የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️
ዛሬ የረመዳን ወር ጾምን ምክንያት በማድረግ ከ127 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር አስጀምረናል።
በለውጡ መንግስት በጀመርነው የሰው ተኮር ስራችን የህዝባችንን የኑሮ ጫና የማቅለልና አለኝታነታችንን በተግባር የማረጋገጥ በርካታ ስራ በመስራት፣ ማዕድ ብቻ ሳይሆን ለወገኖቻችን ክብር እና ፍቅርን እያጋራን የቆየን ሲሆን በዛሬው ዕለትም ለሁሉም የአዲስ አበባ መስጅዶች የሚከፋፈል ቴምር እና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችን ደግሞ ማዕድ አጋርተናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአፈፃፀም ተጠያቂነት ስርዓት ሊተገበር ነው- ትምህርት ሚኒስቴር
*****
(ኢ ፕ ድ)
ከቀጣይ አመት ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራትን ለማምጣት የሚያግዝ የአፈፃፀም ተጠያቂነት ስርዓት ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሰለሞን አብርሃ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ከዚህ ቀደም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥርን ለማሳደግ ሲሰራ ቢቆይም የትምህርት ጥራት ላይ ብዙ ይቀር እንደነበር አስታውሰዋል።
የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ባሰፈረው ምክረሃሳብ፤ የትምህርት ጥራትና አግባብነት ላይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች ሲከናወን መቆየቱን ተናግረዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውጤታማ አለመሆን ከዚህ ቀደም ከሚታዩ ችግሮች መካከል መሆናቸውን አንስተው፤ ተቋማቱን ብቁና ውጤታማ ለማድረግ ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ የማድረግ ሂደት መጀመሩን ጠቅሰዋል።
የስርዓተ ትምህርት፣ የትምህርት ምዘና ማሻሻያ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎችን በትኩረትና በተልዕኮ መስክ የመለየት ስራ ከማሻሻያው መካከል የሚገኙ እንደሆኑም ገልፀዋል።
ከዚህ ቀደም ተቋማት በፋይናንስ አጠቃቀማቸው እንጂ በአፈፃፀም ተጠያቂ የሚሆኑበት ስርዓት እንዳልነበር አንስተው ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ ተቋማት በአፈፃፀማቸው ተጠያቂ የሚሆኑበትን አሰራር መተግበር ይጀመራል ብለዋል።
በተጠያቂነት የአሰራር ስርዓት መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቁልፍ ውጤት አመላካቾች ላይ ውል በማድረግ ስራቸውን እንደሚያከናውኑ ገልፀዋል።
ይህም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትና አግባብነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ያለውን ስራ የሚያግዝ መሆኑን ነው የተናገሩት።
የአፈፃፀም ተጠያቂነት ስርዓቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ተመዝነው የተሻለ አፈጻጻም ያስመዘገቡት እውቅና እንዲያገኙ እንዲሁም ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው ደግሞ የማስተካከያ እርምጃዎች የሚወስዱበት አግባብ የሚፈጠርበት መሆኑንም ነው ያስረዱት።
ሚኒስቴሩ በቀጣይም የትምህርት ጥራትና አግባብነትን ለማረጋገጥ በዘርፉ ያለውን ስብራት ማከም የሚችሉ የተለያዩ አሰራሮችን በጥናት እየለየ እንደሚተገብርም ተናግረዋል።

