የከተማ አስተዳደሩ በክበበ ፀሃይ ያስገነባው የሕጻናት ክሊኒክ እና በልደታ ክፍለ ከተማ የተገነባው የህፃናት ማቆያ ማዕከል ተመረቁ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩ በክበበ ፀሃይ ያስገነባውን የሕጻናት ክሊኒክ እና በልደታ ክፍለ ከተማ የተገነባውን የህፃናት ማቆያ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀምረዋል::
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች ህጻናት ከጽንስ ጀምሮ ተገቢውን እንክብካቤ አግኝተው በአካልና አዕምሮ በልፅገው እንዲያድጉ የከተማ አስተዳደሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል።
የእናቶችን የኑሮ ጫና ማቅለል የሚያስችል የሕጻናት ማቆያ እና የሕፃናቱን ጤንነት ለመከታተል የከተማ አስተዳደሩ የህፃናት ክሊኒክ መገንባቱንም ገልጸዋል::
በሚቀጥሉት ሦስት አመታት 1000 ተጨማሪ የህፃናት ማቆያ ማዕከላት እንደሚገነቡ የገለፁት ከንቲባ አዳነች በህጻናት አስተዳደግ ዙሪያ የቤት ለቤት የግንዛቤ ማስጭበጫ ስራ የሚሰሩ 1400 ባለሙያውዎች በዛሬው ዕለት መመረቃቸውንም ጠቅሰዋል ሲል ከንቲባ ጽህፈት ቤት ዘግቧል::

ተግባራዊ የተደረገው የቤት ግብር ማሻሻያ የቤት ኪራይ ለመጨመር ምክንያት ሊሆን አይችልም - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
******
(ኢ.ፕ.ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተግባራዊ የተደረገው የቤት ግብር ማሻሻያ በጥናት ላይ ተመስርቶ የተከናወነ በመሆኑ የቤት ኪራይ ለመጨመር ምክንያት ሊሆን እንደማይችል የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ገለጸ፡፡
ማሻሻያው የከተማ አስተዳደሩ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚሰራቸውን ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እና መሰረተ ልማቶችን ይበልጥ ለማስፋፋት የሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡
በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘገየ በላይነህ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ የቤት ግብር ማሻሻያ ወቅቱን የዋጀ እና ጥናትን መሰረት ባደረገ መልኩ መከናወኑን ገልጸዋል፡፡
የከተማ ቦታ ኪራይ እና የከተማ ቤት ግብር በሚል በ1937 የወጣው አዋጅ ለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው በ1968 ዓ.ም ነው፡፡
አዋጅ ቁጥር 80/1968 ላለፉት 47 ዓመታት በስራ ላይ የቆዬ ሲሆን የአዋጁ አንቀፅ አምስት፤ በከተሞች የሚገኙ ቤቶች ባለቤት የሆኑ ግለሰቦች፣ ቤተሰቦች፣ ድርጅቶች፣ ወይም ህብረት ስራ ማህበራት ባለቤት በሆኑበት ቤት ላይ ግብር ወይም ታክስ መክፈል እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡
ከአራት አስርት ዓመታት በላይ ሳይሻሻል የቆየው ይህ አዋጅ የቤት ግብር በየጊዜው እንደሚሻሻል እና ወቅታዊነቱን እንደሚያመላክት አቶ ዘገዬ ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት ለረጅም ዓመታት ሳይሻሻል የቆየውን የቤት ግብር ተመን ላይ በጥናት ላይ የተመሰረተ ማሻሻያ ተግባራዊ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
በከተማዋ ውስጥ የቤት ግብር የሚከፍሉት አብዛኛዎቹ ነባር ይዞታዎች እንደነበሩ አስታውሰው፤ በአዲሱ ጥናት መሰረት የጋራ መኖርያ ቤቶች ጨምሮ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ ቤቶች የቤት ግብር እንዲከፍሉ መወሰኑን ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም የቤት ግብር ሲከፍሉ ከነበሩት ውስጥ ከ22 ሺህ በላይ የሚሆኑት ከ10 ብር በታች እና ከ2 ሺህ 500 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከአንድ ብር በታች ግብር ሲከፍሉ እንደነበር ጠቅሰው፤ ይህም የህዝቡን አሁናዊ የልማት ጥያቄ ለመመለስ መሰብሰብ ከሚገባው ገቢ አንጻር እጅግ አነስተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
አሁን የተደረገው ማሻሻያም የቤቶችን ደረጃ፣ መንግስት ለመሰረተ ልማት ያወጣውን ወጪ እና አካባቢያዊ ሁኔታን ታሳቢ በማድረግ ተመጣጣኝ ግብር እንዲከፈል የሚያደርግ በመሆኑ፤ የቤት አከራዮች ኪራይ እንዲጨምሩ የሚያስገድድ በቂ ምክንያት የለውም ብለዋል።
መንግስት የግብር ከፋዩን ጫና ለመቀነስ በማሰብም ግለሰቦች መክፈል ከነበረባቸው 50 በመቶ እንዲሁም ድርጅቶች 75 በመቶ ብቻ እንዲከፍሉ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡
አስተዳደሩ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረጉ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በርካታ የመሰረተ ልማቶችን መገንባቱን ገልጸዋል፡፡
ለአብነትም የተማሪዎች ምገባ፣ መሰረተ ልማቶችን እንዲሁም በርካታ የምገባ ማዕካላትን በመክፈት ህዝቡን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የቤት ግብር ማሻሻያውም አስተዳደሩ ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የጀመራቸውን የልማት ስራዎች ይበልጥ ለማስፋፋት የሚውል ገቢ ለመሰብሰብ ሲባል በፍትሐዊነት የተወሰነ መሆኑን ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትናትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ የጣሪያ እና ግድግዳ ግብርን ምክንያት በማድረግ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት እንደማይቻል መወሰኑ ይታወቃል።

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በኢትዮጵያ ከቱርክ አምባሳደር ጋር ተወያዩ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በኢትዮጵያ ከቱርክ አምባሳደር በርክ ባራን ጋር በዛሬው እለት ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም ቱርክ በትምህርት፣ በጤና እና ማህበራዊ ልማት እንዲሁም በቱሪዝም ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ እያከናወነች ላለው ስራ አቶ ኦርዲን ምስጋና አቅርበዋል።
ሀረር ከተማ የጀጎል ግንብን ጨምሮ በዩኔስኮ የተመዘገቡ አለም አቀፍ ቅርሶች መገኛ መሆኗን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን የተለያዩ ባህል እና እምነት ያላቸው ህዝቦች በሰላም በፍቅርና በመቻቻል የሚኖሩባት ከተማ ስለመሆኗ ገልፀውላቸዋል።
በቱርክ ከሚገኘው Şanlıurfa ከተማ ጋር እህትማማችነትን እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማጠናከር ይሰራል ብለዋል።
የቱሪክ አምባሳደር በርክ ባራን በበኩላቸው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዘመናትን ያስቆጠረ እና በመልካም ወዳጅነት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ተናግረዋል።
አምባሳደሩ ኢትዮጵያና ቱርክም ከፍተኛ የኢኮኖሚ አጋር መሆናቸውን አውስተዋል ሲል የክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

ባለጉዳዮች ዉሳኔ ያገኙ የወንጀል መዛግብት ላይ አቤቱታቸውን ማቅረብ የሚያስችል የኦንላይን ስርዓት ወደ ስራ ገባ
******
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ዉሳኔ ያገኙ የወንጀል መዛግብት ላይ ቅሬታና አቤቱታ ያላቸዉ ተገልጋዮች ባሉበት ሆነዉ ማቅረብ የሚያስችላቸዉን ኦንላይን ስርዓት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና ፔራጎ ከተባለ ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጁትን ድረ ገጽ ስራ አስጀመረ፡፡
በፍትህ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና የሪፎርም ስራዎች ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ኤርሚያስ የማነብርሃን ይህንን ስርዓት አስመልክተዉ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ በፍትህ ሚኒስቴር የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀልጣፋና በቴክኖሎጂ የተደገፉ ለማድረግ ስራዎች እየተሰሩ ናቸዉ።
ከነዚህም ዉስጥ የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የወንጀል መዛግብት ዉሳኔዎች ላይ ተገልጋዮች የሚኖራቸዉን ቅሬታና አቤቱታ ባሉበት ሆነዉ በአነስተኛ ወጭና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ መልኩ ሳይንገላቱ እንዲያቀርቡ ታስቦ ዌብሳይቱ መበልጸጉን ተናግረዋል።
የዜጎች ፍትህ የማግኘት መብት ቀላልና ቀልጣፋ ሊሆን እንደሚገባ የገለፁት ዶክተር ኤርሚያስ አገልግሎቱ ለተገልጋይ ዜጎች፣ለዘርፉ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ስራቸዉን በብዙ መልኩ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።
በተለይም የፍትህ ስርአቱን ዘመናዊ በሆነ መልኩ በማደራጀት በኩል የራሱ የሆነ ጠቀሜታ እንደሚኖረዉና በቀጣይም የወንጀል ፍትህ አስተዳደሩን በዚሁ መልኩ ለማደራጀት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዉ በዚህ ስራ ለተሳተፉ አካላትም ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡
አገልግሎቱ በልደታ የሚገኙ የወንጀል ጉዳይ ዳይሬክቶሬቶች፣ በአዲስ አበባ በሚገኙ 10 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች፣ እንዲሁም በድሬድዋና በሀዋሳ የሚገኙትን ፅ/ቤቶችን እንደሚያካትት የቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ጉዳይ መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌቱ ታደሰ ተናግረዋል፡፡
በዚሁ መሰረትም ማንኛዉም ቅሬታና አቤቱታ ያላቸዉ ተገልጋዮች በ
https://www.eservices.gov.et
ብለዉ በመግባት ባሉበት ቦታ ሆነዉ አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