Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በክልሉ የአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ተኪ ምርቶችን ለማምረት ታቅዷል
****
(ኢ ፕ ድ)

በ2016 በጀት ዓመት አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ተኪ ምርቶችን ለማምረት መታቀዱን የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በአማራ ክልል የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተጀመረ ጀምሮ በዘርፉ በርካታ ውጤቶችን ማስገኘት እንደቻለ ተገልጿል፡፡ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ተፈሪ ታረቀኝ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አዳዲስ የሀገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስተሮችን መሳብ፣ የተኪ ምርቶችን ምርት ማሳደግ፣ ነባር ኢንዱስትሪዎች ላይ ያሉ ማነቆዎችን መፍታት የሚሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጓል፡፡

በንቅናቄው በ2015 በጀት ዓመት በአጠቃላይ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ በተኪ ምርት በማዘጋጀት የውጭ ምንዛሬን ማዳን የተቻለ ሲሆን፤ በ2016 በጀት ዓመት በተኪ ምርቶች አማካኝነት ከአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113230
የውሃ ሀብት ልማትንና አጠቃቀምን በማዘመን ከኢኮኖሚ ችግሮች ለመውጣት ትኩረት ያሻል
*****
(ኢ ፕ ድ)

የውሃ ሀብት ልማትንና አጠቃቀምን በማዘመን ከኢኮኖሚ ችግሮቻችን ለመላቀቅ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ምህንድስና መምህርና ተመራማሪ በፕሮፌሰር መኮንን አያና አስታወቁ፡፡

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ምህንድስና መምህርና ተመራማሪ በፕሮፌሰር መኮንን አያና በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ የውሃ ሀብት ዝናብ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ይህን በዝናብ ጥገኛ የሆነ የውሃ ሀብት አጠቃቀምን በማዘመን ከኢኮኖሚ ችግሮች ለመውጣት ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የውሃ ሀብትና የምግብ ሰብል የማምረት አቅማችን ዝናብ ላይ የተመሠረተ ነው ያሉት ፕሮፌሰሩ፤ ይህን በዝናብ ላይ የተመሠረተ በውሃ ሀብታችን በልማትና አጠቃቀሙን በማዘመን ከብዙ ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻችን መውጣት ይገባል ብለዋል፡፡

ውሃን በትክክል የማልማት አቅም በመገንባት ከብዙ ችግሮች መላቀቅ የሚቻል መሆኑን ተገንዝቦ በልዩ ትኩረት መሥራት እንደሚያስፈልግ አመልክተው፤ በውሃ ዙሪያ የሚሠሩ ተቋማትን.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113231
በኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሁለት ሺህ 802 ጨረታዎች ወጥተዋል
*****
(ኢ ፕ ድ)

በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ሁለት ሺህ 802 ጨረታዎች መውጣታቸውን የግዢና ንብረት ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ 161 የፌዴራል ተቋማት በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ግዢ ለመፈጸም ዕቅድ ማቅረባቸውም ተጠቁሟል፡፡

የግዢና ንብረት ባለሥልጣን ኤሌክትሮኒክስ ግዢ ላይ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ትናንት ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ የተገኙት የግዢና ንብረት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀጂ ኢብሳ እንደገለጹት፤ በተያዘው በጀት ዓመት የፌዴራል መሥሪያ ቤቶች ግዢ ሙሉ ለሙሉ በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ብቻ ይፈጸማል። በዚህ መነሻነትም በኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሁለት ሺህ 802 ጨረታዎች ወጥተዋል፡፡

ከ 169 የፌዴራል ተቋማት 161 ተቋማት በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ግዢ ለመፈጸም ዕቅድ ማቅረባቸውን ጠቁመው፤ ቀሪዎቹ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሥርዓቱን.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113251
ሚኒስቴሩ ነባርም ሆኑ አዲስ ነጋዴዎች ፈቃድ እንዲወስዱ አሳሰበ
****
(ኢ ፕ ድ)

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጫት የወጪ ንግድ ሥራ ፈቃድ አውጥተው የሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎችም ሆኑ ወደ ንግዱ መግባት የሚፈልጉ ነጋዴዎች ሚኒስቴሩ ባዘጋጀው አዲስ የቅድመ ፈቃድ ብቃት መስፈርት መሠረት እስከ ህዳር 15 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ፈቃድ እንዲወስዱ አሳሰበ፡፡

ኢትዮጵያ ከጫት ምርት የምታገኘው የውጭ ምንዛሪ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን በመግለጫው ያስታወቀው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፤ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ነጋዴዎች ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ በመላካቸው፣ የንግድ ሥራ ፈቃድን ለሌላ ወገን በማስተላለፍ ሥራ ላይ መሳተፋቸውና፣ የኮንትሮባንድ ንግድ ከልክ በላይ መስፋፋት የጫት ወጪ ንግድ ገቢ በእጅጉ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113252
የዘውዲቱ ሆስፒታል ማስፋፊያ ግንባታ በአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር እየተከናወነ ነው
***
(ኢ ፕ ድ)

የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ማስፋፊያ ፕሮጀክት በአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር እየተከናወነ እንደሚገኝ የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ማስፋፊያ ግንባታው 33 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱ ተገልጿል፡፡

በትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተወካይ አርክቴክት ነጋሽ መሐመድ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የዘውዲቱ ሆስፒታል ማስፋፊያ የሆስፒታሎችን ግንባታ ደረጃ ባሟላ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል።

የሆስፒታሉ የማስፋፊያ ፕሮጀክት በአንድ ሺህ ስምንት መቶ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ እየተከናወነ መሆኑን የገለጹት አርክቴክት ነጋሽ፤ ከአንድ ዓመት በፊት የተጀመረው የማስፋፊያ ግንባታው አፈጻጸም ከ33 ነጥብ ሶስት በመቶ በላይ መድረሱን አስታውቀዋል።

የግንባታው ሂደት አምስተኛ ወለል ላይ መድረሱን የገለጹት ተወካዩ፤ ግንባታው ስምንት ወለሎች የሚኖሩት በመሆኑ ቀሪ ሦስት ወለሎችን ሥራ በፍጥነት....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113253
የወተት ምርትን ለማሳደግ የሚረዳ የዝርያ ማሻሻያ መመሪያ ተግባራዊ ሊደረግ ነው
*****
(ኢ ፕ ድ)

የወተት ምርትን ለማሳደግ የሚረዳ ሀገር አቀፍ የወተት ላም ዝርያ ማሻሻያ መመሪያ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሚኒስቴሩ የእንስሳትና ዓሣ መሪ ሥራ አስፈጻሚና የወተት ሀብት ልማት ዴስክ ኃላፊ አቶ ለማ ገመዳ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የወተት ምርትን ለማሳደግ የሚረዳ ወጥ የሆነ ሀገር አቀፍ የወተት ላም ዝርያ ማሻሻያ መመሪያ ተዘጋጅቷል።

የወተት ምርት ላይ ያተኮረ የሥነ-ተዋልዶ ባዮቴክኖሎጂ ዘዴዎች አተገባበር የሚል መመሪያ በማዘጋጀት ለተለያዩ ክልሎች መላኩን አመላክተዋል። መመሪያውን ለማዘጋጀት አንድ ዓመት ያክል ጊዜ የወሰደ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ለማ፤ መመሪያው ከክልል እስከ ወረዳ ተግባራዊ እንዲሆን ለ300 ባለሙያዎች ሥልጠና ተሰጥቷል ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ለማ ገለጻ፤ ከዚህ ቀደም በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ የወተት ላም ዝርያ ማሻሻያ መመሪያ ባለመኖሩ የወተት ምርትን በሚፈለገው መጠን ማሳደግ አልተቻለም፡፡ አሁን የተዘጋጀው መመሪያ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113254
አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከተሰናባቹ የተመድ የልማት ፕሮግራም ተወካይ ቱርሃን ሳልህ ጋር ተወያዩ
******
(ኢ ፕ ድ)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ቆይታቸው ካጠናቀቁት የተመድ የልማት ፕሮግራም ተወካይ ቱርሃን ሳልህን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

የተመድ የልማት ፕሮግራም ተወካይ ቱርሃን ሳልህ በበኩላቸው፤ ድርጅቱ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እና ከብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ጋር በአቅም ግንባታ ላይ በቅርበት ሲሰራ መቆየቱን በውይይቱ ተገልጿል።

የተመድ የልማት ፕሮግራም በአገሪቱ የተለያዩ ተቋማት አቅም በማሳደግ ረገድ ያለውን ሚና አሰታወሰው፣ መንግሥት ከተመድ የልማት ፕሮግራም (UNDP) ጋር ላለው ግንኙነት ትልቅ ቦታ እንደሚሰጥ አምባሳደሩ ገልጸዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ የተመድ የልማት ፕሮግራም በኢትዮጵያ ከአራት ዓመታት በላይ በተለያዩ ተቋማት አቅም ግንባታ ላይ ሲሰሩ የቆዩትን ቱርሃን የግል አመራር አድንቀው ለቀጣይ የስራ ጊዜ መመኘታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም
"ኢትዮጵያ ለዳታ ማዕከላት ልማት ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነው" በለጠ ሞላ (ዶ/ር)
******
(ኢ ፕ ድ)

የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እውን ለማድረግ ለዳታ ማዕከላት ልማት ትኩረት በመስጠት እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ።

