የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ
***
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ እና ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር ጋር በዛሬው እለት ተወያይተዋል።
አምባሳደር ታዬ ለልዑካን ቡድኑ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ሂደት ላይ ገለፃ የሰጡ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት በስምምነቱ አፈፃፀም ላይ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
አክለውም የሽግግር ፍትህ እና ብሔራዊ ምክክር ሂደት ዝግጅቶች ያሉበትን ደረጃም አብራርተዋል።
በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከስዋቲኒ አቻቸው ፎሊል ሻካንቱ ጋር ተወያዩ
******
(ኢ ፕ ድ)
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከስዋቲኒ አቻቸው ፎሊል ሻካንቱ ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያዩ።
በሁለትዮሽ፣ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ማዕቀፍ በተመለከተ የልምድ ልውውጥ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ መክረዋል። ሁለቱ አገሮች በመካከላቸው የንግድ ግንኑኝነት ለመመስረት ከመግባባት ደርሰዋል።
የልዑካን ቡድኑ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉብኝት አድርጓል።

ኢትዮጵያና ካናዳ ያላቸውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በትኩረት ይሰራሉ
*****
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያና ካናዳ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በትኩረት እንደሚሰሩ የሁለቱ ሀገራት የፓርላማ አባላት ገለጹ፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የካናዳ የፓርላማ አባላት በሁለቱ ሀገራት ሁለንተናዊ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡
የቋሚው ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ፈትሂ ማህዲ እንዳሉት፣ የውይይቱ ዓላማ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ነው፡፡
የኢትዮጵያና የካናዳ ዲፕሎማሲያዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ከተመሰረተ ግማሽ ክፍለ ዘመናት ማስቆጠሩን ተናግረዋል።
የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ መሆኑንም አክለዋል፡፡
ይህ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢንቨስትመንትና በአየር ንብረት ለውጥ ዘርፎች እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡
ድህነት ቅነሳ፣ ምግብ ዋስትና፣ ግብርና እና ዘላቂ ልማት ደግሞ ሌላኛው የሁለቱ ሀገራት የትብብር መስክ መሆኑን አመልክተዋል።
በቀጣይም ግንኙነታቸውን በማህበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል፡፡
የካናዳ የፓርላማ አባል አሚና ገርባ በበኩላቸው፤ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር የሚያስችል ፍሪያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ በቀጣይም ካናዳ ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች ትብብሯን አጠናክራ የምትቀጥል መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአሁና ኢዛኩኗ ጋር ተወያዩ
*****
(ኢ ፕ ድ)
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ጸሃፊ ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ረዳት አስተዳዳሪ እና የአፍሪካ ሪጅናል ዳይሬክተር ከሆኑት አሁና ኢዛኩኗ ጋር ውይይት አድርገዋል::
በውይይታቸው በቀጣይነት በወጣቶችና በሴቶች የስራ እድል ፈጠራ እንዲሁም በተለያዩ የልማት አጀንዳዎች ዙሪያ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)
በአፍሪካ ህብረት 37ኛው መደበኛ ጉባኤ ጅማሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን ፕሬዝዳንት አኪንዉሚ አዴሲና ጋር ተወያዩ።
ባንኩ በኢትዮጵያ እያደረገ ስላለው ትብብር እና ጥረት አጠር ያለ ውይይት ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የካቲት 9 ቀን 2016 ዓ.ም

በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ችግሮችን በንግግር ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው
*****
(ኢ ፕ ድ)
👉 በተደረጉ ሕዝባዊ ውይይቶች ጠቃሚ ግብዓቶች ተገኝተዋል
በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በተለይ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመሩ ጥረቶችን ማስቀጠል የመንግሥት ጽኑ አቋም መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነትና የውጭ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ገለጹ። ሰሞኑን በተለያዩ ክልሎች ከተደረጉ ሕዝባዊ ውይይቶችም ጠቃሚ ግብዓት መገኘቱን ተናግረዋል።
አቶ አዲሱ ሰሞኑን የተካሄዱ የሕዝብ ውይይት መድረኮችን ዓላማና ስኬት አስመልክተው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፣ የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች እስከታች ወርደው ከሕዝቡ ጋር ውይይት እንዲያደርጉ የተፈለገበት ዋነኛ ምክንያት፣ በመንግሥት የሚወርዱ ሀገራዊ አጀንዳዎች ተግባራዊነታቸው ያለበትን ደረጃ ለመረዳትና አሁናዊውን የሕዝብ ጥያቄ በተገቢው መንገድ በማጤን ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ነው።
በዚህም መሠረት የጸጥታ ችግር፣ የኑሮ ውድነት፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ሥራ አጥነት በቅደም ተከተል ከሕዝቡ የተነሱ ቁልፍ ጉዳዮች መሆናቸውን አቶ አዲሱ ገልጸዋል።
የለውጡ መንግሥት ወደ ሥልጣን ሲመጣ ዘላቂ ሰላም፣ ሁለንትናዊ ብልጽግና፣ ጠንካራ ዲፕሎማሲና አሳታፊ የዴሞክራሲ ሥርዓት
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=121031

የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ‼️
#ቤኒን
#ሁበርት_ማጋ
ኢትዮጵያ “የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩትን የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ በማገናኘትና ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም እንዲመጡ አድርጋለች።
በዚሁ መሰረት ግንቦት 1955 ዓ.ም 32 መስራች አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።
ለዚህ ድርጅት እውን መሆን ፊርማቸውን ካኖሩ አገራት መካከል የቀድሞ ቤኒን ፕሬዚዳንት ሁበርት ማጋ አንዱ ናቸው።
በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱ አማረኛ ነበር።

የ51 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃ እየተጣራ ነው
******
(ኢ ፕ ድ)
የ51 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃ እየተጣራ መሆኑን የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንን የስድስት ወራት አፈፃፀም ሰሞኑን ገምግሟል።
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት፤ የትምህርት ማስረጃ የማጥራት ሥራው ከታሰበው በላይ ቁጥሩ የሰፋ እና ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ የሚገኝ ነው።
ለትምህርት ማስረጃ የማጥራት ሂደቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሰብሳቢነት የሚሳተፍበትና የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ የትምህርትና ሥልጠና እና የትምህርት ሚኒስቴር የተካተቱበት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሠራ የሚገኝ መሆኑን አመልክተዋል።
ዲግሪና ከዲግሪ በላይ የትምህርት ማስረጃ ያላቸው የ51 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች መረጃ ተሰብስቦ እየተጣራ እንደሚገኝ ኮሚሽነር
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=121043