Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#ዲፕሎማሲያችን_ለብሔራዊ_ጥቅማችን

"ዲፕሎማሲያችን ለብሔራዊ ጥቅማችን" በሚል መሪ ሃሳብ የተከፈተው የዲፕሎማሲ አውደ ርዕይ በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እየተጎበኘ ይገኛል።

አውደ ርዕዩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው።
በዛሬ ማለዳ መርሀ ግብር የኮከበ ጽባህ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሳይንስ ሙዚየም ተገኝተው አውደ ርዕዩን ጎብኝተዋል።

በሳሙኤል ወንድወሰን
የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም
የደብረብርሃን - አንኮበር አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ዋና ዋና ሥራዎች ተጠናቀቁ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
የደብረብርሃን - አንኮበር 42 ኪሎሜትር አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ዋና ሥራዎች የተጠናቀቁ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ።

ቀሪ ውስን ሥራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ነውም ብሏል፡፡
አሁን ላይ ከግንባታው አጠቃላይ ሥራ 98 በመቶው ተጠናቋል።

ከግንባታ ሥራዎች መካከል የ39 ኪሎሜትር የአስፋልት ንጣፍ ፣ የውኃ መፋሰሻ ቱቦ ፣ ሰብቤዝ ፣ የመንገድ ዳር የአደጋ መከላከያ አጥር እንዲሁም የትራፊክ ጠቋሚ ምልክቶች የማቅለም ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡

ሀገር በቀሉ ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘ ሲሆን ፣ የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን ደግሞ ኮር ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

ፕሮጀክቱን ለማካሄድ የተመደበው አንድ ቢልዮን ስድስት መቶ ሃያ ሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ ዘጠና አራት ብር በፌደራል መንግስት በጀት የተሸፈነ ነው ተብሏል።

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኘው ይህ መንገድ በጠጠር ደረጃ ተገንብቶ ላለፉት በርካታ ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ነው፡፡

ሆኖም ግን ከአገልግሎት ብዛት አኳያ መጎዳቱ ፤ የቦታው አስቸጋሪ ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ በጠጠር ደረጃ ለነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት አመቺ አለመሆኑ እንዲሁም ያለው በርካታ ሀገራዊ እና ማኅበራዊ ጠቀሜታ ከግምት ውስጥ ገብቶ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እየተገነባ ይገኛል፡፡

ከዚሁ የደብረብርሃን-አንኮበር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በተጨማሪ የአንኮበር-ዱለቻ እና የዱለቻ-አዋሽ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ሶስት ፕሮጀክቶች ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቁ ከዚህ ቀደም ወደ አፋር ለመሄድ ይወስድ የነበረውን ዙሪያ ጥምጥም ጉዞ ለማስቀረት እንደ አማራጭ ሆነው ያገለግላሉ፡፡

የአንኮበር ከተማ የተለያዩ ታሪካዊ ቅርሶችን በውስጡ የያዘው የአጼ ምኒሊክ ቤተመንግስት መገኛ በመሆኑ ፣ መንገዱን ለቱሪስቶች ምቹ በማድረግ በኩል ግንባር-ቀደም ሚና ይጫወታል፡፡

በተጨማሪም ምቹ የትራንስፖርት ፍሰት እንዲኖር በማስቻል የኅብረተሰቡን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በእጅጉ የሚያቃልል ከመሆኑም ባሻገር ምርት በቀላሉ ወደ ማዕከላዊ ገበያ እንዲደርስ በማስቻል የአርሶ-አደሩን ተጠቃሚነት ይጨምራል ተብሏል፡፡

የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም
የእናትነት ወር ለቅድመ ወሊድ ክትትል ትኩረት ሰጥቶ ተከብሯል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በኢትዮጵያ ለ18ኛ ጊዜ የተከበረው የእናትነት ወር ለቅድመ ወሊድ ክትትል ትኩረት የሰጠ እንደነበር የአዲስ አበባ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የእናቶችና ሕፃናት ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሪት ስንዱ መኩሪያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ የእናትነት ወሩ ከጤና ሚኒስቴርና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በከተማዋ በሚገኙ 11 ክፍለ ከተሞችና 11 የመንግሥት ሆስፒታሎች ተከብሯል።

“ፍትሐዊ ተደራሽነትና ጥራት ያለው የቅድመ ወሊድ ክትትል በማስጀመር ጤናማ እናትነትን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል በተደረገው ንቅናቄ የቅድመ ወሊድ ክትትል ጠቀሜታ ላይ ሰፊ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ተሠርቷል። እናቶች ካረገዙበት ሰዓት ጀምሮ ወይም ነፍሰ ጡር መሆናቸውን ካወቁበት ጊዜ ጀምሮ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=120663
በዞኑ ከ300 በላይ የገጠር ትምህርት ቤቶች ‘ቡኡረ ቦሩ’ ከፍተዋል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን 305 የገጠር ትምህርት ቤቶች ቡኡረ ቦሩ (የገጠር ትምህርት ቤቶች መዋዕለ ሕፃናት) ከፍተው አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት ብቻ 85 የገጠር ትምህርት ቤቶች ቡኡረ ቦሩ ከፍተዋል፡፡

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቶሎሳ ተፈራ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በገጠር ትምህርት ቤቶች የቅድመ መደበኛ ትምህርት አለመሰጠቱ በትምህርት ጥራት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያመጣ ቆይቷል፡፡

የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እንደመንግሥት ትኩረት ተሰጥቶ የሕፃናት ትምህርትን ባካተተ መልኩ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ሥራ ተሠርቷል፡፡
በዚህም ዞኑ በገጠር ትምህርት ቤቶች የመዋዕለ ሕፃናት...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=120637
በጋምቤላ የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት የመሰብሰብ ሥራ በየካቲት መጨረሻ ይጀመራል
**********
(ኢ.ፕ.ድ)
በጋምቤላ የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት የመሰብሰብ ሥራ በተያዘው የየካቲት ወር መጨረሻ ሳምንት እንደሚጀመር የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡጁሉ ሉአል ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በዘንድሮ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ወደ 14 ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል፡፡

በአንድ ሄክታር መሬት 35 ኩንታል የስንዴ ምርት እንደሚጠበቅ የጠቆሙት አቶ ኡጁሉ፤ የደረሰውን ምርት ከማሰባሰብ በተጨማሪ 41 ሄክታር መሬት ላይ ተጨማሪ ስንዴ ለመዝራት ዝግጅት መደረጉን አመላክተዋል።

ለአካባቢው የሚስማማ የስንዴ ምርጥ ዘር ከግብርና ምርምር ተቋምና ከግብርና ኮርፖሬሽን ለማግኘት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል። በዘንድሮ የበጋ መስኖ ስንዴ ሥራ በክልሉ ሰፊ መሬት በስንዴ ምርት ለመሸፈን መታቀዱን የተናገሩት አቶ ኡጁሉ፤...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=120664
በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረ ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ወርቅ ተያዘ
******
(ኢ.ፕ.ድ)

በህገ- ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ወርቅ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

ተጠርጣሪው ሊያዝ የቻለው አንድ ኪሎ ግራም ወርቅ በሻንጣ ውስጥ ደብቆ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሕገ-ወጥ መንገድ ከሀገር በማስወጣት ላይ እንዳለ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባደረገው ጥብቅ ፍተሻ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እያተጣራበት እንደሚገኝ ታውቋል።

የተያዘው ህገ-ወጥ ወርቅም በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ በኤግዚቢትነት ተይዞ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል።

የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሸበሌይ ሪዞርት ግንባታ ስፍራን ጎብኝተዋል
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት ከ’ገበታለትውልድ’ የልማት ቁልፍ ስፍራዎች አንዱ ሆኖ በሶማሌ ክልል የሚገኘውን የሸበሌይ ሪዞርት ግንባታ ስፍራ ጎብኝተዋል።

ከጅግጅጋ ከተማ 29 ኪሎ ሜትር ርቀት 385 ሄክታር በሚሸፍን ስፍራ ላይ የሚገነባው ኘሮጀክት የጅግጅጋ ከተማ እና አካባቢውን ወደ ግምባር ቀደም የቱሪዝም መዳረሻነት የሚለውጠው የቱሪዝም ስራ አምድ አካል ነው።

ይህ ስራ ኢትዮጵያ የያዘችውን የዘላቂ ቱሪዝም ስራ እና የኢኮኖሚ እድገት መንገድ አጉልቶ የሚያሳይ ነው።

የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም
“የባህር በር ስምምነቱ ጅግጅጋን የምሥራቅ አፍሪካ ዱባይ ለማድረግ ምቹ ዕድል ይፈጥራል”
- ኢንጅነር ሻፊ አህመድ የጅግጅጋ ከተማ ከንቲባ
*******
(ኢ.ፕ.ድ)

ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ ያደረጉት ስምምነት ጅግጅጋ ከተማን የምሥራቅ አፍሪካ ዱባይ ለማድረግና ልማቷን ለማፋጠን እንዲሁም ሕዝቡን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ምቹ ዕድል ይፈጥራል ሲሉ የጅግጅጋ ከተማ ከንቲባ ኢንጅነር ሻፊ አህመድ ገለጹ።

ኢንጅነር ሻፊ አህመድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የባህር በር ስምምነቱ ወደ ተግባር
ሲገባ ጅግጅጋ ከተማ የመተላለፊያ ማዕከል (ኮሪደር) ትሆናለች። ይህን ተከትሎም ብዙ ሎጅስቲክስ ፣ ንግድና የሰው ኃይል የሚንቀሳቀስበት ከተማ መሆኗ አይቀርም።
ይህም ስምምነቱ ጅግጅጋን የምሥራቅ አፍሪካ ዱባይ ለማድረግ ምቹ ዕድል ይፈጥራል።

ከተማዋን የምሥራቅ አፍሪካ መተላለፊያ ማዕከልና ዱባይ ለማድረግም ከአሁኑ ጀምሮ ሥራዎች እየተሠሩ
ነው ያሉት ኢንጂነር ሻፊ፤ ይህን ታሳቢ ....https://www.facebook.com/share/p/6kZzbcpSXh75qT2p/?mibextid=2JQ9oc
በበጀት ዓመቱ አራት አዳዲስ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጀምሯል
***
(ኢ.ፕ.ድ)

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በዘንድሮ በጀት ዓመት አራት አዳዲስ የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ ማስጀመሩን አስታወቀ።

በሚኒስቴሩ የመስኖ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ብርሃኑ ሌንጂሶ (ዶ/ር) ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በዘንድሮ በጀት ዓመት አራት አዳዲስ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታን አስጀምሯል።

ሁለቱ የመስኖ ፕሮጀክቶች ማለትም ሽኒሌና አዳበቹ የከርሰ ምድር ሲሆኑ፤ ሎግያና ፈንታሌ ደግሞ የገጸ ምድር ናቸው።

የመስኖ ፕሮጀክቶቹ በአፋር፣ በሶማሌና በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ናቸው ያሉት ብርሃኑ ሌንጂሶ (ዶ/ር)፤ እነዚህን ፕሮጀክቶች ....https://www.facebook.com/share/p/15gCwXGHaTdaKMWg/?mibextid=2JQ9oc
“የካናዳ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ሰፊ ጥረትእየተደረገ ነው”
- ፍጹም አረጋ በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር
****
(ኢ.ፕ.ድ)

በማዕድንና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ከፍተኛ አቅም ያላቸው የካናዳ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ተናገሩ።

አምባሳደር ፍጹም አረጋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያና ካናዳ ያላቸውን የ70 ዓመት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በኢኮኖሚው ዘርፍ እየተሠራ ነው።

ኢትዮጵያና ካናዳ በትምህርት፣ በአቪዬሽን፣ በማዕድን፣ በአግሮ ፕሮሰሲንግና በሌሎች ዘርፎች ከፍተኛ ግንኙነት እንዳላቸው ጠቁመው፤ ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት አማራጮች ለካናዳ ባለሀብቶች በማስተዋወቅ በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እየተሠራ ነው ብለዋል።

በካናዳ በማዕድን ልማቱ ከፍተኛ አቅምና ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ያላቸው ኩባንያዎች እንደሚገኙ ገልጸው፤ ኢትዮጵያ ያሏትን ....https://www.facebook.com/share/p/NjGqknQo8U3Jcef1/?mibextid=2JQ9oc
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባሕር ዳር ከተማ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ተመለከቱ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የፌዴራል መንግሥት ልዑክ ከትናንት ጀምሮ በክልሉ የልማት ሥራዎች ዙሪያ ከክልሉ መንግሥት አመራሮች ጋር እየመከሩ ነው።

ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እንዲሁም የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በባሕር ዳር ከተማ የሚገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

እንደ አሚኮ ዘገባ፤ የአዲሱን የዓባይ ድልድይ የግንባታ ሂደት የተመለከቱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው ብሔራዊ ባንክ እያስገነባው ያለውን ሕንጻም በቦታው ተገኝተው አስጀምረዋል።

በመጨረሻም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታን ተመልክተዋል።

የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም