Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የሲዳማ የሽምግልና ሥርዓት ሕዝቡ በመተማመን እንዲኖር ማስቻሉን የአገር ሽማግሌዎች ተናገሩ
****
(ኢ ፕ ድ)
የሲዳማ ክልል አቦ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት ብይን ከመስጠት ባለፈ የእርቅ ሥርዓት የሚከናወንበት ማኅበረሰቡ በይቅርታና በመተማመን አብሮ እንዲኖር በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የአካባቢው ሽማግሌዎች ተናገሩ። ሥርዓቱ ሕጋዊ እውቅና አግኝቶ ከመደበኛው ፍርድ ቤት ጎን ለጎን አገልግሎት እንደሚሰጥም ተመልክቷል።

በወንሾ ወረዳ አካባቢ ሽማግሌ አቶ አለሙ ዮኔ፤ ከትውልድ ትውልድ በመሸጋገር እየተከናወነ የሚገኘው አቦ ወንሾ ባህላዊ ዳኝነት ለሲዳሞዎች ትልቅ እሴት እንደሆነ ነው የገለጹት።

ሥርዓቱ ለአገር የሚጠቅም፣ ወቅታዊ ችግሮችን መፍታት እንደሚያስችል በመጠቆምም፤ ሲዳሞዎች በባህላቸው አስከሬን አስቀምጠው ይቅር የሚባባሉበት ‹‹አፍን›› ሥርዓት መረጋጋትን በመፍጠር፣ ሰላም እንዲሰፍን በማድረግ ለግጭት የሚያነሳሱ ጉዳዮች እንዲረግቡ ጉልህ ሚና እንደነበረው አመልክተዋል።

አፍን ቂም በቀልን በመተው እርቅ የሚፈጸምበት ሥርዓት እንደሆነ የጠቆሙት የአገር ሽማግሌው፤ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት ቢስፋፋ ኖሮ እርስ በእርስ ግጭት አይኖርም፣ ጦርነት ውስጥም አይገባም፣ የታለፈው አይነት ችግርም አይደርስም ነበር ብለዋል።

አሁን አሁን የሕይወትና የንብረት ውድመት የተባባሰው የእርቅ ሥርዓት ባለመስፋፋቱ ነው። እሴቱን መጠበቅም ማስፋፋትም ይገባል ብለዋል። በሁሉም አካባቢ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሥርዓቱን..
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85736
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio
የቱሉ ዲምቱ-ቃሊቲ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት እስከ ሰኔ 30 ይጠናቀቃል
👉 ለግንባታው ማጠናቀቂያ መንግሥት 2 ቢሊዮን ብር መድቧል
*****
(ኢ ፕ ድ)
በነዋሪዎች ዕለታዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና ሲያሳድር የቆየውና የግንባታ ሂደቱ የተጓተተው የቱሉ ዲምቱ-ቃሊቲ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በተያዘው በጀት ዓመት ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ።

ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ መንግሥት ሁለት ቢሊዮን ብር መድቦ ሥራው እየተከናወነ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ እያሱ ሰለሞን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የቱሉ ዲምቱ-ቃሊቲ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 11 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 50 ሜትር የጐን ስፋት ያለው ሲሆን ግንባታው በ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ወጪ እየተከናወነ ይገኛል።

መንገዱ ከደቡብ፣ ከምስራቅና ከሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ አቅጣጫና ከጅቡቲ የሚመጡ ተሽከርካሪዎች የመውጫና የመግቢያ መስመር በመሆኑ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የጎላ ነው ያሉት አቶ እያሱ፤ እስካሁን ባለው ሂደት የመንገዱ 55 በመቶ የሚሆነው ግንባታ ተጠናቋል፤በተለይ ከፍተኛ ጊዜና በጀት...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85719
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio
ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው
***
(ኢ ፕ ድ)
ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ በያዝነው ወር መጨረሻ ላይ በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ የኢኖቬሽንና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም አስታወቀ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ኃላፊ ዶክተር አብዮት ባዩ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ጉባኤው በኢትዮጵያ መካሄዱ የአፍሪካውያን የኢንተርኔት አጠቃቀምና የተደራሽነት ችግር እንዲሁም የባህል ወረራ ላይ በመወያየት መፍትሔ ለማበጀት ዕድል የሚፈጥር ነው።

እንደ ዶክተር አብዮት ገለፃ፣ ኢንተርኔት በዓለም ላይ የብዙ ኔትዎርኮች ጥርቅም በመሆኑ በባለቤትነት የሚያስተዳድረው አካል የለም። ስለዚህ በጉባኤው የአፍሪካውያን የኢንተርኔት አጠቃቀምና የተደራሽነት ችግር እንዲሁም የባህል ወረራን ለመከላከል የሚያስችል ውይይት ይደረጋል።

በዚህም በእያንዳንዱ የሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ለውጥ እያመጣና በሰዎች ላይ የሚያመጣውም ተጽዕኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ችግሩን ለመቅረፍ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85715
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio
"የሰላም ስምምነቱ የኢትዮጵያን ቁርጠኝነትና የአፍሪካን የመፍትሔ ምንጭነት ችሎታ ያመላከተ ነው"
-አቶ አባተ ኪሾ የቀድሞ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
*****
(ኢ ፕ ድ)
በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት መካከል የተካሄደው የሰላም ስምምነት የኢትዮጵያን ቁርጠኝነትና የአፍሪካን መፍትሔ አምጭነት ችሎታ ያመላከተ ነው ሲሉ የቀድሞው የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባተ ኪሾ አስታወቁ።

በሕዝብ ልብ ውስጥ የጦርነቱ መቆም የፈጠረው የእፎይታ ስሜት በፖለቲከኞቹና በአክቲቪስቶቹ አካባቢም ቢፈጠር ሰላሙን በአግባቡ ማጣጣም ይቻላል ብለዋል።

አቶ አባተ ከኢፕድ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ የጥይት ድምጽ እንዳይሰማና ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሚያደርግ ስምምነት መደረጉም ትልቅ ስኬት ነው፡፡ ይኸው በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ ላይ በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት መካከል የተካሄደው የሰላም ስምምነት የኢትዮጵያውያኑን ቁርጠኝነትና ጽኑ አቋም ያሳየ ነው፡፡ አፍሪካ ለራሷ ችግር በራሷ ልጆች መፍትሔ ማምጣት እንደምትችልም ያመላከተ ሲሆን፣ ሌሎቹ የአፍሪካ አገራትም በአህጉሪቱ ላይ እምነት እንዲያሳድሩ የሚያደርግ ነው፡፡

