ደዕዋ ቲቪ || 𝐃𝐚𝐞𝐰𝐚 𝐓𝐕 – Telegram
ደዕዋ ቲቪ || 𝐃𝐚𝐞𝐰𝐚 𝐓𝐕
4.46K subscribers
1.71K photos
554 videos
3 files
1.71K links
ይህ የደዕዋ ቲቪ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።

★★★★★
📡 የ ዳዕዋ ቲቪ ስርጭትን በ ናይል ሳት
ለመከታተል:– 👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11636
ሲምቦልሬት:- 27500
ፖላራይዜሽን:- vertical
★★★★★

Youtube
https://www.youtube.com/@daewa_tv

Facebook
https://www.facebook.com/daewatv/

Telegram
https://news.1rj.ru/str/daewa_tv
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሁሉም ቀድሞ ተፅፏል
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
2👍1
ፊሪሀቢል አያህ (ክፍል 17) |በሸይኽ አብዱሰላም አንዋር|

👉 https://youtu.be/ciC0hRjqnak
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat 
Frq [11636]  Pol [v]  S.rate [27500]

©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
ደዕዋ ቲቪ || 𝐃𝐚𝐞𝐰𝐚 𝐓𝐕
Photo
የዒልሙ ገበሬ

የታላቁ ዓሊም የሸይኽ አብዱል ሐሚድ ከቶ
ዘመን ተሻጋሪ አጭር የህይወት ታሪክ


በወሎ ምድር፣ በቦረና አውራጃ ውስጥ "ከቶ" የምትባል አንዲት መንደር አለች። ይህች መንደር እንደማንኛዉም ተራ መንደር  የምትታሰብ አይደለችም፤ ይልቁንም የሺህ ደረሶች ማረፊያ፣ የኢዕራብ አነብናቢዎች ድምፅ ጩኸት የማይለይባትና የኢልም (የእውቀት) ምንጭ ሆና የኖረች የተከበረች መንደር ናት። ለዚህ ሁሉ ክብር ደግሞ መነሻው አንድ ታላቅ ሰው ናቸው። ሸይኽ አብዱል ሐሚድ ከማል በሽር (ሸህ ከቶ) ።

ሐጂ አብዱል ሐሚድ በ1918 (ዓ.ል) በወረሂመኖ አውራጃ "ጥጋት" በተባለች መንደር ተወለዱ። የተገኙት ከቀላል ቤተሰብ አይደለም፤ አባታቸው ሸህ ከማል በሽር የታወቁ ዓሊም ነበሩ። የቤተሰባቸው የትውልድ ሀረግም እስከ ቀድሞው የሸዋ ክፍለ ሀገር "ኢፋት" ሙስሊም ሱልጣኔት ድረስ የሚመዘዝ ሲሆን፣ እርሳቸውም በቅድመ አያቶቻቸው የሸህነት መስመር 13ኛው ተረካቢ ሆኑ።

ገና በአምስት ዓመት እድሜያቸው በአባታቸው እጅ ቁርአንን መቅራት የጀመሩት ታዳጊ፣ በለጋነታቸው የእውቀት ጥማት አንገብግቧቸው ነበር። አባታቸው ሸይኽ ከማል በ165 እና ከዛ በላይ ደረሶች ተከበው ሲያስተምሩ እያዩ በማደጋቸዉ ፣ በልባቸዉ  ውስጥ የእውቀት ዘር ቀድሞ ተዘራ። ከወሎ እስከ ጎጃም ዒልምን ፍለጋ ታተሩ የእውቀት መንገድ አልጋ በአልጋ አልነበረም።

አባታቸው ሸህ ከማል በሽር እስልምናን ለማስፋፋትና ለማስተማር ሲሉ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰዋል። 1923 (ዓ.ል)  ወደ በጌምድር (አንሻር) ተጓዙ። 1927 (ዓ.ል) ወደ ጎጃም (ደብረወርቅ - አሞናት) አቀኑ። ወቅቱ ጣሊያን ኢትዮጵያን የወረረችበት ነበር ፣ ጣሊያን የሸይኽ ከማልን ተሰሚነት የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ ሞክሮ ነበር። ሆኖም ግን "እኔ የመጣሁት እውቀትን ላካፍል እንጂ ስልጣን ፍለጋ አይደለም" በሚል ጽኑ አቋም የጣሊያንን የ'ቃዲነት' ግብዣ ውድቅ በማድረግ በሳቸዉ በኩል ሀገር እንዳትወጋ ጣሊያን ላይ በሩን ዘግተዋል። አባታቸው በ1930 (ዓ.ል) በሞት ሲለዩ፣ ወጣቱ አብዱል ሐሚድና ቤተሰባቸው ወደ ትውልድ ስፍራቸው ወሎ ተመለሱ።

ሸይኽ አብዱል ሐሚድ ዓሊምን ለመቅሰም የሄዱበት ርቀት እጅጉን የሚደነቅ ነው። ራሳቸውን ለእውቀት አስገዝተው ለ16 ተከታታይ ዓመታት በተለያዩ መሻይኾች ዘንድ ዒልም ፍለጋ ተንከራተዋል። በጫቀታ ኮኔና ለሚ፦ ለ8 ዓመታት ፊቅህ እና ተውሂድ ያለማቋረጥ ጠንቀቅዉ ተምረዋል ።

በማጎሌ (ከሸህ ይማም አሰን)፦ ነህዉ፣ ሶርፍ እና በላጋ። በሃዶና ደሴ፦ ተፍሲር፣ ኡሱል እና ኢልም አል-ሐዲስ እነ ሸይኽ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢብን ጨምሮ በርካታ መሻይኾች ላይ ተጨማሪ ለተከታታይ 8 ዓመታት ዒልምን ቀስመዋል ። የዚህ ሁሉ ልፋት ዉጤት እሳቸውን በወሎ ምድር  "ሙፍቲ" (ታላቅ ፈትዋ ሰጪ) አደረጋቸው። የዘመኑ ተመራማሪዎች እንደሚሉት፣ የእርሳቸው እውቀት ዛሬ ባለው ሚዛን ቢለካ "ከሙሉ ፕሮፌሰር" በላይ ነበር ይላሉ።

በ1952 (ዓ.ል) ወደ "ከቶ" ያቀኑት ሐጅ አብዱል ሐሚድ፣ በዚያም የራሳቸውን ዛውያ (ሀሪማ) መሠረቱ። በመጀመሪያ በሳር ቤት፣ በኋላም በቆርቆሮ በተሠራው መስጊዳቸው ውስጥ ከሁሉም አቅጣጫዎች (ከኤርትራ፣ ከከፋ፣ ከጎንደር፣ ከጉራጌና ከኢሊባቦር) የሚመጡ ደረሶችን ማስተማር ጀመሩ። ሐጅ አብዱል ሐሚድ የኪታብ አዋቂ ብቻ አልነበሩም፤ የህዝብ አለኝታም ነበሩ። የሥራ ባህል፦ "እሮብ አይሠራም፣ ሐሙስ አይሠራም" የሚሉ የተሳሳቱ አመለካከቶችን በመቃወም፣ "ሁሉም የአላህ ቀን ነው፣ ሰርቶ መብላት ግን ግዴታ ነው" በማለት ህዝቡን ለሥራ አነሳስተዋል። እሳቸው ራሳቸው ደረሶቻቸውን ይዘው የአቅመ ደካማዎችን አዝመራ ያርሙ፣ ያጭዱና ቤታቸውንም ይጠግኑ ነበር።

ሐጅ አብዱል ሐሚድ  እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ የእስልምና ሃይማኖት እውቀትን ለማስፋፋት ታግለዋል። በወቅቱ አከባቢዉ ላይ ተንሰራፍቶ የነበረዉን ገሪባ እና ፉቅራ መጤ የሆኑና በኢስላም ስም ከሃይማኖቱ ውጪ የሆኑ ተግባራትን የሚፈፅሙ ኹራፊዎችን  በዕውቀትና በጽናት ተከላክለዋል። ዛሬም ድረስ "ቦረና ከቶ" ስትነሳ፣ የሳቸው ስም እንደ ጧፍ ይበራል። እሳቸው "ሞተውም የሚኖሩ"፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ኡለማዎችን ያፈሩ የታሪክ ባለውለታ ናቸው። በዋናነት ሃሪማቸዉ የሚታወቀው በነህው ሲሆን በላጋ፣ መንጢቅ፣ አሩድ…በጥቅሉ ፈናፈንና  ተፍሲር ይቀራበታል።

በሺህ የሚቆጠሩ ደረሶች ከሁሉም የኢትዮጰያ ክፍል እየመጡ ተምረዋል። የጎጃም፣ የወረሂመኖ፣ የራያ እና ቃሉ ደረሶች አብላጯውን ቁጥር ይይዛሉ፡፡ ከሀሪማዉ በሺህ የሚቆጠሩ ታላላቅ ኡለማኦች ተመርቀዉ የወጡ ሲሆን በአንድ ግዜ ሃሪማዉ ዉስጥ ከ50-150 ደረሶች ይገኙ ነበር። ሸይኽ አብዱልሃሚድ ከማል (ሸህ ከቶ)  ካፈሯቸዉ አያሌ መሻይኾች መካከል ከታዋቂዎቹ የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያክል፦

ሸይኽ ሙሀመድ ሀሚዲን (ዶ/ር) ፣
ሸይኽ ዑመር ኢድሪስ (ረ)
ሸይኽ ሙሀመድ በሺር (የሀጂ ሙሀመድ ወሌ ወንድም) ረ.
አባባ ሸህ አደም ሙሳ (ደሴ አረብ ገንዳ) ረ.
ሸይኽ ሚስሰባህ ሙ/አሚን፣ (ደርቢቱ ሀሪማ) ረ.
ሸይኽ ሀሰን ሓሚዲን (ደሴ አረብ ገንዳ መስጂድ) ፣
ሸይኽ አብደሠላም አቤ (ሸህ ሆጀሌ መስጅድ)፣
ሸይኽ ሙሣ (ጀርመን መስጅድ)፣
ሸይኽ ሰይድ መህዲ (ዐለም ባንክ)
ሸይኽ ዙበየር አብዱልመጅድ (ረ) ፣
ሸይኽ ያቁት አብዱልመጅድ (ደሴ ሸዋ በር መስጂድ) ፣ ይገኙባታል።

ሀጂ አብዱል ሀሚድ በሺህ የሚቆጠሩ መሻይኾችን እና 9 ልጆችን አፍርተዉ መጋቢት 29/1987 (ዓ.ል) ይህችን አለም ተሰናብተዋል። አላህ መልካም ስራቸዉን ተቀብሎ በእዝነቱ የጀነትን ፀጋዎች ያጎናፅፋቸዉ በህይወት ያሉ የቀድሞ ደረሶቻቸዉን የዛሬ ኡለማኦቻችን በሰላም ፣ በዓፊያ ሀያታቸዉን አርዝሞ የምንጠቀምባቸዉ ያድርገን!

