Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የአፍሪካ አገሮች በሙሉ ለኢትዮጵያ ስንዴ የገበያ መዳረሻ ናቸው
******************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ በመስኖ ለምታለማው የስንዴ ምርት ግብጽን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች በሙሉ የገበያ መዳረሻ ናቸው ሲሉ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ አስታወቁ።
ዶክተር ማንደፍሮ ለኢፕድ እንዳስታወቁት፤ ኢትዮጵያ ስንዴ በማምረቱም ሆነ በገበያው ብዙ ዕድሎች ስላሏት የአፍሪካ ሀገሮች የገበያዋ መዳረሻ ይሆናሉ።
በአሁን ወቅት የሌላውን አገር በመተው አፍሪካን ብቻ ብንወስድ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99904
በኢትዮጵያ ከሚታረሰው መሬት 43 ከመቶ በአሲዳማነት እየተጠቃ ነው
👉 በቀጣዩ ዓመት የአፈር ለምነት ሀገራዊ ንቅናቄ ይካሄዳል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ አሁን ከሚታረሰው መሬት 43 ከመቶው (ሰባት ሚሊዮን ሄክታር የሚጠጋ መሬት) በአሲዳማነት እየተጠቃ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። አፈርን ከአሲዳማነት ለመታደግ በቀጣዩ ዓመት የአፈር ለምነት ሀገራዊ ንቅናቄ እንደሚካሄድም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ የኢፌዴሪ የኮሙኒኬሽን አገልግሎት እና የፌዴራልና የክልል መገናኛ ብዙኃን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99924
በትግራይ ክልል የማዕድን ልማቱን ወደሥራ ለማስገባት እየተሠራ ነው
****************
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ሥራቸው ተስተጓጉሎ የነበረው በማዕድን ልማት ላይ የተሠማሩ ኩባንያዎች ከሰላሙ በኋላ ወደ ልማቱ ለመመለስ በእንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ሰላም ከተፈጠረ በኋላ በትግራይ ክልል በማዕድን ልማት እየተደረገ ስላለው እንቅስቃሴ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በክልሉ በማዕድን ፍለጋ የተሠማሩና ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99915
200 ሰዓታትን የፈጀው አንፀባራቂው የሙሽራ ቀሚስ ⌚️

እጅግ ውድ የሆኑ የሰርግ ልብሶችን ዲዛይን በማድረግ በምትታወቀው ጣልያናዊቷ ዲዛይነር ሚሼላ ፌሪኢሮ የተሰራው የሙሽራ ቀሚስ በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ሰፍሯል።

ከ50 ሺህ በላይ በሆኑ አንፀባራቂ ትንንሽ ጌጦች (ክሪስታል) የተሰራውን ይሄንን የሙሽራ ቀሚሱን ሰርቶ ለማጠናቀቅ 200 የስራ ሰዓታት መፍጀቱ ተገልጿል።

ዲዛይነሯ ሚሼላ ፌሪኢሮ የተለያዩ የሰርግ ቀሚሶችን ዲዛይን የምታደርግ እና የምትሰራ ስመ ጥር ዲዛይነር ስትሆን በጣም ውድ የተባሉ የሰርግ ቀሚሶችንም በመስራት ትታወቃለች፡፡

ዲዛይነሯ የሰራችው ልብስ እያንዳንዱ ክፍል በእነዚህ አንፀባራቂ ክሪስታሎች( ጌጣጌጦች) የተሰራ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ተብሏል።

ይህ 200 ሰዓታትን የፈጀው የሙሽራ ቀሚስ ከመሰራቱ በፊት በማቀድ እና ዲዛይን በማውጣት ደረጃ 4 ወር ፈጅቷል ወደስራ ከተገባ በኋላም ቀሚሱን ሰፍቶ ለማጠናቀቅ ከእውቋ ዲዛይነር በተጨማሪ የሌሎችን እገዛ ግድ ብሎ ነበር፡፡

‹‹ምንም እንኳን ትልቅ እና ፈታኝ ቢሆንም፤ ከአጠገባችሁ የምትወዱት ሰው ካለ እያንዳንዱ ህልማችሁ እውነት መሆኑ አይቀርም›› ስትልም ነው ስሜቷነ የገለጸችወ።

በአለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ከዚህ ቀደም እንዲህ ያለ ሪከርድ እ.አ.አ በ 2011 በቱርካዊቷ ዲዛይነር የተመዘገበ ሲሆን፤ እሱም በ45 ሺህ 24 ጌጦች የተሰራ ቀሚስ ነበር።

ይህ የጣልያናዊቷ የእጅ ውጤት የሆነው የሙሽራ ቀሚስ ግን በ50 ሺህ 890 አንፀባራቂ ጌጦች የተሰራ በመሆን ሪከርዱን ሊሰብር ችሏል።

