁን ነው።

ግልጽ ለማድረግ በbot-ኡ በኩል "መመዝገብ እፈልጋለሁ" ወይም "Register me" እያላችሁ ላኩልን Private Channel-ኡን የምትቀላቀሉበትን link እንልክላችኋለን።

bot-ኡ ይሄው👉 @codeBiruhTutor_bot
sample-ኦቹን ለማየት ይሄው👇
              @codebiruh_sample


ማንኛውንም ጥያቄ comment ጋ ጻፉልን።
👍4
Code Biruh©
Photo
🌤 በአሁኑ ጊዜ ዓለማችን ላይ የገነኑት ሁለቱ programming language-ኦች።

ከ700 በላይ programming languages ወይም የኮምፒውተር ቋንቋዎች ቢኖሩም እንደነዚህ እንደሁለቱ ግን በስፋት ተጠቃሚን ያገኙ የሉም።
የመጀመሪያው የቀላልነትና የAI ንጉስ ሲሉት ሁለተኛውን ደግሞ የweb ንጉስ ይሉታል። Python እና JavaScript

🧶 🅟🅨🅣🅗🅞🅝
አሁን ላይ በብዙዎች በኩል ተቀባይነት ያገኘ ቋንቋ ሲሆን በዋነኛነት ለdata science 🗑️ ለAI 🤖 ለweb development 🧑‍💻 ለAutomation 🚌 እና cyber cecurity 💻 ለመሳሰሉት ተመራጭ እና ቀዳሚ ያደርገዋል።

👑 ካልጠፋ 700በላይ ቋንቋ ለምን python ላይ ሰው ተጣበቀ😊 ካልን፦

➊ ለመማርና ሌላ ሰው የጻፈውን code ለመረዳት ቀላል ነው።
➋ ለብዙ field-ኦች ስለሚያገለግል ብዙ language ከመማር እሱን መጨረስ።
➌ ጠንካራ የሆነ እና ብዙ የሚማርና የተማረ community ማግኘት ስለሚቻል
➍ በትልልቅ ካምፓኒወች ስለሚዘወተር እና በመሳሰሉት ተመራጭ ሆኗል።

🎒 በpython የተሰሩ ወይም ከሌሎች programming language-ኦች📺 በተጨማሪ pythonን በዋናነት ከጨመሩ
application-ኦች መካከል YouTube, Instagram, Spotify, Netflix ይጠቀሳሉ።

🧶 🅙🅐🅥🅐🅢🅒🅡🅘🅟🅣
ሌላው በብዙዎች በኩል ተቀባይነትን ያገኘ ቋንቋ ሲሆን የweb የጀርባ አጥንት(backbone) እያሉ ያሞካሹታል።😊

በዋነኛነት ለweb development front-end እና back-end ቋንቋ በመሆን ያገለግላል።

👑 አሁንም በድጋሜ ካልጠፋ 700በላይ ቋንቋ ለምን JavaScript ላይ ሰው ተጣበቀ😊 ካልን፦

➊ web browsers ላይ run ማድረግ ስለሚቻል፣
➋ ከbrowser በተጨማሪ ወደ back-end ሁሉ መሄድ ስለሚችል፣
➌ ጠንካራ የሆነ እና ብዙ የሚማርና የተማረ community ማግኘት ስለሚቻል እና ብዙ developer-ኦች ስላሉ
➍ ከweb በተጨማሪ በሌሎችም tecjnology-ኦች ላይ መጠቀም ስለሚያስችል። ለምሳሌ፦ game development, AI, Mobile development ወ.ዘ.ተ
➎ በትልልቅ ካምፓኒወች ስለሚዘወተር እና በመሳሰሉት ተመራጭ ሆኗል።

🎒 በJavaScript የተሰሩ ወይም ከሌሎች programming language-ኦች📺 በተጨማሪ JavaScriptን በዋናነት ከጨመሩ
application-ኦች መካከል facebook, google, linkedin, Netflix የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ።

🕸 እናንተ የትኛውን የበለጠ ትወዱታላችሁ?
Python or JavaScript?

@codebiruh

#Python #JavaScript #JS #ethiocoders #freecodecamp
👍73🔥1
#update

ውድ የCode Biruh ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ🥰

🔖 update ይኖረናል ባልነው መሰረት ልንነግራችሁ ነው።

📣 እንንገራችሁ?
አዎ ከሆነ ...
እስኪ reaction 👍🔥 + comment ga yes/አዎ እያላችሁ ጻፉልን።

@codeBiruh
👍13🔥31
#Update #Discount

እንኳን ደስ አላችሁ 🎉

update ያልናችሁ ይሄው👇
CodeBiruh C++ tutor በብዙዎች ተወዳጅ እየሆነ መጥቷል። ከተማሪዎቻችን ጋር ብዙ ተወያይተን ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የ50% ቅናሽ ማድረጋችን ስንገልጽ በደስታ ነው።

ስለዚህ የተለያዩ ሶስት አማራጮችን ይዘን መጥተናል።

➊ኛ Group Package: በግሩፕ ወይም ከሁለት በላይ ሁናችሁ ለምትመጡ የተለየ ቅናሽ ይኖራል።

➋ኛ Gift Package: የምትወዷቸውን ጓደኞቻችሁ surprise የምታደርጉበት ሲሆን፤ gift የሚቀበሉት ልጆች private ቻናሉ ጋ Gift celebration ይደረግላቸዋል።

Personal Package: በዚህ አንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለሚመዘገብ ሰው የ50% ቅናሽ ተደርጎለታል።

🔥 ፍጠኑ ይሄ እድል ለእናንተ ነው።

👨‍🏫👩‍🏫 Sample-ኦቹን ለማየት👇
@codebiruh_sample

👨‍🚀👩‍🚀ለመመዝገብ 👇
@codeBiruhTutor_bot

🙇‍♂️🙇‍♀️ቻናሉን ለመቀላቀል
@codeBiruh

@codeBiruh

#ethiocoders #adiscoders #shecods #alx #icoglabs
👍31🔥1🙏1
🔴 ሁለተኛ ዙር ምዝገባ ተጀመረ!!!

🔴 ማየት ማመን ነው🤩

C++ (Computer Programming-ን)
➊ በተብራራ ኖት ና አዝናኝ በሆነ መልኩ
➋ Mid እና Final ፈተናዎች ከነመልሳቸው
❸ ሙሉ የማጠቃለያ ጥያቄዎች ከነማብራሪያቸው
❹ የአጠናን ዘዴዎች እና tip-ኦችን ያገኙበታል።

👨‍🏫👩‍🏫 Sample-ኦቹን ለማየት👇
@codebiruh_sample

👨‍🚀👩‍🚀ለመመዝገብ 👇
@codeBiruhTutor_bot

🙇‍♂️🙇‍♀️ቻናሉን ለመቀላቀል
@codeBiruh

👨‍💼👩‍💼ለተጨማሪ መረጃ
@Now1207

⚡️በተለይ Fresh-Man 2nd Semister ለሆናችሁ የቀረበ ወርቃማ እድል።

Thank You🙏
🌼Code Biruh🌼
Empowering Minds, Brewing Solutions.
👍3🔥1
ለእስልምና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች

🌙 እንኳን ለ1 ሺህ 446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ዒድ ሙባረክ!

@Codebiruh
👍3
Code Biruh©
Photo
The Cloud ☁️ (Invisi Comp)
    " አባባ  ደመና ☁️ 😊 "


➦ ዛሬ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ በስፋት ስለምንጠቀመው Computer እናወራለን አብራችሁን ቆዩ🙌

➬ ልጅ እያለን ቤተሰቦቻችንን ስናስቸግር (ስንረብሻቸው) አባባ ደመና መጣብህ/ሽ እያሉ ያስፈራሩን ነበር። ስናድግ ግን ይሄ አባባ ደመና የሚባል ሰው እንደሌለና ሰማዩ ላይ dark grey (ዝናብ ሲዘንብ) ቀለም ሰርቶ የሚታየን ነገር እንደሆኘ አወቅን።😊

➬ በcomputer science መንደር ደግሞ እኛ አባባ ደመና የሚባል አለ ይሉናል። እንዴት?

❤️ Cloud Computing (The Cloud) (data-ን የሚያዘንበው ደመና😂)
ማለት የcomputing አገልግሎቶችን ማለትም servers, storage, databases, networking, software, እና የመሳሰሉትን ቦታ ሳይወስነን በinternet አማካኝነት ማቅረብ መቻል ነው።

〽️ Google, Amazon, Microsoft የሚባሉ ታላላቅ company-ኦችን እንዴት የምናገኛቸው ይመስላችኋል? በcloud computing concept ነው። እንደዛ ባይሆንማ ስልካችን አሊያም pc-ኣችን search ባደረግንበት ቁጥር ይሞላ ነበር😊 ምክንያቱም data store የሚደረግበት database ስለሚያስፈልግ ነው።

🔴 cloud computing እንዴት ተመራጭ ሆነ?

