Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በአዲስ አበባ ባጋጠመ የእሳት አደጋ 21 ሱቆች ወደሙ
******************
(ኢ ፕ ድ)

በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ሰፈራ አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ 21 የንግድ ሱቆች መቃጠላቸውን የእሳትና አደጋ ስጋትሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

አደጋው የደረሰው ከጠዋቱ 1 ሰዓት ከ50 ደቂቃ መሆኑን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ገልጸዋል፡፡

በአደጋው የተቃጠሉት ሱቆችም የተለያየ የንግድ ሥራ የሚከናወባቸው መሆናውን ተናግረዋል፡፡

የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር 11 የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሁለት የውሀ ቦቴዎች ከ70 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ጋር መሠማራታቸውን ጠቁመዋል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

የንግድ ቤቶቹ የተገነቡበት ቁሳቁስና ቤቶቹ ተጠጋግተው መሰራታቸው እንዲሁም ለአደጋ ምክንያት የሚሆኑ አሰራሮች መኖራቸው የእሳት አደጋው በቀላሉ እንዲስፋፋ ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

አደጋው ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር መቻሉንና ሥራውም 3 ሰዓት መውሰዱን አስገንዝበዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዓመቱ 200 አውሮፕላን አብራሪዎችን አሰልጥኖ ወደ ስራ ለማስገባት መዘጋጀቱን ገለጸ
*********************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ በየዓመቱ 200 አውሮፕላን አብራሪዎችን አሰልጥኖ ወደ ስራ ለማስገባት መዘጋጀቱን ገልጿል።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው እንደገለጹት በአየር ትራንስፖርቱ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠል ሰፊ የመሰረተ ልማት እና ብቁ የሰው ኃይል ማፍራት ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል ብለዋል።

ብዙ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች በኮቪድ ምክንያት ሰራተኞቻቸውን በመቀነሳቸውና ገበያው ላይ አዳዲስ የሰው ኃይል ባለማግኘታቸው እየተፈተኑ መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚው አንስተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ነባሮቹን ባለመቀነስና አዳዲስ ባለሙያዎችን በማፍራት በስኬቱ ቀጥሏል ነው ያሉት።

በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2035 የረጅም ጊዜ ዕቅዱ የያዘውን ራዕይ ለማሳካት በኢትዮጵያ አቪየሽን ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ 1 ሺህ 100 ተማሪዎች በተለያዩ ሙያዎች እየሰለጠኑ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህንን ዕቅዱን በማስፋትም በቀጣይ ዓመት 1 ሺህ 600 ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን መዘጋጀቱን ነው የጠቀሱት።

አየር መንገዱ ዘንድሮ ከ170 በላይ አውሮፕላን አብራሪዎችን አስመርቆ ወደ ስራ ማስገባቱን ጠቅሰው፤ ይህም በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው ነው ብለዋል።

ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ በየዓመቱ 200 አውሮፕላን አብራሪዎችን ለማፍራት ዕቅድ መያዙንም ነው ዋና ስራ አስፈጻሚው ጨምረው ያስታወቁት።

ለዚህም ጥር ወር ላይ የተመረቀው የሀዋሳ የአውሮፕላን አብራሪዎች ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አንስተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተቋማዊ ስኬቱ ጠንካራ የስራ ባህል ግንባታን ከሰራተኞች ጥቅም ጋር አስተሳስሮ እየተጓዘ መሆኑን ነው የተናገሩት።

በዚህም የ17 ሺህ ቋሚ ሰራተኞቹን የማስጠበቅ ስራ አጠናክሮ መቀጠሉን ዋና ስራ አስፈጻሚው አንስተዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ በዚህም ሰራተኞች በራሳቸው ወጪ መኖረያ ቤት እንዲሰሩ ሲያስተባብር መቆየቱን ለአብነት ጠቅሰው፤ በመጀመሪያው ዙር ለ5 ሺህ ሰራተኞች የመኖሪያ ቤት የሚሆኑ ባለ 20 ወለል ህንጻዎች ግንባታ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በቅርቡ ይጀመራል ብለዋል።
ባለፉት 11 ወራት ከ3.5 ቢሊዬን ብር በላይ ገቢ መሠብሰቡን የክልል ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ
*******************
(ኢ ፕ ድ)

