Ministry of Education Ethiopia – Telegram
Ministry of Education Ethiopia
142K subscribers
3.72K photos
33 videos
6 files
531 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በክብርት ቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በተገነባ የት/ቤት ምርቃት ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት
------------------------- // -------------------------

በክብርት ቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በሱርማ ወረዳ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የተገነባ ትምህርት ቤት ርክክብ ሥነሥርዓት ላይ ስንገኝ በአካባቢው የትምህርት መስክ እድገት ረገድ ዐቢይ ተግባር በመሆኑ ደስታ ይሰማናል።

ትምህርት ቤቱ በቀዳሚነት ከአካባቢው ለሚመጡ ተማሪዎች የአዳሪ ትምህርት ቤት በመሆን ያገለግላል።

ግቢው ማደሪያ ክፍሎችን፣ መማሪያ ክፍሎችን፣ በፀሃይ ኃይል የሚሰሩ በቂ ኮምፒውተሮች ያሉት የኮምፒውተር ላብራቶሪ፣ የንፁህ ውሃ ጉድጓድ፣ የተሟላ የምግብ ማብሰያ ክፍል፣ ቤተ መፃሕፍት እና የአስተዳደር ሕንፃን አካትቶ የተገነባ ነው።

ይኽ ምሉዕነት ያለው የትምህርት ከባቢ የተማሪዎችን አካዳሚያዊ ልህቀት እና ደኅንነት ለማረጋገጥ ታስቦበት የተሰራ፣ ለወጣት ተማሪ ልጆቻችን ሁሉን አቀፍ እድገት አዲስ እድል የፈጠረ ተቋም ነው።
በትምህርት ዙሪያ በምንም መልኩ በድሃና በሀብታም መካከል ልዩነት እንዳይኖር በሁሉም አካባቢዎች ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች እየተሰሩ መሆኑ ተገለፀ ።

በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ የተገነባው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቋል።
-------------------------// ----------------------

(ጥር 09/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ከሰዎች ለሰዎች ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ያስገነባው የሳውላ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ በህ/ተ/ም/ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትሩ ተስፋዬ ቤልጅጌ(ዶ/ር) እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ መርቀውታል።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንደ ሀገር በትምህርት ዙሪያ በድሃና ሀብታም መካከል በምንም መልኩ ልዩነት መኖር የለበትም በሚል የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል ዜጎች ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

በዚህም ተማሪዎች ትምህርት ቤቶቻቸውን ወደውና ፈልገው እንዲመጡ የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል በትምህርት ለትውልድ ህዝባዊ ንቅናቄ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1D8TwWBmSb/
መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች በቴክኖሎጂ የታገዘ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እንዲከታተሉ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
--------------------------- // ----------------------------

‎(ጥር 10/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኔስኮ አለም አቀፍ የአቅም ግንባታ ተቋም ለአፍሪካ (UNESCO IICBA) እና ከጃፓን መንግሥት ጋር በመተባበር በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግር በተጎዱ አካባቢዎች የሚሰሩ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮችን ሙያዊ አቅም ለማሻሻል በተዘጋጁ ኮርሶች የቫሊዴሽን አውደጥናት አካሂዷል።

‎የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ዴስክ ሃላፊ ወ/ሮ አሰገድ ምሬሳ መድረኩን ሲከፍቱ እንደገለጹት አጫጭር ሙያዊ ስልጠናዎችን ዲጂታላይዝድ በማድረግ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች በያሉበት ስልጠና እንዲወስዱ የሚያስችሉ ተግባራት እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

‎ትምህርት ሚኒስቴር በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት ለመምህራንና ለት/ቤት አመራሮች አጫጭር የስራ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ቢሆንም ከመምህራንና ከትምህርት ቤቶች ቁጥርና ብዛት አንጻር የሙያ ማሻሻያ ስልጠናዎችን መምህራኑ ባሉባቸው ትምህርት ቤቶች መስጠት ማስፈለጉን ወ/ሮ አሰገድ ገልጸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17z34HPtpt/