Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የመቻል ስፖርት ክለብን 80ኛ ዓመት ምስረታ በዓልን አስመልክቶ በአዲስ አበባ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ተጀመረ
*******
(ኢ ፕ ድ)

መቻል ስፖርት ክለብን ወደ ቀደመ ገናና ስሙ የመመለስና ክለቡን የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ ይገኛል። የክለቡን 80ኛ የምስረታ ዓመት በዓልን አስመልክቶ የገቢ ማሰባሰቢያ በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በዝግጅቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች፣ ባለሃብቶች፣ ብሔራዊ ስፖርት ፌዴሬሽንና ማኅበራት፣ የመቻል ስፖርት የቀድሞ ስፖርተኞች፣ የስፖርትና የኪነ-ጥበብ ሙያተኞችና ጥሪ የተደረገላቸው ግለሰቦች ታድመዋል፡፡

ክለቡን ለማጠናከርና በኢትዮጵያ ስፖርት ውስጥ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት በሚደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ሕብረተሰቡ፣ ባለሃብቶች፣ ተቋማትና ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ ቀርቧል፡፡

የመቻል ስፖርት ክለብን መደገፍ የሚፈልጉ አካላት በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በመወደወል ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ።

• 0961910613

• 0961338325

• 0961875492

• 0961940938

• 0961997624

• 0961504532

በሌላ በኩል ከታች በተዘረዘሩት በገቢ ማሰባሰቢያ ሒሳብ ቁጥሮች ገንዘብ ገቢ ማድረግ እንደሚቻል ጥሪ ቀርቧል፡፡

• 1000603377137 (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

• 190757676 (አቢሲኒያ ባንክ)

• 0579717935011 (ዳሽን ባንክ)

• 013071350236800 (አዋሽ ባንክ)

• 1042400179571 (ኦሮሚያ ህ/ስራ ባንክ)

• 10702376 50215 (ስንቄ ባንክ)

• 1724954200001 (ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል)

• 9900032504845 (አማራ ባንክ)

• 00111849630400001 (እናት ባንክ)

• 1000000894676 (መቻል ስፖርት ክለብ)

መቻል የእግር ኳስ ክለብ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወቃል።

በሳሙኤል ወንደሰን

ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️

የአራት ኪሎ-ቀበና-ኬንያ ኤምባሲ ኮሪደር ሥራ ተጠናቋል። አካባቢውን አረንጓዴ የማድረግ ጥረቱ በጉልህ ይታያል። ባለፉት ሳምንታት የምሽቱን ውበት እንዳደነቅነው ዛሬ ደግሞ የማለዳን እይታ በኮሪደር ልማታችን ተመልክተናል። ለስኬቱ በሥራው ለተሳተፉት የከተማው አስተዳደር እና በሙሉ ፈቃድ ለተሳተፉ የግሉ ሴክተር ምስጋና ይገባል።

የከተማችንን የመኪና ማቆሚያ እጥረት የሚቀርፉ የፓርኪንግ ቦታዎች ተገንብተዋል። የእግር ጉዞን የሚያበረታቱ የእግረኛ መንገዶች ተስፋፍተው ተሰርተዋል።

ይህን ባሕል መንከባከብ እና ማሳደግ ይገባል። ሁላችንም ህልውና ለሆነው አዲስ መልክ ጠባቂዎች መሆን አለብን።

ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓም
የአራት ኪሎ-ቀበና-ኬንያ ኤምባሲ ኮሪደር ሥራ ተጠናቋል፤ የአራት ኪሎ-ቀበና-ኬንያ ኤምባሲ የኮሪደር ልማት በፎቶ‼️

ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓም
ቢያዳፍኑት፤ በይርጋ የማያልፈው ሕገወጥነት
****
(ኢ ፕ ድ)

ከሰሞኑ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለቋሚ ኮሚቴ መርቷል። ረቂቅ አዋጁ ማንኛውም ሰው ያፈራውን ገንዘብ ከሕጋዊ ምንጭ ስለመገኘቱ ማረጋገጫ እንዲኖረው የሚያስገድድ ነው።

ከዚህ በፊት በነበሩ ድንጋጌዎች ምንጩ ያልታወቀ ንብረት የሙስና ወንጀል በመሰኘት ለመንግሥት እና ሕዝባዊ ድርጅቶች ሠራተኞች ብቻ የወንጀል ተጠያቂነትን ያስከትል እንደነበር ረቂቅ አዋጁ ጠቅሷል። ሆኖም አሁን በተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ ማንኛውም ግለሰብ እና ሕጋዊ ሰውነት ያለው ተቋም ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ ሲገኝባቸው ተጠያቂ የሚደረጉ መሆኑን ያትታል።

ይህን አዋጅ ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱና ዋንኛው ምንጩ ያልታወቀ ሀብትን የመውረስ ድንጋጌው እስከ 10 ዓመታት ወደኋላ ተመልሶ ተፈጻሚ እንደሚሆን መደንገጉ ነው።

ታዲያ ይህ አዋጅ በዘርፉ ምሁራን ዘንድ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡበት ይገኛል። በአንደኛው ጎራ ያሉ የዘርፉ ምሁራን ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ምንም ያህል ጊዜ ወስዶ ቢደረስበት ከተጠያቂነት መዳን የለበትም ይላሉ። በሌላኛው ጎራ ያሉት የሕግ አዋቂዎች ደግሞ ከረቂቁ ወደኋላ 10 ዓመታትን ተመልሶ ተጠያቂ ያደርጋል የሚለውን ድጋጌን በማንሳት አንድ ሕግ ወደ ኋላ ሄዶ አይተረጎምም፤ ይህም ከሕግ አሠራር....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131599