በበጀት ዓመቱ ባለፉት አስራ አንድ ወራት ከ3.5 ቢሊዬን ብር በላይ መሠብሰብ መቻሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀደቀ ከፍታው፣ በጀት ዓመት ከ4.1 ቢሊዬን ብር በላይ ገቢ በመሠብሠብ የገቢ አቅምን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል። ባለፉት አስራ አንድ ወራት ከ3.5 ቢሊዬን ብር በላይ መሠብሰብ ተችሏል። አሁን ባለው ሁኔታ እቅዱን ሙሉ በሙሉ ማሳካት የሚቻልበት ሁኔታ ነው ያለው ብለዋል።

የደረጃ ሐ ግብር ከፍዮች የዕለት ገቢ ግመታ ስራ በክልሉ አመራሮች እየተመራ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የግመታ ስራው ሁሉን አሳታፊና በዕውቀት የታገዘ እንዲሆን በክልሉ በሶስት ማዕከል በቦንጋ በሚዛንና በተርጫ ማዕከል ከ350 በላይ ለሚሆኑ ለገማችና አጣሪ ኮሚቴዎችና የአወሳሰን ባለሙያዎች ጭምር ስልጠና መሠጠቱን አብራርተዋል።
ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ በቤቱ አከማችቶ የተገኘው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለፀ
******
(ኢ ፕ ድ)

በአዲስ አበባ ከተማ ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ በቤቱ አከማችቶ የተገኘው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ገለፀ።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር የዋለው ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ አከማችቶ ማስቀመጡን ኅብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት በሰጠው ጥቆማ መሠረት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር በመኖሪያ ቤቱ በተደረገው ፍተሻ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል።

የፀጥታ አካላቱ በተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት ባደረጉት ፍተሻ 64 የተለያዩ ዓይነት ሽጉጦች እና 587 የሽጉጥና የክላሽንኮቭ ጥይቶች እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ በመጣስ ከመቶ ሺህ ብር በላይ በቤቱ ውስጥ 197 ሺህ 400 ብር አስቀምጦ በመገኘቱ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራው እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ከተጠርጣሪው ጋር በሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር ግንኙነት ፈጥሮ ሲሰራ እንደነበር ኅብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ መሠረት ፖሊስ በግለሰቡ ላይ ባደረገው ብርቱ ክትትል በቦሌ ክፍለ ከተማ ጎሮ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተጠርጣሪውን ከአንድ ማካሮቭ ሽጉጥ እና ከተመሳሳይ 20 ጥይቶች ጋር በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራው እየተጣራ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል።

ተከማችቶ የተገኘው ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ በፀረ-ሰላም እጅ ቢገባ ኖሮ ጉዳቱ እጅግ የከፋ ይሆን እንደነበር የገለፀው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኅብረተሰቡ ለሰጠው ጥቆማ ምስጋና እያቀረበ በቀጣም ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ በሀገርና በህዝብ ሰላምና ፀጥታ እንዲሁም በዜጎች ሕይወትና ንብረት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ተገንዝቦ ለፀጥታ አካላት እያደረገ ያለውን ከፍተኛ ትብብር አጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ ጥሪውን አቅርቧል።
በሀረሪ ለክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

በሀረሪ ክልል "የወል እውነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፋ"በሚል ርዕስ ለክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።

በመርሀ ግብሩ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ አሻድሊ ሀሰን ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ሂክማ ኬይረዲን እና የአዲስ አበባ ባህል ፤ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ሂሩት ካሳው ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተጠናቋል ሲል የክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን የመክሰስ አባዜ-ከጥንት እስከ ዛሬ‼️

... ሀገሮች የሚሰጡት ርዳታ የፖለቲካ ግብ ማስፈጸሚያ ነው፡፡ ለዚህ ነው ርዳታ አልቀበለም ማለት ከእነዚህ ሀገሮች ጋር ወደ ግጭት የሚያስገባው፡፡ ርዳታ መስጠት ፖለቲካዊ እንደሆነው ሁሉ፤ ርዳታ ማቆምም በፖለቲካዊ ውሳኔ የሚከናወን ፖለቲካዊ ትርጉም ያለው ተግባር ነው፡፡

