Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ባደረጉት ንግግር ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ‼️

👉 ኢኮኖሚያችን አዲስ የታሪክ እጥፋት ላይ ነው

👉 በግብርና መስክ ባለፈው አመት 6 ነጥብ 9 በመቶ እድገት ተመዝግቧል

👉በ2016 በጀት አመት 230 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ተመርቷል

👉 በ2016 በጀት አመት 26 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ታርሷል፤

👉 በሌማት ቱሩፋት በሁሉም ክልሎች ከፍተኛ ምርት ተገኝቷል፤

👉በአረንጓዴ ዐሻራ ባለፉት ስድስት አመታት 40 ቢሊዮን ችግኝ ተተክሏል፤

👉 በኢንዱስትሪው መስክ 9 ነጥብ 2 በመቶ እድገት ተመዝግቧል፤

👉 የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ምርታማነት እድገት 59 በመቶ ደርሷል፤

👉 395 ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ ተመልስዋል፤

👉በአገልግሎት መስክ 7 ነጥብ 9 በመቶ እድገት ተመዝግቧል፤

👉 737 የመንግስት አገልግሎቶች በኤሌክትሮኒክስ እየተሰጡ ነው፤

👉 የሁሉም ባንኮች ሀብት 2 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር ደርሷል፤

👉የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች 39 ነጥብ 6 ሚሊዮን ደርሷል፤

👉 በዲጂታል የተላለፈ የብር መጠን 9 ነጥብ 6 ትሪሊዮን ብር ደርሷል፤

👉የመንገድ ሽፋን 169 ሺ 600 ደርሷል፤

👉 የሞባይል ስልክ ተጠቃሚ ቁጥር 83 ነጥብ 3 ሚሊዮን ደርሷል፤

👉የንጹህ ውሃ ተጠቃሚዎች ቁጥር 74 ነጥብ 8 ሚሊዮን ደርሷል፤

👉 የአባይ ግድብ አጠቃላይ ግንባታ 96 ነጥብ 7 በመቶ በላይ ተጠናቋል
👍19🕊6😁2🤔1
"በ2017 በጀት አመት 8 ነጥብ 4 በመቶ እድገት ለማስመዝገብ ጥረት ይደረጋል"
- አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት
🔥11👍2
በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን አስመልክቶ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ‼️
👍2😁1
የአፍሪካ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፈረንስ ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
**************
(ኢ ፕ ድ)
የአፍሪካ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፈረንስ ዛሬ በአዲስ አበባ በዓድዋ ድል መታሰቢያ “አፍሪካን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማላቅ” በሚል ይካሄዳል፡፡

በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት የሚካሄደዉ 3ኛው ዙር ፓን አፍሪኮን ኤ.አይ 2024 ኮንፈረንስ ለሁለት ቀናት መስከረም 28 እና 29፣ 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ ኢንሰቲትዩት አሰታውቋል።

መስከረም 28 ቀን 2017 ዓም
👍2
በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ውስጥ የኢትዮጵያን ተሳትፎ ለማሳደግ የንግድ ማህበራት በትኩረት ሊሠሩ ይገባል
******************
(ኢ ፕ ድ)
በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ውስጥ የኢትዮጵያን ተሳትፎ ለማሳደግ የንግድ ማህበራት በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለጸ።

የዓለም አቀፍ ንግድ ፖሊሲ ባለሙያ አቶ ጃሌቶ ገመዲ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ በቅርቡ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ዙሪያ ሊኖሩ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ውጤታማ ትግበራ እንዲኖር ለማስቻል እንዲሁም የግሉ ሴክተር እና ላኪዎችን ተደራሽነት ለማሳደግ ያለመ ጥናት መካሄዱን ጠቁመው፤ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ዙሪያ የንግዱ ማህበረሰብ ግንዛቤ አናሳ መሆኑን አንስተዋል።

በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ውስጥ የኢትዮጵያን ተሳትፎ ለማሳደግም የንግድ ማህበራት በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባም ገልጸዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የተቀመጡ አሠራሮችና ሕጎች፣ ውስብስብ የፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓቶችና የቁጥጥር ማነቆዎች ተግዳሮት እየፈጠሩ መሆኑን የጠቀሱት ባለሙያው፤ ወጥነት የጎደለው የአፈፃፀምና የአሰራር ቅልጥፍናም ተጽዕኖ እየፈጠረ ይገኛል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ላይ ያላትን ግንዛቤ የተመለከተውን ጥናት መነሻ አድርገው እንደገለጹት፤ በተለይም ከአፈፃፀሙ ጋር በተያያዙ የተለያዩ ተግዳሮቶች መኖራቸውን....

https://press.et/?p=138142
1👍1👎1
የማህበረሰቡ ልሳናት
************
(ኢ ፕ ድ)
ሀገራዊ እሴቶችን በማህበረሰቡ ቋንቋ ለየአካባቢው ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ የማህበረሰብ መገናኛ ብዙኃን የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑ እሙን ነው።

በሌሎች መገናኛ ብዙኃን የማይሸፈኑ አካባቢያዊ መረጃዎችን ለማህበረሰቡ በማድረስ የማህበረሰቡ ወግ፣ ባህልና ቋንቋ እንዲዳብር ከመስራት በተጨማሪ የማህበረሰቡ ትስስር እንዲጠናከርና ሰላም እንዲሰፍን በየአካባቢው ቋንቋ በማህበረሰቡ ዘንድ ግንዛቤ ሊፈጥሩ እንደሚገባ ይገለጻል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ተኮር ሬዲዮ ጣቢያ ጊዜያዊ ተጠሪ አቶ ኤፍሬም አክሊሉ እንደሚገልጹት፤ የሬዲዮ ጣቢያው በድሬዳዋ ከተማና አካባቢው ለሚኖሩ ዜጎች መረጃን ተደራሽ ለማድረግ በ2014 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን፤ ለአንድ ዓመት የሙከራ ስርጭት ካከናወነ በኋላ ወደ መደበኛ ስርጭት መግባት ችሏል።

በአካባቢው የተለያዩ የሬዲዮ ጣቢያዎች ቢኖሩም ከእነኝህ ጣቢያዎች በተለየ መልኩ ታችኛውን የማህበረሰብ ክፍል አጠቃላይ እንቅስቃሴ የሚዳሰሱባቸውን መሰናዶዎች......
https://press.et/?p=138139
👍2
በሊባኖስ የተፈጠረውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በችግር ላይ የነበሩ 51 ዜጎች ወደሀገራቸው ገቡ
****************
(ኢ ፕ ድ)
በሊባኖስ የተፈጠረውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በችግር ላይ የነበሩ 51 ዜጎች በሁለት በረራዎች ዛሬ ማለዳ ወደሀገራቸው ገብተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው እና የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) ለዜጎቹ አቀባበል አድርገዋል።

አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው እንደገለፁት፤ በሊባኖስ በተከሰተው ወቅታዊ ሁኔታ ለአደጋ ተጋላጭ ዜጎችን ወደሀገራቸው ለመመለስ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

በዚህም ዜጎቹን ለመመለስ እየተደረገ ባለው ጥረት የሚያስተባብር አመራር ወደ ሊባኖስ ተልኮ ሥራውን ጀምሯል።

በአካል እና በዲጂታል የምዝገባ ስርዓት ተዘርግቶ ዜጎች እየተመዘገቡ ይገኛሉ ያሉት አምባሳደር ነቢያት፤ ዜጎች ሊባኖስ በሚገኘው ቆንስላ ጽህፈት ቤት አማካኝነት በፈለጉት አማራጭ ተመዝግበው ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጀመሪያው ዙር 51 ዜጎች በዛሬው ዕለት ወደሀገራቸው መመለስ መቻሉን አምባሳደሩ ጠቁመዋል።

አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ መንግስት እያከናወነ በሚገኘው የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ተግባር በዬትኛውም ሁኔታ በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ በአትኩሮት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ይህ ተግባር መንግስት በሀገር ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ጉዳይ የሚያሳስበውን ያህል በተለያዩ ሁኔታዎች ከሀገራቸው የወጡ ዜጎችም ሁኔታ እንደሚያሳስበው ማሳያ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይም መንግሥት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለዜጎቹ የክትትል እና ድጋፍ ስራ እንደሚያከናውን ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።

በቃልኪዳን አሳዬ
መስከረም 28 ቀን 2017
👍6👏2
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
👍1
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የ10 ኪሜ ሩጫ የውድድር ደረጃዎች ውስጥ ተካተተ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የዓለም አትሌቲክስ አስተዳዳሪ ዎርልድ አትሌቲክስ የ2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪሜ ሩጫን የሌብል ደረጃ ያለው የጎዳና ላይ ውድድር ሲል ዕውቅና ሰጥቶታል።

