አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከ ዩኒዶ ተወካይ ጋር ተወያዩ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በዛሬው ዕለት ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት(ዩኒዶ) ተወካይ ኦሬሊያ ካላብሮን ጋር ተወያይተዋል፡፡
የሁለቱ ወገኖች ውይይት በኢትዮጵያ እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) መካከል ያለውን አጋርነት ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መሆኑ ታውቋል።
አምባሳደር ምስጋኑ በዚህ ወቅት ፥ ኢትዮጵያ ከዩኒዶ ጋር በአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪዎች፣ በጨርቃ ጨርቅ፣ በቆዳና ቆዳ ውጤቶችና በፋርማሲዩቲካል ምርቶች ላይ አጋርነቷን ለማሳደግ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
ተወካይ ኃላፊዋ ኦሬሊያ ካላብሮን በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ ያለውን የማሻሻያ እርምጃዎች አድንቀዋል፡፡
በተጨማሪም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ ለማከናወን ስላቀዳቸው ተግባራት ተወያይተዋል።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሀገር አቀፍ የጤና ዐውደ ርእይ መክፈቻ ላይ ያደረጉት ንግግር።
በዘንድሮው ክረምት ሁለት ሚሊዮን በጎ ፍቃደኞች ይሳተፋሉ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ ለአምስት ወራት በሚቆየው በዘንድሮው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር ሁለት ሚሊዮን በጎ ፍቃደኞች እንደሚሳተፉና በዚህም ከመንግሥት ወጪ ይደረግ የነበረ ሶስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር እንደሚድን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ አደራጎት ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ አደራጎት ማስተባበሪያ ኮሚሽን የበጎ ፍቃድ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=103055

"በመንገዱ መጓተት ምክንያት ለእንግልት ተዳርገናል”
የጎንደር አዘዞ ነዋሪዎች
"ግንባታው የዘገየው በኮንትራክተሩ የአፈጻጸም ማነስ ነው”
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
በጎንደር አዘዞ መንገድ ሥራ መጓተት ምክንያት ተጉላልተናል ሲሉ የአዘዞ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ፅህፈት ቤት በበኩሉ መንገዱን የሚሰራው ኮንትራክተር የአፈፃፀም ማነስ ነው ብሏል።
የጎንደር አዘዞ ነዋሪው ሙሉቀን አካልነህ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ መንገዱ ለዓመታት ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=103048
(ፎቶ ፋይል)

የባሕልና ስፖርት ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦን የሚያሳይ የመረጃ ሥርዓት አለመኖሩ የዘርፉ ሚና እንዳይጎላ አድርጓል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
ባሕልና ስፖርት ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት ያለውን አስተዋጽኦ የሚያሳይ አገራዊ የመረጃ ሥርዓት አለመኖሩ የዘርፉ ስነምጣኔያዊ አስተዋጽኦ ጎልቶ እንዳይወጣ አድርጓል ሲል የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ገለጸ።
በአምስተኛው አገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ጉባዔ ባህልና ስፖርት ለአገር ኢኮኖሚዊ ልማት ....
https://press.et/?p=103081

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
ሕጻናት- የነገ ተስፋ ለአዲስ አበባ!
የሀገራችንን ሁለንተናዊ ለውጥ በዘላቂነት ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና የሚኖረው የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አጠናቅቀን ትግበራውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል የአንድ ሳምንት ከተማ አቀፍ ንቅናቄ በዛሬው ዕለት አስጀምረናል።
ከፅንስ ጀምሮ እስከ ስድስት ዓመት የዕድሜ ክልል ባሉ ጨቅላ ሕፃናት ላይ ትኩረት አድርጎ በሚሰራው በዚህ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም እንደ ሀገር በትውልድ መካካል ያጋጠመንን ስብራት ክምንጩ ለመፈወስ በዚህ የዕድሜ ክልል ላይ አበክረን መስራት እንዳለብን ተረድተናል።
ለዚህም እንዲያመች በዛሬው ዕለት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርታችንን ለማሸጋገር የሚያስችል በጥናት እና ምርምር ላይ የተደገፈ ስራ ለመስራት ከአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለንን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመናል።
የቀዳማይ ልጅነት ልማት እና እንክብካቤ የሚካሄድበት የዕድሜ ክልል ብዙም ትኩረት ያልተሰጠው፣ ነገር ግን በሰው ልጅ ሕይወት ወሳኙ የሁለንተናዊ ዕድገት መሠረት የሚጣልበት የዕድሜ ክልል በመሆኑ እንደ ከተማ አስተዳደር ለዚህ ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥተን “ሕጻናት - የነገ የአዲስ አበባ ተስፋ’’ የሚል ፕሮግራም ቀርጸን ወደ ትግበራ ገብተናል።
ነጋችንን ዛሬ ላይ እንሰራለን!
አዲስ አበባን ሕጻናት ለማሳደግ ምርጥ የአፍሪካ ከተማ ለማድረግ ራዕይ ሰንቀናል!

የከተማ አስተዳደሩ በክበበ ፀሃይ ያስገነባው የሕጻናት ክሊኒክ እና በልደታ ክፍለ ከተማ የተገነባው የህፃናት ማቆያ ማዕከል ተመረቁ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩ በክበበ ፀሃይ ያስገነባውን የሕጻናት ክሊኒክ እና በልደታ ክፍለ ከተማ የተገነባውን የህፃናት ማቆያ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀምረዋል::
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች ህጻናት ከጽንስ ጀምሮ ተገቢውን እንክብካቤ አግኝተው በአካልና አዕምሮ በልፅገው እንዲያድጉ የከተማ አስተዳደሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል።
የእናቶችን የኑሮ ጫና ማቅለል የሚያስችል የሕጻናት ማቆያ እና የሕፃናቱን ጤንነት ለመከታተል የከተማ አስተዳደሩ የህፃናት ክሊኒክ መገንባቱንም ገልጸዋል::
በሚቀጥሉት ሦስት አመታት 1000 ተጨማሪ የህፃናት ማቆያ ማዕከላት እንደሚገነቡ የገለፁት ከንቲባ አዳነች በህጻናት አስተዳደግ ዙሪያ የቤት ለቤት የግንዛቤ ማስጭበጫ ስራ የሚሰሩ 1400 ባለሙያውዎች በዛሬው ዕለት መመረቃቸውንም ጠቅሰዋል ሲል ከንቲባ ጽህፈት ቤት ዘግቧል::