Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#ጥምቀት በባቱ በወጣት ሁሴን ባቶ አንደበት

ወጣት ሁሴን ባቶ ይባላል። በደምበል ሐይቅ ጥምቀት በዓል ላይ በአስተባባሪነት በየዓመቱ ይሳተፋል።

ወጣቱ የእስልምና እምነት ተከታይ ቢሆንም በዓሉ የፍቅርና የአንድነትና በመሆኑ እዚህ ቦታ ላይ መገኘቱን ገልጾልናል።

ጥምቀት ከኢትዮጵያ አልፎ የዓለም ቅርስ የሆነ በዓል ስለሆነ በየዓመቱ በዓሉ ላይ በአስተባባሪነት እሳተፋለሁ ብሏል።

ሁላችንም በዓሉን በፍቅርና በአንድነት ልንጠብቀው፣ ልንንከባከበውና ልናከብረው ይገባል ብሏል።

#ባቱ #ጥምቀት #ቱሪዝም #የዓለምቅርስ

በፋንታነሽ ክንዴ

ጥር 11 ቀን 2017 ዓም
6👍4👏1
ሁላችንም በፍቅርና በአንድነት በመቆም ለሀገር ሰላምና እድገት የሚጠበቅብንን ልንወጣ ይገባል
- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
*****
(ኢ ፕ ድ)
ሁላችንም በፍቅርና በአንድነት በመቆም ለሀገር ሰላም እና እድገት የሚጠበቅብንን ሃላፊነት ልንወጣ ይገባል ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ገለጹ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአደባባይ ከምታከብራቸው ሃይማኖቶታዊ በዓላት መካከል ጥምቀት አንዱ ነው። በአዲስ አበባም በጃንሜዳ የጥምቀት በአል በልዩ ልዩ ሀይማኖታዊ ክንዋኔዎች በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በመላው ሀገሪቱ የጥምቀትን በዓል እያከበሩ ለሚገኙ ምዕምናን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የሰው ልጅ ዘላቂ ሕይወትን መቀዳጀት የሚችለው ፈርሃ እግዚአብሄርን መላበስ ሲችል ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በአሁኑ ጊዜ ፈጣሪ ከሰዎች የሚጠብቀውን መልካም ስብእናዎች ከመላበስ አኳያ የሚስተዋሉ ችግሮች የሰው ልጅን ለአደጋ ሲያጋልጡ ማስተዋል እየተለመደ መምጣቱን ጠቅሰው፤ ሁሉም ቆም ብሎ ስለሰላም ማሰብ ይኖርበታል ብለዋል።

ሁሉም በፍቅርና በአብሮነት በመቆም ለሀገር ሰላም እና እድገት የሚጠበቅበትን ሃላፊነት መወጣት እንዳለበት ነው የገለጹት።

ህብረተሰቡ ፈጣሪ የሰጠውን ጸጋ በመጠቀም እርስ በእርስ በመተሳሰብና በአብሮነት ለሀገር ሰላም እና እድገት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን መቅረፍ ይኖርበታል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

#ጥምቀት
👍133👏2
የአረንጓዴ ዓሻራ ስራችን በፍራፍሬ እጅጉን ተስፋ ሰጪ ጅማሮ ያሳያል"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍8
"በሕገ-ወጥ ድርጊት በሚሳተፉ አካላት ላይ የሚወሰደው ርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል" - የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት
***
(ኢ ፕ ድ)

የማጭበርበር የወንጀል ድርጊቶችን ጨምሮ የተለያዩ የፋይናንስ ወንጀሎች ውስጥ የተሳተፉ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ፡፡

አገልግሎቱ በሰጠው መግለጫ÷ የፋይናንስ ወንጀሎች በሀገር ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ዘርፈ ብዙ እና ከፍተኛ በመሆኑ ኢትዮጵያ ወንጀሎቹን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተለያዩ ህጎችን አውጥታ በመተግባር እንደምትገኝም አስገንዝቧል፡፡

ለአብነትም በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ የማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 780/2005 እየተተገበረ መሆኑ ይታወሳል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ቀድሞ በተለያዩ ህጎች ውስጥ ተበታትነው የሚገኙ የህግ ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ ራሱን የቻለ የንብረት ማስመለስ አዋጅ በቅርቡ መጽደቁን አስታውሷል፡፡

የንብረት ማስመለስ አዋጁም ሆነ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጠጠር የወጣው አዋጅ ዓላማ የፋይናንስ ወንጀሎች አትራፊ አለመሆናቸውን በማረጋገጥ በሀገር ላይ የሚያደርሰው ሁሉን አቀፍ አደጋ መግታት ነው ብሏል፡፡

በሌላ በኩል ለጤናማ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ምቹ መደላድል እንደሚፈጥርም ነው ያስረዳው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ ግለሰቦች ህጎችን ለማደናገሪያነት በመጠቀም እንዲሁም የተለያዩ ተቋማትን አካላትን ስም በመጥቀስ በማጭበርበር እና በማስፈራራት ገንዘብ ለማግኘት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸው ክትትል በማድረግ የተደረሰበት መሆኑን ገልጿል።

