የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️
ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ በኢስታና ላደረጉልኝ አቀባበል አመሰግናለሁ። በቅርቡ ለጀመሩት የጠቅላይ ሚኒስትርነት ኃላፊነትም እንኳን ደስ አለዎ ለማለት እፈልጋለሁ።
ሁለቱ ሀገሮቻችን እርስ በርስ የሚማማሩት ብዙ ጉዳይ አለ። የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነታችንን ከፍ ለማድረግ፣ በአቅም ግንባታ፣ በሲቪል ሰርቪስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በላቀ የማኑፋክቸሪንግና ቱሪዝም ልማት ትብብራችንን ለማጠናከር ተስማምተናል። የወዳጅነት ትብብራችንን ይበልጥ ለማስፋት የምንሰራም ይሆናል።
ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓም

የዓባይ ግድብ ባለፉት አስር ወራት በሁለት ተርባይኖች ከ2ሺ 700 ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ ኃይል አመንጭቷል
*****
(ኢ ፕ ድ)
በሁለት ተርባይኖች ኃይል እያመነጨ የሚገኘው የዓባይ ግድብ በ2016 በጀት ዓመት አስር ወራት ከዕቅዱ የ26 በመቶ ብልጫ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨቱን የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አሰታወቀ።
በዘርፉ የዕቅድ ቢሮ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ጥሩወርቅ ሺፈራው እንደገለጹት ግድቡ በበጀት ዓመቱ አስር ወራት 2 ሺ 152 ነጥብ 8 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ለማመንጨት አቅዶ 2 ሺ 711 ጊጋ ዋት ሰዓት አመንጭቷል።
ባለፋት አስር ወራት ከመነጨው የ16 ሺ 900 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል የዓባይ ግድብ የ16 በመቶ ድርሻ አለው።
ኃይል በማመንጨት ላይ የሚገኙት የግድቡ ሁለቱ ተርባይኖች እያንዳንዳቸው 375 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን በግድቡ ላይ የሚተከሉት ቀሪ 11 ዩኒቶች ኃይል ማምረት ሲጀምሩ በሀገሪቱ ያለውን የማመንጨት አቅም በ83 በመቶ እንደሚያሳድገው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይ መረጃ ያመለክታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላለፉ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላለፉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ምርጫ ሕዝብ እውነተኛ የሥልጣን ባለቤት መሆኑ የሚገለጥበት ነው።
"ወዳጄ ናሬንድራ ሞዲ ሰላማዊ ምርጫ በማካሄድ ለድል በመብቃትዎ እንኳን ደስ ያለዎ" ብለዋል።
በህንድ በተካሄደ ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በሕንድ በተካሄደው ምርጫ ለሦስተኛ ጊዜ አሸንፈዋል።
ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም

አፍሪካ ያላትን ከዓለም 30 በመቶ የማዕድን ክምችት ለመጠቀም ጠንካራ ሥራ ይጠይቃል
************
(ኢ ፕ ድ)
አፍሪካ ያላትን ከዓለም 30 በመቶ የሚሆነውን የማዕድን ክምችቷን አውጥቶ ለመጠቀም ተግባራዊ የሆነ ስትራቴጂ መንደፍና ጠንካራ ሥራ ማከናወን እንደሚገባ የአፍሪካ ማዕድን ልማት ማዕከል አስታወቀ፡፡
ለዓለም ካርቦን ቅነሳ መሠረታዊ የሆኑ ማዕድናትን ጥቅም ላይ ከማዋል አንፃር የአፍሪካ አቅም የሚያድግበት ሁኔታ ላይ የመከረ ጉባኤ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንና በአፍሪካ ማእድን ልማት ማዕከል አማካኝነት ሰሞኑን ተካሂዷል።
የአፍሪካ ማዕድን ልማት ማዕከል ጊዜያዊ ዳይሬክተር ማሪት ያየህይራድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አፍሪካ ከዓለም 30 በመቶ የሚሆነውን የማዕድን ክምችት...
https://press.et/?p=129348

አዲስ የሥራ ባህል የፈጠረው አዲስ ልማት
************
(ኢ ፕ ድ)
ጥቁሩ የአስፓልት መንገድ ምቹ ሆኗል፤ የግራና የቀኝ እግረኛ መንገዱ ሁሌም ሂዱብኝ ሂዱብኝ ይላል፡፡ ሕንፃዎቹ ውበትን ተላብሰዋል፡፡
በተለይ የኮሪደር ልማቱ ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ የሚወስደውን መንገድ ሁለተናዊ ውበትና ምቹነት አላብሶታል፡፡
የመዲናዋ የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ውበት የሚጨምሩ የሕዝብ መናፈሻ ስፍራዎች፣ ፋውንቴኖችና የአረንጓዴ ስፍራዎች እንዲሁም የመንገድ ሥራዎች እየተጠናቀቁ ነው፡፡ የተጠናቀቁም እንዳሉ ተመልክተናል።
ይህንን ፕሮጀክት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጪ በምሽት ጭምር የግንባታ ሥራው እየተሠራ እንደሆነ የኢፕድ ሪፖርተሮች ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ኮሪደር ልማት ሥራው ላይም የብሎኬት፣ የግንብ፣ የጠርዝ ሥራዎችን ሲሠሩ ያገኛቸውን አቶ አባይነህ ናናን አነጋግረናል።
የኮሪደር ልማቱ የመዲናዋን የኢኮኖሚ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴን በማሳለጥ ረገድ ትልቅ ትርጉም ያለው ከመሆኑም በላይ የሥራ ባህላችንን......
https://press.et/?p=129347