ይህን የአህጉሪቷን መንገድ ሌሎች አገሮችም ሊያከብሩላት ይገባል ያሉት አቶ አባተ፣ አፍሪካውያንም ችግር ቢፈጠርባቸው ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ እንዲሰባሰቡ በማድረግ ረገድ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85710
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በነገው እለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪይ ይሰጣሉ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በነገው እለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ ነገ ህዳር 06 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን እንደሚያካሂድ የምክር ቤቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ለኢዜአ ገልጿል፡፡
በመደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ አመላክቷል።
በዚህም ምክር ቤቱ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል፡፡
በዕለቱ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio
"በደም የተከበረውን የአገራችን ነፃነት በላባችን ለማፅናት አገራዊ አጀንዳ ተቀርፆ እየተተገበረ ይገኛል"
-ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ
***************
(ኢ ፕ ድ)
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሌማት ትሩፋት ማስተዋወቂያ መርሐግብር የከተማና የክፍለ ከተማው ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች ከ2000 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል።
መርሀግብሩ ያወያዩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ የሀገር ግንባታና ሉዓላዊነት ማፅናት የሚቻለው በደም ብቻ ሳይሆን ዘላቂ የኢኮኖሚ አቅም ያላት አገር መፍጠር ሲቻል ነው ብለዋል።
እስካሁን በአረንጓዴ አሻራና በሌሎች ፕሮጀክቶች ያሳካናቸው እንዳሉ ሁሉ እንደአቃቂ ቃሊቲ መንገዶች ያሉ በወቅቱ ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ በአዲስ መልኩ ወደ ስራ መገባቱን አስታውሰዋል።
በመሆኑም በክፍለ ከተማው በሌማት ትሩፋት አጀንዳ የሚፈጸሙ የዶሮ እርባታ፣ የወተትና ወተት ውጤቶች፣ የጓሮ አትክልትን ጨምሮ ለሌማት ትሩፋት ተግባራዊነት ሁሉም ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
የሰላም ስምምነቱም የኢትዮጵያን አሸናፊነት ያረጋገጠ መሆኑን መረዳትና ለአገር አንድነትና ተከባብሮ መኖር ስለሠላምና ልማት በጋራ የመሥራት አጀንዳችን የጋራ መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አበራ ብሩ፣ ኢትዮጵያውያን አመጋገባችንን መቀየር የሚያስችሉ የዶሮ፣ የእንቁላል፣ የወተት ተዋፅኦና ከአዝዕርት ውጤቶች ጋር በማድረግ ምግባችንን የማሻሻል ተልዕኮ መወሰድ አለበት ብለዋል።
እያንዳንዱ አባወራ እና እማወራ ቢያንስ አምስት አምስት ዶሮ ማርባት ይጠበቅበታል። ማህበረሰቡም ለአከባቢውን ሰላም ዘብ በመቆምና አከባቢውን ከማልማት ጀምርሮ የድርሻውን በመወጣት ከመንግስት ጋር በቀጣይነት ሊሰራ እንደሚገባ አመላክተዋል።
በኃይሉ አበራ
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio
ከ25 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በነገው እለት ለባለእድለኞች በዕጣ ይተላለፋሉ
👉 300 ባለሶስት መኝታ ቤቶች ለነባርና ለ2005 ተመዝጋቢዎች በእጣ ይተላለፋሉ
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ያስገነባቸው 25 ሺ 791 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በነገው እለት ለባለእድለኞች በዕጣ ይተላለፋሉ።
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽንና የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ባለፈው አመት ሀምሌ ወር ላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ቢወጣም በተፈጠረው ችግር እጣው መሰረዙ ይታወቃል።
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ያስሚን ወሃቢረቢ እንደገለጹት፣ ባለፈው የተከሰተው ችግር ተለይቶ በጥንቃቄ ሲሰራ ቆይቶ በተዘረጋው አዲስ ስርዓት ታግዞ በነገው እለት 25 ሺ 791 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ይወጣባቸዋል።
መስፈርቱን ያሟሉ የ20/80 የ1997 ተመዝጋቢዎችና ሶስተኛ ዙር የ40/60 ቆጣቢዎች በድምሩ146 ሺ 892 ቆጣቢዎች እጣ ውስጥ እንደሚገቡም ተገልጿል።
የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት በበኩላቸው በእጣው ብቁ የሚሆኑት የ20/80 (ስቱዲዮ፣ ባለ 1 እና ባለ 2) ነባር ተመዝጋቢዎች (1997) በመመሪያው መሠረት ዝቅተኛውን የ60 ወራት ቁጠባ መጠን እንዲሁም የባለ 3 መኝታ ነባርና አዲስ ተመዝጋቢዎች (2005) ዝቅተኛውን የ84 ወራት ቁጠባ መጠን ያሟሉ ናቸው ብለዋል።
እንዲሁም የ40/60 ተመዝጋቢዎች ከ40% እና ከዚያ በላይ ቁጠባ ያላቸው ለእጣ ውድድር ብቁ የሚሆኑት እስከ የካቲት 21/2014 ዓ.ም ድረስ የቆጠቡ ናቸው ብለዋል።
ሀምሌ ወር ላይ ወጥቶ በነበረውና በተሠረዘው እጣ ሳይካተት ቀርተው ጥያቄ ተነስቶበት የቆየው የባለ ሶስት መኝታ ቤቶች ጉዳይንም በተመለከተ እልባት ተስጥቷል።
በዚህም መሠረት 300 ባለሶስት መኝታ ቤቶች ለነብልርና ለ2005 ተመዝጋቢዎች በእጣ እንደሚተላለፉ ተገልጿል።
እንደ ቢሮ ሃላፊዋ ማብራሪያ፤ 18 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ለቤቶች ግንባታ፣ 2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ለመሰረተ ልማት በድምሩ 21 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ለግንባታ ወጭ ተደርጓል።
በሞገስ ተስፋ
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthi
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያመጠቀቻት ሳተላይት ተልዕኮዋን አሳክታለች
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያመጠቀቻት ETRSS-1 የመሬት ምልከታ ሳተላይት ተልዕኮዋን በአግባቡ ማሳካት መቻሏን የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ሳተላይቷ ከታቀደላት ጊዜ በላይ አገልግሎት እየሰጠች ነው።
የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ ኢትዮጵያ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ማምጠቅ የቻለች ሲሆን፤ ተጠቃሽ የሆነችው ETRSS-1 የመሬት ምልከታ ሳተላይት ከመጠቀችበት ታኅሣሥ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተልዕኮዋን በአግባቡ ማሳካት ችላለች። ሳተላይቷ በዋናነት የመሬት ምልከታ ሥራዎችን ስትሠራ ቆይታለች።
እንደ አቶ አብዲሳ ገለጻ፤ መጀመሪያ ዲዛይን ሲደረግ ሳተላይቷ ለሁለት ዓመት ተኩል እንደምታገለግል ተደርጎ የታቀደ ሲሆን፤ አሁን ላይ ከታቀደላት ጊዜ በላይ ተጨማሪ አምስት ወራትን አገልግላለች። ከመጠቀች አሁን ላይ ወደ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85784
ተሰርዞ የነበረው የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ሥነሥርዓት ዛሬ ይከናወናል
👉 146 ሺ 892 ቆጣቢዎች ዕጣ ውስጥ ተካተዋል
*******
(ኢ ፕ ድ)
ባጋጠመ ችግር ምክንያት ተሰርዞ የነበረው የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ሥነሥርዓት ዛሬ እንደሚከናወን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ አስታወቀ። 146 ሺ 892 ቆጣቢዎች ዕጣ ውስጥ ተካተዋል ተብሏል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ ያስሚን ወሃቢረቢ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የከተማ አስተዳደሩ የ20/80 14ኛ ዙር እና የ40/60 3ኛ ዙር የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ አወጣጥ ሥነሥርዓት በዛሬው ዕለት ከስምንት ሰዓት ጀምሮ ይከናወናል።

ቀደም ሲል ሐምሌ 1/2014 ዓ.ም. የ20/80 14ኛ ዙርና የ40/60 3ኛ ዙር የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት በይፋ መካሔዱን አስታውሰው፤ ባጋጠመ የወንጀል ጥቆማ መሠረት በተደረገ ኦዲት ዕጣው ሙሉ ለሙሉ እንዲሰረዝ ተደርጎ በጉዳዩ የተጠረጠሩ አካላትም በሕግ አግባብ እንዲጠየቁ መደረጉን አንስተዋል።

ቢሮ ኃላፊዋ በመግለጫቸው፤ በጉጉት ሲጠባበቅ የነበረውን ኅብረተሰብ እጅግ ያሳዘነ ቢሆንም የተሠራው ሕገወጥ ተግባር ተቀባይነት የሌለውና የብዙኃኑን ጥቅም በእጅጉ የሚጎዳ ስለነበር ዕጣው መሠረዙ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85785
"በጦርነቱ የቆሰሉ አዕምሮዎች መታከም አለባቸው "- አቶ ኤርሚያስ ኪሮስ የስነልቦና ባለሞያ
******
(ኢ ፕ ድ)
ጦርነቱ የብዙ ሰዎችን አዕምሮ የጎዳ እና አጠቃላይ ሕይወታቸውን ያዛባ በመሆኑ በጦርነቱ የቆሰሉ የወገኖቻችን አዕምሮዎች መታከም እንዳለባቸው የስነልቦና ባለሙያው አቶ ኤርሚያስ ኪሮስ ተናገሩ።

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነቱ በተካሄደባቸው አካባቢዎች ተገኝተው የስነልቦና ህክምና ሲሰጡ የቆዩት የስነልቦና ባለሙያው አቶ ኤርሚያስ ኪሮስ ለኢፕድ እንደተናገሩት፤ ጦርነቱ ብዙዎች የመኖር ትርጉም እንዲጠፋባቸው አድርጓል። ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ጤናማ አስተሳሰባቸውን አጥተዋል። አሁንም በመጥፎ ትዝታ ውስጥ ናቸው። ብዙ ሰዎች ዓይናቸውን ሲከድኑ አስከሬን ሊመለከቱ ይችላሉ። ለመተኛት ሲያስቡ የሚረብሻቸው ድምፅ ይኖራል። ዛሬም ያኔ ከሰሙት ድምፅ ማምለጥ አልቻሉም።

እንደ አቶ ኤርሚስ ገለጻ፤ ጦርነቱ ሰዎች ራሳቸውን እና ማህበረሰቡን የሚመለከቱበትን ዕይታ ጎድቷል። የስነልቦና ተፅዕኖ አስከትሎ አልፏል፤ የአዕምሮ ቁስል አስከትሏል፤ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ እና የተደፈሩ ሴቶች ቤተሰባቸውን ብቻ ሳይሆን ራሳቸውንም ጭምር ያጡ በመሆናቸው፤ መጀመሪያ ጦርነቱ የአዕምሮ ቁስል ፈጥሮ ማለፉን በማመን እና በመቀበል በዘመቻ ከዚህ ቁስል የሚድኑበት መንገድ ሊፈጠር ይገባል።

አቶ ኤርሚያስ እንደገለጹት፤ የዓለም ተሞክሮም ሆነ የጥናት ውጤቶች እንደሚሳዩት ብዙ ጊዜ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85783