በሰሚራ በርሄ
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የሚኒስትሮች የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ 2ኛውን የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳን ዛሬ ተመልክቷል። በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀጣይ ተግባር አቅጣጫዎችን አስቀምጠው የ100 ቀን ግምገማውን ዛሬ ማጠናቀቁን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈትቤት አስታውቋል።
የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ ለኢትዮጵያ የስንዴ ምርት የገበያ መዳረሻዎችን አስመልክተው ይናገራሉ‼️

👉 ኢትዮጵያ በመስኖ ለምታለማው የስንዴ ምርት ግብጽን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ አገራት የገበያ መዳረሻ ናቸው፣

👉 ኢትዮጵያ ስንዴ በማምረቱም ሆነ በገበያው ብዙ ዕድሎች ስላሏት የአፍሪካ ሀገሮች የገበያዋ መዳረሻ ይሆናሉ፤

👉 53ቱ የአፍሪካ አገራት ለኢትዮጵያ የስንዴ ምርት የገበያ መዳረሻ ናቸው፣

👉 ኢትዮጵያ ለስንዴ ተስማሚ የሆነ አየር ንብረት አላት፤ ሀገሪቱ በክረምትም ሆነ በበጋ ማምረት ትችላለች፣

👉 በሌላ አገር የሚመረተው አንዴ ነው፤ በበረዶ የተሸፈነ ስለሚሆን በረዶው እስከሚያልፍ ይጠብቃሉ፣ ትልልቅ አምራች የሚባሉት እንደ ራሺያ፣ ዩክሬን፣ ጀርመን የመሳሰሉት በዚህ የታጠሩ ናቸው፣

👉 የሌላውን አገር ትተን አፍሪካን ብቻ ብንመለከት ከእኛ የተሻለ ስንዴ ምርት ያላት ግብጽ ብቻ ናት፣ ኢትዮጵያ ወደ 82 ሚሊዮን ኩንታል እንናመርታለን፤ ግብጽ ወደ 100 ሚሊዮን ታመርታለች፣

👉 ትኩረት ሰጥን በፕሮግራም ደረጃ የያዝናቸው የገቢ ምንጮች አሉ፤ ስንዴ፣ ሩዝ፣ የአኩሪ አተር ሰብሎች ይጠቀሳሉ፣

👉 አኩሪ አተር ወደ ኢንዱስትሪ ይሄዳል፤ ዘይት ይወጣዋል፤ ተረፈ ምርቱ ለዶሮ ወይም ለከብቶች ምግብ ይሆናል፣

👉 በመስክ ሥራ ከአርሶ አደሩ ጋር አብሮ ይሰለፋል፤ ሥራውን በተግባር እየሠራም ያሳያል፤ ወደ 3 ነጥብ 2 ሚሊዮን አካባቢ የሚሆን የአርሶ አደር ቤተሰቦች ይዟል፣

👉 እነዚህ አርሶ አደሮች ውስጥ 85 ሺህ ኩታ ገጠም እርሻዎች አሏቸው፣

👉 ለአብነት ያህል ሲዳማ ክልል ውስጥ ለአቡካዶ እርሻ በኩታ ገጠም የተደራጁ አርሶ አደሮች አሉ፤ እነሱን አቡካዶን ለግብዓትነት ከሚፈልጉ ኢንዱስትሪዎች ጋር ትስስር ፈጥረዋል፣

👉 አንድ ኩታ ገጠም እርሻ ቢያንስ 30 ሔክታር ይሆናል፤ ለኩታ ገጠም እርሻዎች 10 የመካናይዜሽን ማዕከላት ተቋቁመዋል፣

👉 የተለያዩ የእርሻ ማሸነሪ አንቀሳቃሾችን በኦፕሬተርነት ያሰለጥናል፣

👉 የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስትዩትነት በፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ጥናት የማድረግ ኃላፊነት ተጨምሮለታል፣

የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ ከኢፕድ ጋር ያደረጉትን ሙሉ ቃለምልልሱን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ  https://www.press.et/?p=99932
ጽንፈኝነት ምንጩ፣ ጉዳቱ እና አደጋው
*************
(ኢ ፕ ድ)

አሁን አሁን ጽንፈኝነት በአገራችን ከሃሳብ አልፎ ጉዳቱ በተግባር እየታየ መምጣቱን ብዙዎች ይስማማሉ።ጽንፈኝነት በብሔር ወይም በሃይማኖት ዋሻ በመደበቅ የራሳቸውን ፖለቲካዊ ፍላጎት ለማሳካት የሚፈልጉ ኃይሎች መሰባሰቢያም ነው።

ጽንፈኝነት ለሌላው አመለካከት ቦታ የማይሰጥ በመሆኑ አብሮ የመኖርን እና በመነጋገር ችግሮችን ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99975