👍1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በሶስት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል
*****
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባው በሶስት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
ለከተማዋ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅም ጉልህ ሚና ባላቸው ጉዳዮች ላይ በዛሬው ዕለት ተወያይቶ አጽድቋል።
በዚህም መሰረት፤
1ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን የተሽከርካሪ አስተዳደር ህግ እና ሥርዓት ለማስከበር የከተማ አስተዳደሩ ባወጣው የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት አሰጣጥ ረቂቅ ደንብን ለአሰራር በሚያመች መልኩ ሀሳብ ተሰጥቶበት ፀድቋል።
2ኛ. የከተማዋን ስታንዳርድና መዋቅራዊ ፕላን ለማስጠበቅ እንዲሁም መልሶ ማፍረስ እንዳይገጥም፤ ግንባታዎች ከመንገድ ያላቸው ርቀት ከዚህ በኋላ ወጥነት ያለው የከተማ አሰራር አንዲኖር በማሰብ ከመንገድ መራቅ ያለባቸውን 3 ደረጃዎች ለማውጣት በቀረበው መተዳደሪያ ደንብ ላይ በመወያየት ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባው ፤ ከንዑስ ዋና መንገድ 5 ሜትር ርቀት፤ ሰብሳቢ መንገድ ደግሞ 3 ሜትር ርቀት በተጨማሪም የውስጥ ለውስጥ መንገድ 2 ሜትር ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸው ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
3ኛ. የነገዋ የሴቶች ተሀድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ማቋቋሚያ ደንብ ማዕከሉን በተለይም ለጎዳና ህይወት ፤ ለፆታዊ ጥቃት ለተጋለጡ እና ለወሲብ ንግድ ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች ፣ መጠለያ፣ ማገገሚያና የተመሰቃቀለ ህይወታቸውን እንደገና ለማደስ የሚያስችል የሙያ እና ክህሎት ሥልጠናዎች የሚያገኙበትንና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ የሚያግዝ አቅም ያለዉ ማዕከል እንዲሆን ለማስቻል በሚያግዘው ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ካቢኔው ተወያይቶ አጽድቋል።

በመዲናዋ የሞተርና የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል የትራንስፖርት አገልግሎትን ለመወሰን አዲሰ መመሪያ ተዘጋጀ
*******
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የሞተርና የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን ለመወሰን የሚያስችል አዲስ መመሪያ መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሰታወቀ።
በከተማዋ የሞተር ሳይክል ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላትን በአሰራርና በተደራጀ ሁኔታ ለመምራት የሞተር ሳይክል እና የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን ለመወሰን መመሪያ ቁጥር 155/2016 ተግባራዊ አድርጓል፡፡
በመመሪያው ከአሽከርካሪው ውጪ ሌላ ሰው መጫን እንደማይቻልና ለዕቃ ማመላለሻ ብቻ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ፣ ከኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ውጪ አዲስ የአገልግሎት ፍቃድ እንደማይሰጥ ተመላክቷል።
ከ250 አባላት ጀምሮ በማህበር በመደራጀት ፍቃድ እንደሚሰጥና አሁን በስራ ላይ የሚገኙ የሞተር ሳይክሎች ቢሮው በሚያስቀምጠው የጊዜ ገደብ ወደ ኤሌክትሪክ የሞተር ሳይክል መለወጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመመሪያው መሰረት አገልግሎቱን የማይሰጡ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች እንደ ጥፋቱ እርከን ቅጣት እንደሚጣልባቸው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሰታወቀ።

የፑንትላንድ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳለው ገለፀ
******
(ኢ ፕ ድ)
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በፑንትላንድ የገንዘብ ሚኒስትር መሀመድ ፋራህ መሀመድ የተመራ ከፍተኛ የሚኒስትሮች ልዑካን ቡድንን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
የፑንትላንድ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።
በንግድ፣በኢንቨስትመንት፣ በኢነርጂና በመሠረተ ልማት መስክ ትብብር ትኩረት እንደሚሰጥ ተጠቅሷል። ኢትዮጵያ በተለይ በጸጥታና በትምህርት ዘርፍ ለፑንትላንድ እያደረገች ላለው ድጋፍ ልዑካን ቡድኑ ምስጋና አቅርቧል።
ኢትዮጵያ ከፑንትላንድ ጋር ያላት ግንኙነት እንዲጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን አምባሳደር ምስጋኑ ተናግረዋል።
የፑንትላንድ መንግስት በቅርቡ ላካሄደው የተሳካ ምርጫ ሚኒስትር ዴኤታው መልዕክት ማስተላለፋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ ከግድቡ ግንባታ ባሻገር ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን መሠረት ያደረገ ድርድር እንዲካሄድ ጥራለች -ኢንጂነር ተፈራ በየነ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ባለፉት 13 ዓመታት ከግድቡ ግንባታ ጎን ለጎን ከታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ጋር ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ ድርድር እንዲካሄድ ከፍተኛ ጥረት አድርጋለች ሲሉ ኢንጂነር ተፈራ በየነ ገለጹ፡፡
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የድንበር እና ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች አማካሪ ኢንጂነር ተፈራ በየነ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ዓባይ ለኢትዮጵያ ትልቅ ሀብት ቢሆንም ሕዝቡ ባለፉት ዘመናት በኤሌክትሪክ በኃይል እጥረት ሲቸገር ቆይቷል፡፡
ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የዓባይ ግድብ ግንባታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያም ከግድቡ ግንባታ ጎን ለጎንም ከታችኛው የተፋሰሱ ሀጋራት ጋር ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን መሠረት ያደረገ ድርድር እንዲካሄድ ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ነው፡፡
የዓባይ ወንዝ ለዘመናት ለሀገሩ ጥቅም ሳይሰጥ መቆየቱ ሕዝቡ ላይ ቁጭት ፈጥሮ እንደነበር አስታውሰው፤ የዓባይ ግድብ ግንባታ የዛሬ 13 ዓመት ሲጀመር ሕዝቡ በተነሳሽነትና በቁርጠኝነት የበኩሉን አስተዋጽኦ በማበርከት ግድቡን አሁን ያለበት ደረጃ ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ እስካሁን ድረስ የብሔር፣ የሃይማኖትና የጾታ ልዩነት ሳይገድበው ለግድቡ የአቅሙን እያዋጣ ይገኛል ያሉት ኢንጂነሩ ፤ የኢትየጵያ መንግሥትም ላለፉት 13 ዓመታት ግድቡን ከመገንባት ጎን ለጎን በዓባይ ተፋሰስ ሀገራት....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124962

