በክልሎች የአንበጣ መንጋ ምልክት በመታየቱ የቅድመ መከላከል ሥራ እየተሠራ ነው
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በአፋርና በትግራይ ክልል የተበታተነ የአንበጣ መንጋ ምልክት በመታየቱ ተራብቶ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የቅድመ መከላከል ሥራ እየተሠራ ነው ሲል የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ::
በግብርና ሚኒስቴር የእፅዋት ጥበቃ መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ በላይነህ ንጉሤ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ2015/16 ዓ.ም የመኸር ወቅት በአፋርና በትግራይ ክልል በተደረገ የአንበጣ መንጋ የዳሰሳና የትንበያ ጥናት ሥራ የተበታተነ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ ምልክት አሳይቷል:: የታየው የተበታተነ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ ተራብቶ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የክትትልና ቁጥጥር ሥራ እየተሠራ ነው::
በአፋርና በትግራይ ክልል የታየው የተበታተነ የአንበጣ መንጋ በሳርና በሰብል ላይ ጉዳት ማድረስ የሚችል አይደለም ያሉት ሥራ አስፈፃሚው፤ የታየውን ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106107

በትግራይ ክልል የአሸንዳ በዓል በልዩ ድምቀት ይከበራል-ቢሮው
******************
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል የአሸንዳ በዓል በልዩ ድምቀት እንደሚከበር የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ሃላፊ ዶክተር አፅበሃ ገብረእግዚአብሄር ለኢዜአ እንደገለጹት በአሉ የተገኘውን ሰላም ማጽናት በሚያስችል መልኩ ይከበራል።
በአሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የመከባበርና የመደጋገፍ እሴቶች የሚጎለብቱበት በመሆኑ በልዩ ድምቀት በባህላዊ ኩነቶች እንደሚከበር አመላክተዋል።
በአሉ ከተለያዩ አካባቢዎች ልጃገረዶችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የፌዴራልና የክልል የስራ ሀላፊዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።
ከነሀሴ 16 - 18 ቀን 2015 ዓ.ም ለሶሰት ቀናት በሚከበረው በዓል የጎዳና ላይ ትርኢትን ጨምሮ የልጃገረዶች ባህላዊ አልባሳትና ባህላዊ ጨዋታዎች እንደሚቀርቡበትም አመላክተዋል።
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለበአሉ ዝግጅት ድጋፍ ማድረጉን የገለጹት ሀላፊው በአሉ ቱሪዝሙን የሚያነቃቃ መሆኑን አስታውቀዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሴቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ አለማት አማረ በበኩላቸው አሸንዳ በየዓመቱ በሴቶች የሚከበር በዓል ነው ብለዋል።
ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ከአሜሪካ ግምጃ ቤት ምክትል ረዳት ፀሐፊ ጋር ተወያዩ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ከአሜሪካ ግምጃ ቤት ምክትል ረዳት ፀሐፊ ኤሪክ ሜየር ጋር በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር ላይ ተወያዩ ።
በውይይቱም ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ የአሜሪካ ግምጃ ቤት በኢትዮጵያ እድገትን ለማፋጠንና የኢኮኖሚ መረጋጋት እንዲመጣ እየተወጣ ላለው ገንቢ ሚና ምስጋና ማቅረባቸውን ባንኩ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

#ከኢፕድ_ማህደር
22 ጠንቋዮች ራሳቸውን አጋለጡ
ወሎ ውስጥ በደላንታ ወረዳ የኢላና ትምህርት ቤት መምህራን ከጣርዳት፣ ከደሀናንና ከዝባን የገበሬ ማኅበራት ጋር በመተባበር በመካከላቸው የተሰገሰጉትን 22 አባይ ጠንቋዮች ራሳቸውን አጋልጠው ክቡር ወደሆነው የሥራ መስክ እንዲሰማሩ አደረጉ።
እነዚሁ 22 አባይ ጠንቋዮች በተሰጣቸው ትምህርት አምነው ድቤዎችን (ከበሮዎችን)፣ እንዲሁም በእጃቸው ይገኙ የነበሩትን ልዩ ልዩ የጥንቆላ ዕቃዎችንና መጽሐፍት ለገበሬ ማኅበራቱ በራሳቸው ፈቃድ አስረክበዋል።
አባይ ጠንቋዮቹ ካስረከቧቸው ዕቃዎች ውስጥ በተለይ ከበሮዎቹ በአካባቢው ለሚቋቋመው የኪነት ቡድን መገልገያ እንዲሆን መሰጠቱ ተገልጧል።
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መጋቢት 23 ቀን 1971 ዓ.ም ታትሞ የወጣ

"ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ ያላቸውን ትብብር በማጠናከር በአህጉሪቱ የመሪነት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል"
- ዶክተር ናሌዲ ፓንዶር
********************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ ያላቸውን ትብብር በማጠናከር በአህጉሪቱ የመሪነት ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችና ትብብር ሚኒስትር ዶክተር ናሌዲ ፓንዶር ገለፁ።
የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችና ትብብር ሚኒስትር ዶክተር ናልዲ ፓንዶር ሁለቱ አገራት ለፓን አፍሪካኒዝምና የአፍሪካ ኅብረት ማበብ ጉልህ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል።
ሁለቱ አገራት በተለይም ለአፍሪካ ኅብረትና ለአፍሪካ ኅብረት የልማት ኤጀንሲ-ኔፓድ ምስረታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልፀው አጋርነታቸው መጠናከር አለበትም ብለዋል።
ይህንንም ተከትሎ ሁለቱ አገራት በአፍሪካ ጉዳዮች ላይም የመሪነት ሚናቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ ነው የገለጹት።
ከሰሞኑ በአዲስ አበባ የተካሄደው 4ኛው የኢትዮ-ደቡብ አፍሪካ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብስባ በአገራቱ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማጠናከር እንደሚያስችል ተናግረዋል።
ሁለቱ አገራት ለአፍሪካ 2063 አጀንዳ መሳካትም አዳዲስ የትብብር መስኮች መለየታቸውንና ለዚህ መሳካት በትብብር እንደሚሰሩ መስማማታቸውን አብራርተዋል።
አገራቱ በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ በተለይም በግብርና ዘርፍ በጋራ ተባብሮ በመሥራት ለአህጉሪቱ ልማት እድገት ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ነው ያብራሩት።
ሚኒስትሯ ባሰለፍነው ሰኞ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያና የአፍሪካ ልማት ፈንድ የ84 ነጥብ ሶስት ሚሊየን ዶላር የልማት ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ
********************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያና የአፍሪካ ልማት ፈንድ ለስንዴ ምርትና ምርታማነት ማሻሻያ የሚውል የ84 ነጥብ ሶስት ሚሊየን ዶላር (4. 5 ቢሊየን ብር) የልማት ድጋፍ ስምምነት ተፈራርሙ፡፡
ከልማት ደጋፋ ውስጥ 54 ሚሊየን ዶላር ከአፍሪካ ልማት ፈንድ፣ 20 ሚሊየን ዶላር ከኔዘርላንድ መንግሰት፣ 10 ሚሊየን ዶላር ኦ.ሲ.ፒ አፍሪካ ከተባለ ድርጅት እንዲሁም ቀሪውን 3 መቶ ሺህ ዶላር ግሎባል ሴንተር ፎር አዳብቴሽን ከተባለ ተቋም የተገኘ መሆኑ ታወቋል፡፡
የልማት ድጋፋ በአነስተኛ እርሻ የስንዴ አምራች ገበሬዎችን ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል የሚውል ሲሆን ይህን ዕውን ለማድረግ እንዲቻል ድጋፉ ከአካባቢ ጋር ተስማሚ የስንዴ ምርት ለማምረት ፣ የገበያ መሰረተ ልማቶችንና ትስስርን ለማሳደግ እንዲሁም በዘርፋ ያሉ ፕሮጀክቶችን ለማስተዳደር የሚውል ነው፡፡
ይህ ድጋፍ በተለይ የሀገር ውስጥ የስንዴ ፍላጎትን በሀገር ውስጥ ምርት ለማሟላት የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ሲሆን በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ የሚተገበር ይሆናል፡፡
የልማት ድጋፋን ስምምነት በኢትዮጵያ መንግስትን በኩል የገንዘብ ሚነስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እንዲሁም የአፍሪካ ልማት ፈንድን በመወከል ዶ/ር አብዱል ካማራ በምስራቅ አፍሪካ የአፍሪካ ልማት ባንክ ምክትል ዳይሬክተር መፈረማቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓም

ከአማራ ክልል የጸጥታ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ያስተላለፉት መልዕክት‼️
በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ የፀጥታ ችግሮች አሳሳቢ እየሆኑ መጥተዋል።
በመሰረቱ ብዙ ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች ይኖራሉ፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ጠቃሚው መንገድ ሰላማዊና የውይይት አግባብ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ያለው አካሄድ
1. የጥያቄዎችን መፍቻ መንገድ የሚያደናቅፍ
2. ያለንን የሚያሳጣ
3. በዘላቂነት ሊታዩ ይገባቸዋል የምንላቸውን ጉዳዮች እንዳይፈቱ የሚያወሳስብ አካሄድ ነው፡፡ 'ሰላም ከሌለህ ሁሉን ታጣለህ' የሚባለውን እውነታ ከልብ በማጤን በአስተውሎት መጓዝ በሚገባን ታሪካዊ ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡
በየዘመኑ ብዙ ፈተናዎች እና ችግሮች ሲገጥሙ በጥበብ ተሻግረው ያሻገሩንን የአባቶቻችን ጥበብና አስተውሎት ማጥበቅ ይጠይቃል፡፡ የሀገር ሽማግሌ የጠፋበት፣ ታላቅ የሌለበት፣ መካሪ የሃይማኖት አባት የታጣበት ይመስል ሁላችንንም የሚያባላና የሚበላ አካሄድ ይስተዋላል፡፡
የዚህ መጨረሻ በግራም በቀኝም ከውጭም ከውስጥም ላሰፈሰፉ ኃይሎች ሰርግና ምላሽ ሆኖ አቅም የሚያሳጣ፣ ክብራችንን የሚጎዳ፣ ተጋላጭነታችንን የሚያሰፋ በአጠቃላይ ሁሉንም የሚያሳጣ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡
ከለውጡ ብዙ የጠበቅናቸው ግን ደግሞ ምላሽ ያላገኘንባቸው ያላረኩንና ሌሎች ችግሮችና ስሜቶች ይኖራሉ፡፡
ለእነዚህ ጉዳዮች ቆም ብለን በማሰብ በሰላሙ መንገድ ዘላቂ መፍተሄ እንዲያገኙ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ለዚህም የሁሉም ዋስትና የሆነውን ህግና ሥርዓት በተሟላ መልኩ ማክበርና ማስከበር ይገባል፡፡

ከውጭ ሀገር ጎብኚዎች ከሦስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ
-በበጀት ዓመቱ ከ900ሺህ በላይ የውጭ ዜጎች ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል
*************
(ኢ ፕ ድ)
በ2015 በጀት ዓመት ከውጭ ሀገር ጎብኚዎች ከሦስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። በበጀት ዓመቱ ከ900 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል።
የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ከቱሪስት መዳረሻ መሠረተ ልማት፣ ከአገልግሎት ጥራትና ከዓለም አቀፍ የንግድ ትስስሮች የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ በበጀት ዓመቱ የተሻለ ነበር።
በዓመቱ ከ900 ሺህ በላይ የውጭ ዜጎች ኢትዮጵያን የጎበኙ ሲሆን፤ ከሦስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢም ተገኝቷል።
እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2015 በጀት ዓመት የሠላም ሰምምነቱን ተከትሎ በርካታ የቱሪዝም ሥራዎች ተሰርተዋል። በቱሪስት መዳረሻ ልማት አዳዲስ የቱሪስት መረጃ ማዕከላትን መገንባት ተችሏል።
የቱሪስት መስህቦችን የማልማት ስራዎች ላይ የእሴት ጭማሪ ሥራዎች ተከናውነዋል። በገበያና ማስታወቂያ በኩል በዓለም አቀፍ ደረጃ………
https://press.et/?p=106159

