Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍4👏1
የሀሚድ ድልድይ ለትራፊክ አገልግሎት ክፍት ተደረገ
**
(ኢ ፕ ድ)

የወልዲያ - ሮቢት መንገድ የሀሚድ ወንዝ የብረት ድልድይ ጥገና ተጠናቆ ለትራፊክ አገልግሎት ክፍት ተደርጓል።

በኮንክሪት ለመገንባትም ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን በዚህ ዓመት መጨረሻ ግንባታው እንደሚጀመር ተገልጿል።

ድልድዩ ከዚህ ቀደም ከተፈቀደው ክብደት በላይ በጫነ ከባድ ተሽከርካሪ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር ይታወቃል።

በወቅቱ ተለዋጭ መንገድ በማዘጋጀት ተሽከርካሪዎች እንዲገለገሉ ማድረግ ተችሏል።

የብረት ድልድዩን መልሶ ለመገንባትም በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት፣ የድልድይና ስትራክቸር ዳይሬክቶሬት ባደረጉት ጥገና ለትራንስፖርት እንቅስቃሴ ክፍት ማድረግ ተችሏል።

45 ነጥብ 7 ሜትር ርዝመት ያለው ይኸው ድልድዩ አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ክፍት ተደርጎ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

አሽከርካሪዎች በሕግ በተፈቀደው የጭነት ልክ በመጫን እንዲገለገሉ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አሳስቧል።

መጋቢት 13 ቀን 2017 ዓም
👍10👏2
ኢፍጣር በአፋር
#PMOEthiopia
👏13👍4
ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የፍጻሜ ውድድሮች

በቻይና ናንጂንግ ከተማ እየተካሄደ ባለው 20ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው ሁለት የፍጻሜ ውድድሮች ዛሬ ይካሄዳሉ።

ከቀኑ 9 ሰዓት ከ28 ላይ በሴቶች የ1500 ሜትር ፍጻሜ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ እና አትሌት ድርቤ ወልተጂ ይወዳደራሉ።

ከቀኑ 9 ሰዓት ከ54 በ800 ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር አትሌት ጽጌ ዱጉማ እና አትሌት ንግስት ጌታቸው ይሳተፋሉ።

ኢትዮጵያ እስከ አሁን በሻምፒዮናው በአትሌት ፍሬወይኒ ኃይሌ በ3000 ሜትር ሴቶች ወርቅ እና በወንዶች 3000 ሜትር በአትሌት በሪሁ አረጋዊ የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።

#ቻይና #ስፖርት
👍6👏2😁1