የከንቲባ አደነች አቤቤ መልዕክት ‼️
“ተግዳሮቶች ያልበገረው ለውጥ” ብለን የጀመርነውን የ2015 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማችንን ዛሬ አጠናቅቀናል።
በ2015 በጀት ዓመት ውጤት ያገኘንባቸው ስራዎቻችን የምንረካባቸው ሳይሆኑ የጀመርናቸውን በማስፋት የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል፣ ለኑሮ ምቹ፣ ተወዳዳሪና የኢትዮጵያ ብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ከተማ ለመገንባት ይበልጥ ተነሳሽነት የፈጠርንባቸው ነበሩ።
የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓታችንን ቀልጣፋና ፍትሃዊ ለማድረግ የጀመርናቸው የሪፎርም ስራዎችን በማጠናከር፣ ፍትሐዊ አገልግሎት ለህዝባችን ለማድረስ፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በማስተካከልና አገልግሎት አሰጣጣችንን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ረገድ መሻሻል ቢኖርም በቀጣይ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራው ስራ ይሆናል።
ለውጡ ህዝብ ፈልጎ ያመጣውና የሚደግፈው በመሆኑ ተግዳሮት የሚያደናቅፈው አልሆነም።
እኛም ይህን የህዝባችንን እምነት ጉልበት በማድረግ፣ የአመራራችንን አቅም በማጎልበት እና ለህዝብ የሚወግኑ ተቋማትን እየገነባን የነዋሪዎች የዘመናት ጥያቄ የሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እና የኑሮ ጫናን የሚያቀሉ ፕሮጀክቶች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተን መስራታችንን እንቀጥላለን።
የከተማችንን ሰላም ለማስከብር ከሰላም ወዳዱ ህዝባችን ጋር በመሆን ነዋሪዎቻችን በሰላም ወጥተው በሰላም የሚገቡባት ከተማ መሆኗ ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ ለፀረ ሰላም ኃይሎች በእብሪት የሚመጣ ስልጣን እንደሌለ አሁንም ከተማችን ጥሩ ማሳያ ትሆናለች።
ጽንፈኝነትና አክራሪነት በተግባር በህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነት የተሸነፈባት፣ ሰላምዋ በዘላቂነት በህዝብ ተሳትፎ የተረጋገጠላትና ለሁሉም የምትመች፣ እንደስምዋ የተዋበች አዲስ አበባን እውን ለማድረግ በትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን።
ነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ል

በሽብር ቡድኖች፣ በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርና በሙስና ተሳትፎ የነበራቸው ከ3 ሺ በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
****
(ኢ.ፕ.ድ)
በሽብር ቡድኖች፣ በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርና በሙስና ተሳትፎ የነበራቸው ከ3 ሺ በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዓመታዊ አፈፃፀሙን መገምገሙንና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ማስቀመጡን አስመልክቶ ለኢፕድ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ሀገራዊ፣ አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን በመሰብሰብና በመተንተን የደኅንነት ሥጋቶችን አስቀድሞ የሚያከሽፍ፤ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ የሆነ እንዲሁም ፕሮፌሽናል ተቋም ለመገንባት የሚያስችሉ ተከታታይ የሪፎርም ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡
ከእነዚህ ስኬታማ ተግባራት ጎን ለጎንም ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን የጸጥታ ችግሮች በመፍታት ፈተናዎችን እንድትሻገር ያስቻሉ የተልዕኮ ሥራዎች በበጀት ዓመቱ መከናወናቸው ተገምገሟል።
የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ አፈጻጸም በተገመገመበት መድረክ በበጀት ዓመቱ ከ9 ሺ በላይ መረጃዎች ተቀምረው እንደ አስፈላጊነታቸው ጥቅም ላይ እንዲውሉ መደረጋቸው ተገልጿል፡፡
በአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ተሰብስበውና ተተንትነው ጥቅም ላይ ከዋሉት ከእነዚህ መረጃዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ የተለያዩ የሽብር ቡድኖች እና ኢመደበኛ አደረጃጀቶች እዚህም እዚያም ለመፍጠር እየሞከሯቸው ያሉ የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት የዋሉ መሆናቸው በተቋሙ ዓመታዊ ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ተጠቁሟል፡፡
በዚህም በሽብር ቡድኖች፣ በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በሙስናና በሌሎችም ሕገወጥ እንቅስቃሴዎች ተሳትፎ የነበራቸው ከ3 ሺ በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ተቋሙ በሸኔ የሽብር ቡድን እንቅስቃሴ ላይ ባደረገው መረጃ የማሰባሰብ ሥራ ሁለት ሺ 327 የቡድኑ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና አንድ ሺ 849 ታጣቂዎች ላይም ክትትሉ ተጠናክሮ መቀጠሉን እንዲሁም በበርካታ የሽብር ቡድኑ አባላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ መደረጉ በግምገማው ተመልክቷል፡፡
በቤህነን፣ ጉምዝ፣ ቅማንትና ሎሌች የታጠቁ ቡድኖች ላይም አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ተመሳሳይ የመረጃ ስምሪት ማከናወኑ በግምግማው ተገልጿል፡፡
በተያያዘ ሽብርተኝነትን ለመከላከል ተቋሙ ከውጭ አቻ የመረጃና ደኅንነት ተቋማት ጋር የመረጃ ልውውጥ በማድረግ በንፁሃን ዜጎች ላይ ሊፈፁሙ የነበሩ የሽብር አደጋዎችን በመቀልበስ በዚሁ ሴራ እጃቸው ያለበትን 165 የአልሸባብ አባላት እንዲሁም 121 የአይ ኤስ አባላት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉ በግምገማ መድረኩ ተነስቷል፡፡
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በተለያዩ ተቋማት ላይ ከተፈፀሙ የሙስና ወንጀሎች ጋር በተያያዘ መረጃዎችን አጠናቅሮ በማቅረብ 225 ተጠርጣሪዎች እንዲያዙ ሲደረግ፤ በ691 ተጠርጣሪ ግለሰቦች ላይ ደግሞ መረጃ መሰብሰቡንም በተቋሙ የበጀት አመቱ ዕቅድ አመጻጸም ተጠቁሟል፡፡
በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርና የውጭ ምንዛሪ ዙሪያ በተደረገ ክትትልና እርምጃ ከ61 ሚልዮን 781 ሺ በላይ የኢትዮጵያ ብር፤ ከ1 ሚሊዮን 769 ሺ በላይ የአሜሪካ ዶላር፤ ከ509 ሺ በላይ ዩሮና ከፍተኛ መጠን ያላቸው የተለያዩ ሀገራት የገንዘብ ኖቶች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡
ከሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ጋር በተያየዘም 295 ግለሰቦች፤ ከሕገወጥ የገንዘብ ምንዛሪ ጋር በተያያዘ ደግሞ 117 ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም የተቋሙን ዓመታዊ እቅድ አፈፃፀም ግምግማ ዋቢ በማድረግ መግለጫው ይፋ አድርጓል፡፡