የአራት ኪሎ ፒያሳ መንገድ ግንባታ በሰባት ወራት ይጠናቀቃል
******************
(ኢ ፕ ድ)
ከአራት ኪሎ አደባባይ እስከ ፒያሳ ያለውን የመንገድ ግንባታ የማስፋት ሥራ በሰባት ወራት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሰተራ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ።
በአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የማዕከላዊ አዲስ አበባ መንገድ ሀብት አስተዳደር ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ነስረዲን ሰማን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በአዲስ አበባ ከተማ ከአራት ኪሎ አደባባይ ወደ ፒያሳ የሚወስደው መንገድ ከፍተኛ የሆነ የእግረኛ ተጠቃሚ ፍሰት ያለበት በመሆኑ በከተማዋ በጸደቀ የማስተር ፕላን መሰረት መንገዱን የማስፋት ሥራ እየተከናወነ ነው።
ይህም በእግረኞች ላይ ሊደርስ የሚችል የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ያስችላል።
የመንገድ ግንባታው አጠቃላይ 2 ነጥብ 2 ኪ.ሜ ርዝመት እና 5 ነጥብ 4 ሜትር ስፋት ያለው መሆኑንና በከተማ አስተዳደሩ በሚሸፈን ከ21 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት እየተከናወነ መሆኑንም አቶ ነስረዲን ገልጸዋል።
ይህ መንገድ የማስፋት እና የማስዋብ ሥራ የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ.ም የተጀመረ እና የአንድ አመት ፕሮጀክት መሆኑን ጠቅሰው፤ አሁን………
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=106192

ከድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣና 10 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
በ2015 በጀት ዓመት ከተለያዩ ምርቶች 10 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣና አስታወቀ። በነጻ የንግድ ቀጣናው ለሁለት ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩ ተገልጿል።
የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሚል ኢብራሂም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በዘንድሮው ዓመት ከነጻ የንግድ ቀጣናው በቀጥታና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ 10 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።
ገቢው በዋናነት ለውጭ ገበያ ከቀረቡ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም የድርና ማግ ምርቶች የተገኘ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=106161

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ ከኢፕድ ጋር በጋራ ያዘጋጁት የፎቶግራፍ አውደርዕይ በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተክፈተ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና የ80 አመት ጉዞውን የሚያሳይ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተክፈተ።
ቢሮው ላለፉት 80 አመታት የወሳኝ ኩነት ቢሮ በሚል ስያሜ እንደ ሞት፣ ልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺ፣ የመታወቂያና ሌሎች አገልግሎቶችን ለከተማዋ ነዋሪዎች ሲሰጥ የቆየ ሲሆን በዚህ አመት አሰራሩን ለማዘመን በአዲስ መልክ "የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ" በሚል ተደራጅቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አንጋፋ ልምዱን በመጠቀም ኤጄንሲው በ80 አመታት ውስጥ ለከተማዋ ነዋሪዎች በምን መልኩ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር የሚያሳዩ ታሪካዊ ፎቶግራፎች የተካተቱበትን የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ አዘጋጅቷል።
የፎቶግራፍ አውደ ርዕዩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የከተማ አስተዳደሩ የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተከፍቷል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በተመሳሳይ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተዘጋጀውን ጨምሮ ለሌሎች ተቋማትም ተመሳሳይ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ ማዘጋጀቱ ይታወቃል።
በሞገስ ተስፋ
ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓም

ለመዲናዋ የመንግሥት ሠራተኞች ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር የቤት ኪራይ ድጎማ ተደርጓል
******************
(ኢ ፕ ድ)
በ2015 በጀት ዓመት ለአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር የቤት ኪራይ ድጎማ መደረጉን የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን የበጀት ዓመቱን የሥራ እንቅስቃሴ አስመልክተው ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ከቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ ከሠራተኞች ጥያቄ ሲነሳ እንደነበር ጠቅሰዋል።
የከተማ አስተዳደሩ አመራር ውይይት አድርጎ አቅም በፈቀደ መጠን ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር የቤት ኪራይ ድጎማ መደረጉን ገልጸዋል። ይህም ሠራተኞች ያላቸውን የክፍያ ምጣኔ ታሳቢ ያደረገና እስከ አንድ ሺህ 500ብር እንደሆነ ጠቁመው፤ ይህ አሁን ያለውን መሠረታዊ የቤት ኪራይ ክፍያ ጥያቄ የሚፈታ ባይሆንም በተወሰነ ደረጃ ችግሩን ማቃለል ያስቻለ ነው ብለዋል።
ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተያይዞ ሠራተኛው የሚያነሳቸው ጥያቄዎች እንዳሉ የገለጹት ኃላፊዋ፤ በሁሉም የመንግሥት መስሪያ ቤት ካፍቴሪያዎች ላይ የሚከፈሉ ክፍያዎችን በተወሰነ መጠን መንግሥት መደጎም መቻል እንዳለበት ታምኖ በ2015 መመሪያ ተዘጋጅቶ…………
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=106158