ሰው ሠራሽ አስተውሎት – የነገዋ ኢትዮጵያ አንዱ ተስፋ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ(የሰው ሠራሽ አስተውሎት) ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሕይወታችን ውስጥ ያለው ወሳኝ ሚና እየጨመረ ይገኛል፡፡
የሶፍትዌር መሐንዲሶች እንደሚገልጹት የሰው ሠራሽ አስተውሎት ኮምፒዩተሮችና ማሽኖች እንደ ሰው ልጅ እንዲያመዛዝኑ፤ ነገሮችን እንዲገነዘቡ፤ ማንኛውንም ነገር እንዲማሩ፤ እንዲያቅዱና ፈጠራዎችን እንዲከውኑ በማድረግ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ እንዲያሳኩ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው።
ቴክኖሎጂ የራሱ የሆነ አወንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖዎች ቢኖሩትም አውንታዊ ጎኑን መረዳትና በአግባቡ መጠቀም ይገባል፡፡
ወጣት ቶማስ ወርቅነህ ይባላል፤ በምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአይ ሲቲ ትምህርት ክፍል የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ነው፡፡
ወጣቱን ያገኘነው በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው 14ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ላይ የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን........
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131653

ሕዝብና መንግሥትን ያስታረቀው – የዱግና ድልድይ
******************
(ኢ ፕ ድ)
በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን መዋቅር ሥር ከሚገኙ ወረዳዎች፣ ሎካ አባያ ወረዳ አንዱ ነው።
ይህ ወረዳ 23 ቀበሌዎች ያሉት ሲሆን፤ በወረዳው ከሚገኙ ትልልቅ ወንዞች አንዱ የሆነው ግዳቦ ወንዝ ወረዳውን ለሁለት ከፍሎ ያልፋል።
ወንዙ ላይ ተሽከርካሪ የሚያልፍበት፣ ሰው የሚሻገርበት ዘመናዊ ድልድይ ለዘመናት ስላልነበረ፤ ምጥ የተያዘች ወላድ እንዲሁም በጽኑ የታመመ በሽተኛ በቃሬዛ ሆነው በሰው ሸክም ነበር ወደ ጤና ተቋም የሚያመሩት።
ወንዙ ሲሞላ ሁሌም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው አይሄዱም ነበር።
በተለይ በክረምት ወራት የአንድ ወረዳ ማህበረሰብ እንዲሁም የቤተሰብ አባላት ጭምር ከወንዝ ወዲህና ወዲያ ሆነው በዓይን እየተያዩ በኀዘንና በደስታ መገናኘት አይችሉም ነበር ይላሉ የወረዳው ነዋሪ አቶ ካሳሁን ከበደ።
ሁሌም ክረምት በመጣ ቁጥር ወንዙን እንሻገራለን እያሉ የብዙ ሰዎች ሕይወት ያልፋል የሚሉት አቶ ካሳሁን፤ “የአህያ ባል ከጅብ አያድን” እንዲሉ የአካባቢው ማህበረሰብ ወንዙ ላይ በእንጨት ርብራብ ይሠራው የነበረው ባሕላዊ ድልድይ ክረምት ሲመጣ በጎርፍ ስለሚወሰድ፤ ወንዙን አያሻግርም።
ሆኖም ሁሌም ክረምቱ ሲያልፍ የአካባቢው ማህበረሰብ “ለሰውና ለእንስሳት መተላለፊያ” በሚል በእንጨት ርብራብ ባሕላዊ ድልድይ እየሠራ......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131643