🖊በሺር ሸይኽ ሀሰን

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]

©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
👏6👍1
''የዕውቀት ቅርስ'' ምዕራፍ 2 |ክፍል 18|
👉 https://youtu.be/Ds7-ovRp3Xc
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዑስማን (ረ.ዐ)
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
ደዕዋ ቲቪ || 𝐃𝐚𝐞𝐰𝐚 𝐓𝐕
Photo
أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِ وَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنْتُمْ مُسْلِمُونَ
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢውን መፍራት ፍሩት፤ ሙስሊሞች ሆናችሁ እንጂ አትሙቱ።"
(ሱረቱ ኣሊ-ዒምራን: 102)

فَاسْأَلُوا أَهْلَ الذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
"የማታውቁም ብትኾኑ የዕውቀትን ባለቤቶች ጠይቁ፡፡"
(ሱረቱል ነህል: 43)

አላህ (ዓዘ ወጀል) በሁሉም ጉዳዮች ላይ የማያውቁ ሰዎች ዑለማዎችን መጠየቅ እንዳለባቸው ያዛል። ጥያቄዎች ሲኖሩ እነሱ እንዲጠየቁ ማዘዙ፤ ዑለማዎች ፍትሃዊና ታማኝ መሆናቸውን መመስከሩን እንረዳለን። ይህም አላህ (ዓዘ ወጀል) ባወረደው ወህይ ላይ እንዳመናቸው ያሳያል። እነሱን በመጠየቅ አላዋቂው እውቀትን ያገኛል፣ ግራ የተጋባውም የዲኑን መፍትሄ ይሰማል።
📚 تفسير السعدي (ተፍሲሩ አሰዕዲ)

عن النبي ﷺ قال: "مَنْ يُرِدِ اللَّهُ بِهِ خَيْرًا يُفَقِّهْهُ فِي الدِّينِ"
"አላህ መልካምን ነገር የሻለትን ሰው ሃይማኖቱን ያስገነዝበዋል (ጥልቅ እውቀት ይሰጠዋል)።"
(ቡኻሪና ሙስሊም)

قال ابن القيم رحمه الله: "العِلْمُ حَيَاةُ القُلُوبِ وَنُورُ البَصَائِرِ... وَتَقْوَى اللهِ لَا تَكُونُ إِلَّا بِعِلْمٍ"
"እውቀት የልብ ሕይወትና የዓይን ብርሃን ነው። አላህን መፍራትም ያለ እውቀት አይገኝም።"
(መዳሪጁ ሳሊኪን)

ዕውቀት የዒባዳ መሰረት ነው! አላህን በዕውቀት እንድንገዛውና ጾማችን በሱና እንዲያጌጥ የዘወትር ረቡዕ ዝግጅታችን እነሆ!

ዳዕዋ ቲቪ "ሊፈሩት ዘንድ" በተሰኘውና በፆም ወቅት የሚያጋጥሙ ጉዳዮችን በሚዳስሰው ልዩ የጥያቄና መልስ ፕሮግራም፤ ከታዋቂው ሸይኽ አብደላህ ኢብራሒም ጋር ቆይታ ያደርጋል። ፕሮግራሙን ዘወትር ሰኞ ከቀኑ 10፡30 ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት እና በሁሉም ማህበራዊ ገጾቻችን እንዲከታተሉ በአክብሮት እንጋብዛለን።

ጥያቄዎቻችሁን በቀጥታ ስልክ ቁጥራችን
0932666664 ላይ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ!
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat Frq [11636] | Pol [V] | S.rate [27500]
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ!
👏1
ቀንዲል 5 |ክፍል 18|
👉 https://youtu.be/KLOfe72YHug
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የእሳት ሰዎች
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
1
ቀንዲል ቂርዓት |ክፍል 11| በሸይኽ ሙሀመድ ሓሚዲን(ዶ/ር)
👉 https://youtu.be/4ZNPZtOjmxg
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat 
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]

©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
ደዕዋ ቲቪ || 𝐃𝐚𝐞𝐰𝐚 𝐓𝐕
Photo
ራሚስ ባንክ ከሱና ዩኒቨርሲቲ እና ዳዕዋ ቲቪ ጋር ስትራቴጂካዊ ውይይት አደረገ

•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
-ዳዕዋ ቲቪ የካቲት 30/2018 ዓ.ል| ረመዷን 20/1447 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ             
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

