በቀጣይ አስር ቀናት ውስጥ የሚኖረው የአየር ሁኔታ ለበልግ አብቃይ አካባቢዎች ምቹ ነው
******
(ኢ ፕ ድ )
በሀገሪቱ በቀጣይ አስር ቀናት ውስጥ የሚኖረው የአየር ሁኔታ ለበልግ አብቃይ አካባቢዎች ምቹ መሆኑን የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለኢፕድ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በቀጣይ አስር ቀናት ውስጥ የበልግ ዝናብ በአብዛኛዎቹ የበልግ አብቃይ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ እየተጠናከረና እየተስፋፋ የሚሄድ ሲሆን በርካታ ቦታዎችን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው የዝናብ መጠን ያገኛሉ።
በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ፣ የሰሜን ምስራቅ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ እንደሚኖረውም ተጠቁሟል።
በዚህም በአብዛኛው የበልግ ዝናብ አብቃይ ስፍራዎችን የሚሸፍን እርጥበት ያገኛሉ። ይህም ቀደም ብለው ለተዘሩ ሰብሎችና ለቋሚ ተክሎች የውሃ ፍላጎትን መሟላት እንዲሁም የረጅም ጊዜ ሰብሎችን ለመዝራት እና የማሳ ዝግጅት ለማከናወን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=125155

በርካታ ህዝብ የታደመበት የአዲስ አበባው የድጋፍ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል -የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል
*******
(ኢ ፕ ድ)
በርካታ ህዝብ የታደመበትና በአዲስ አበባ የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አስታወቀ ፡፡
ለሰልፉ በሰላም መጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱና ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ የፀጥታ አካላት ምስጋና አቅርቧል፡፡
በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ በስኬት እና በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል።
የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የታደሙበት የድጋፍ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁን ግብር ኃይሉ አስታውቋል።
በያዝነው ዓመት በርካታ ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት የታደመባቸው ልዩ ልዩ ኹነቶች ሃይማኖታዊ በዓላት እና ስፖርታዊ ዝግጅቶች በሰላም መከናወናቸውንም የግብረ-ሃይሉ መግለጫ አስታውሷል።
ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም የተለመደውን ትብብር በማድረጉና በተለይ መላው የፀጥታ አካላት ድካማቸውን ተቋቁመው ሃላፊነታቸውን በትጋት በመወጣታቸው በ2016 ዓ.ም ከተማችን ያስተናገደቻቸው አበይት ኩነቶች ፍፁም ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ ማድረጉም ተገልጿል።
መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓም

የባህርዳር- ጎንደር ኮማንድ ፖስት ወደ አዲስ አበባ ሊጓዝ የነበረ ሽጉጥና ጥይት በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ
*****
(ኢ ፕ ድ )
የባህርዳር- ጎንደር ኮማንድ ፖስት መነሻውን ጎንደር ከተማ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ሊጓዝ የነበረ ሽጉጥና ጥይት በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።
ኮማንድ ፖስቱ እንዳስታወቀው መነሻውን ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 በተለምዶ ማራኪ በመባል ከሚታወቀው ስፍራ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ-3 58581 አዲስ አበባ በሆነ አይሱዚ መኪና 45 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ ከአንድ ሺህ 801 ጥይት ጋር ከቤት ዕቃ ጋር በድብቅ ጭኖ ሲጓዝ በተደረገበት ጥብቅ ክትትል መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ባህርዳር ከተማ መግቢያ ዘንዘልማ ኬላ ላይ መያዙን ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል።
ሁለት ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ጨምሮ ተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል።
ኮማንድ ፖስቱ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠት እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ማሳሰቡ ከሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ78 ዓመታት የስኬት ጉዞውን በማስመልከት በልዩ ዝግጅት በረራ ሊያደርግ ነው
*****
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ78 ዓመታት የስኬት ጉዞውን በማስመልከት በታሪኩ የመጀመሪያ በረራ ወዳደረገበት ካይሮ በልዩ ዝግጅት በረራ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1946 መጋቢት 29 በአሥመራ በኩል በማድረግ ወደ ግብጽ ካይሮ በ/5C-47/ አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራውን አደረገ።
የኢቪዬሽን ኢንዱስትሪውን በተቀላቀለበት 78 ዓመታት ጉዞው በርካታ ፈተናዎችን በማለፍ በስኬታማነት በአፍሪካ ግዙፍ የአየር ትራንስፖርት ኩባንያ መሆን ችሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ ለማ ያዴቻ፤ አየር መንገዱ በኢቪዬሽን ኢንዱስትሪው አሁንም በፍጥነት እያደገ ያለ ግዙፍ ተቋም መሆኑን ገልፀዋል።
በአህጉሪቷ የመጀመሪያ የሆኑትን የጀት ምርቶች በማስገባት ቀዳሚ ሲሆን፤ የመጀመሪያዎቹን የ/B767/፣ /B777-200LR/፣ /B787/ ድሪም ላይነር እና የ/787-9/ አውሮፕላኖችን በፍጥነት ወደ ገበያው ያስገባ ስኬታማ አየር መንገድ መሆኑን ተናግረዋል።
በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆኑትን የአልትራ ሞደርን ኤር-ባስ /A350-900/ አውሮፕላኖችን በወቅቱ በብቸኝነት በመግዛት ወደ ሥራ ያስገባ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በዓለም አደባባይ የኢትዮጵያ የኩራት መገለጫና የብራንድ አምባሳደር ከመሆኑም በላይ የአፍሪካውያን የስኬት ማሳያና የኩራት ምንጭ ስለመሆኑ አንስተዋል።
በተለይም አፍሪካን ከአውሮፓና ከተቀሩት የዓለም አገራት ጋር በማስተሳሰር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቀዳሚዎቹ መካከል የሚጠቀስ መሆኑን ገልፀዋል።
የአየር ትራንስፖርት አገልግሎቱን በየጊዜው እያዘመነና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሠራር በመከተል በፍጥነት እያደገ ይገኛል።
ለአየር መንገዱ የስኬት ጉዞም የሠራተኞች ብርቱ ትጋት፣ የጠንካራ ስትራቴጂክ አመራር ብቃት፣ በቴክኖሎጂ የታገዙ ዘመናዊ አሠራሮችና ሌሎችም ይጠቀሳሉ ብለዋል።
ከሰባት አሥርት ዓመታት በላይ የዘለቀውን ስኬት በማስመልከትም የመጀመሪያ በረራውን ወዳደረገበት ካይሮ ነገ እሁድ ምሽት በልዩ ዝግጅት ለመብረር መዘጋጀቱን አቶ ለማ ገልፀዋል።
በእለቱም የአየር መንገዱ ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች ለደንበኞች ልዩ የመስተንግዶ አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑን ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2011 የስታር አሊያንስ አባል ለመሆን የበቃ ሲሆን፤ ይህም በዓለም አቀፉ ግዙፍ የአየር ትራንስፖርት ትስስር ውስጥ ያለውን ሚና የላቀ እንዲሆን አስችሎታል ብለዋል።
አየር መንገዱ በራዕይ 2025 ለ15 ዓመታት ባስቀመጠው ግብ መሠረት 25 በመቶ እድገቱን በዕቅዱ ማሳካት መቻሉን ገልጸው፤ ለራዕይ 2035 ፍኖተ-ካርታም ከወዲሁ ስኬቶችን እየተጎናፀፈ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁን ላይ በ147 አውሮፕላኖች 136 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን፤ በካርጎ አገልግሎቱም በ16 አውሮፕላኖች 67 ዓለም አቀፍ ከተሞች ይበራል።
በአፍሪካ ከ63 በላይ ከተሞች በመብረር አህጉራዊ ትስስሩን እያፋጠነ ስለመሆኑም አንስተዋል።
አሁን ላይ ከ100 በላይ ዘመናዊና ግዙፍ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ስምምነት አድርጎ አውሮፕላኖቹ በትዕዛዝ ላይ ናቸው ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2035 ዓመታዊ ገቢውን ወደ 25 ቢሊየን ዶላር ከፍ ለማድረግና በዓመት 67 ሚሊየን መንገደኞችን ለማጓጓዝ ራዕይ አስቀምጦ እየሰራ ይገኛል።

የኢድ አል ፈጥር በዓል ጨረቃ ከታየች ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ ረቡዕ ይከበራል
******
(ኢ ፕ ድ)
1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ጨረቃ ሰኞ ከታየች በዓሉ ማክሰኞ፤ ካልታየች ዕሮብ ሚያዚያ 02 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ 1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ የዘንድሮው የኢድ አል ፈጥር በዓል ጨረቃ ከታየች ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ ረቡእ ይከበራል።
ፕሬዚዳንቱ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በመረዳዳት፣ በመተዛዘን፣ የተቸገሩት በማገዝ እንዲያሳልፉ አሳስበዋል።
በረመዷን የጾም ወር የታየው የመረዳዳትና የመተዛዘን ተግባር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል።
የኢድ አል ፈጥር በአል የሰላም፣ የደስታና የአብሮነት እንዲሆን በመመኘት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
በአማን ረሺድ

በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የተደረገው የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ኦዲት በስኬት ተጠናቀቀ
- የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት
******
(ኢ ፕ ድ)
የአሜሪካ የትራንስፖርት ደኅንነት አስተዳደር በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ያደረገው የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ኦዲት በስኬት መጠናቀቁን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢፕድ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ የአሜሪካ የትራንስፖርት ደኅንነት አስተዳደር (TSA) ከመጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ኦዲት ሲያከናውን ቆይቷል፡፡
የኦዲት ልዑክ ቡድኑ በቆይታው የመንገደኞች፣ የሻንጣ፣ የካርጎ ጭነቶች፣ የዙሪያ ጥበቃና ፍተሻ እንዲሁም የአውሮፕላን ደኅንነትን ለማረጋገጥ የሚወሰደው የሴኪዩሪቲ እርምጃ ከዓለም አቀፍ አሰራር አንጻር አጠቃላይ ያለበትን ደረጃ በተመለከተ ሁሉን አቀፍ ኦዲት አድርጓል፡፡
በኦዲቱ ጥልቅ የሠነድ ግምገማ እና የአካል ምልከታ የተደረገ ሲሆን፤ በልዑኩ በቀረበው የማጠቃለያ ሪፖርት ወደ አሜሪካ ሀገር በሚደረጉ በረራዎችም ሆነ አጠቃላይ በአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ኦፕሬሽናል ሂደቶች ላይ ምንም ዓይነት የደኅንነት ስጋት እንደሌለ በድጋሚ መረጋገጡ ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ ጠንካራ የሆነ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ስርዓት መገንባቱን እንዲሁም በቀጣይም በአፍሪካ ምርጥ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ለመሆን የተያዘውን ስትራቴጂክ ዕቅድ ለማሳካት የሚያስችል መሰረት እንደተጣለ የትራንስፖርት ደኅንነት አስተዳደር (TSA) ተወካይ ገልጸው በሁለቱ ተቋማት ብሎም ሀገራት መካከል በዘርፉ የሚደረገው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ዋና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አስራት ቀጀላ የኦዲት ሪፖርቱ በቀረበበት መርሐ ግብር ባደረጉት ንግግር በአገልግሎት መስሪያ ቤቱ በተሰጠው ልዩ ትኩረት በሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ዋና መምሪያ የተደረገው ሁሉን አቀፍ ሪፎርም፣ የተዘረጋው አሰራር፣ የሰው ኃይል ልማት፣ የቴክኖሎጂ እምርታ እና ከምንጊዜውም በላይ የተጠናከረው የኤርፖርት ባለድርሻ አካላት ቅንጅት የትራንስፖርት ደኅንነት አስተዳደርን (TSA) እና ከዚህ ቀደም የተደረጉ ሌሎች ተከታታይ ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ምዘናዎችን ስኬት ለመጎናፀፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አንደነበራቸው ገልፀዋል፡፡
በኦዲቱም ለተገኘው ሀገራዊ ውጤት ሌት ተቀን ሲተጉ ለነበሩ የዋና መምሪያው ሠራተኞችና አመራሮች እንዲሁም በኤርፖርት ለሚገኙ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በቀጣይም በሚደረገው ሀገራዊ የዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ኦዲት ሁሉም በከፍተኛ ቅንጅት፣ ቁርጠኝነት እና ትብብር በመስራት ኢትዮጵያን በከፍታ ማስጠራት እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ለሀገራዊ ኦዲቱም ከወዲሁ ስራዎች ተለይተው እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የአሜሪካ የትራንስፖርት ደኅንነት አስተዳደር ከሐምሌ 10 እስከ ሐምሌ 12 ቀን 2015 ዓም ድረስ ለተከታታይ ሦስት ቀናት በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ባካሄደው የበረራ ደኅንነት ልዩ ኦዲት በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት ምንም አይነት የደኅንነት ክፍተት (ግኝት) እንደሌለበት መግለጹ ይታወሳል፡፡
የአሜሪካ የትራንስፖርት ደኅንነት አስተዳደር ሐላፊ ዴቪድ ፕኮስኬ የኦዲት ውጤት መገኘቱን ተከትሎ ነሐሴ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በተቋሙ ባደረጉት ጉብኝት ለኢትዮጵያ የበረራ ደኅንነት አጠባበቅ አድናቆታቸውን መግለጻቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢፕድ የላከው መረጃ አመልክቷል፡፡
በመጨረሻም በዋና መምሪያው የተጀመረውን ሪፎርም አጠናክሮ በማስቀጠልና በኤርፖርቱ የሚገኙ ሁሉንም በለድርሻ አካላት አቀናጅቶ በማነቃነቅ ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት አሰራሮች ተዘርግተው እየተተገበሩ መሆኑን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጠቁሟል።
ተገልጋዩ በኤርፖርቱ ማህበረሰብ ከሚሰጡ አገልግሎቶቾ ጋር በተያያዘ አስተያየትና ቅሬታ ሲኖረው በኤርፖርት ውስጥ በተዘረጋው የአስተያየትና የጥቆማ መስጫ ስርዓት በግልጽ ሀሳቡን በመስጠት የተሻለ አገልግሎቶች ማግኘት እንዲችል በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል።