የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️
ዛሬ ጠዋት ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሃፊ ሞሊ ፊ፣ እና የአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክል ሀመር ጋር በአህጉራዊ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት ለማድረግ ተገናኝተናል።
የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም

የባህር በር ስምምነቱ የቀጣናውን ሀገራት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከር የሚያስችል ነው
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የባህር በር ስምምነቱ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ሀገራትን የኢኮኖሚ ትስስርን በማጠናከር ዕድገታቸውን በፈጣን ሁኔታ ማሳደግ የሚያስችል ነው ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ሽመልስ ኃይሉ ገለጹ፡፡
መምህር ሽመልስ ኃይሉ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ሀገራት በወደብ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ኢኮኖሚያዊ ትስስራቸውን ካጠናከሩ የተሻለ ዕድገት ማስመዝግብ ይችላሉ።
በቀጣናው ያለውን ሀብት ይበልጥ ለመጠቀም ሀገራቱ የተሻለ ትስስር መፍጠር ይገባቸዋል ያሉት መምህሩ፤ ከጦርነት ይልቅ በጋራ የመልማት ልምድን በማዳበት የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን የተሻለ መጥቀም የሚቻልበት ሰፊ አማራጭ መኖሩን ጠቁመዋል።
የባህር በር ለኢትዮጵያ ቅንጦት ሳይሆን የሀገርን ሉዓላዊነት፣ ኢኮኖሚ፣ ደህንነትና ወታደራዊ እንቅስቃሴን የሚወስን በመሆኑ ለነገ የሚተው ጉዳይ እንዳልሆነ አንስተዋል። ቀይ ባህርና የኤደን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=120828

የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ‼️
ኢትዮጵያ “የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩትን የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ በማገናኘትና ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም እንዲመጡ አድርጋለች።
በዚሁ መሰረት ግንቦት 1955 ዓ.ም. 32 መስራች አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።
ለዚህ ድርጅት እውን መሆንም ኢትዮጵያ በመሪዋ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የመሪነት ሚና ተጫውታለች።
በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱ አማረኛ ነበር።

44ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ተጀመረ
📌 አማርኛ የህብረቱ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ጥያቄ ቀርቧል
****
(ኢ.ፕ.ድ)
44ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በስብስባው ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳፋኪ መሃመት፣ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ፣ የሕብረቱ አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና ዲፕሎማቶች፣ የሕብረቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ ቀጣናዊ የአፍሪካ ተቋማት ኃላፊዎች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ ባደረጉት ንግግር፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለአፍሪካውያን ችግሮች አፍሪካዊ መፈትሔ በሚለው እሳቤ እየሰራበት ነው። በዚህም በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተከሰተውን ችግር ተከትሎ የተደረሰውን የፕሪቶሪያ
የሰላም ስምምነት ተግባራዊ እያደረገ ነው ብለዋል።
እንዲሁም ሀገራዊ የምክክር ኮምሽን ተቋቋሞ የሚከሰቱ ችገሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን አንስተው፤ አማርኛ ቋንቋ የህብረቱ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ጥያቄ አቅርበዋል።
ምክር ቤቱ በስብሰባው በአፍሪካ የልማት አጀንዳዎች ላይ ስትራቴጂካዊ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ኢንዲሁም በንግድ፣ በትምህርት፣ በወጣቶችና ሴቶች፣ በግብርና፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በሰላምና ፀጥታ እንዲሁም በሌሎች የአህፍሪካን የ2063 አጀንዳ ዕውን ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች በጥልቀት ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።
ስብሰባው ዛሬና ነገ የሚካሄድ ሲሆን 37ኛው የህብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ደግሞ የካቲት 9 እና 10 ቀን 2016 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል።
በቃልኪዳን አሳዬ

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከጣሊያን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጋር ተወያዩ
***
(ኢ.ፕ.ድ)
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከጣሊያን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አድሚራል ጁሴፔ ቻቮ ጋር ተወያዩ።
በጣሊያን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አድሚራል ጁሴፔ ቻቮ የተመራ ልዑክ መከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ሲደርስ በጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና በጀነራል መኮንኖች አቀባበል ተደርጎለታል።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከጣሊያን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አድሚራል ጁሴፔ ቻቮ ጋር ሁለቱ ሀገራት በወታደራዊ ትብብር ዙሪያ አብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት አድርገዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ በሌላ መልኩም ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን መልካም ግንኙነት ማጠናከርና በጋራ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ዙሪያ ተወያይተዋል።

የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ ‼️
#አህመድ_ቤን_ቤላ
“የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩት የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ ተገናኝተው ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም መጥተው ግንቦት 1955 ዓ.ም. 32 የአፍሪካ አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።
ይህንን ድርጅት ከመሰረቱ የአፍሪካ አባቶች መካከል የቀድሞው የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት አህመድ ቤን ቤላ አንዱ ናቸው።
በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱ አማረኛ ነበር።
#አህመድ_ቤን_ቤላ
“የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩት የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ ተገናኝተው ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም መጥተው ግንቦት 1955 ዓ.ም. 32 የአፍሪካ አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።
ይህንን ድርጅት ከመሰረቱ የአፍሪካ አባቶች መካከል የቀድሞው የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት አህመድ ቤን ቤላ አንዱ ናቸው።
በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱ አማረኛ ነበር።
አማርኛ የአፍሪካ ህብረት የስራ ቋንቋ እንዲሆን ኢትዮጵያ ጠይቃለች‼️
44ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በዚህ ጉባዔ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ አፍሪካ ህብረት የአማርኛ ቋንቋን የስራ ቋንቋው እንዲያደርግ ጥያቄ አቅርበዋል።
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ግንቦት 17 ቀን 1955 ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ ተመሥርቶ የድርጅቱ መመሪያ ውል በ32 መሥራች አገር መሪዎች ጸድቆ ተፈርሟል።
የምሥረታ ቻርተሩ ከተዘጋጀባቸው አራት ቋንቋዎች መካከል አማርኛ አንዱ ነበር።
የድርጅቱም ፅኅፈት ቤት በአዲስ አበባ እንዲሆን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት እስካሁን ድረስ በአዲስ አበባ ላይ ይገኛል።
ይህ ድርጅት በ1994 ዓ/ም የአፍሪካ ኅብረት በሚባለው ስያሜ ተተክቷል።
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሰረተበትና በአማረኛ የተጻፈውን ቻርተር ከስር ይመልከቱ

#ምዋሚ_ምዋምቡትሳ IV
“የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩት የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ ተገናኝተው ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም መጥተው ግንቦት 1955 ዓ.ም. 32 የአፍሪካ አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።
ይህንን ድርጅት ከመሰረቱ የአፍሪካ አባቶች መካከል የቀድሞው የብሩንዲ ንጉሥ ምዋሚ ምዋምቡትሳ IV አንዱ ናቸው።
በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱ አማረኛ ነበር።
(ኢ.ፕ.ድ የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም)