ሥራ ፈላጊ ነዎት❓
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
🥰1
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
በሰሜን ተራሮች የሚገኙ የዋልያዎች ቁጥር ወደ 300 መውረዱን የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አሰታወቀ 👉 ብዝሃ ሕይወትና የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎችን ለመንከባከብ እስከ 300 ሚሊዮን ብር ያሰፈልጋል ******* (ኢ ፕ ድ) በሰሜን ተራሮች የብርቅዬ ዋልያዎች ቁጥር ከዚህ በፊት ከነበረው ተመናምኖ ወደ 300 ዝቅ ማለቱን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አሰታወቀ።
በሰሜን ተራሮች የሚገኙ የዋልያዎች ቁጥር ወደ 300 መውረዱን የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አሰታወቀ
👉 ብዝሃ ሕይወትና የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎችን ለመንከባከብ እስከ 300 ሚሊዮን ብር ያሰፈልጋል
*******
(ኢ ፕ ድ)
በሰሜን ተራሮች የብርቅዬ ዋልያዎች ቁጥር ከዚህ በፊት ከነበረው ተመናምኖ ወደ 300 ዝቅ ማለቱን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አሰታወቀ።
የዱር እንስሳት ልማት እና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኩማራ ዋቅጅራ ለኢፕድ እንደገለፁት፤ በሰሜን ተራሮች የብርቅዬ ዋልያዎች ቁጥር ከዚህ በፊት አደጋ ላይ መውደቁን ተከትሎ በተሠራ የእንክብካቤ ሥራ የዋልያዎቹ ቁጥር አንድ ሺህ መድረስ ችሎ ነበር ብለዋል።
በሰሜኑ ክፍል ካለው የፀጥታ ችግር ሳቢያ የቁጥጥር መላላት፣ የእሳት አደጋና የሕገወጥ አደኖች መበራከት አንድ ሺህ መድረስ ችሎ የነበረው የሰሜን ተራሮች የዋልያዎች ቁጥር ተመናምኖ ወደ 300 መውረዱን ገልጸዋል።
እአአ በ1973 ሀገራት ቁጥራቸው እየተመናመኑ የሚገኙ እንስሳትና ዕፅዋትን ከጥፋት ለመታደግ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካኝነት "ሳይተስ" የሚባል ስምምነት አድርገዋል፤ ስምምነቱ ዓለም አቀፍ ንግድን የሚቆጣጠር አሠራር ነው። ኢትዮጵያም ከ1989 ጀምሮ የስምምነቱ አካል ሆናለች።
ከስምምነቱ አስቀድሞ በርካታ የእንስሳትና እፅዋት ዝርያዎች ለዓለም አቀፍ ንግድ ይውሉ ነበር። አብዛኞቹም ለመጥፋት የተቃረቡበት ወቅት ነበር የሚሉት አቶ ኩመራ፤ አሁን ላይ 38 ሺህ የሚደርሱ ዕፅዋትና የዱር እንስሳት ዓለም አቀፍ የንግድ ቁጥጥር እንደሚደረግባቸው አመላክተዋል።
የብዝኃ ሕይወትና የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎችን ለመንከባከብ እስከ 300 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግና ይህን የፋይናንስ ክፍተት መሙላት እንደሚገባ ገልጸዋል። https://press.et/?p=147765

👍2👏1😁1
ለኢትዮ ፌሪስ ጣና የሀገር ውስጥ የውኃ ትራንስፖርት የተገዙት ሁለት ዘመናዊ ጀልባዎች እየገቡ ነው
******
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ለኢትዮ ፌሪስ ጣና የሀገር ውስጥ የውሃ ትራንስፖርት እንዲያገለግሉ የተገዙት ሁለት ዘመናዊ ጀልባዎች ከጅቡቲ ወደብ ተጭነው ወደ ሀገር ቤት በማምራት ላይ ናቸው።
ጣና ነሽ ፪ የተሰኘችው ዘመናዊ የህዝብ ትራንስፖርት ጀልባ 38ሜ እርዝመት እንዳላት እና በአንድ ግዜ 188 ሰዎችን የመጫን አቅም እንዳላት መዘገቡ ይታወሳል።
ሌላኛዋ መለስተኛ ፈጣን ቃኝ ጀልባ ዘመናዊ የሰው ማጓጓዣና የመዝናኛ ጀልባ እንደሆነች የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መረጃ ያመለክታል።
መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓም

👍7👏2
የአፍሪካ ህብረት በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚደረጉ ጥረቶችን እንደሚደግፍ ገለጸ
***
(ኢ ፕ ድ)
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት የሚደረጉ ጥረቶችን እንደሚደግፍ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ የሱፍ ገለጹ።
ሊቀመንበሩ የአንጎላ ፕሬዝዳንት እና የወቅቱ የህብረቱ ሊቀመንበር ጆአኦ ሎሬንሶ ኮንካልቬስ በሉዋንዳ የሰላም ሂደት በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል ያለውን ግጭት ለመፍታት እያደረጉት ላለው ጥረት እውቅና ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንት ሎሬንሶ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው ውጥረት እንዲረግብ፣ ውይይቶች እንዲደረጉና የጋራ መተማመን እንዲፈጠር ቀጣይነት ባለው መልኩ እያደረጉት ያለውን ውይይትና ቁርጠኝነት አድንቀዋል።
በአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የእርቅ ጥረቶች ግንባር ቀደም ሚና በመወጣት ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ እንዲመጣ ተምሳሌታዊ የአመራር ቁርጠኝነት አሳይቷል ሲሉ ሊቀመንበሩ ገልጸዋል።
ዩሱፍ የሉዋንዳ የሰላም ሂደቱ ለውይይት ምቹ ሁኔታ የፈጠረ እና ለቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተሳትፎ በር የከፈተ መልካም አጋጣሚ እንደሆነም ተናግረዋል።
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የሚያስችል መድረክ ፈጥሯል።
የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኬዲ እና የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ያሳዩትን ቁርጠኝነትም አድንቀዋል።
አፍሪካ የሚያገጥሟት ችግሮች በአፍሪካ መር የመፍትሄ አማራጮች መፈታት አለባቸው ያሉት ሊቀ መንበሩ በዚህ ረገድም የአፍሪካ ህብረት በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት የሚያመጡ ጥረቶችን እንደሚደግፍ ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት ሰላም እና ፀጥታን ጨምሮ አፍሪካ እያጋጠሟት ያሉ ፈተናዎች በአፍሪካውያን መሪነት እና ባለቤትነት እንዲፈቱ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንደሚወጣ መግለጻቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

👍12🥰1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነባውንና ከማሳ ወደ ገበታ ሙሉ የምግብ ምርት ሰንሰለት የሚያጎላውን ዘመናዊ የዳቦ ፋብሪካም መርቀዋል።
ፋብሪካው በተገጠሙለት ዘመናዊ ማሽኖች 420 ኩንታል ስንዴ በቀን መፍጨት ይችላል። 300 ሺህ ዳቦዎችንም በ24 ሰዓታት ማምረት ይችላል።
- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

👍9👏2😁2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው አፋር ክልል የግብርና እና የኢንደስትሪ አቅሞች የሚያሳዩ ቁልፍ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
ጉብኝታቸው ከስድስት ወራት በፊት ምርት የጀመረውንና 15 ቶን በሰዓት የሚያመርተውን የአዮዳይዝድ ጨው ማምረቻ፤ የበጋ ስንዴ ልማት ሥራና የአይሮላፍ መኖ ባንክ ልማት ማዕከልን ጎብኝተዋል።
በክልሉ ስላለው የግብርና አቅም የነበረውን የተሳሳተ ምልከታ በማሸነፍ በመስኖ የለማ የስንዴ ምርት መገኘት ችሏል።
- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
መጋቢት 13 ቀን 2017 ዓም

👍12👏2