የዳታ ማዕከላትን ለፋይናንስ ዘርፍና ለአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጅማሮ ማዋል የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ባለድርሻ አካላትና ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የዳታ ማዕከላትን ለማልማት ከተለያዩ አካላት ጋር እየሰራች መሆኑን ገልፀዋል። ለአብነትም በአራት አፍሪካ ሀገራት ውስጥ አገልግሎት እየሰጠ ያለው ዊንጉ አፍሪካ በአይሲቲ ፓርክ ውስጥ ኢንቨስት ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡

የአይ ሲቲ ፓርክ ኮርፖሬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ሄኖክ አህመድ በበኩላቸው፤ የግሉ ዘርፍ በዳታ ማዕከላት ልማት እንዲሳተፍ ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን ገልፀዋል። ከ ዊንጉ አፍሪካ በተጨማሪም በቀጣይ ወደ ገበያው የሚገቡ አስር የዳታ ማዕከላት በሂደት ላይ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

የዳታ ማዕከላት ልማት መስፋፋት የፋይናንስ ተቋማት የራሳቸውን ዳታ ማዕከል መገንባት ሳያስፈልጋቸው አገልግሎት ወደሚያቀርቡት ድርጅቶች በመሄድ መገልገል እንዲችሉ ዕድል ስለሚሰጥ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።

በተስፋ ፈሩ

ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም
በሰመራ በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባ ሪፈራል ሆስፒታል የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ
*******
(ኢ ፕ ድ)

በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባው ደረጃውን የጠበቀ ሪፈራል ሆስፒታል በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

ርዕሰ መስተዳደር አወል ሆስፒታሉ ለህብረተሰቡ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዲሰጥና ለከተማዋ የሚመጥን ተደርጎ እንደሚገነባ ተናግረዋል።

በዋናው የአገሪቱ አውራ መንገድ ላይ የምትገኘው ሰመራ ከተማ ላለፉት ዓመታት የሪፈራል ሆስፒታል ሳይኖራት መቆየቷን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ የሚገነባው ሆስፒታል ከከተማዋ ነዋሪዎች ባለፈ የከተማዋን ዋናው ጎዳና ለሚጠቀሙ አካላትም እንደሚያገለግል መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ ስርዓት ላይ የተገኙት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ያሲን ሃቢብ በበኩላቸው እንዳሉት ሆስፒታሉ በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ ደረጃውን ጠብቆ ይገነባል።

የሰመራና የአካባቢው ነዋሪዎች ለዓመታት ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ደሴ፣ መቀሌ፣ አዳማ እንዲሁም አዲስ አበባ እንደሚጓዙ አስታውሰው፣ "የሆስፒታሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ ወደተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ለሕክምና የሚደረገውን ጉዞ ያስቀራል" ብለዋል።

የሪፈራል ሆስፒታሉ በመንግስት በጀት፣ በአጋሮች ተሳትፎ እና በህብረተሰቡ የተጠናከረ ትብብር እንደሚገነባም አመልክተዋል። ሆስፒታሉ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ለሰመራ ሎጊያና አካባቢው ማህበረሰብ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን እንደሚሰጥ ተመላክቷል።

ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ካለማቸው 21 የቴክኖሎጂ ስርዓቶች ሶስቱን ወደ ሰራ አስገባ
*******
(ኢ ፕ ድ)

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ለሁለት ዓመታት ካለማቸው 21 የቴክኖሎጂ ስርዓቶች ሶስቱን አስመርቆ ወደ ሰራ አስገብቷል።

በመርሃግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ ኢትዮጵያ እንደ ሃገር እየሰራችበት ያለችውን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከማሳደግ አንጻር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ብለዋል።

ሲስተሞቹ ሉሲ (lucy )፣ ብቁ (BEQU)እና ሲኦሲ (COC) ይሰኛሉ ያሉት ሚኒስትሯ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር አብረው መስራታቸውን አስታውቀዋል።

በዳግማዊት አበበ

ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም
የፓኪስታን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዕዋለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱም ጥሪ ቀረበ
*******
(ኢ ፕ ድ)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር ሚያን አጢፍ ሸሪፍ ጋር የሁለቱ ሀገራት ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ በጽህፈት ቤታቸው ውይይት አድርገዋል።

በኢትዮጵያና በፓኪስታን መካከል በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በአቪዬሽን፣ በባህልና ቴክኒክ ድጋፍ ዙሪያ ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የፓኪስታን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዕዋለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱም ጥሪ አቅርበዋል።

አምባሳደር ሚያን አቲፍ በበኩላቸው ፓኪስታን ከኢትዮጵያ ጋር በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ያላትን ትብብር ለማሳደግ ፅኑ ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣በፋርማሲዩቲካልና በኮንስትራክሽን ዘርፍ ያላትን ትልቅ የኢንቨስትመንት አቅም የፓኪስታን ባለሃብቶች እንዲጠቀሙበት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም