Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥብ‼️

#በኢኮኖሚ ጉዳዮች

👉 ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ በዓለም አቀፍ በተከታታይ በሚያደርሱብን ቀውስ ውስጥ ነው ያለነው፤

👉 በቅርብና በሩቅ ያለው ቀውስ ወደ እኛ ሲመጣ የኢኮኖሚ ጉዞውን አተካች አድርጎብናል፤

👉 የለውጡ መንግስት በተለየ የገጠሙን ተግዳሮቶች ነበሩ፤ አንደኛው የወረስነው እዳ ነው፤

👉 መሮጥ በሚገባን ልክ ለመሮጥ ፈተና የጋረጠብን ቢሆንም፤ ከፈተናዎች ውስጥ እድልን ፈልቅቆ የማውጣት በተቀየረ የአሰራርና የስራ ባህል መከተል በመቻላችን እጅግ ስኬታማ አመት ነወ ያሳለፍነው፤

👉 በዚህ አመት በሁሉም ዘርፍ በስኬት ነው ያሳለፍነው፤

👉 ኢትዮጵያ ውስጥ 64 ሺህ ሰዎች የሚከፍሉት ግብር ኢትዮጵያ ለምታስበው ልማት ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመምራት እንቸገራለን፤

👉 ላለፉት ስድስት አመታት አንድ ዶላር ኮሜርሻል ብድር አልወሰድንም፤

👉 ኢትዮጵያ ያለበት ዓለም አቀፍ ብድር ወደ 17 ነጥብ 5 ከጂዲፕው ዝቅ ብሏል፤

👉 ዘንድሮ ከአምና 4 በመቶ የበለጠ የውጭ ንግድ ገቢ ተገኝቷል፤

👉 አሁንም ኢትዮጵያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ናት፤

👉 ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሆኑ ምርቶችን በአገር ውስጥ ምርት መተካት ችለናል፤

👉 የፋብሪካ ምርቶችን 40 በመቶ በአገር ውስጥ ምርት መተካት ችለናል፤

👉 ለነዳጅ አራት ቢሊዮን ፣ ለማዳበሪያ አንድ ቢሊየን እንዲሁም ለእዳ ክፍያ 2 ቢሊዮን ዶላር በአመት እናወጣለን

👉 ከለውጡ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ መኪና በእጥፍ አድጓል፤ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የግል መኪናዎች ናቸው፤

👉 የፋይናንስ ዘርፉ ባንኮች ዛሬ ከ17 ወደ 32 ደርሰዋል፤ ቅርንጫፎቻቸውም አድጓል፤

👉 38 ሚሊዮን የነበረው የቁጠባ ደብተር ከ100 ሚሊዮን በልጧል፤

👉 የፋይናንሻል ዘርፉ ጤናማና መሻሻል ያሳየ ነው፤ ባንኮች ትርፋማም ናቸው፤
"ከ64 ሺህ ግለሰቦችና ተቋማት ግብር በመሰብሰብ የ120 ሚሊየን ዜጎችን ጥያቄ ለመመለስ እየሰራን ነው"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥብ‼️

👉 ዛሬ 47 ሚሊዮን ዜጎች በሞባይል ባንኪንግ ይጠቀማሉ፤

👉 እዚህ የደረስነው ኢትዮ ቴሌኮም ለዘመናት ተኝቶ ከነበረበት ሳፋሪኮም ሊመጣ ነው ሲባል ነቅቶ ነው፤

👉 ይሄንን ስኬት በባንኮች መድገም እንፈልጋለን፤

👉 ለረጅም ጊዜ ዘግተን አቆይተናቸዋል፤ አሁን እንደዛ አንቀጥልም፤

👉 የዋጋ ግሽበት ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የሁሉ ዓለም አጀንዳ ሆኗል፤

👉 በዓለም ላይ ባሉ አገራት በሚካሄዱ ምርጫዎች ዋናው የመከራከሪያ ጉዳይ ይሄው የኑሮ ውድነት ሆኗል፤

👉 ስንዴ ባለፈው አመት 395 ሚሊዮን ነበር ያመረትነው፤ ዘንድሮ 587 ሚሊዮን ኩንታል ነው ያመረትነው፤

👉 ከዚህ በላይ ምርት የማሳደግ አቅምና እድል አለን፤

👉 ከለውጡ በኋላ ዘመናዊ ቀፎ ቁጥር 1 ሚሊዮን ደርሷል፤ የማር ምርት ከሰባት እጥፍ በላይ አድጓል፤

👉 ምግብ ነክ ለሆኑ ከውጭ የገቡ ምርቶች መንግስት ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ የግብር እፎይታ ሰጥቷል፤

👉 የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ወደ 23 በመቶ ዝቅ ብሏል፤

👉 ዘንድሮ 24 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ለማረስ እቅድ ተይዟል፤

👉 ዘንድሮ አንድ የተሳካልን መስክ ቢኖር የኢንዱስትሪው ዘርፍ ነው፤ ይሄ የሆነው ኢትዮጵያ ታምርት በሚለው ንቅናቄ ነው፤

👉 ዘንድሮ በነባር የሲሚንቶ ፋብሪካ ብቻ 30 በመቶ የምርት እድገት መጥቷል፣

👉 ለሚ በቅርቡ ስራ ይጀምሯል፤ ይሄ ፋብሪካ አሁን እንደ አገር የሚመረተወን ምርት 50 በመቶ ያህል ብቻውን ያመርታል፤

👉 በተለይ የሌማት ትሩፋት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና እያበረከተ ይገኛል፣

👉 መንግስት 10 ቢሊዮን ብር ገቢ በመተው መሰረታዊ ሸቀጦችን ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ አድርጓል፣
"የኤክስፖርት ገቢ ከአምናው ከ4 በመቶ በላይ ዕድገት ተመዝግቧል፣ ከሬሚታንስ 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ተገኝቷል"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥብ‼️

👉 ኢትዮጵያ 15 ሚሊዮን ኩንታል የአፋር ማዳበሪያ ነው የምታስገባው፤ ወደብ ሳይኖራት ይሄንን ማስገቧቷ ትልቅ ስራ ነው፤

👉 ከዚህ ውስጥ ከ13 ሚሊዮን በላይ ኩንታሉ ተሰራጭቷል፤

👉 የስንዴ ልማት ስንጀምር አገር ውስጥ ምርጥ ዘር አልነበረም፤ ከውጭ ነበር የምናስመጣው፤

👉 ይሄ አደገኛ ነው ብለን በሰራነው ስራ በስንዴ 67 በመቶ ደርሰናል፤ በሚቀጥሉት አመታት በሌሎች ሰብሎችም በምርጥ ዘር አቅርቦት ራሳችንን እንችላለን፤

👉 ዘንድሮ ብቻ 40 ሺህ የውሃ ፓመፕ ወደ አገር ውስጥ ገበቷል፤

👉 ከ3 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ስራ አስይዘናል፤ ከዚህ ውስጥ 3 ነጥበ 4 በአገር ውስጥ ነው፤

👉 3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ያልነው ከመጣልን ሪፖርት ውስጥ 17 በመቶውነ ቆርጠን ነው፤ የተጋነነ እንዳይሆን፤

👉 በውጭ አገር 332 ሺህ ሰው በህጋዊ መንገድ ሰልጥኖ ወደ ውጭ አገር ለስራ ተልካል፤ ይሄ ከአምናው በእጥፍ ያደገ ነው፤

👉 ሌላው ተስፋ ሰጪ ዘርፍ ስታርታፕ ብለን የጀመርነው ነው፤ በዚህ ዘርፍ 60 ሺህ ሰው ደርሷል፤ እነዚህ ከፍተኛ ተከፋይ ናቸው፤
"የዋጋ ግሽበትን ከ30 በመቶ ወደ 23 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል፤ ነገር ግን ይህ በቂ አይደለም ብለን ጠንክረን እየሠራን ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስለ መምህራን እና ወታደሮች ምን አሉ?

👉 ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ካደረጉ ወሳኝ ምሰሶዎች መካከል ሶስቱን ብቻ ብጠቅስ አርሶ አደር፣ ወታደር እና መምህር ናቸው፤

👉 አርሶ አደሩ ማዳበርያም እየደጎምን ኩታ ገጠምም እያልን የውሃ ፓምፕም እያቅረብን ኑሮው ከጊዜ ወደ ጊዜ ለውጥ እያሳየ ነው፤

👉 ወታደርና መምህር ግን ለኢትዮጵያ ደማቸውን ከመስጠት ውጭ አስካሁን ባለው ሁኔታ ከኢትዮጵያ ነገ በልጆቻችን እናየዋለን ከሚል ተስፋ ውጭ በቂ ነገር አግኝተው አያውቁም

👉 ከማንም በላይ ህይወታቸውን እውቀታቸውን የሚገብሩ የስራ መስኮች ሆነው በቂ ክፍያ የማያገኙ ናቸው፤

👉 መምህራንና ወታደሮችን ምሰሶ ሆነው ተርበው ባያስተምሩ ኖሮ እንደ ሀገርስ መቀጠል እንችል ነበር ወይ የሚል ጥያቄ ያስነሳል፤

👉 የተከበረው ምክር ቤት በዚህ አጋጣሚ ለኢትዮጵያ መምህራንና ወታደሮች ክብር እንዲሰጥልኝ በትህትና አጠይቃለሁ፤

👉ህይወታቸውን ለማሻሻል ተጨማሪ እርምጃዎች መንግስት ይወስዳል፤

👉የሚገባቸውን ባይሆንም በመጠኑም ቢሆን ይሰጣቸዋል፤
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥብ‼️

👉 ዘንድሮ 45 ሚሊዮን ዶላር አወጥተን በርካታ መጻህፍት ሳትመን አስገብተናል፤

👉 በዩኒቨርሲቲ መስክ ለውጥ ከመጣ ጀምሮ በአንድም ቦታ አንድም ዩኒቨርሲቲ አልሰራንም፤

👉 እየሰራን ያለነው ቅድመ ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋት ላይ ነው፤

👉 ዩኒቨርስቲን ማስፋት ሳይሆን ጥራት ማስጠበቅ ላይ ማተኮር ይሻላል፤

👉 እስካሁን ባለው ሁኔታ መምህራንና ወታደሮች ደማቸወን ላባቸው ከመስጠት ውጭ ከኢትዮጵያ በቂ ክፍይ አላገኙም፤

👉 የተከበረው ምክር ቤት ለኢትዮጵያ መምህራንና ወታደሮች ክብር እንዲሰጥልኘ እጠይቃለሁ፤

👉 እስካሁን በአገር ውስጥ ስናመርት የነበረውን መድሃኒት ከ8 በመቶ ወደ 36 በመቶ አሳድገናል፤

👉 ከጤና ተቋማት ግንባታ አንጻርም በመንግስትመ በግልም ዓለም አቀፍ ደረጃቸወን የጠበቁ ተቋማት ተገንብተዋል፤

👉 ዘንድሮ በኢኮኖሚ 7 ነጥብ 9 በመቶ እድገት ይጠበቃል፣

👉 ለቀጣይ አመት 971 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዟል፤ አብዛኛው በጀት ለድህነት ቅነሳ የተያዘ ነው፤

👉 ይሄ በጀት በቂ አይደለም፤ ነገር ግን የበጀት ጉድለቱ ከዚህ በላይ እንዲሆን አልፈቀደልንም፤

👉 ከለውጡ ወዲህ የኢትዮጵያን ጂዲፒ በእጥፍ አሳድገናል፤

👉 ከለውጡ መንግስት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ስድስቱ ጎረቤቶቻችን ተደምረው የእኛን ኢኮኖሚ አያክሉም፤

👉 በዘንድሮው ዓመት በአገር አቀፍ ደረጃ የኮሌራ ወረርሽኝን ለመከላከል 10 ሚሊዮን ክትባት ተሰጥቷል፣

👉 የኩፍኝ ወረርሽኝን ለመከላከልም በ58 ወረዳዎች ክትባት ተሰጥቷል

👉 የወባ አጎበር ስርጭትም ተከናውኗል፣

👉 በተለይ የመድሃኒት አቅርቦትን በአገር ውስጥ በመተካት ረገድ ከ8 በመቶ ወደ 36 በመቶ ማደረስ ተችሏል፣
"ሦስት ክላሽ ሲይዙ አራት ኪሎ ይታያቸውና ውር ውር ይላሉ፤ትንሽ ሲቆነጠጡ ጄኖሳይድ ተፈጸመ ይላሉ"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥብ‼️

👉 ለውጡ ያስፈለገው ሰው ለመቀያየር አይደለም፤ ስብራቶቻችንን ለማከም ነው፤

👉 አንዱ ስብራታችን የነበረው የኢኮኖሚ ስብራት ነው፤ በአገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲዎቻችንን እዳን ቀንሰናል፤

