በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ200 ሚሊየን ብር የተገነቡ መሠረተ-ልማቶች ተመረቁ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚገኘው ሺንትስ ኢቲፒ ጋርመንት በ200 ሚሊየን ብር ወጪ ያስገነባው የተለያዩ መሠረተ-ልማቶች ተመርቀዋል።
መሠረተ-ልማቶቹ ለሠራተኞቹ አገልግሎት እንዲውሉ የተገነቡ ናቸው ተብሏል።
በምረቃው ላይ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሰሐ ይታገሱ (ዶ/ር)፣በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ጁንግ ካንግ፣ የኩባንያው ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ቻ ሚን ሆን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።
ህዳር 13 ቀን 2017 ዓም

👍8👏3
የአርሲ ወተት አምራች ማሕበር በቀን ዘጠኝ ሺህ ሊትር ወተት ለአዲስ አበባ እያቀረበ ነው
******************
(ኢ ፕ ድ)
በአርሲ ዞን የሌሙና ብልብሎና ወረዳ ወተት አምራች ማሕበር ለአዲስ አበባ በቀን ዘጠኝ ሺህ ወተት ለአዲስ አበባ እያቀረበ መሆኑን አስታወቀ።
በአርሲ ዞን የሌሙና ብልብሎ የወተት አምራች ማሕበር በመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት የሚዲያ ቡድን ተጎበኘ።
በጎብኝቱ ወቅት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ደኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ እንደ ተናገሩት፣ አርሲ ዞን የአትሌቶች ምንጭ ብቻ ሳትሆን የወተት ምንጭ ናት።
የአትሌቶቹ ጥንካሬ ምስጥር አንዱ ይሄ ነው። በመንግሥት የተጀመረው የተማና የገጠርን የሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቭ በተለይ በገጠር ተጨባጭ ማምጣት መቻሉ ይህ የወተት አምራች እንቅስቃሴ አመላካች ነው።
የማሕበሩ ሰብሳቢ አቶ ሙሉጌታ ቱፋ በበኩላቸው፣ አርሲ እምቅ የወተት ሀብት ቢኖረውም ቀደም ሲል በገበያ እጦት ምክንያት ተጠቃሚ አለመሆኑን አውስተው፤ አሁን ላይ ማሕበሩ በመቋቋሙ ከእርሶ አደሮች ጥራት ያለውን ወተት አንድ ሊትር 45 ዋጋ እየተረከበ ለአዲስ አበባ በቀጥታ እያቀረበ ነው ብለዋል።
ማሕበሩ ከተቋቋመው ገና ሶስት ወር ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ አስር ሚሊዮን ብር ካፒታልና 642 አባላት አሉት።
አርሶ አደር ደበሌ ቱራ የማሕበሩ አባል ሲሆን ከዚህ ቀደም ለግል ፍጆታ ከመጠቀም ውጭ ወተት ለገበያ እንደ ማያቀርቡ ገልጸው፤ አሁን ግን አንድ ሊትር ወተት በ45 ብር በድምሩ በቀን 72 ሊትር ወተት ለማሕበሩ እያቀረቡ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዋቅሹም ፍቃዱ

👍14❤2👎1
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
"ሁሉ አቀፍ የህብረተሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት" በሚል የተዘጋጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ካውንስል ጉባዔ አካሂደናል።
ሌተቀን የከተማቸውን ሰላም በመጠበቅ፣ የጎደሉ በየአካባቢው ያሉ መሰረተ ልማቶችን በህብረተሰቡ ተሳትፎ በመስራትና በልማት ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ፣ ማህበራዊ ጫናዎችን በመቀነስና በርካታ የበጎ ፈቃድ ስራዎች በገንዘባቸው፣ በጉልበታቸው፣ በእውቀታቸው ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ የከተማችንን ነዋሪዎችንና የብሎክ አደረጃጀቶችን እስከ አሁን ለሰሩት ስራ እውቅና ሰጥተን የ2017 እቅድ ላይ ተወያይተናል።
ቀና ልብ ያላቸው በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር የበርካቶችን የመኖር ተስፋ ያለመለሙ ስራዎችን ለሰራችሁና ላስተባበራችሁ ሁሉ በነዋሪዎቻችን ስም እያመሰገንኩ የከተማችንን ፈጣን ለውጥ ቀጣይነት ባለው መንገድ ለማስቀጠል ከህብረተሰባችን ጋር በትብብር መስራታችንን እንቀጥላለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ህዳር 13 ቀን 2017 ዓም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et

👍6❤3👎2
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️
የ’ጥራት መንደር’ን ዛሬ በይፋ ከመመረቃችን ቀደም ብሎ የገነባነውን ብሔራዊ የጥራት መሠረተ ልማታችንን ትናንት የመጎብኘት እድል ነበረኝ።
ይኽ ወሳኝ ተቋም የሀገር ውስጥ ምርቶቻችን በአለም ገበያ የሚኖራቸውን ተወዳዳሪነት በማላቅ በአለም የእሴት ሰንሰለት የሚኖራቸውን ተሳትፎ የሚያጎለብት ነው።
ከሀገራችን መሪ ተቋማት አንዱ በመሆን የውጭ ንግድ አቅሞቻችንን በማጠናከር በአለምአቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ ሆነን እንድንዘልቅ የሚያስችለንም ይሆናል።
ህዳር 14 ቀን 2017 ዓም

👍3👎1