"ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት የሁለትዮሽና ግንኙነት ያድጋል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ
******
(ኢ ፕ ድ)
በአዲሱ የስልጣን ዘመኔ ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት የሁለትዮሽና ግንኙነትና አጋርነት ያድጋል ሲሉ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ገለጹ፡፡
በሕንድ በተካሄደው ምርጫ ናሬንድራ ሞዲ ለሦስተኛ ጊዜ ማሸነፋቸውን ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወቃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ላስተላለፉላቸው መልዕክት ምሰጋና አቅርበዋል።
ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የሁለትዮሽ ግንኙነት ከፍተኛ ትኩረት ትሰጣለችም ብለዋል።
ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓም

#ጽዱኢትዮጵያ #CleanEthiopia
በሰሜን አሜሪካ የአትሌቶች ማህበር አባላት 8 ሺህ300 የአሜሪካን ዶላር ለ“ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” ድጋፍ አደረጉ
👉 እስከ አሁን 29 ሺህ 445 የአሜሪካ ዶላር እንዲሁም 74 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ተሰብስቧል፣
****
(ኢ ፕ ድ)
ለ“ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” በሰሜን አሜሪካ የአትሌቶች ማህበር አባላት 8 ሺህ300 የአሜሪካን ዶላር የገንዘብና አንድ መጸዳጃ ቤት ለመስራት የአይነት ድጋፍ አደረጉ።
ድጋፋቸውን በአሜሪካ የኢትየጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ አስረክበዋል።
የማህበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት አትሌት ሀይሉ መኮንን ኢትዮጵያ በምትፈልጋቸው ወቅት ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የማህበሩ አባላት በተለያዩ አገራዊ ጥሪዎች ላይ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አምባሳደር ስለሺ በቀለ
ጠቅሰው አሁንም ማህበሩ ለ”ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” ኢንሼቲቭ ላደረገው ድጋፍ ያላቸውን ምስጋና አቅርበዋል።
በአሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ለ”ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” እስከ አሁን በአጠቃላይ በጥሬ ገንዘብ 29 ሺህ 445 የአሜሪካ ዶላር እንዲሁም 74 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ተሰብስቧል።
በዓይነት 21 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ 14 መጸዳጃ ቤቶችን ለመስራት ቃል መግባታቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

በአማራ ክልል በተደረገ የሰላም ጥሪ ከ10 ሺህ በላይ የታጠቁ ኃይሎች ለሰላም እጃቸውን ሰጥተዋል
****************
(ኢ ፕ ድ)
አማራ ክልል ያደረገውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ ከ10 ሺህ በላይ የታጠቁ ኃይሎች ለሰላም እጃቸውን እንደሰጡ የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ በተሠራው የሕግ ማስከበር ሥራ የስምንተኛ ክፍል ፈተና በሁሉም የወረዳ ማዕከላት መድረሳቸው ተመላክቷል።
የቢሮው ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የነበረውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በተሠራው የሕግ ማስከበር ሥራ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል።
ክልሉ ባደረገው የሰላም ጥሪ መሠረት ለሰላም እጃቸውን የሰጡት ከ10 ሺህ በላይ የታጠቁ ኃይሎች ምክርና ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ትውልድ አካባቢያቸው መመለሳቸውን አስታውቀዋል።
በአንዳንድ አካባቢዎች ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የጽንፈኛ ኃይሎችን እንቅስቃሴ በመግታት ሰላም ለማስፈን በርካታ .....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129406

አሳሳቢው የትራንስፖርት ችግርና የተገልጋዮች መጉላላት
***************
(ኢ ፕ ድ)
መገናኛ እንደ ስሟ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ የከተማዋ ነዋሪዎችን ስታገናኝ ትውላለች። ከፍተኛ የሕዝብና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ከሚያስተናግዱባቸው የከተማዋ ቦታዎች መካከልም አንዷ ናት።
በአሁኑ ወቅት ደግሞ ከኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ ሌላ መልክ እየያዘች መጥታለች። እኔ በቦታው የተገኘሁት አንድ ሰአት ተኩል ሲል ነው። ትራንስፖርት ፈላጊው ሕዝብ ወደ ሥራ አልያም ጉዳዩን ለማስፈጸም በየአቅጣጫው ይጣደፋል።
የትራንስፖርት ጉዳይ ግን ረፋድና አመሻሽ ላይ በአካባቢው ለተገኘ ተመልካች ጭንቅ የሚል ስሜት ይፈጥራል። ለታክሲ ብቻ ሳይሆን ለአውቶቡስና ለሀይገር ተሰልፎ የሚታየው ሰው ለዓይን ይደክማል።
ከረጃጅሞቹ ሰልፎች ወደ መጨረሻ የተሰለፈውን በመጠጋት ስለችግሩ አስተያየቱን እንዲያጋራኝ ጠየኩት። ቃለ አብ እውነቱ ይባላል። የኮንስትራክሽን ባለሙያ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ስድስት ኪሎ አካባቢ በሕንፃ ግንባታ ውስጥ እየሠራ እንደሆነ ነግሮኛል። ሥራዬ በተለያዩ ቦታዎች......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129405

የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ባህር ዳር እና ጎንደር ገቡ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋየ ይገዙ ባሕር ዳር ከተማ ገብተዋል።
መሪዎቹ ባሕር ዳር ከተማ ሲደርሱ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማውን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
መሪዎቹ በባሕር ዳር ከተማ በሚኖራቸው ቆይታ በከተማዋ በመገንባት ላይ ያሉ የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን ተዘዋውረው እንደሚጎበኙ ተገልጿል።
በባሕር ዳር ከተማ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በሚደረገው የውይይት መድረክ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።
በተመሳሳይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) እና የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ርስቱ ይርዳው ለስራ ጉብኝት ጎንደር ከተማ ገብተዋል።
የክልሉ አመራሮች፣ የከተማው ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሀይና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በቆይታቸው ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን ጉብኝት የሚያደርጉ ሲሆን ውይይቶችንም ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የአሚኮ ዘገባ ያመላክታል።

በደቡብ ኮሪያ የተደረገው ጉብኝት የሁለቱን አገራት የኢኮኖሚ ትብብር ለማሳደግ አይነተኛ ሚና ያለው ነው"
- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
**********************
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ኮሪያ ያደረጉት ጉብኝት የሁለቱን አገራት የኢኮኖሚ ትብብር ለማሳደግ አይነተኛ ሚና ያለው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በጉብኝቱ የአንድ ቢሊየን ዶላር የፋይናንስ ማእቀፍ እንዲፈረም አስችሏል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ ሳምንታዊ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎችን አስመልክተው ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ ኮሪያ ያደረጉት ጉብኝት በደቡብ ኮሪያና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን ጠንካራ የኢኮኖሚ ትብብር ለማሳደግ አይነተኛ ሚና ያለው ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ 60 አመታትን የዘለለ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያላቸው አገራት መሆናቸውን የገለጹት ቃል አቀባዩ፣ ጉብኝቱ ዘርፈ ብዙና የተጀመረውን ትብብር ለማሳቀጣል መግባባትን የፈጠረ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
በቀጣይ አራት አመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ለሚከናወኑ የተለያዩ ፕሮጀክቶች የአንድ ቢሊየን ዶላር የፋይናንስ ማእቀፍ መፈረሙንም ጠቁመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ከደቡብ ኮሪያ በተጨማሪ በሲንጋፖር ያደረጉት ጉብኝት የሁለቱን አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከማጠናከር በተጨማሪ፣ ተጨባጭ የዘመናዊ ከተማ ልማት፣ ግብርና፣ አረንጓዴ ኢኮኖሚና ቱሪዝም ላይ ልምድ መቅሰም የተቻለበት እንደሆነም አስታውቀዋል።
በተጨማሪም የሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ተወካዮች ልዑክ ጋር ውይይት ማድረጋቸውንና ይህም በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንትና የንግድ ከባቢያዊ ሁኔታዎች መኖራቸውን ለማስተዋወቅ እድል የሰጠ እንደነበር ተናግረዋል።
በአዲሱ ገረመው
ግንቦት 30 ቀን 2016

"የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት አይነተኛ ሚና ይጫወታል"
-አምባሳደር ዘሪሁን አበበ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጎረቤት ሀገሮች ጉዳዮች ዳይሬክተር
**********************
(ኢ ፕ ድ)
እየተጠናከረ የመጣው የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት አይነተኛ ሚና ይጫወታል ሲሉ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጎረቤት ሀገሮች ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ዘሪሁን አበበ ገለጹ።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጎረቤት ሀገሮች ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ዘሪሁን አበበ ለኢፕድ እንደገለጹት፤የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እየጠበቀ መምጣቱ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት አይነተኛ ሚና ይጫወታል።
የኢትዮ-ደቡብ ሱዳን ግንኙነት የሁለቱ ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ያደረገና ግንኙነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ የመጣ ነው ያሉት አምባሳደር ዘሪሁን፤ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ለሰላምና መረጋጋትና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ዓላማ ላይ ለነጻነቷ ከፍተኛ ዋጋ ከፍላለች ብለዋል።
አምባሳደር ዘሪሁን፤ ሁለቱ ሀገራት የረጅም ጊዜ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸው፤ በሕዝቦች ለሕዝቦች፣ ፖለቲካዊ ግንኙነት እንዲሁም በሁለቱ ሀገራት መሪዎች መካከል ያለው ግንኙነት ጠንካራ......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129408

የሚኒስትሮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ውሳኔዎች‼️
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 34ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
✍️ ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የ2017 በጀት አመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ የበጀት አዋጅ ላይ ነው፡፡ የ2017 ዓ.ም. የፌደራል መንግስት በጀት የአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የሆነውን የ2016-2018 የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችን እና የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና የፊስካል ማዕቀፍን ማስፈጸም እንዲቻል በሚያደርግ መልኩ ፤ የ2016 የፌደራል መንግስትን የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ፤ የመንግስት የፋይናንስ አቅም እና ተጠባቂ ገቢዎችን ታሳቢ በማድረግ እንዲሁም አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የተሰጣቸውን ተልኮና ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስፈልጋቸውን ወጪ በመገምገም እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡
በዚሁ መሰረት ለፌዴራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች ፣ ለካፒታል ወጪዎች ፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ እና ተጠባባቂ ወጪን ጨምሮ ወደ አንድ ትሪሊየን የሚጠጋ በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግስት የ2017 ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
✍️ በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያ እና አስተዳደሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ላይ ነው፡፡ በአረንጓዴ አሻራ የተጀመሩ ሰፊ ሥራዎች ቀጣይነትን ለማረጋገጥ፣ ሀገራችን ካላት የቆዳ ስፋት ከግማሽ በላይ የሆነው የተጎሳቆለ መሬት እንዲያገግም ለማድረግ፣ የደን ዘርፉ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዲሰጥ ለማስቻል፣ በአሁኑ ወቅት በተበጣጠሰ መልኩ በፌዴራል መንግስትም ሆነ በክልል መንግስታት ፋይናንስ እየተደረገ እየተሰራ የሚገኘውን የአረንጓዴ አሻራ ልማት በተቀናጀና ተገቢውን ሀብት መመደብ በሚያስችል የፋይናንስ አሰራር ስርዓት መደገፍ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድን ማቋቋሚያ እና አስተዳደሩን ለመወሰን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
✍️ በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ተቋማት ለሚሰጧቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመወሰን በቀረቡ ረቂቅ ደንቦች ላይ ነው፡፡ ተቋማቱ የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች፣ አሰራሮችና የሰለጠነ የሰው ሀይል በማዘመን የአገልግሎት አሰጣጣቸውን የጥራት ደረጃ ማሻሻል ብሎም የተጠቃሚውን ማህበረሰብ አቅም ባገናዘበ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት እንዲችሉ የሚያስችል ስርአት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ ደንቦቹ ተዘጋጅተው ቀርበዋል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቦቹ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውሉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

በኦሮሚያ ክልል ከሁለት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በላይ ወጣቶች የሥራ እድል ተፈጠረ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
በ2016 በጀት ዓመት አስር ወራት ከሁለት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ወጣቶች የሥራ እድል መፈጠሩን የኦሮሚያ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ ኤባ ገርባ (ኢ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በዘንድሮው በጀት ዓመት ባለፉት 10 ወራት ከሁለት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በላይ ወጣቶች የሥራ እድል መፍጠር ተችሏል።
ለሥራ ዕድል ፈጠራው በመንግሥት ደረጃ እየተተገበሩ ያሉ የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብሮች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ኃላፊው አንስተዋል።
በኦሮሚያ ክልል በየዓመቱ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ወጣቶች ወደ ሥራው ዓለም ይቀላቀላሉ ተብሎ ይገመታል ያሉት ኃላፊው፤ በበጀት ዓመቱ በክልሉ ያሉ በርካታ የሥራ እድል ፈጠራ.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129447

በሶማሌ ክልል ከለውጡ በኋላ ብቻ ከ230 በላይ አዳዲስ ፋብሪካዎች ሥራ ጀምረዋል
******************
(ኢ ፕ ድ)
ከለውጡ በኋላ ባሉት ስድስት ዓመታት ብቻ በክልሉ ከ230 በላይ አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ፋብሪካዎች መከፈታቸውን የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ገለጹ።
የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በክልሉ ለተሠማራው የጋዜጠኛ ቡድን እንደገለጹት ፤ ክልሉ ያገኘውን ሰላም ተከትሎ የኢንቨስተሮች ቁጥር እያደገ መጥቷል። ከለውጡ በኋላ ባሉት ስድስት ዓመታት ብቻ በክልሉ ከ230 በላይ አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ፋብሪካዎች ተከፍተዋል።
ቀደም ሲል በክልሉ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ይህ ነው የሚባል ሥራ እንዳልነበር የጠቀሱት ፕሬዚዳንት ሙስጠፌ ፤ ለዚህም ምክንያቶቹ፣ የሰላም እጦት ፣ የኢንቨስተሩ ዋስትና ማጣት እንዲሁም የነበረው መንግሥት ለኢንቨስትመንት ትኩረት አለመስጠቱ እንደሆኑ ጠቅሰዋል። በዚህም ምክንያት ከለውጡ በፊት በክልሉ አጠቃላይ የነበሩት ፋብሪካዎች....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129478