Can be accessed anywhere (የትም ስለሚገኝ) ፦ የትም ቦታ ብንሆን internet እስካለ ድረስ መጠቀም እንችላለን። file store ማድረግ ሊሆን ይችላል። info access ማድረግም ሊሆን ይችላል እንደ ፍላጎታችን።

Storage ፦ የምንጠቀምበት device ላይ ስለ space መጨነቅ አይጠበቅብንም።

super affordable : ከሚባለው በላይ ርካሽ ነው። ይህ ሲባል አንዳንድ በጣም expensive አሉ። ግን generally አንድ ሰው ውድ የሆነ device መግዛት አይጠበቅበትም፣ በቀላል ስልክ access ማድረግ ይችላል።

Collaboration ፦ በግል ከመስራትም በላይ ከሌሎች ሰዎች ጋር በጋራ ለመስራት። ለምሳሌ Google Docs, Microsoft Office 365, Git and Trello የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል።

በተጨማሪም

➾ photo,file... ለማስቀመጥ።
➾ online game-ኦችን ለመጫወት
➾ tv show & movies ለማየት። ለምሳሌ Netflix, Disney+, and YouTube.
➾ music make & share ለማድረግ።
ወ.ዘ.ተ ስለሚያገለግል ተመራጭ ያደርገዋል።

🔴 So data የት ነው የሚቀመጠው? ደመና ላይ?🤔

🔹 😂 አሰራሩ እንደዛ ይመስላል። ነገር ግን ይሄን service deliver የሚያደርጉ company-ኦች የራሳቸው የሆነ data center አላቸው። በነዚህ data center-ኦች ውስጥ ደግሞ ግዙፍ የሆኑ server-ኦች ተቀምጠዋል።

🔸 ስለዚህ file ስንጭን ወይም online game ስንጫወት ወይም ሌላ የcomputing ስራ ስንሰራ እኛ የምንጠቀምበት device መልእክት ለነዚህ server-ኦች ይልካል። ከserver-ኡ የተቀበለውን data screen-ኣችን ላይ እንዲታየን ያደርጋል።

@codeBiruh

ጽሑፉን ከወደዳችሁት ,👍 አይረሳ።

ተጨማሪ tech related መረጃዎችን ለማግኘት join ያድርጉ።

አባባ ደመና 👨‍🦳 መጣባችሁ😂 🙌

#cloud #cloud_computing #AI #ethiocoders #codeafrica
5👍5🔥1
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ
እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

@codeBiruh @2017
7🙏1
#AI Now ...

🎯 ከትንሽ ጊዜ በኋላ ስለ AI ማውራት አዲስ ነገር እየሆነ አለመምጣቱ ይታወቃል።

🪢 AI ግን ብዙዎቻችን እንደምናስበው ጽሑፍ እየሰጠነው ስለዚያ እንዲያስረዳን ወይም image or any media generate እንዲያደርግ አይደለም አላማው።

❄️ AI የመጨረሻ ግቡ ከሰው ቁጥጥር ውጭ የሆነ ሌሎች AI-ኦችን መፍጠር የሚችል system መገንባት ነው። ይሄ ትንሽ ያስፈራል አይደል😀

📌 ለምን ብለን ከጠየቅን scientist-ኦቹ በሰው ልጅ አቅም ሊፈቱ ያልቻሉ ችግሮችን መፍታት የሚችል system ሊኖር ይገባል። ይላሉ😊። ትስማማላችሁ?

📌 ይህ AI Super AI(Self awared System) በመባል ይታወቃል። አንዳንዶች ስለዚህ system ሲናገሩ የሰው ልጆች ላይ አደጋ የሚጥል (የሚያጠፋ) system ብለውታል።

📌  ደረጃ ላይ ለመድረስ ግን ብዙ የAI stage-ኦችን ማለፍ ይኖርበታል። ምክንያቱም አሁን ያለው AI ጠባብ ወይም narrow AI ይባላል። ምክንያቱም እያንዳንዱን መረጃ እኛ እየሰጠን ስለምናሰለጥነው ነው።

📌 ቀጣዩ አሁን ላይ የዓለማችን ትልልቅ ድርጅቶች ሳይቀር እየሰሩበት የሚገኘው AGI (Artificial General Intelligence ) የሚባለው AI ነው።
ይሄ ልክ እንደ ሰዎች ማሰብ የሚችል system ነው። በራሱ ማሰብ የሚችል እንደማለት ነው። ለምሳሌ openAI $40 billion fund አድርገው እየሰሩበት ይገኛሉ። የGoogle DeepMind-ም... ሌሎቹም... በቅርቡ እናመጠዋለን እያሉ ነው።

🔶 AGI በቅርቡ ዓለም ላይ የሚመጣ ይመስላችኋል? እስኪ comment ላይ ፃፉልን👇

@codeBiruh


#AI #Ai #ASI #AGI #deepseek #Gpt
👍42