በዚህም በተደራጀ አግባብ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት ውስጥ 3 ግለሰቦች ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም እጅ ከፍንጅ ተይዘው ጉዳዩ በምርመራ ላይ ይገኛሉ ብሏል፡፡ ሌሎችንም በቁጥጥር ስራ ለማዋል እየተሰራ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡

አገልግሎቱ ከራሱ ምንጮችና ከጥቆማ በሚደርሱት መረጃዎች መሰረት የማጭበርበር የወንጀል ድርጊቶችን ጨምሮ የተለያዩ የፋይናንስ ወንጀሎች ድርጊት ውስጥ የተሳተፉ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል ብሏል።

በርካታ ጉዳዮችም በህግ ተይዘው ይገኛሉ ያለው አገልግሎቱ የወንጀል ድርጊት ፈጻሚዎች የህግ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ አገልግሎቱ የሚወስዳቸውን ርምጃዎች የበለጠ አጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።

ህብረተሰቡም ማጭበርበርን ጨምሮ ሌሎች የፋይናንስ ወንጀል በመፈጸም የሚገኝን ገንዘብ ህጋዊ ለማስመሰል የሚፈጸሙ ድርጊቶችን ሲመለከት በ9796 ነፃ ስልክ ለፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት በመደወል ጥቆማ በመስጠት የተለመደ ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

ጥር 12 ቀን 2017 ዓም
👍101
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍2
ባለፉት ስድስት ወራት ከቡና 908 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለፀ
****
(ኢ ፕ ድ)

ባለፉት ስድስት ወራት ከቡና ወጪ ንግድ 908 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ የቡናና ሻይ ባለስልጣን አሰታወቀ።

የስድስት ወራትን አፈጻጸምአሰመልክተው መግለጫ የሰጡት የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ኡመር እንደገለጹት፤ የቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ምርትን በማሻሻል የውጭ ምንዛሪ ግኝት የማሳደግ ስራ ተሠርቷል።

አሠራርን በማሻሻል ከቡና የሚገኘው ገቢ እያደገ ነው ያሉት አቶ ሻፊ ኡመር፣በ2017 400 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት እቅድ ተይዞ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ባለፈው ስድስት ወር ከ204 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለውጭ ገበያ በማቅረብ 908 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።

ከ2017 እቅድ አንፃርና ከባለፈው ተመሣሣይ አመት ጋር ሲነፃፀር ትልቅ ብልጫ እንዳለው ገልፀዋል።

በሞገስ ጸጋዬ

ጥር 12 ቀን 2017 ዓም
👍8
ጥምቀትና ቃና ዘገሊላ በዓላት በድምቀት ተከብረው መጠናቀቃቸውን የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል አስታወቀ
******
(ኢ ፕ ድ)

የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ ካስመዘገበቻቸው ከማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ በሰላም መጠናቀቁን አስታውቋል።

በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት የተከበረው የቃና ዘገሊላ በዓልም በሰላም መከበሩን ጨምሮ ገልጿል።

በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር የበኩላቸውን ድርሻ ላበረከቱት ለመላው የሀገራችን ሕዝብ፣ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለምዕመናን፣ ለሰላም ሠራዊት አባላት እና ለበዓሉ አስተባባሪዎች እንዲሁም የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት ለተወጡት የፀጥታ ተቋማት አመራርና አባላት የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል በመግለጫው ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል።

ጥር 12 ቀን 2017 ዓም
👍7👌1
በሀረሪ ክልል ከ13ሺህ ሊትር በላይ በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ነዳጅ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ
*******
(ኢ ፕ ድ)

በሀረሪ ክልል ከ13 ሺህ 480 ሊትር ነዳጅ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን እንዳሉት በክልሉ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትን ለማስቆም በአንድ ወራት በተሰራው ስራ በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 13ሺ 480 ሊትር ነዳጅ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ነዳጁ በቁጥጥር ስር የዋለው በኬላዎች ላይ በተደረገ ፍተሻና ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በሕገወጥ መንገድ በቤት ውስጥ ተከማችቶ የተገኘ መሆኑን ገልጸዋል።

በመኖሪያ ቤታቸው ደብቀው የተገኙ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን ጠቅሰዋል።

መንግስት ከፍተኛ በጀት መድቦ የሚያስገባው ነዳጅ ለታለመለት አላማ ሊውል ይገባል ያሉት ኮሚሽነሩ በህገወጥ ግብይት በሚሳተፉ አካላት ላይ በቀጣይም የተጠናከረ ክትትል በማድረግ አስተማሪ የሆነ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል።

በቀጣይም ሕገ ወጥ ነዳጅን ጨምሮ ሌሎች ሕገ ወጥ ተግባራትን ለመከላከል የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ማህበረሰብ ሕገወጥ የነዳጅ ግብይትን ሲመለከት በአካባቢው ለፖሊስ ጽ/ቤት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

ጥር 12 ቀን 2017 ዓም
👍3
ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሐላ ፈጸሙ
********
(ኢ ፕ ድ)
ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል፡፡

በቃለ መሐላ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሀገሪቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንቶች፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ የተለያዩ የዓለም ሀገራት የቀድሞና የአሁን መሪዎችን ጨምሮ ከ500 በላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ኅዳር ወር በተካሄደው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን ማሸነፋቸው ይታወሳል።

ጥር 12 ቀን 2017 ዓም
👍11