ሕዝበ ሙስሊሙ ለሀገር ሰላምና ለሕዝቦች አብሮነት መጠናከር ሚናውን ሊወጣ ይገባል
**************
(ኢ ፕ ድ)
ሕዝበ ሙስሊሙ በረመዳን የመጨረሻ አስር ቀናት ለሀገር ሰላምና ለሕዝቦች አብሮነት መጠናከር ግንባር ቀደም ሚናውን በመወጣት ሊያሳልፈው እንደሚገባ የእስልምና የሃይማኖት አባቶች አሳሰቡ፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር አደም ካሚል ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ሰላም የኢስላም መሠረት በመሆኑ በረመዳን በመጨረሻዎች ቀናት ወቅት ሕዝበ ሙስሊሙ ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር ያለውን አብሮነት በማጠናከር የሰላም ዘብ መሆን አለበት፡፡
ሕዝበ ሙስሊሙ የሌሎችን እምነት ክብርና ማንነት በጠበቀ መንገድ የእርስ በእርስ ግንኙነትን ከምንጊዜውም በበለጠ ሁኔታ ማጠናከር ይኖርበታል ያሉት ኃላፊው፤ኢትዮጵያ የተለያዩ እምነት ተከታዮች እንደመሆኗ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የመለያየት መንፈስን በማስወገድ በመረዳዳት፣ በመዋደድና በመቻቻል መኖር እንደሚገባቸውም አስረድተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ሼይኽ ሁሴን በሽር በበኩላቸው፤ ቀሪ አስር ቀናትን ለጾም የሚዘጋጁ ምግቦችን ከጎረቤት ጀምሮ ለተቸገሩ ወገኖች በማካፈል አለኝታ በመሆን.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124977

የሲዳማ ክልል የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ አዲስ ፓኬጅ ቀረጾ ወደ ትግበራ ሊገባ ነው
****************
(ኢ ፕ ድ)
የሲዳማ ክልል የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ 7 ኢንሼቲቭና 67 ፓኬጆችን የያዘ 767 የተሰኘ ፓኬጅ ቀርጾ ወደ ትግበራ ሊገባ መሆኑን አስታውቋል።
በክልሉ የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ዳዊት ሀዬሶ(ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፣ 767 የተሰኘው ኢንሼቲቭና ፓኬጅ እርሻን፣ የእንስሳት ሀብት ልማት፣ ቱሪዝም፣ ትምህርት እና ስልጠና፣ ኢንዱስትሪ፣ ንፅህናን እንዲሁም የማህበረሰብና አካባቢ ደህንነትን ያካተተና በውስጡም 67 ፓኬጆችን አቅፎ የያዘ ነው።
ኢንሼቲቭና ፓኬጁ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የሚተገበር ሲሆን፣ትግበራው በጥናት በተለየው መሰረት እንደ የአካባቢው ተፈጥሯዊ ባህርይ ሊለያይ ይችላል።
የክልሉ መንግሥት የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ላለፉት ሶስት ዓመታት የተለያዩ የልማት ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።
የሲዳማ ክልል በክልልነት ከተደራጀ ጀምሮ የሕዝቡን ፍላጎት መነሻ ባደረገ መልኩ የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተለያዩ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱንም አውስተው፤በመንገድ፣ በግብርና ፣ በንጹህ መጠጥ ውሃ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በመልካም አስተዳደር እና በተሻሻለ እንስሳት ዙሪያ ተጠቃሽ ሥራ መሠራቱን.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124992

የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ አንድ ነጥብ አምስት ቢልዮን ብር በላይ ካፒታል አሰባሰበ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ሥራ ለመጀመር ያስፈልገኛል ብሎ ካቀደው ከሁለት እጥፍ በላይ የሆነ ተሳትፎን በማሳካት ካፒታል የማሰባሰብ ሂደቱን ማጠናቀቁን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳወቀ።
የገበያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ጥላሁን እስማኤል (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ከሀገር ውስጥና ከውጪ ባለሀብቶች ከተጠበቀው በላይ የሆነ ምላሽን በማግኘት በድምሩ ብር አንድ ነጥብ 5 ቢሊየን (26 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር) ካፒታል ማሰባሰብ ችሏል።
ይህም በመጀመሪያ ከታቀደው የብር 631 ሚሊየን (11.07 ሚሊየን ዶላር) ካፒታል በ240 በመቶ የሚበልጥ ሲሆን በድምሩ 48 በፋይናንስና ከፋይናንስ ዘርፍ ውጪ ባሉ ዘርፎች የተሰማሩ ተቋማዊ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች ተሳትፎ አድርገዋል ብለዋል።
ገበያው ግንባር ቀደም በሆነ የግልና የመንግስት አጋርነት በጥቅምት 2016 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን መንግስት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በኩል የ25 በመቶ የተፈቀደ ካፒታል ድርሻ ሲይዝ የግል ዘርፉ ደግሞ ቀሪውን 75 በመቶ ድርሻ ይዟል ተብሏል።
በዳግማዊት ግርማ
መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

አካል ጉዳተኞችን የዘነጉ ሕንፃዎች
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በመዲናዋ አዲስ አበባ የሚገነቡ አንዳንድ ሕንፃዎች አስፈላጊ ግብዓቶችን ያሟሉ አይደሉም የሚል ተደጋጋሚ ቅሬታ ይቀርባል፡፡
በተለይም አቅመ ደካሞችና የአካል ጉዳተኞች ሕንፃዎችን ለመጠቀም ሲቸገሩ ይስተዋላል፡፡
ጉዳዩን አስመልክቶ ያነጋገርናቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች አንዳንድ ሕንፃዎቻችን ለአካል ጉዳተኛ ቀርቶ ለጤናማው ሰውም የተመቹ አይደሉም የሚል አስተያየት ይሰጣሉ። አንድ ሕንፃ ሊኖረው ይገባል ተብለው የሚታሰቡ እንደ አሳንሰር፣ የአካል ጉዳተኛ መወጣጫ እና መሰል ግብዓቶችን ያሟሉ አይደሉም ይላሉ።
ይህ ችግር በተለይም በጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች ዘንድ በተደጋጋሚ ይደመጣል።
ረጃጅም ፎቅ ባላቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪ የሆኑ አቅመ ደካሞች ደረጃ ላይ አረፍ እያሉ ሲሄዱ ማስተዋል የተለመደባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች መኖራቸውንም ነዋሪዎች ይናገራሉ። በየዕለት እንቅስቃሴም ረጃጅም ፎቆችን መውጣትና መውረዱ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124972

በክልሉ በስምንት ወራት ከአንድ ነጥብ ሰባት ሚሊዮን በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል
******************
(ኢ ፕ ድ)
ባለፉት ስምንት ወራት ለአንድ ነጥብ ሰባት ሚሊዮን በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠር መቻሉን የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ፡፡
የኦሮሚያ ክልል ሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቶሎሳ አጀማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በተያዘው በጀት ዓመት ስምንት ወራት ውስጥ ለአንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ለአንድ ነጥብ 79 ሚሊዮን ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል በመፍጠር የእቅዱን 98 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡
በዓመቱ ለሦስት ነጥብ አንድ ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዶ አስፈላጊ ዝግጅት ማድረጉን ጠቅሰው፤ ለዚህም ቢሮው በከተማና በገጠር የሥራ ፈጠራን የሚያበረታቱ ዕቅዶችን አቅዶ ወደ ሥራ ገብቷል ብለዋል፡፡
ቢሮው ለሥራ አጥ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የትኩረት አቅጣጫዎች አስቀምጦ እየሠራ እንደሚገኝ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ ለዚህም ከሰርተፍኬት ባሻገር ጥራት ያለውና ውጤታማ ስልጠና
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124989

የግል ዳታ ጥበቃ ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ
***************
(ኢ ፕ ድ)
የህዝበ ተወካዮች ምክር ቤት ሶስተኛ ዓመት የስራ ዘመን 20ኛ መደበኛ ስብሰባ የግል ዳታ ጥበቃ ረቂቅ አዋጅን በአብላጫ ድምጽ በዛሬው አጽድቋል፡፡
አዋጁ የግል ዳታ ጥበቃን በተመለከተ ዝርዝር ድንጋጌዎችን የሚያስቀምጥና የግል ዳታ ጥበቃ ተቆጣጣሪ ተቋምን የሚሰይም በመሆኑ ጠንካራ የግል ዳታ ጥበቃ ስርዓት እንዲፈጠር የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የግል ዳታ በሚሰበሰብበትና በሚቀናበርበት ወቅት ጥሰት እንዳይፈጠር ለመቆጣጠርና የወንጀሉ ፈጻሚዎችን አስተማሪ በሆነ አግባብ መቅጣት የሚያስችል ረቂቅ አዋጅም ነው ተብሏል ፡፡
ከዳታ ማቀናበር ስራዎች ጋር የተያያዙ አደጋዎችን ለመቀነስና በኢትዮጵያ የግል ዳታ ጥበቃ ሰርዓት ዓለምአቀፋዊ ደረጃዎችንም በጠበቀ መልኩ ለመገንባትም ዋሳኝ መሆኑም ተነስቷል፡፡
በዳግማዊት አበበ

የዓባይ ግድብ በዓለም ካሉት ውብ የቱሪስት መዳረሻዎች አንዱ ይሆናል
********************
(ኢ ፕ ድ)
የዓባይ ግድብ ግንባታ ሲጠናቀቅ ቦታው በዓለም ላይ ካሉት ውብ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ውስጥ አንዱ ይሆናል ሲሉ ከፍተኛ የቱሪዝም ባለሙያው ዶክተር አያሌው ሲሳይ ገለጹ።
የቱሪዝም ባለሙያው ዶክተር አያሌው ሲሳይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የዓባይ ግድብ የሚያርፍበት ቦታ የውሃውን ይዞታ ጨምሮ አንድ ሺህ 740 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ይሸፍናል።
ግድቡ የሚይዘው 74 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ ወደ ኋላ 246 ኪሎ ሜትር ይረዝማል።
በዚህም እያንዳንዳቸው ከአምስት ሔክታር በላይ ስፋት ያላቸው 70 ደሴቶች ይፈጠራሉ፡፡
ይህም የዓባይ ግድብ ሲጠናቀቅ አካባቢው በዓለም ካሉት ውብ የቱሪስት መዳረሻዎች አንዱ ያደርገዋል፡፡
ትልቁ ደሴት ሁለት ሺህ 800 ሔክታር ስፋት እንደሚኖረው መረጃዎች ያመለክታሉ ያሉት ዶክተር አያሌው፤ የዓባይ ግድብ ግንባታ ሲጠናቀቅ ቦታው በዓለም ላይ ካሉት ውብ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ውስጥ አንዱ እንደሚሆን ገልጸዋል።
ዓባይ ተራ ወንዝ ብቻ ሳይሆን የስልጣኔ እና የባህል ምልክት ነው። ይህም ግድቡን በቀላሉ ለዓለም ሕዝብ ማስተዋወቅ ያስችላል ያሉት ዶክተር አያሌው፤ ይህም ቱሪስቶች ከዓባይ ወንዝ ጋር የተያያዘውን ውበት እና የበለፀገ ባህልና ታሪክን.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=125001