Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአደባባይ በዓላት በድምቀት ተከብረው እንዲጠናቀቁ አስተዋጽዖ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል
********************
(ኢ ፕ ድ)
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ የአደባባይ በዓላት በድምቀት ተከብረው እንዲጠናቀቁ አስተዋጽዖ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።

ከንቲባ አዳነች በተለይም ከአዲስ ዓመት ዋዜማ ጀምሮ በአዲስ አበባ የተከበሩት በዓላት ፍጹም ሰላማዊ፣ የተረጋጋ፣ ደማቅ፣ ህዝቡን ባከበረ እና ላቅ ባለ ዲስፒሊን በተሞላበት መንገድ ኃላፊነታቸውን የተወጡ የጸጥታ አካላትን፣ በየደረጃው የሚገኙ የከተማ አስተዳደሩን አመራሮችን እንዲሁም መላው የከተማውን ህብረተሰብ አመስግነዋል::

የአደባባይ በዓላት ለከተማዋ ተጨማሪ ውበት እና የቱሪስት መስህብ ናቸው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ነዋሪውን የሰላሙ ባለቤት በማድረግ ከተማችን አዲስ አበባን ሰላማዊ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የጀመርነውን ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል::

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው የአደባባይ በዓላቱ በድምቀት ተከብረው ለመጠናቀቃቸው የከተማ አስተዳደሩ ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ለሰራው ስራና ለተገኘው ውጤት አመስግነው ይበልጥ ውጤታማ ስለሚያደርገን በጋራ መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ማለታቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

መስከረም29 ቀን 2017 ዓም
👍42
ለአሻም ሚዲያ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ
****
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ለአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን አሰታወቀ።
👍2👎2
ለአንድ ወር የሚቆይ የፋይዳ መታወቂያ የምዝገባ ዘመቻ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ይጀመራል

👉 በአንድ ወር ዘመቻው ከአንድ ሚሊየን በላይ ነዋሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዷል
*******
(ኢ ፕ ድ)

የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽህፈ ቤትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባን በጋራ እንደሚያካሂዱ አሰታወቁ።

ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ ዘሚካኤል ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፣ በአዲስ አበባ የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገ ዘመቻ  ይጀመራል።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በአዲስ አበባ ከተማ ባጠረ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ጠቅሰው፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባው ምንም አይነት ክፍያ የለውም ብለዋል።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በኢትዮጵያ የዲጂታል ስትራቴጂ 2025 እቅድ አካል መሆኑን በመግለጽ ፋይዳ የሀገሪቱን የሰው ሀብት ለማወቅ ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችል ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በበኩላቸው፣ የፋይዳ ምዝገባ በሁሉም ወረዳዎችና ዋና መስሪያ ቤት እንዲሁም ሁለት ቅርንጫፎች ላይ ይካሄዳል።

ለምዝገባ ሥራ የጋራ ግብረሀይል መቋቋሙን ጠቅሰው የትስስር ስርዓቱ በከተማ ደረጃ የተጀመረውን የዲጂታል አገልግሎት ለማስቀጠል እንደሚያስችል ገልጸዋል።

ዘመቻው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም በመተባበር የሚካሄድ ነው ተብሏል።

በማርቆስ በላይ

መስከረም 29 ቀን 2017 ዓም
👍71
በዲጂታል ዓለም ወረቀት ለምን ተወደደ?
************
(ኢ ፕ ድ)
የንባብ ባህልን ለማዳበር እንደ አብርሆት ቤተ መጽሐፍ አይነት ግዙፍና ማራኪ ቤተ መጽሐፍ ተገንብቷል። ቤተ መጽሐፉ ግን በቀደመው ዘመን የተጻፉ ብቻ የሚነበቡበት መሆን የለበትም።

አዳዲስ መጻሕፍት፣ ጋዜጦችና መጽሔቶችም የሚገኙበት መሆን አለበት። የቀድሞዎችን ብቻ ለማንበብ ከሆነ ቤተ መጽሐፍ ሳይሆን ቤተ መዘክር ሆነ ማለት ነው። የኢንተርኔት መጠቀሚያ ብቻ መሆን የለበትም።

እንደዚያ ያማረ፣ የሚመስጥ እና ፀጥ ያለ ግርማ ሞገስ ያለው ቤተ መጽሐፍ የኢንተርኔት መጠቀሚያ ብቻ ሊሆን አይገባም። ኢንተርኔት የትም ሆኖ መጠቀም ይቻላል።

አዳዲስ መጽሐፎች በብዛት ይታተሙ ዘንድ፣ ጋዜጦችና መጽሔቶች አማራጭ የሚዲያ አይነቶች ይሆኑ ዘንድ፣ በአጠቃላይ የንባብ አብዮት ይፈጠር ዘንድ መንግሥት በወረቀትና የማተሚያ ግብዓቶች ላይ ያለውን ቀረጥ መላ ሊለው ይገባል።

የንባብ ባህል ባልዳበረበት ማህበረሰብ ውስጥ ወረቀትና የማተሚያ ግብዓት እንደ ቅንጦት መታየት የለበትም፤ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=137968
👍2😢1
በመስከረም ወር ለውጭ ገበያ ከቀረበ ቡና ከ90 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ
*****
(ኢ ፕ ድ )

በመስከረም ወር 22 ሺ ቶን ቡና ወደ ውጭ ገበያ በመላክ 90 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ በሐምሌና ነሐሴ ወራት 83ሺህ ቶን ቡና በመላክ 380 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኝቷል።

በቀጣይ አሁን በተመዘገበው ውጤት ልክ ማስመዝገብ ከተቻለ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ማሳካት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት 326 ሺህ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ በማቅረብ አንድ ነጥብ 8 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዷልም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ቡናን ለአምስት ትላልቅ አገራት በስፋት ታቀርባለች። በሁለት ወራት ውስጥ ያለው የገበያ መረጃ የሚያሳየው ጀርመን 20 በመቶ ያህሉን የኢትዮጵያ ቡና በመግዛት ቀዳሚ አገር እንደሆነች ገልጸዋል፡፡

ከጀርመን በመከተል ጃፓን፣ ደቡብ ኮርያ፣ ቻይናና ቤልጅየም የኢትጵያን ቡና በመግዛት ቀዳሚ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ለዓለም ገበያ ከቀረበ ቡና ከአንድ ነጥብ 4 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ይታወሳል፡፡

https://press.et/?p=138235
👍5🕊4👏1
ጀነራል አበባው ታደሰ በደብረብርሃን የፊቤላ ኢንዱስትሪያል የመኪና መገጣጠሚያን ጎበኙ
*******
(ኢ ፕ ድ)

የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ በደብረብርሃን የፊቤላ ኢንዱስትሪያል የመኪና መገጣጠሚያን ጎበኝተዋል።

በጉብኝቱም ላይ የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ሹማ አብደታ፣ የአማራ ክልል የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊን ጨምሮ የክልሉ የዞንና የሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የፊቤላ እንዱስትሪያል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የመኪና መገጣጠሚያ ተመርቆ ስራ ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የፕሮዳክሽንና ቴክኒክ ክፍል ሃላፊ አቶ ሳሙኤል ቀለመወርቅ ተናግረዋል።

የተሸከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካው በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሸከርካሪዎችን እያመረተ የሚገኝና በሀገሪቱ ኢኮኖሚ የራሱን አሻራ ለማሳረፍ የተቋቋመ መሆኑን መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

መስከረም 29 ቀን 2017 ዓም
👍113👏2
የጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ያሰለጠናቸውን ምልምል ወታደሮች ነገ ያስመርቃል
****
(ኢ ፕ ድ)

የጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመሠረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን ምልምል ወታደሮች በነገው ዕለት እንደሚያስመርቅ አስታውቋል።

የጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ዋና አዛዥ ብርጋዴል ጄነራል ጡምሲዶ ፊታሞ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ለዘጠነኛ ዙር የመሠረታዊ ውትድርና ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ሰልጣኞች በነገው ዕለት ይመረቃሉ።

ማሰልጠኛው ሁለገብ የሆነ ስልጠና በመስጠት ለሀገር ሉዓላዊነት የሚተጉ የሰራዊት አባላትን እያፈራ ይገኛል።

ሰልጣኞቹ በመሰረታዊ ውትድርና ማግኘት ያለባቸውን ስልጠናዎችን በተገቢው መንገድ መከታተላቸውን ተናግረዋል።

በማሰልጠኛው የሰራዊት ስነልቦና ግንባታ ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ተከስተ አስገዶም በበኩላቸው የዘጠነኛው ዙር ሰልጣኞች ምረቃ ዝግጅት ተጠናቋል። ከደርግ ዘመነ መንግስት ጀምሮ በብሔራዊ ውትድርና እንዲሁም ከመንግስት ለውጥ በኋላም የተሃድሶና የተለያዩ ስልጠናዎች እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በልጅዓለም ፍቅሬ(ጦላይ)

መስከረም 29 ቀን 2017 ዓም
👍9👏63😁1
የኢትዮጵያን ቡና በብዛት የሚገዙ ሀገራት‼️
🔥4
ኢትዮጵያ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሆና ተመረጠች
*****
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሆና ተመርጣለች።

ኢትዮጵያ 171 አገራት የድጋፍ ድምጽ በማግኘት የተመረጠች ሲሆን ከ2025 አንስቶ እስከ 2027 ለሶስት ዓመት የምክር ቤት አባል ሆና እንደምታገለግል ተገልጿል።

ኢትዮጵያ የሲቪል፣ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ መብቶች በዓለም ላይ እንዲከበሩና ለታዳጊ አገራት የሚሰጡ የአቅም ግንባታና የቴክኒክ ድጋፎችን ለማሳደግ በትኩረት እንደምትሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ከአፍሪካ ቤኒን፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ጋምቢያ እና ኬንያ፤ ቦሊቪያ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ አይስላንድ፣ ሜክሲኮ፣ ኳታር፣ ሰሜን ሜቄዶኒያ፣ ስዊዘርላንድ፣ ኮሪያ ሪፐብሊክ፣ ታይላንድ፣ ስፔን፣ ኮሎምቢያ፣ ቆጵሮስና ማርሻል አይላንድስ ሌሎች የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሆነው የተመረጡ አገራት ናቸው።

ኢትዮጵያ ከእ.አ.አ 2013 እስከ 2015 እንዲሁም ከእ.አ.አ 2016 እስከ 2018 የምክር ቤቱ አባል ሆና አገልግላለች።
👍105
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሂዳል
*****
(ኢ ፕ ድ)

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን አንደኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሂዳል።

በስብሰባው የምክር ቤቱን 3ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ተገልጿል።

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የኤሌክትሮኒክስ ፊርማ፣ የኢትዮጵያ የሕንፃ ረቂቅ አዋጅ፣ የመድኃኒት ፈንድና የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎትን ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራም ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር፤ እንዲሁም የሪል ስቴት ልማትና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መስከረም 30 ቀን 2017 ዓም
👍4👎1
ዜሮ ታሪፍ ፖሊሲ ኢትዮጵያ የንግድ እንቅስቃሴዋን እንድታሳድግ ያግዛታል
******
(ኢ ፕ ድ)

የቻይና ዜሮ ታሪፍ ፖሊሲ ኢትዮጵያ ወደ ውጪ የምትልከውን የምርት መጠን እንድታሳድግ እና አጠቃላይ የንግድ እንቅስቃሴን ለመቀየር ያግዛታል ሲሉ በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት ዳዊት ሀይሶ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

መምህር ዳዊት ሀይሶ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የዜሮ ታሪፍ ፖሊሲው ኢትዮጵያ ወደ ቻይና የምትልከውን የምርት መጠን አቅርቦት ለማሳደግና እንዲሁም ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት የላቀ ጠቀሜታ ይኖረዋል።

እንደ መምህር ዳዊት(ዶ/ር) ገለጻ፤ ኢትዮጵያ ወደ ቻይና የምትልካቸው ምርቶች ከቀረጥ ነጻ መሆናቸው የውጭ ምንዛሪ ገቢን ለማሳደግ እና ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል ለመፍጠር ይረዳል ብለዋል።

በተጨማሪም ኢንቨስተሮችን ለመሳብ እና በቻይና ገበያ ውስጥ እንዲገባ እንደሚያግዝ አውስተው፤ ከቀረጥ ነጻ ወደ ቻይና እንዲላኩ የተፈቀዱት ምርቶች በርካታ እንደመሆናቸው ይህን ዕድል በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ አውስተዋል።

ፖሊሲው በኢትዮጵያ ያሉ ላኪዎች ምርታቸውን.....https://press.et/?p=138268
👍5
የበለስ-መካነ ብርሃን አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ 75 ነጥብ 2 በመቶ ደረሰ
****
(ኢ ፕ ድ)

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅና ጃናሞራ ወረዳዎችን የሚያገናኘው የበለስ-መካነ ብርሃን አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ አፈጻጸም 75 ነጥብ 2 በመቶ ደርሷል።

አሁን ላይ የአስር አነስተኛና ከፍተኛ ድልድዩች ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቋል።

የመንገድ ፕሮጀክቱ 36 ነጥብ 42 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል። ለግንባታው አንድ ቢሊዮን 018 ሚሊዮን 952ሺህ 362 ብር በፌደራል መንግስት ተመድቧል።

የአካባቢው የቀድሞ ገጽታ ምንም ዓይነት የመንገድ መሠረተ ልማት ያልነበረው፣ በኅብረተሰቡ ጥያቄ መሠረት ቦታው ካለው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አንጻር፣ በመንግስት ተወስኖ አሁን ላይ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ በመገንባት ላይ ይገኛል።

የመንገዱ መገንባት የደባርቅና ጃናሞራ ሕዝብ በቅርበት ደረጃውን በጠበቀ መንገድ የሚያገናኝ ነው። በመንገዱ የበለስ፣ ወይና፣ ሚጊራና መሰል ከተሞች ዕድገት ያፋጥናል።

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መዳረሻ እንደመሆኑም የቱሪዝም ዘርፉን በማነቃቃት በኩል የጎላ ሚና እንደሚኖረው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታውቋል።

መስከረም 30 ቀን 2017 ዓም
👍1😁1