Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ባለፉት ስድስት ወራት 202 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶችን መሳብ ተችሏል
**
(
ኢ ፕ ድ)
ባለፉት ስድስት ወራት 202 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶችን መሳብ መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ ።

አቶ መላኩ እንደገለፁት ኢትዮጵያ አሁን ላይ ባላት መልካም የውጪ ግንኙነትና የብሪክስ አባል ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ኢንቨስትመንት የመሳብ አቅሟ እየጨመረ መጥቷል።

በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት 202 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶችን መሳብ ተችሏል። ከዚህም ከ49 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያሰመዘገቡ የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ወደ ስራ ከገባ ጀምሮ በአምራች ኢንዱስትሪው ላይ የተንሰራፉትን ችግሮች በቅንጅትና ስትራቴጂካዊ በሆነ መልኩ በመፍታት ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት አበረታች ውጤት አምጥቷል።

በተለይም ተግባራዊ የሆነው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ተኪ ምርትና የኤክስፖርት ምርቶችን በተፈለገው መጠንና ጥራት እንዲመረት በማስቻል በኢኮኖሚው ውስጥ ሊፈጠር የሚችለውን ጫና ከመቀነስ አልፎ ሀገራዊ ምርትን እንዲያሳድግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

መንግስት ባለፉት ሶስት ዓመታት ያደረጋቸው የፖሊሲ ማሻሻያዎች በኢንዱስትሪ ዘርፉ ትልቅ እድል ነው። የኑሮ ውድነትን የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ከኢኮኖሚ ማሻሻያው ባለፈ የምርት መጠንን ማሳደግ አስፈላጊ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በዳግማዊት አበበ

ጥር 16 ቀን 2017 ዓም

#ኢትዮጵያ_ታምርት #አምራች_ኢንዱስትሪ #ኢንቨስትመንት #ብሪክስ
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው ከኢፕድ ጋር በነበራቸው ቆይታ ያነሷቸው ነጥቦች‼️

👉ፋሲለደስ ለዘመናት የተረሳ ቦታ ነበር፣ አሁን ግን ብርሃን አይቷል፣

👉 ዕድሳቱ የተከናወነው ታሪኩን በሚመጥን መልኩ ነው፣

👉 ዕድሳቱ እየጠፋ ያለውን ታሪክ መመለስ አስችሏል፣

👉 ዕድሳቱና የኮርደር ልማቱ የቱሪስት ፍሰት በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር አድርጓል፣

👉 የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር መፅሐፍ ሽያጭ ለዕድሳቱ እንዲውል ተደርጓል፣

#መደመር #ጎንደር #ፋሲለደስ #ቱሪዝም #የቅርሶች_ዕድሳት
👍6
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍3
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዳውሮ ዞን የተገነባውን የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካን መረቁ
******
(ኢ ፕ ድ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የተገነባውን የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳስታወቁት በዛሬው ዕለት በዳውሮ ዞን የተገነባውን የኢቲ ማዕድን ልማት አ.ማ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ መርቀን ስራ አስጀምረናል ብለዋል።

ፋብሪካው በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የድንጋይ ከሰል ምርት ከማሻሻል ባሻገር ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል እንደፈጠረም አስገንዝበዋል፡፡
ጥር 16 ቀን 2017 ዓም
👍151👏1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን በተገነባው ኢቲ ማዕድን ልማት አ.ማ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ ያደረጉት ጉብኝት‼️
ኢትዮጵያ ለታንዛኒያ 100 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ታከናውናለች

👉 የሦስትዮሽ የኃይል ሽያጭ ሥምምነት ተፈረመ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ  ኃይል፣ የታንዛኒያ የኤሌክትሪክ አቅራቢ ኩባንያና የኬንያ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ኩባንያ ሲያካሂዱት የቆዩትን የሦስትዮሽ የኃይል ሽያጭ ድርድር አጠናቀው ከስምምነት ላይ ደረሱ።

ስምምነቱ በኤሌክትሪክ ሽያጭ የህግ፣ የኮሜርሻልና የቴክኒክ ጉዳዮች ላይ መሠረት ያደረገ እንደሆነም ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ከታንዛኒያ ጋር የኃይል ሽያጭ፤ ኬንያ ከታንዛንያ ጋር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር የኪራይ ውል ስምምነት ተፈራርመዋል።

የኃይል ሽያጭ ሥምምነቱ በሀገራቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ፀድቆ ከሚያዝያ 2017 ዓም ጀምሮ ይተገበራል ተብሏል።

በሥምምነቱ መሠረት ኢትዮጵያ ለታንዛኒያ 100 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ታከናውናለች።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የህግ መምሪያ ዳይሬክተር አቶ መርክነህ ይገዙ የሦስትዮሽ ሥምምነቱ ከኃይል ሽያጭ ባለፈ ለቀጣናዊ የንግድና ኢኮኖሚ ትስስር ፋይዳው የጎላ ነውም ብለዋል።

የሦስትዮሽ ሥምምነቱ ኢትዮጵያ በኬንያ በኩል ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ለማከናወን የሚያስችላትን መብት የሚሰጣት መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ ለሦስትዮሽ ድርድሩ ሴኬት ምስጋና አቅርበዋል።

የታንዛኒያ የኤሌክትሪክ አቅራቢ ኩባንያ የዕቅድ፣ ምርምር እና ኢንቨስትመንት ምክትል ዳይሬክተር ሚስስ ሬንታ ንድጌ ድርድሩ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ እንዳስደሰታቸው ገልፀው ተቋማቱ ለተግባራዊነቱ እንዲሰሩ መጠየቃቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ ያመለክታል።

ጥር 16 ቀን 2017 ዓም
👍12👎3👏1