ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጅግጅጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ዉሀ ፕሮጀክትን ጎበኙ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዛሬዉ እለት በሶማሊ ክልል 2ኛዉን ዙር የጅግጅጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ዉሀ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ እና ከሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በዛሬዉ እለት 2ኛዉን ዙር የጅግጅጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ዉሀ ፕሮጀክት የስራ እንቅስቃሴን መመልከታቸውን ከክልሉ መገናኛ ብዙኃን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታለመለት የነዳጅ ድጎማ 28 ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል
***
(ኢ.ፕ.ድ)
አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ለመደጎም የነዳጅ ድጎማ ተግባራዊ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ለታለመለት የነዳጅ ድጎማ 28 ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የሚኒስቴር መስራ ቤቱን የ2016በጀት ዓመት የስድስት ወራት አጠቃላይ እቅድ አፈጻጻሙን ያቀረቡት የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ኡርጌሳ ባይሳ የድጎማ ስርዓቱ ተግባራዊ መደረግ መንግስት የነበረበትን 180 ሚሊዮን ብር በማቃለል ወደ117.5 ሚሊዮን ብር ማውረድ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
የድጎማ ስርዓቱ ተግባራዊ ከተደረገ ጀምሮ 199 ሺ333 ተሸከርካሪዎች የስርዓቱ ተጠቃሚ ሲሆኑ ባለፉት ስድስት ወራት ሁለት ሚሊዮን 19 ሺህ 455 ሜትሪክ ቶን ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው.መረጃ ያሳያል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት ‼️
ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር በመሆን የጂግጂጋ ዱቄት እና ዳቦ ፋብሪካን አስመርቀናል። ይህ ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጠው ፕሮጀክት በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት እየተሰሩ ካሉ ደሃ ተኮር ስራዎች አንዱ ሲሆን በመላው ሀገራችን እየተሰሩ ካሉ 12 መሰል ፋብሪካዎች ስምንተኛው ነው። ለዘላቂ ልማት በምናደርገው ስራ እና ህዝባችንን ለመደገፍ ባለን ጥረት የተገኘ አንድ ርምጃ ነው።

የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባት ጀመሩ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
በ44ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚዎች ምክር የሚሳተፉ የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።
ከትላንት ምሽት ጀምሮ የሶማሊያ ፣ ቡሩንዲ ፣ ኬኘቨርዲ ፣ ኮሞሮስ እና የካሚሮን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገብተዋል።
የህብረቱ የአስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል።

በተያዘው በጀት ዓመት የ103 ቢልዮን ብር ግዢ መፈፀሙን ተገለፀ
****
(ኢ.ፕ.ድ)
በተያዘው በጀት ዓመት የ103 ቢሊዮን ብር ግዢ እንደተፈፀመ የፌደራል ግዢ እና የንብረት ቁጥጥር አስተዳደር አስታወቀ።
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሐጂ ኢብሳ እንዳሉት፤63 በመቶ የሀገሪቱ በጀት ለግዢ ይውላል።
ይህ ከፍተኛ ወጪ የሚወጣበት የግዢ ሂደት ዘመናዊ የቁጥጥር አሰራር ተዘርግቶለት እየተተገበረ ይገኛል።
በመሆኑም በዚህ የግጭ ሥርዓት ያልተካተቱ ክልሎች ጥቂት እንደሆኑ በመጥቀስ፤አሰራሩ ለመዘርጋት እንደ ፌደራሉ ሊፈጥን ባይችልም እየተሰራ ነው ብለዋል።
ሥርዓቱን ለመዘርጋት እንቅፋት ከሆኑት ዋነኛ ምክንያቶች ኢንፍራስትራክቸር እንደሆነ በመጥቀስ፤ይህም በሂደት የሚፈታ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በሔርሞን ፍቃዱ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች በዓለም መንግሥታት ጉባኤ እየተሳተፉ ነው
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም መንግሥታት ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቆይታቸው ወቅት በከተማ ፕላን እንዲሁም የወደፊት ከተሞችን በተመለከተ ከሚኖራቸው ውይይት በተጨማሪ በሌሎች መድረኮች እና የፓናል ውይይቶች ላይ በመታደም የወደፊት የአስተዳደር ዘርፎች ላይ የሚያተኩሩ የጎንዮሽ ውይይቶች ላይ የሚሳተፉ ይሆናል::
በውይይት መድረኩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢ/ር አይሻ መሃመድ እንዲሁም የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሃብታሙ ኢተፋ ተሳታፊ ሆነዋል::