Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#ሆራ ሀርሰዲ ኢሬቻ በዓል የኢሬፈና ስነስርዓትን በፎቶ‼️
🔥2
"የፍራፍሬ ስራችን ፍሬያማነቱ መገለጫ፤ የዛሬ ሶስት ዓመት በፊት የተከልናቸው"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍3
የኮሪደር ልማቱ ከመሰረተ ልማትና ውበትም ባለፈ የእኩልነት መገለጫ ነው- አቶ ኦርዲን በድሪ
*****
(ኢ ፕ ድ)

የኮሪደር ልማቱ ከመሰረተ ልማትና ውበትም ባለፈ የእኩልነት መገለጫ መሆኑን የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት በአሁኑ ጊዜ በስፋት እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት መኪናዎች በመኪና መንገድ፣ ሳይክሎች በሳይክል መንገድ እንዲሁም እግረኞች በእግረኛ መንገድ እንዲጓዙ የሚያስችል ነው።

ይህም የተሻለ ገቢ ያላቸው የማህበረሰቡ አካላት በመኪናዎቻቸው በመኪና መንገድ እንዲሄዱ የሚያስችል እንደመሆኑ መጠን ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውም በምቹ የእግረኛ መንገድ እንዲራመዱ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም ተፈጥሮ የለገሰችንን የመሬት ሀብት በእኩልነት ለመጠቀም እድል የሚሰጥ መሆኑን ጠቅሰው ለጤናም ለጉብኝት ተመራጭ ምቹ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል።

በተለይም የትራፊክ አደጋንም በመቀነስ ረገድ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ጠቀለመው የእግረኛ መንገዶችን ማስፋፋት፣ መጠበቅና በአግባቡ መጠቀም የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን አመላክተዋል ሲል የክልሉ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

መስከረም26 ቀን 2017 ዓም
1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
"የሆራ ፊንፊኔና የሆራ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓላት በስኬት መጠናቀቃቸው የኦሮሞን ህዝብ ታላቅነት የሚያረጋግጥ ነው"-

- ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ
****
(ኢ ፕ ድ)

የሆራ ፊንፊኔ እና የሆራ ሃርሰዴ የኢሬቻ ክብረ በአላት ያለአንዳች እንከን ዕሴቱን በጠበቀ አኳኋን በስኬት መጠናቀቃቸው የኦሮሞን ህዝብ ታላቅነት ያረጋገጡ ናቸው"ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለፁ፡፡

የአዲስ አበባና የቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪዎች የበአሉን ታዳሚዎች በፍቅር በመቀበል ስላኮራችሁን አመሰግናለሁ ብለዋል።

የኦሮሞ ህዝብ ሰላም ወዳድ፣ ለአንድነትና ለወንድማማችነት ክብር ያለዉ፣ በተግባርም ባህላዊ እሴቶቹን የተላበሰ መሆኑን ዳግም በማረጋገጡ በራሴና በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስም ምስጋናዬን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ ብለዋል።
👍10💩4😁2