#ለከተራና_ለጥምቀት በዓል
ከጥር 10 እስከ ጥር 12 ቀን 2017 ዓም ድረስ ጃንሜዳና አቃቂ ቃሊቲ ታቦት ማደሪያ በሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
👉 ከ6 ኪሎ አደባባይ - ምኒልክ ሆስፒታል
👉 ከምኒልክ ሆስፒታል - መከላከያ 3ኛ ሻለቃ አደባባይ
👉 ከ3ኛ ሻለቃ አደባባይ - 6 ኪሎ አደባባይ እንዲሁም አቃቂ ቃሊቲ አካባቢ
👉 ከዋልያ ቢራ - ጥሩነሽ ቤይጂንግ ሆስፒታል
👉 ከአቃቂ ዋናው መንገድ - ጥሩነሽ ቤይጂንግ ሆስፒታል
👉 ከ08 - አቃቂ ድልድይ ድረስ ከጥር 10 ቀን 2017 ዓም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ ዝግ ይሆናሉ።

👍1
"የሠላም አማራጮችን በመቀበል ለሚመጡ የመንግስት የሰላም በር ዛሬም ክፍት ነው" - ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር )
******
(ኢ ፕ ድ)
የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ፣ መንግስት ባለፉት አመታት ሠላም ለማስጠበቅ ያከናወናቸው ተግባራት አበረታች ውጤት ተመዝግቦባቸዋል።
በቤኒሻንጉል፣ ጋምቤላ እንዲሁም በአፋርና ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች የተገኙት ውጤቶች ማህበረሠቡ ወደ ሠላማዊ እንቅስቃሴው እንዲገባ አስችሏል።
በቅርቡም በኦሮሚያ ክልል በትጥቅ ትግል ውስጥ የነበሩ ወደሠላማዊ እንቅስቃሴ አየተመለሱ ናቸው።
በአማራ ክልልም በሺዎች የሚቆጠሩ የተደረገውን ጥሪ ተቀብለው ስልጠና ወስደው ወደ ሠላማዊ እንቅስቃሴ የገቡ ሲሆን። ሌሎችም በሺዎች የሚቆጠሩ በአሁኑ ወቅት በስልጠና ለይ ይገኛሉ። አብዛኛው የአማራ ክልል አካባቢዎችም ወደ ሠላማዊ እንቅስቃሴ ተመልሰዋል።
በመንግስት በኩል እነዚህ ተግባራት ተጠናክረው የሚቀጥሉ ሲሆን ዛሬም የሠላም አማራጮችን በመቀበል ለሚመጡ የመንግስት በር ዛሬም ክፍት ነው ብለዋል ።
በተጨማሪም በኢኮኖሚውም ዘርፍ የብር ምንዛሬ ተመን በገበያ እንዲወሠን መደረጉ ኢመደበኛና የኮንትሮባንድ ንግድና አጠቃለይ ህገወጥ እንቅስቃሴዎች ወደህጋዊ መስመር እንዲገቡ አስችሏል።
ብሔራዊ ባንክ በታሪኩ ለመጀመሪያ ግዜ ከፍተኛ ወርቅ ለመቀበልም ችሏል። የተፈጠረው ሠላምና እየተከናወኑ ያሉ የከተማ ልማት ስራዎችም የቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በነዳጅ አቅርቦት ረገድ የሚታዩ ተገቢ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎችን ለማስቆምም የተጀመሩ የቁጥጥር ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል ብለዋል።
በራስወርቅ ሙሉጌታ
ጥር 9 ቀን 2017 ዓም

👍3❤1
ሥራ ፈላጊ ነዎት❓
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢራን ሪፐብሊክ መንግስት ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ከሚመራው ልዑካን ቡድን ጋር በብሔራዊ ቤተ-መንግስት በፎቶ‼️
❤3👍3
#ጎንደር #ጥምቀት
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለጥምቀት ክብረ በዓል ጎንደር ገቡ
አዲስ አበባ ፤ ጥር 10/2017(ኢዜአ)፦ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እና የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የጥምቀት በዓልን ለማክበር ጎንደር ከተማ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እና የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ አፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ የክልሉና የጎንደር ከተማ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የጥምቀት በዓልን ለማክበር ጎንደር አፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኜው እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ጥር 10 ቀን 2017 ዓም

👍4❤1
በባቱ ደምበል ሐይቅ ላይ ለሚከበረው የጥምቀት በዓል 48 የሞተር ጀልባዎች ተዘጋጁ
*****
(ኢ ፕ ድ)
በባቱ ከተማ ደምበል ሐይቅ ላይ ለሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓልን በድምቀት ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የባቱ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።
የባቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመዲን ኡስማኢል የከተራና የጥምቀት በዓል አከባበርን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
ጥምቀት በድምቀት ከሚከበርባቸው ቦታዎች አንዱ ባቱ ነው ያሉት ከንቲባው፤ በዓሉን ለመታደም በርካታ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር እንግዶች ወደ ከተማዋ እየገቡ ነው።
ከተማ አስተዳደሩ ጸጥታን በማረጋገጥ፣ የበዓል ማክበሪያ ሥፍራዎችን የማጽዳትና የማዘጋጀት ሥራ ተከናውኗል።
አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገዋል ብለዋል።
ጥምቀትን በባቱ በደምበል ሐይቅ ላይ በጀልባ አማካኝነት የሚከበር በመሆኑ ለየት ያደርገዋል። ለዚህም 48 የሞተር ጀልባዎች በዓሉን ለማድመቅ መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።
በፋንታነሽ ክንዴ(ባቱ)

👍2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
**
(ኢ ፕ ድ)
ጥምቀት ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ኅብረ ብሔራዊ በዓላችን ነው። በሃይማኖታዊነቱ የኢየሱስ ክርስቶስን ከሰማያት ወርዶ፣ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ መጠመቅ እናስብበታለን። ይሄም የጠፋውን አዳም ለመፈለግ የተደረገ ጉዞ ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ አዳም በወደቀበት በእያንዳንዱ ዱካ ከቤተልሔም እስከ ቀራንዮ ተከትሎ ዋጅቶታል። በዚህም አዳምን ወደ ጥንት ክብሩ መመለስ ብቻ ሳይሆን ከጥንቱ የበለጠ ክብር ሰጥቶታል።
ይሄም ለዛሬዋ ኢትዮጵያ የሚያስተምረን ብዙ ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ ከቤተልሔም እስከ ቀራንዮ የወደቀችበት ብዙ ነው። በእያንዳንዱ በወደቀችበት ውድቀት ተከትለን ማንሣት አለብን። የትርክት፣ የሀገረ መንግሥት፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የመግባባት ውድቀቶቿን ወደ ትንሣኤዋ መቀየር አለብን።
ክርስቶስ አዳምን ሲያድነው እንዲህ ወይም እንዲያ ማድረግ አለብህ አላለውም። አዳም ዐቅም እንደሌለው ያውቃልና። መዳኑን እርሱ ራሱ ሊያደርገው እንደማይችል ያውቃል። ስለዚህ ክርስቶስ ተገኝቶ ፈጸመለት።
ኢትዮጵያችን በዘመናት መከራዎች ደክማለች። በዘመናት ድህነትና ኋላ ቀርነት ተጎድታ ዐቅም አጥታለች። እንዲህ ወይም እንዲያ ማድረግ ነበረባት የሚለው አሁን ለውጥ አያመጣም። መደረግ ያለበትን እኛ ልጆቿ ዛሬ እናድርገው።
ስለሀገራችን እኛ ቤዛ እንሁን። ቤተልሔም መወለድ ካለብን እንወለድ። በባሕር መካከል መቆም ካለብን እንቁም። መሰደብ ካለብን እንሰደብ፣ መሰቀል ካለብንም እንሰቀል። ነገር ግን ይህ ሁሉ የኢትዮጵያን ትንሣኤ የሚያመጣ ይሁን። ዛሬ እያደረግነው ያለነውም ይሄንኑ ነው።
ጥምቀት ባህላዊ በዓላችንም ነው። የኢትዮጵያ የመስክ ላይ ትዕይንት ማቅረቢያ በዓል ነው። መስኩና ወንዙ ይታይበታል፤ ልብሳችንና የወግ ዕቃዎቻችን ለዓለም እናሳያለን። የፀጉር አሠራራችንንና ዜማዎቻችንን እናቀርባለን። ጥምቀት የኢትዮጵያ ባህል የአደባባይ ሙዝየም ነው።
ብዙ ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ይሄንን ወቅት ከሚመርጡበት ምክንያቶች አንዱ ይሄ የአደባባይ ሙዝየም ነው። ከገጠር እስከ ከተማ ፤ ከዳር እስከ መሐል፤ ከውጭ እስከ ሀገር የጥምቀት በዓል የእኛነታችን መገለጫ ነው።
ጥምቀት ኅብረ ብሔራዊ በዓልም ነው። የኢትዮጵያን ብሔሮች፣ ቋንቋዎች፣ ባህሎች ለማየት የፈለገ ሰው አንዱ አማራጩ የጥምቀት አደባባይ ነው። በአንድ አደባባይ ሺህ ዓይነቱን ኀብረ ብሔራዊ ማንነታችንን ማየት ይቻላል።
የክት የተባለው የባህል ልብሳችን ይወጣል፤ ታይተው የማያውቁ ጌጣጌጦች ብቅ ይላሉ፤ በጥምቀት የኢትዮጵያን መልከ ብዙ ገጽታ ማየት ይቻላል።
እነዚህን የመሰሉ ዕሴቶቻችንን ስላስረከቡን ቀደምቶቻችንን እናመሰግናቸዋለን። ጥምቀት ከተማን ከገጠር ያገናኛል። ብዙዎች ወገኖቻቸውን ለማግኘት ገጠር ይወርዳሉ። የውጭውንም ከሀገር ቤት ያስተሣሥራል። ሚሊዮን ወገኖቻችን ጥምቀትን አብረውን ለማክበር ከውጭ ገብተዋል። ይሄም ኅብረ ብሔራዊ ትሥሥራችንን ይበልጥ የሚያጠናክር ነው።
የጥምቀትን አስተምህሮ ለሀገር ግንባታ በመጠቀም፤ ባህላዊ እሴቱን በማጎልበትና ኅብረ ብሔራዊነቱን በማጠናከር በዓሉን እንድናከብር አደራ እላለሁ።
በድጋሚ መልካም የጥምቀት በዓል ይሁን።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ጥር 10፣ 2017 ዓ.ም

👍12🤣1