👉 በማንኛውም ጉዳይ ብትመረምሩ ሙስናን ጨምሮ ታግለን ላመጣነው ፍሬ እውቅና የመስጠት ባህል የለንም፤

👉 ለውጡ በፖለቲካው መስክም ከኤርትራም ከኬንያም ከጫካም ያሉትን ጋብዟል፤

👉 የሰላም ችግር በአገራችን ውሎ ያደረ ስር የሰደደ በሽታ ነው፤

👉 ኢትዮጵያ ውስጥ መፈንቅለ መንግስት ጭራሽ አይሳካም፤

👉 አንድ እንሁን ሰብሰብ እንበል የጋራ አገር ነው ያለን፤

👉 በአማራም በኦሮሚያም ክልል ያለው ችግር በሁለት ተከፍሎ የሚታይ ነው፤

👉 አንደኛው ዱር ግባ የሚል ፕሮፖጋንዳ ሰለባ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ ጥራኝ ዱሩ የሚል ነው፤

👉 አማራ ኦሮሚያ ትግራይ ሰላም ካልሆነ የመጨረሻ ተጎጂ እኛ ነን፤ ያሰብነውን መስራት አንችልምና፤

👉 በፕሪቶሪያ ስምምነት ምክንያት ተኩስ ቆሟል፤ የሚሞት ሰው ቆሟል፤ የታሰሩ ተፈተዋል፤ የቆሰሉ ታክመዋል፤ ከስራ የታገዱ ስራ ይዘዋል፤ የተለያዩ ቤተሰቦች ተገናኝተዋል፤

👉 የትግራይ ህዝብ ያገኘው እፎይታ የእኛም እፎይታ ነው፤

👉 በራያና ጸለምት የተፈናቀሉ ሰዎች እየተመለሱ ነው፤

👉 በትግረይ ክልላዊ ሽግግር መንግስት በህወሓት ዋና ዋና መሪዎች ላይ እምነት አለኝ፤ ችግሩ በሰላም እንዲፈታ ፍላጎት አላቸው፤

👉 አሁንም ግን እልህኘነትና ቁጣ ያላቸው አሉ፤ ይሄ አካሄድ ይጎዳል፤

👉 እኛ አማራም በኦሮሚያም በትግራይም ግጭት አንፈልግም፤
"በግጭት በሽፍታነት በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን እንይዛለን ብሎ ማሰብ እንደተበላ ብሎን ነው፤ ይሽከረከራልእንጂ አይጠብቅም፣ አይሰራምም"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥብ‼️

👉 ብዙ የአፍሪካ አገራት የሚታመሱት ሰብአዊ መብት በሚል ታርጋ ነው፤

👉 ሰብአዊ መብት በሙሉ መልኩ ነው መታየት ያለበት እንጂ በሚዲያ ብቻ በሚነዛ ነገር አይደለም፤

👉 የሰብአዊ መብት ተቋማት ከእኛም ከሌላ አለም አቀፍ አካልም ነጻ መሆን አለባቸው፤ የእኛዎቹ ከእኛ ነጻ ሆነዋል፤

👉 ሙስና ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ የሆነ ምልከታ አለው፤

👉 ሌብነት ነቀርሳ ነው፤ ሌባ ሰው ምንም ቢሆን ዋጋ የለውም፤

👉 ኢትዮጵያ ውስጥ የተጀመረው ሌብነት የተጀመረውን ጉዞ ያደናቅፋል፤

👉 ይሄ ፓርላማ ሙስናን እንድንታገል ይፈልጋል ወይ፤ የኢትዮጵያ ህዝብስ ይፈልጋል ወይ፤

👉 የኢትዮጵያ መንግስት በመቶ በመቶ የማረጋግጥላችሁ መንግስታዊ ሌብነት አያካሂድም፤

👉 ይሄ ማለት ግን በግለሰብ ደረጃ ሌብነት የለም ማለት አይደለም፤

👉 ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሙስና አፍሪካ ውስጥ ካለው ሙስና ጋር አይወዳደርም፤

👉 አቅማችን በፈቀደ መጠን ሌቦችን እየተከታተልን ርምጀጃመውሰድ አለብን፤ እንቀጥላለን፤

👉 የፕሪቶሪያው ስምምነት ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ረገድ የባህል ለውጥ ያመጣንበት ነው ፣

👉 ተኩስን በማቆም አገልግሎትን በማስጀመር ትልቅ ድል አግኘተንበታል፡፡

👉 ባንኮች፣ አየር መንገድ፣ ቴሌኮምን ጨምሮ በርካታ አገልግሎቶችን ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል

👉 በስምምነቱ መሰረትም በጦርነቱ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ስራ ጀምረናል፣
"የትግራይ ህዝብ ዕፎይታ የእኛም ዕፎይታ ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥብ ‼️

👉የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት በርካቶችን ለውጧል፤

👉የኮሪደር ልማቱን ስራ ስንሰራ አልጋ በአልጋ አልነበረም፤

👉እንደዚህ አይነት ጅምሮች ከሚዛናቸው በላይ ማድነቅ አይጠበቅብንም፤ ገና ብዙ ስራ አለን፤


👉ዲፕሎማሲያችን ጎረቤት ተኮር ነው፤ በሱዳን የምንከተለው ፖሊሲ ለሁለቱም ወገን መቶ በመቶ ገለልተኛ ሆነን ነው፤

👉የሶማሌ መንግስት በአንድ ሰአት በረራና በአንድ ሰአት ውይይት ፍላጎት ካለው ይሄንን ነገር ማስተካከል ይችላል፤

👉የመረጠው ግን በየሰፈሩ እየዞሩ እኛን መክሰስ ነው፤

👉የኢትዮጵያ መንግስት ሶማሊያ እንድትፈርስ እንድትበተን አይፈልግም፤ ለዛም ነው ልጆቻችንን ልከን የምንጠብቃት፤

👉የኢትዮጵያ መንግስት ለጋራ ጥቅም ሁሌም ዝግጁ ነው፤ እነሱም እንደዛ ማሰብ አለባቸው፤

👉ኢትዮጵያን ለማጽናት ማገር እንጂ መጋዝ መሆን የለብንም
የ2017 የፌዴራል መንግስት በጀት 971 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ሆኖ ፀደቀ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበለትን የ2017 የፌዴራል መንግስት በጀት አጽድቋል።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው መደበኛው ስብሰባው የፌዴራል መንግስት የ2017 በጀትን 971 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር እንዲሆን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያም ሰጥተዋል።
ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓም
ኢትዮጵያውያን የተረጂነት ሥነ-ልቦናን በማሸነፍ የተከበረች ሀገር ለቀጣዩ ትውልድ ሊያስተላልፉ ይገባል
*******************
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያውያን የተረጂነት ሥነ-ልቦና በማሸነፍ ምርታማነቷ የተረጋገጠና የተከበረች ሀገርን ለቀጣዩ ትውልድ ሊያስተላልፉ እንደሚገባ አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሀዳ ሲንቄዎች ገለጹ፡፡

የኦሮሞ አባ ገዳ ኅብረት ጸሐፊና የቱለማ አባ ገዳ ጎበና ሆላ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የነፃነት ተምሳሌት የሆነች ኢትዮጵያን ክብርና ሉዓላዊነት እየተገዳደረ የሚገኘውን የተረጂነት ችግር ኢትዮጵያውያን ተባብሮ በመሥራት ምርታማነቷ የተረጋገጠና የተከበረች ሀገርን ለቀጣዩ ትውልድ ሊያስተላልፉ ይገባል፡፡

በገዳ ሥርዓት ውስጥ አንድ ሰው በሕይወት ቆይታው እራሱን ለመቻል ምን መደረግ እንዳለበት በግልጽ መቀመጡን ገልጸው ከተረጂነት አስተሳሰብ ለመውጣት የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በመቀናጀት መሥራት ይኖርበታል ብለዋል፡፡

ተረጂነት ክብረነክ መሆኑን የጠቀሱት አባ ገዳ ጎበና ይህም በኢትዮጵያ ባሕል ውስጥ አጸያፊና ነውር የሆነ ተግባር ነው ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያን ፀጋ በማልማት ጥቅም ላይ ማዋል ባለመቻሉ ተረጂነትና ልመና ልምድ ሆኖ መቀጠሉን ገልጸው ይህም የመሥራት........
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131282
በሀረሪ ክልል በነገው ዕለት የዲያስፖራ አባላት 500 ሺህ ችግኞችን ይተክላሉ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