የአለም አትሌቲክስ የሌብል ደረጃ ሲል የሰየማቸው ውድድሮች በጥራት ዝግጅቶችን ከማድረግ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ ከመሆን እና የተሳታፊዎች ውድድሩ ላይ የነበራቸው ቆይታ፣ የከተማ አስተዳደሮች ለዝግጅቱ ያላቸውን ድጋፍ፣ ዝግጅቱ በአትሌቲክስ ውድድር ዘርፍ አበረታች መድኃኒት ላይ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑ ተጠቅሷል።

እጅግ በርካታ የሩጫ ውድድሮች ባሉበት ዓለም ይህንን የሌብል ደረጃ ማግኘት ዝግጅቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ያሳየውን ዕድገት እና በዓለማችን ካሉ ቀዳሚ እና ተመራጭ የጎዳና ላይ ውድድሮች መሀከል መሆኑንም እንደሚያሳይ ተጠቁሟል።

የአለም አትሌቲክስ አስተዳዳሪው አካል (World Athletics) ውድድሮችን በመመዘን በየአመቱ ደረጃዎችን የሚሰጥ ሲሆን፤ የመሮጫ ኮርስ ልኬት፣ የውድድር ሰዓት ምዝገባ እና የኤሊት አትሌቶች ተሳትፎ ከግምት ውስጥ የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው።

24ኛው ዙር ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪሜ ህዳር 8 ቀን 2017 በ50ሺ ተሳታፊዎች እንደሚካሄድ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

መስከረም 28 ቀን 2017 ዓም
🙏31
የምግብ ዘይትን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ተግባር ውጤት አስገኝቷል
************************
(ኢ ፕ ድ)
የምግብ ዘይትን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ተግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ በመሻሻሉ ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የምግብና መጠጥ ምርምርና ልማት ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ በቀለ መኩሪያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤የምግብ ዘይትን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ተግባር ውጤት እያስገኘ ነው።

የምግብ ዘይት ፍጆታን በሀገር ውስጥ ምርቶች ለመተካት ወደ ሥራ ከገቡት በተጨማሪ በሰፊው የማምረት አቅም ያላቸው አዳዲስ የዘይት ፋብሪካዎች እየተቋቋሙ ነው ያሉት አቶ በቀለ፤ በጥሬ እቃ አቅርቦት፣ ፋብሪካዎቹን በማስፋፋትና በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ የድጋፍ ክትትል እንዲሁም የተለያዩ የአቅም ግንባታ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

እንደ አቶ በቀለ ገለጻ፤ ከሦስትና አራት ዓመት በፊት ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነው የምግብ ዘይት ፍጆታ ከውጭ የሚገባ ነበር። አሁን ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው የምግብ ዘይት መጠን 81 በመቶ ዝቅ.....

https://press.et/?p=138174
👍2👏1😁1
ችግሮችን ለመፍታትና ሕይወትን ለማቅለል ወሳኝ የሆነውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አቅምና አጠቃቀም ማሳደግ ይገባል
******************
(ኢ ፕ ድ)
ችግሮችን ለመፍታትና ሕይወትን ለማቅለል ወሳኝ የሆነውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አቅምና አጠቃቀም ማሳደግ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

3ኛው ፓን አፍሪኮን ኤአይ 2024 "አፍሪካን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማላቅ" በሚል ሀሳብ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።

በመድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እንደገለጹት፤ ኤአይ የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት፣ የማህበረሰቡን ኑሮ ለማቃለል፣ ለኢኮኖሚያዊ እድገት፣ ለስራ እድል ፈጠራ፣ ለግብርና፣ ለጤና እና ለሌሎች ዘርፎች የሚያበረክተው ሚና ከፍተኛ ነው።

ችግሮችን ለመፍታትና ሕይወትን ለማቅለል ወሳኝ የሆነውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አቅምና አጠቃቀም ለማሳደግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የመረጃ አያያዝ ቴክኖሎጂን ማሳደግ፣ ብቁ የሰው ኃይል ማፍራት፣ የማሽን ቋንቋ ያልሆኑ ሀገረኛ ቋንቋዎችን ማሽን እንዲያውቃቸው የማድረግ እንዲሁም የግብርናውን ዘርፍ ችግሮች ከመፍታት አንጻር በርካታ ስራዎችን ማከናወኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲቲዩት ያዘጋጀው 3ተኛው ዙር ፓን አፍሪኮን ኤ.አይ 2024 ኮንፈረንስ መካሄድ የጀመረ ሲሆን፤ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ይቆያል ተብሏል።

በኮንፈረንሱ የኢፌደሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴድሮስ ምህረት፣ የድሬዳዋ ከንቲባ ከድር ጀዋርን ጨምሮ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በሄለን ወንድምነው
መስከረም 28 ቀን 2017 ዓም
👍61🤝1