ርዳታን በተመለከተ የሚሰጡ መግለጫዎችም ይሄንኑ ፖለቲካዊ ፍላጎት የሚያስፈጽሙ ናቸው፡፡ በዓለም ላይ ከርዳታ ድርጅቶች ቀጥለው የምግብ ርዳታ እንዲሰጥ የሚወተውቱት የለጋሽ ሀገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መሆናቸው የርዳታውን ፖለቲካዊ ሚዛን የሚሳይ ነው።

ርዳታ ምን ያህል የፖለቲካ ውሳኔ ማስፈጸሚያ እንደሆነ ለማየት ኢትዮጵያና ሶማልያ ውስጥ የተከሠቱ አራት የታሪክ አጋጣሚዎችን እንመልከት። በ1970፣ በ1977፣ በ1944- 70 እና በ2012-13 ዓ.ም።

በ1969/70 ዓ.ም በኢትዮጵያ ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102615
ህጋዊ የንግድ ፍቃድን ሽፋን በማድረግ የተሰረቁ ንብረቶችን የሚሸጡ 4 ግለሰቦቸውን መያዙ ፖሊስ አስታወቀ
**************************
(ኢ ፕ ድ)

በተለያዩ ጊዜ የተሰረቁ ግምታቸው ከ1ሚለዮን ብር በላይ የሚያወጡ ንብረቶችን መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ህጋዊ የንግድ ፍቃድን ሽፋን በማድረግ የተሰረቁ ንብረቶችን እየገዙ በቅናሽ የሚሸጡ 4 ግለሰቦቸው ተይዘው ምርመራ መቀጠሉ ታውቋል፡፡

ለወንጀል መስፋፋት ልዩ ልዩ ምክንያቶችን ማንሳት ይቻላል፡፡ ተቀባይ ከሌለ ሌባ አይኖርም እንደሚባለው የአዲስ አበባ ፖሊስ የተሰረቁ እቃዎች በሚገዙ ግለሰቦች ላይ እያደረገ ያለውን ክትትል አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሰኔ 8 ቀን 2015 ዓ/ም ወረዳ 8 ይርጋ ሀይሌ ህንፃ ውስጥ የተሰረቁ እቃዎችን እየገዙ በሚሸጡ ግለሰቦች ላይ ባደረገው ክትትል ከልዩ ልዩ ስፍራዎች የተሰረቁ ግምታቸው 1ሚሊዮን 210 ሺ ብር የሚያወጡ 42 ላፕቶ ፣ 12 የዴስክ ቶፕ ሞኒተሮችንና አንድ ኪቦርድ በኤግዚቢትነት ይዟል፡፡ ህጋዊ የንግድ ፈቃድን ሽፋን በማድረግ የተሰረቁ እቃዎች በመግዛት በርካሽ ዋጋ የሚሸጡ አራት ግለሰቦችም ተይዘው ምርመራው ቀጥሏል፡፡

ህጋዊ የንግድ ፍቃድን ሽፋን በማድግ የተሰረቁ እቃዎችን ገዝተው በቅናሽ ዋጋ የሚሸጡ ግለሰቦች ህጋዊ መንገድን ተከትለው በሚሰሩ ነጋዴዎች ላይ ከሚያሳድሩት ጫና ባሸገር ለወንጀል መስፋፋት ምክንያት በመሆናቸው ህገወጥ ድርጊታቸውን ለመከላከል በሚሰሩ ስራዎች ህጋዊ ነጋዴዎች ጥቆማ በመስጠት በኩል አስፈላጊውን ትብብር ሊያደርጉ እንደሚገባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

ከዚህ ቀደም ላፕቶፕና የዴስክ ቶፕ ኮፒውተር ሞኒተር የጠፋባቸው ግለሰቦች አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በመቅረብ ንብረቶቻቸውን መለየት እንደሚችሉ ፖሊስ ተገልጿል፡፡
የሸገር ከተማ ህገ ወጥ የመሬት ወረራን ለማስቀረት ሰፊ ሥራ መሰራቱን አስታወቀ
****
(ኢ ፕ ድ)