በሀረሪ ክልል በነገው እለት የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዲያስፖራ አባላትና የክልሉ ነዋሪዎች በተገኙበት በይፋ ይጀመራል።

ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የክልሉ የዲያስፖራ አባላትም በነገው እለት በሚጀመረው ክልላዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ላይ 500 ሺህ ችግኞችን ይተክላሉ። የዲያስፖራ አባላቱ እንደየመጡበት አካባቢ የመትከያ ስፍራ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል።

ሀገራዊውን ጥሪን በመቀበልና በ26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን ለመሳተፍ በርካታ ሀረሪዎችና የሀረር ተወላጆች ወደ ሀገር ቤት መግባታቸው የሚታወስ ሲሆን የሚያስፖራ አባላቱ በሚኖራቸው ቆይታም በአረንጓዴ አሻራ በተጨማሪ በበጎ ፍቃድ አገልግሎትና በሌሎች መርሃግብሮች ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል።

አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል አስፈላጊውን ዝግጅት መጠናቀቁ ይታወሳል።
ሰኔ 28 ቀን 2016 ዓም
ሀገራዊ መረጃዎች እንዳይጠፉ ተቋማት ለሰነድ አያያዝና አወጋገድ ትኩረት እንዲሰጡ ተጠየቀ
******************
(ኢ ፕ ድ)

ሀገራዊ መረጃዎችን የያዙ ሰነዶች በእርጅና ምክንያት እንዳይጠፉ ተቋማት ለሰነድ አያያዝና አወጋገድ ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጽሐፍት አገልግሎት ጠየቀ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጽሐፍት አገልግሎት ዋና ዳሬክተር አቶ ይኩኑአምላክ መዝገቡ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የተለያዩ ተቋማት ለሥራ የሚያመነጯቸው ሰነዶች ከጊዜ በኋላ ሀገራዊ መዛግብት በመሆናቸው ተቋማት ለሰነድ አያያዝና አወጋገድ ልዩ ትኩረት ሊሠጡ ይገባል፡፡

እንደ አቶ ይኩኑአምላክ ገለጻ፤ በርካታ ተቋማት የቦታ ጥበት አጋጥሞናል በሚል ምክንያት መዛግብቶችን በጆንያ እያከማቹና ከሕግ አግባብ ውጪ ጥቅም አይሰጥም በሚል እስከማቃጠል የደረሱ አሉ፡፡

የሰነዶችን አያያዝ በሚመለከት የወጡ ጥብቅ ሕጎች ቢኖሩም ከግንዛቤ ማነስና በሌሎች ምክንያቶች አስፈላጊ ሰነዶች እየጠፉ.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131309
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️
የህዝብን ቅሬታ በመስማት የኢሚግሬሽን ስራ ማስተካከያ የሚሹ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት እና ተቋማዊ ለውጦችን በማከናወን በጥቂት ወራት ውስጥ ብዙ ማሻሻያዎች እየተተገበሩ ይገኛሉ። ለምሳሌ ያህል፤
👉 በቀን 900 ፓስፖርት መስጠት የነበረውን አገልግሎት ወደ 1700 ማድረስ ተችሏል፣
👉 ቀደም ብለው የተጠራቀሙ ጥያቄዎችን አስተናግዶ ለመጨረስ በተሰራ ስራ አንድ ሚሊየን ፓስፓርት ታትሞ ገብቶ እስከ 87 በመቶ ተሰራጭቷል፣
👉 የተከማቹ ቅሬታዎች 100% ተፈትተዋል፣
👉 በኢትዮዽያ በህገወጥ መንገድ የሚኖሩ 10,467 ሰዎችን መመዝገብ ተችሏል፣
👉 ሃሰተኛ ማስረጃ የያዙ 18,000 ሰዎች ቅጣት እንዲከፍሉ ተደርጓል፣
👉 በ88 ሀገሮች የቪዛ አገልግሎት በመክፈት ለ819 278 ተስተናጋጆች e-visa ጨምሮ የቪዛ አገልግሎት ተሰጥቷል
👉 ለ4,276,474 ግለሰቦች በአየርና በየብስ መዳረሻ ጣቢያዎች አገልግሎት ተሰጥቷል
በአሁኑ ወቅትም ተቋሙን የዘመነ እና አገልግሎቱን በጥራት የሚሰጥ ተቋም ለማድረግ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ ነው።
ሰኔ 28 ቀን 2016 ዓም