Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ለአገር ግንባታ ላበረከተው አስተዋጾ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እጅ እውቅና ተቀብሏል።
#የምትተክል_ሀገር_የሚያፀና_ትውልድ‼️

የ#አረንጓዴዓሻራ የችግኝ ተከላ ወቅት ሥራችን ያስቀመጥነውን ግብ በሚያሳካ መልካም አጀማመር ላይ ይገኛል። የኅብረተሰባችንም የችግኝ ተከላ ተነሳሽነት ከፍተኛ ነው። ዛሬ በጫካ ፕሮጀክት ስፍራ የአፕል ችግኞችን ተክለናል። በአካባቢው የተደረገውን የዘንድሮውን ችግኝ ተከላ ለየት የሚያደርገው ቀድሞ የነበረው የባህርዛፍ ሽፋን ተወግዶ በሀገር በቀል የእርከን ሥራ እና ተክል የተተካ መሆኑ ነው። ከሀረር አካባቢ እና ከኮንሶ የመጡ ህዝቦቻችን አፈር እንዳይሸረሸር የሚያደርገውን ጊዜ የማይሽረውን ክህሎታቸውን አካፍለውናል። በከተሞች የምንሠራውን የአረንጓዴ አሻራ ጥረቶቻችንን በጋራ በማስፋፋት የአዲስ አበባን አረንጓዴ ሽፋን መጨመር እንችላለን።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
የግብር አሰባሰባችን የቤት ሥራዎች
************
(ኢ ፕ ድ)

መንግሥት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ አድገት ለማፋጠን ከፍተኛ ሃላፊነት አለበት:: ይሄን ኃላፊነት ለመወጣት የራሱ ገቢ ያስፈልገዋል:: ይሄንኑ ሥራ የሚያከናውንበትን ገቢ ከሚያሰባስበብበት የገቢ ምንጭ መካከል ግብር አንዱና ዋነኛው መሆኑ ይታወቃል::

ለዚህም ነው ግብር ወይም ታክስ ዋናው የመንግሥት የፋይናንስ ምንጭ በመሆን የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ ልማትን እና እድገት የጀርባ አጥንት ነው ሲሉ የዘርፉ ባለሙያዎች የሚገልጹት::

በሌላ በኩል ሰሞኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት በሀገራችን ግብር የሚከፍለው ማህበረሰብ ቁጥር ከ 64 ሺህ ያልዘለለ ነው:: በሌላም በኩል የግብር ሥወራም አንዱ የዘርፉ ፈተና ነው::

በዚህና በሌሎች ምክንያቶችም በሀገራችን ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት አንጻር የሚሰበሰበው ገቢ ከሰባት ከመቶ ያልዘዘ ሲሆን ይህ ደግሞ በአፍሪካ ቀንድም ጭምር ዝቅተኛ እንዲሆን.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131799
👍1
ቡና ላኪዎች የግዢ ክፍያዎችን ማዘግየታቸው ከአምራቾች ጋር እያጋጫቸው መሆኑን አቅራቢዎች ተናገሩ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

ቡና ላኪዎች ለሚገዙት ቡና ክፍያ በወቅቱ ባለመፈፀማቸው ምክንያት ከአምራቾች ጋር እየተጋጩ መሆኑን ቡና አቅራቢዎች አስታወቁ፡፡

የቡና የግብይት ሰንሰለትን በማሳጠር ችግሩ ሙሉ ለሙሉ ተፈቷል ሲል የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን በሰጠው ምላሽ አሳውቋል፡፡

ቡና አቅራቢ የሆኑት አቶ አበራ ማንደፍሮ፤ ቡና ከአምራቾች በኩፖን ተረክበው ለላኪዎች እንደሚያቀርቡ ለኢፕድ ገልጸዋል፡፡

ላኪዎች ላቀረብንላቸው የቡና ምርት ክፍያ ሲፈፅሙ ለአርሶ አደሮች በተስማሙበት ዋጋ መሠረት ክፍያ እንደሚፈፅሙ የተናገሩት አቶ አበራ፤ ነገር ግን ቡና ላኪዎች ክፍያ በሰዓቱ እንደማይከፍሏቸው አብራርተዋል፡፡

ይህም ለአምራቶች በተነጋገርነው መሠረት በሰዓቱ መክፈል እንዳይችሉ እንዳረጋቸው እና ወደ አላስፈላጊ ግጭት እንደሚያስገባቸው ነው የገለጹት፡፡

ላኪዎች ለሚቀርብላቸው የቡና ምርት በጊዜ እንደሚከፍሉ ውል ገብተው ቢወስዱም ውላቸውን በተያዘው የጊዜ ገደብ መፈፀም ሳይችሉ ይቀራሉ ያሉት አቶ አበራ፤ በዚህም ለተለያዩ ችግሮች እየተጋለጥን......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131814
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት ‼️

ሀገርን መስሪያ፣ ትውልድን መቅረጫ፣ ባህልና ወግን ማስተዋወቂያ ቀመሩ ሚዲያ ነው፡፡

“ሚዲያ ለሀገር” በሚል መሪ ሐሳብ በተዘጋጀው መርኃ ግብር ላይ ዕውቅና የተቸራችሁ መገናኛ ብዙሃን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡

በሀገር ግንባታ፣ በትውልድ ቅብብሎሽ፣ ታሪክን በመሰነድና መረጃን በማቀበሉ ረገድ የሚዲያ ድርሻ ትልቅ ነው፡፡

በመሆኑም ሚዲያዎች ለብሔራዊ ጥቅም፣ ለሀገር አንድነትና ማህበረሰባዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ስራዎች ላይ የበለጠ ትኩረት እንድትሰጡ አደራ እላለሁ፡፡
ሐምሌ 4 ቀን 2016 ዓም
“ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና”
#ጽዱኢትዮጵያ #CleanEthiopia
#ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ ጥሪ ስናቀርብ ዜጎቻችን በከፍተኛ ተነሳሽነት በሥራው ተሳትፈዋል። ዋናው አላማችን አካባቢያችንን ሳቢ በማድረግ መፀዳጃ ቤት የመጠቀም ባህላችንን ከመሠረቱ ማዳበር ነበር።

ዛሬ በዜጎቻችን በዋጋ የማይተመን የልብ መዋጮና እምነት የተገነቡትን ሥራዎች በቦታው በመገኘት ገምግመናል።

ከፍተኛ ጥራት ባላቸው ጠንካራና ዘመን ተሻጋሪ በሆኑ ቁሶች በመጠቀም ደረጃቸውን የጠበቁ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች ለመገንባት ቁርጠኝነት ይዘናል።

ይህ የሥራው መጀመሪያ ነው። በእናንተ ያላሰለሰ ድጋፍ የጀመርናቸውን ሥራዎች እናስፋፋለን።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)