44 ኪሎግራም ወርቅን ጨምሮ በርከት ያለ መጠን ያላቸው ልዩ ልዩ ማዕድናት በአየር መንገድ በኩል ወደ ውጭ ሊወጡ ሲሉ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም ነው የገለፀው፡፡
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በሀገር ውስጥ ከሚገኙ አጋር ተቋማት ጋር በትብብር በመሥራት እንዲሁም ከውጭ ሀገራት አቻ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ሀገራዊ፣ቀጣናዊና ዓለምአቀፋዊ ሥጋቶች እንዲወገዱ ያላሰለሰ ጥረት ማድረጉ በዓመታዊ አፈጻጸሙ እንደተመለከተ የጠቀሰው መግለጫው፤ ተቋሙ የሀገርን ጥቅምና ደኅንነት ለማስጠበቅ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሁንም ከድርድርና ውይይት ይልቅ መንግሥታዊ ሥልጣንን በኃይል ለመያዝ የሚጥሩ እንዲሁም አጋጣሚዎችን በማቀነባበር ዝርፊያ ለመፈጸም የሚፈልጉ የታጠቁ ቡድኖች፣ ፅንፈኛና አክራሪ ኃይሎች ከውጭ ፀረ ሰላም ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ሀገራዊ የጸጥታ ሥጋት ለመደቀን ሙከራ እያደረጉ መሆኑ ተገምግሟል፡፡
ሰሞኑን በአማራ ክልል እየታየ ያለው ሁኔታም ለዚህ አብነት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ቀደም ሲል ከኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች ጋር በተያያዘ በአማራ ክልል የተከሰቱ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ከሚመለከታቸው መንግሥታዊ ተቋማት፣ከሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ጋር ተከታታይ ጥረቶች ቢደረጉም ችግሩ በሚፈለገው መንገድ አልተፈታም ያለው የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ መግለጫ፤ ለዘረፋ የተደራጁ ጥቂት ኃይሎች አሁን ላይ መንግሥታዊ መዋቅሮች እንዲፈርሱ፤የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት እንዲቋርጡ፤ አንዳንድ ከፌዴራል መንግሥት ጋር የሚያገናኙ የመንገድ መሠረት ልማቶች እንዲዘጉ በማድረግ፤ ሕዝቡ ላይ ማኅበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጫና ለመፍጠር ሙከራ እያደረጉ ይገኛሉ።
በክልሉ ያጋጠመው የጸጥታ መደፍረስ በመደበኛው የሕግ ሥርዓት ሊታረም የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ተከትሎ የአማራ ክልል መንግሥት ባደረገው ጥሪ መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ችግሩን ለመፍታት የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መደንገጉን ያስታወሰው መግለጫው፤ የብሔራዊ መረጃና ደኀንነት አገልግሎትም ዐዋጁን የሚያስፈፅመው የጠቅላይ መምሪያ ዕዝን በማስተባበር የክልሉን ሰላምና ደኅንነትን በአጭር ጊዜ ለማረጋገጥ የሚያግዝ ስምሪት ወስዶ እየሠራ መሆኑን አመልክቷል፡፡
በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በዚህ ሕገወጥ እንቅስቃሴ ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ግለሰቦችና ቡድኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰበው የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ መግለጫ፤ አሁንም ችግሩ በውይይትና በድርድር የሚፈታበት መንገድ ዝግ ባለመሆኑ ተከታታይ ጥረቶች እንደሚደረጉ ጠቁሟል፡፡
ከዚህ መንገድ በማፈንገጥ ለዝርፊያ ከተደራጁ ቡድኖች ጋር የሚንቀሳቀሱ አካላት ካሉ በሚጠናቀሩ መረጃዎችና ማስረጃዎች አማካኝነት አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድባቸውና ሕግ የማስከበር ሂደቱም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ እነዚህ ለዘረፋ የተደራጁ ኃይሎች ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር ለሀገር ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነትና ለብሔራዊ ጥቅም መከበር ጉልህ አስተዋጽዖ ሲያበረክት የኖረውን የአማራን ሕዝብ ታሪክ ለማጠልሸት ሞክረዋል፡፡
መላው የክልሉ ነዋሪዎች ግን መንግሥት እያደረገ ያለውን ሕግ የማስከበር እንቅስቃሴ በመደገፍ ሰላማቸውን ለማረጋገጥ እየጣሩ ነው ያለው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መግለጫ፤ ይህንንም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ነሀሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም

የኮሪያ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገብተዋል
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
የኮሪያ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓርክ ጂን ለሥራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ነሀሴ 2 ቀን 2015 ዓ.ም

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ መልዕክት‼️
የኢኒሼቲቭ ልማት ስራዎችን በማጠናከር ጠንካራ የሆነ ኢኮኖሚ እንገነባለን!
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኢኒሼቲቭ ልማት ትኩረት አድርጎ ከሚሰራባቸው ስራዎች አንዱ የለውዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ነው። በዚህ አመት 200,000 ሄክታር መሬት በለውዝ ለማልማት የታቀደ ሲሆን 225,679 ሄክታር መሬትን በማዘጋጀት በ225,395 ሄክታር መሬትን በለውዝ ሰብል መሸፈን ተችሏል።
የሀገራችን መሬት የተሰጣትን ማብቀል ብቻ ሳይሆን እንደ ለውዝ ያሉ ወደ ውጭ በመላክ ላይ ትልቅ ጠቀሜታ ያላቸውን ምርቶችን በማምረት ላይ ትገኛለች። አሁንም ለህብረተሰባችን ኢኮኖሚ ጠቃሚ የሆኑ ምርቶች ላይ በማተኮር የውጪ ኤክስፖርታችንን ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው።

በኦሮሚያ በ2015 በጀት ዓመት ከቱሪዝም ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ ተገኝቷል
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት ቱሪስት ፍሰት ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሁንዴ ከበደ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ክልሉን ከጎበኙት 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ....
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0XyNss9ScW8awr3qGshD4zqjSEj79vcAdWRjsjqkAipVEATLmaADTTeSnjDGsDjyrl&id=100069403920568&mibextid=Nif5oz

በየዓመቱ አምስት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ ህይወታቸው ያልፋል
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
በየዓመቱ አምስት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ ህይወታቸው እንደሚያልፍ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በግብርና ሚኒስቴር የቬተርነሪ ፐብሊክ ኸልዝ ኃላፊው ዶክተር ሲሳይ ጌታቸው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ በሚገኘው የእብድ ውሻ በሽታ ምክንያት ...
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02VPRyofHtRBpYfJt9J4sSzR4b31SibzmvoZDWSvvQBJhCfN7eFrLNqpY38N6NTAZhl&id=100069403920568&mibextid=Nif5oz

በሀገር ውስጥ የተጀመረው የዲኤን ኤ ምርመራ ለህግ ማስከበር ስራው አጋዥ እየሆነ ነው
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
ሀገር ውስጥ የተጀመረው የዲኤን ኤ ምርመራ ውስብስብ የወንጀል ድርጊትን ከወንጀል ስፍራ በተሰበሰበ የዲኤን ኤ ምርመራ በመለየት ለህግ ማስከበር ስራው አጋዥ እየሆነ መሆኑን ፌዴራል ፖሊስ ገለጸ።
በፌዴራል ፖሊስ የዲኤን ኤ ምርመራ ክፍል ኃላፊና ምርመራ ባለሙያ ዋና ኢንስፔክተር ወንድማገኝ ጸጋዬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ምርመራው ሀገር ውስጥ በመጀመሩ ....
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0bN4kJ9iiVeZEZKZSwkoisj5grDhf66UiPNu9MmwrmrgaBgRniD76ozP25QN1h7Hul&id=100069403920568&mibextid=Nif5oz

ዳያስፖራው በሀገራዊ ምክክሩ ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ለማድረግ እየተሠራ ነው
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚኖሩ ዳያስፖራዎች በሀገራዊ ምክክሩ ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን ግርማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አገልግሎቱ ዳያስፖራዎች ገንዘብ በሕጋዊ መንገድ ወደ ....
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0J1NDbxaCncwLsNcq7guLTNdLoJ121qZWp2uxGkjyjcTUv6ii42vLPNT43qBxgk2cl&id=100069403920568&mibextid=Nif5oz

ከውጭ ከተገዛው ማዳበሪያ 96 ነጥብ አራት በመቶው ጂቡቲ ወደብ ደረሰ
📌 የመጨረሻዋ መርከብ 500 ሺህ ኩንታል ዩሪያ ጭና በቅርቡ ወደብ ትደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለ2015/16 የሰብል ዘመን ከውጭ ከገዛው 13 ሚሊዮን 975 ሺህ 520 ኩንታል ውስጥ 96 ነጥብ አራትበመቶው ጂቡቲ ወደብ መድረሱን ኮርፓሬሽኑ አስታውቋል።
ወደብ ከደረሰው 13 ሚሊዮን 475 ሺህ 419 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እስካሁን 11 ሚሊዮን 882 ሺህ 117 ኩንታል ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዟል።
ትላንት (ነሐሴ 1/2015 ዓ.ም) 524 ሺህ 670 ኩንታል ዩሪያ የጫነች መርከብ ጂቡቲ ወደብ የደረሰች ሲሆን፣ የመጨረሻዋ መርከብ ተጨማሪ 500 ሺህ ኩንታል ዩሪያ ጭና በቅርቡ ጂቡቲ ወደብ እንደምትደርስ ይጠበቃል ተብሏል።
ለ2015/16 የሰብል ዘመን ከውጭ የተገዛው የአፈር ማዳበሪያ 13 ሚሊዮን 975 ሺህ 520 ኩንታል ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 2 ሚሊዮን 788 ሺህ 940 ኩንታል ኤን ፒ ኤስ፣ 5 ሚሊዮን 686 ሺህ 580 ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን እና 5 ሚሊዮን 500 ሺህ ኩንታል ዩሪያ መሆኑ ተገልጿል።
ነሀሴ 2 ቀን 2015 ዓ.ል