"በ2016/17 የመኸር ምርት 9 ሺህ ሄክታር መሬት በበርበሬ ለመሸፈን እየተሰራ ነው"- የሀላባ ዞን ግብርና መምሪያ
****************
(ኢ ፕ ድ)
በበርበሬን በስፋት በማምረት ከሚታወቁ አካባቢዎች መካከል የሀላባ ዞን አንዱ ነው፡፡
የሀላባ በርበሬን የምርታማነት ችግር በመቅረፍ አምራች አርሶ አደሩን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡
የበርበሬን በጥራትና በብዛት በማምረት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እንዲሁም ለኤክስፖርት በሚሆን ደረጃ ለማምረት እንዲቻል ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ።
በ2016/17 የመኸር ምርት ዘመን 9 ሺህ ሄ/ር መሬት በበርበሬ በመሸፈን 108 ሺህ ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ መሆኑን የሀላባ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀጂ ኑሪዬ ተናግረዋል።
በዞኑ በርበሬ በዋናነት የመኸር ሰብል መሆኑን ያነሱት ኃላፊው ከ3 ዓመት ወዲህ በበልግ ማልመት በመጀመሩ የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት እንዳሻሻለ አብራርተዋል።
በዞኑ በተመረጡ 10 ቀበሌዎች በበልግ ወቅት የበርበሬ ልማትን ለማስፋፋት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት በፖርት ሱዳን ተገኝተዋል። ጉዞው ጠቅላይ ሚኒስትር ለሱዳን መረጋጋት የሚያከናውኑት ጥረት ቀጣይ ርምጃ ነው ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓም
ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓም
ኢትዮጵያ በሰኔ ወር 46 ሺህ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ አቀረበች
******
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ በሰኔ ወር 46 ሺህ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ ማቅረቧን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
በወሩ ለውጭ ገበያ የቀረበው የቡና መጠን ክብረወሰን የሰበረ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በዚህም ከቡና ሽያጩ 218 ሚሊዮን ዶላር ማግኘት ተችሏል።
በጠቅላላ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለውጭ ገበያ የቀረበው ቡና 298 ሺሕ 500 ቶን ሲሆን፤ ከወጪ ንግዱ የተገኘው ገቢ 1 ነጥብ 43 ቢሊዮን ዶላር መሆኑ ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር፣ የዘንድሮው በጀት ዓመት የቡና የወጪ ንግድ መጠኑ የ20 በመቶ ብልጫ እንዲሁም ከገቢ አንጻር የ7 ነጥብ 5 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️
የወንድም ሱዳን ህዝብ ችግር የኛም ችግር ሰላማቸውም ሰላማችን በመሆኑ ለሱዳን ህዝብ እፎይታ እና የብልፅግና ጉዞ ዛሬም እንደ ትላንቱ ከልብ እንሰራለን።
ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓም
የወንድም ሱዳን ህዝብ ችግር የኛም ችግር ሰላማቸውም ሰላማችን በመሆኑ ለሱዳን ህዝብ እፎይታ እና የብልፅግና ጉዞ ዛሬም እንደ ትላንቱ ከልብ እንሰራለን።
ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓም
📌 ከተፈቀደ ቦታ ውጪ ቆሻሻ የጣሉ እስከ 100 ሺ ብር ተቀጡ
📌 በመንገድ አካፋይ ላይ ጉዳት ያደረሱ እስከ 300 ሺ ብር ተቀጠዋል
📌 ከተፈቀደው የእግረኞች መንገድ ውጪ የሄዱ እስከ 1000 ብር ተቀጡ
*****
(ኢ ፕ ድ)
በመዲናዋ በበርካቶች የቀን ከሌሊት ልፋት ውብ ተደርገው በተገነቡ መሰረተ ልማቶች ላይ ቆሻሻ የሚጥሉ፣ ከተፈቀደላቸው መንገድ ውጪ የሚሄዱ እንዲሁም ከተማዋን አረንጓዴ ለማድረግ በመንገድ አካፋዮች ላይ የተተከሉ ዛፎችን በግዴለሽነት በተሽከርካሪ በመግጨት ጉዳት ያደረሱ አካላት ተቀጡ።
በዚህም 3 ተቋማት ከተፈቀደ ቦታ ውጪ ቆሻሻ በመጣል እንደየጥፋት ደረጃቸው 100 ሺሕ ፣ 50 ሺ እና 20 ሺሕ ብር የተቀጡ ሲሆን 5 አሽከርካሪዎች በመንገድ አካፋይ ላይ ጉዳት በማድረሳቸው ከ150 እስከ 300 ሺሕ ብር እንዲሁም 11 ሰዎች ከተፈቀደው የእግረኞች መንገድ ውጪ በመሄዳቸው ከ150 እስከ 1000 ብር ተቀጥተዋል።
ነዋሪዎቻችን እነዚህ ደረጃቸውን ጠብቀው የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን በተፈቀደው መንገድ ብቻ በመጠቀምና በመንከባከብ እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ከቅጣትና ከትራፊክ አደጋ እንዲከላከሉ የከተማ አሰተዳደሩ ማሳሰቡን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓም

ቁጭት የወለደው የ’ገበታ ለትውልድ’ ፕሮጀክት
**************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ከ ‘ገበታ ለሀገር’ ፕሮጀክቶች በተጨማሪ ስምንት የ ‘ገበታ ለትውልድ’ ፕሮጀክቶችን አስጀምራለች።
ፕሮጀክቶቹ የኢትዮጵያን ቱሪዝም እንቅስቃሴ በእጅጉ በማነቃቃት ዜጎችን ከዘርፉ ይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መግለጻቸው የሚታወስ ነው።
በመንግሥት ደረጃ ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው ከነዚህ የቱሪዝም ልማት ፕሮጀክቶች መካከል ደግሞ በአርባ ምንጭ አካባቢ የሚገነባው ሰፊ የቱሪዝም ማዕከል ይገኝበታል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጀክቱን በጎበኙበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በአርባ ምንጭ የተፈጥሮ ስጦታው ታላቅ ተስፋን የመጫሩን ያህል የአካባቢውን ምሉዕ አቅም ለመጠቀም የሠራነው ጥቂት በመሆኑ ደግሞ ያስቆጫል ሲሉ አመላክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህ ቁጭት የወለደው የ ‘ገበታ ለትውልድ’ ፕሮጀክት ከአርባ ምንጭ አየር ማረፊያ በተሽከርካሪ ጉዞ የአምስት ደቂቃ ርቀት ላይ እንደሚገኝና በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲሳተፉበት ጥሪ አቅርበዋል።
በዚህ “የምድር ገነት” ድርሻ በመግዛት ኢንቨስት ለማድረግ እድል ቀርቧል በማለት ነበር መልዕክት ያስተላለፉት።
በአካባቢው የተጀመረው ሁሉን አቀፍ ኢንቨስትመንት ለአካባቢው ብሎም ለሀገር ቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት ምን ፋይዳ ይኖረዋል፤ ምንስ ተጨማሪ ጥረት ይጠይቃል፤ በሚሉ ጉዳዮች ላይ ምሁራን.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131707