በሸገር ከተማን ህገ ወጥ የመሬት ወረራን ለማስቀረት ሰፊ ሥራ መሰራቱን ከተማው አስታውቋል፡፡

በሸገር ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ናሲር ሁሴን ከተማው ከተመሰረተ የተከናወኑ ተግባራትና ወደ ፊት አቅጣጫዎች ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያ፣ በሸገር ከተማ ህገ ወጥ የመሬት ወረራን ለማስቀረት ሰፊ ሥራ ተሰርቷል፡፡

እንደ አቶ ናስር ገለጻ የሸገር ከተማን ስማርት ከተማ በማድረግ ለዜጎች ምቹ እንዲሆን እየተሰራ ነው፡፡

ከተማው ኘላን እንዲኖረው ማድረግና የመሬት ሀብትን ማወቅ የመጀመሪያው ተግባር ነው፡፡ በዚህም የመሬት መረጃ አያያዝን ወደ ዲጂታል ማስገባት ተችሏል ብለዋል፡፡

የመሬት አጠቃላይ መረጃ ተሰብስቧል ያሉት አቶ ናስር ህገ ወጥ የመሬት ወረራን ለማስቀረት ሰፊ ሥራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

የሥራ እድል ፈጠራ ተግባራት መከናወኑን ጠቅሰው በቋሚነት ከ62 ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች ሥራ መፍጠር መቻሉን ገልፀዋል፡፡

በግብርና፡በገቢ አሰባሰብ፡በትምህርት እና ጤና ዘርፎች ላይ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ ከተማዋን ዘመናዊና ስማርት በማድረግ ለዜጎች ምቹ እንዲሆን በኘላን ላይ የተመሰረቱ ተግባራት የሚከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

በማርቆስ በላይ
የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ በቅርቡ ወደሥራ ይገባል
****************
(ኢ ፕ ድ)

በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በነበረው ግጭት ምክንያት ሥራ አቁሞ የነበረውን መቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ሥራ ለማስገባት ሲደረጉ የቆዩ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውንና በቅርቡ ወደሥራ እንደሚገባ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ::

የኮርፖሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም ከተማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ረዘም ላለ ጊዜ ሥራ አቋርጦ ቆይቷል:: የፕሪቶሪያን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በአካባቢው የነበረው ጦርነት በመቆሙና ሰላም ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=102704
ለዓባይ ግድብ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ
******************
(ኢ ፕ ድ)

በበጀት ዓመቱ አስር ወራት ለዓባይ ግድብ ግንባታ ከአንድ ቢሊዮን 188 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የግድቡ ብሔራዊ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ግድቡ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ እስከ ሚያዝያ ወር መጨረሻ የተሰበሰበው ጠቅላላ ገንዘብ ከ17 ቢሊዮን 971 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የዓባይ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብርሃም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ለህዳሴ ግድብ ግንባታው ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=102701
በክልሉ ከ5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሩዝ ምርት ይጠበቃል
***************
(ኢ ፕ ድ)

በመጪው የመኸር ምርት ዘመን ከአምስት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ሩዝ ለመሰብሰብ ማቀዱን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የሰብል ዳይሬክተር አቶ አግደው ሞላ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ክልሉ በመጪው የመኸር የምርት ዘመን ከአምናው የተሻለ የሩዝ ምርት ለማግኘት ከወዲሁ በትኩረት እየሠራ ይገኛል፡፡ ከመጪው የመኸር ምርት ዘመንም ከአምስት ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሩዝ ምርት ለማግኘት ታቅዷል፡፡

በክልሉ ባለፈው የመኸር የምርት ዘመን 61ሺ ሄክታር መሬት በሩዝ ልማት መሸፈኑን አስታውሰው፤ ከዚህም በቅድመ ምርት ትንበያ መሠረትም ከሦስት ሚሊዮን በላይ ኩንታል የሩዝ ምርት መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡

እንደ አቶ አግደው ገልጻ፤ ክልሉ በመጪው የመኸር የምርት ዘመን ከ100 ሺ ሄክታር በላይ መሬት ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=102729