መቀመጫውን በሸገር ሲቲ ያደረገውና በሱና ፋውንዴሽን ስር የሚገኘው ሱና ዩኒቨርሲቲ ከዳዕዋ ቲቪ ጋር በመሆን፣ የራሚስ ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ ተቀብለው አነጋግረዋል። ይህ ጉብኝት በተቋማቱ መካከል ያለውን ተቋማዊ ትውውቅ ለማጠናከርና በቀጣይ በጋራ በሚሰሩባቸው ዘርፎች ላይ መላ ለመምታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

​በጉብኝቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የራሚስ ባንክ የሴንተራል ዲስትሪክት ዳይሬክተር ወይዘሪት ኑሪት ሙሀመድ፣ የሸሪዓ መርህን የሚከተሉ የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎታቸውን ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ በትጋት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል። ሱና ዩኒቨርሲቲ በትምህርትና ስልጠና ዘርፍ እያከናወነ ያለው ተግባር ከሌሎች ተቋማት በላቀ መልኩ ልዩ እንደሆነ የገለጹት ዳይሬክተሯ፣ ባንኩ እንዲህ አይነት ትውልድ ገምቢ ተቋማትን የመደገፍ ጽኑ አላማ እንዳለው አረጋግጠዋል። በቀጣይም በሠራተኞች አገልግሎትና በባንኩ የሼር ክፍሎች ዙሪያ በሰፊው ለመወያየትና አብሮ ለመስራት ቃል ገብተዋል።

​የባንኩ የሴንተራል ዲስትሪክት ቢዝነስ ማናጀር አቶ ከማል ኢብራሒም በበኩላቸው፣ ራሚስ ባንክ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጨባጭ ለውጦችን እያስመዘገበ የሚገኝ ተቋም መሆኑን ጠቅሰው፤ ባንኩ ማህበረሰቡን ለማገልገል ባለው አቅም ሁሉ ከሱና ዩኒቨርሲቲ ጎን እንደሚቆም ገልጸዋል። በተመሳሳይ የቦሌ ጃፋር ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ አሚን ኢብራሒም፣ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በጋራ የመሥራት የቆየ ሕልም እንደነበራቸው አውስተው፤ በተለይም በትምህርትና በስልጠና ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

​የእንግዳ አቀባበልና ማብራሪያ የሰጡት የሱና ፋውንዴሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዶክተር ኑሩ ሙሀመድ፣ ዩኒቨርሲቲው የነብያትን የእውቀት ቅብብሎሽ ተልዕኮ ለመወጣት እስካሁን ከ120 በላይ ታላላቅ መሻይኮችን ማፍራት መቻሉን በዝርዝር አብራርተዋል። ዳዕዋ ቲቪ እውቀት ተኮር የሚዲያ ተቋም መሆኑን የገለጹት ዶክተር ኑሩ፣ በሁለቱ ተቋማት መካከል የተጀመረው ይህ ትውውቅ በቀጣይ የእውቀትና የኢኮኖሚ ክፍተትን ለመሙላት እስከ አምባሳደርነት ደረጃ የሚደርስ ጠንካራ አጋርነት እንደሚፈጥር ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

​ይህ የባንክና የትምህርት ተቋማት ጥምረት፣ በማህበረሰቡ ዘንድ ያለውን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚና የእውቀት ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ተብሎ ይጠበቃል።

በኢብራሒም ደሊል
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
#DaewaTV #RamisBank #SunnaUniversity #ShegerCity #IslamicFinance #Education #Ethiopia #DaewaNews #ራሚስ_ባንክ #ሱና_ዩኒቨርሲቲ #ዳዕዋ_ቲቪ
👍3
ፊሪሀቢል አያህ (ክፍል 18) |በሸይኽ አብዱሰላም አንዋር|

👉 https://youtu.be/nQX3x93euNQ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat 
Frq [11636]  Pol [v]  S.rate [27500]

©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዓሊይ(ረዐ)
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
📡 Nilesat
Frq [11636] Pol [v] S.rate [27500]
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