Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ወላጆች ለትምህርት ቤቶች ዕድሳት ከ40 ቢሊዮን ብር በላይ በዓይነትና በገንዘብ ድጋፍ አደረጉ

👉 ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ 30 ሺህ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ተሰርተዋል

👉 ባለፉት ሦስት ዓመታት የተመዘገበው አነስተኛ ውጤት እንደ ሀገር የደረሰንበትን ውድቅት አሳይቶናል፣
*******
(ኢ ፕ ድ)

ወላጆች የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል "ትምህርት ለትውልድ" በሚል ሀሳብ ትምህርት ቤቶችን ለማሻሻል በተደረገ ንቅናቄ 40 ቢሊዮን ብር በዓይነትና በገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ።

ወላጆች በትምህርት ውጤት መስተካከል ላይ የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።

በዚህም 7 ሺህ 500 አዲስ ትምህርት ቤቶች፤ ባለፉት ሁለት አመታት ብቻ 30 ሺህ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ተሰርተዋል፡፡ ነባር 22 ሺህ ትምህርት ቤቶች ተጠግነዋል፡፡ ቤተሰብ ገንዘብ ከማዋጣት አልፎ የልጆቹን የትምህርት ውሎ መከታተል ሲጀምር የተማሪዎች ውጤት የበለጠ እየተሻሻለ ይሄዳል ብለዋል፡፡

ባለፉት ሦስት ዓመታት የተመዘገበው አነስተኛ ውጤት እንደ ሀገር የደረሰንበትን ውድቅት አሳይቶናል፡፡ ውጤቱን የማስተካከል ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ፤ ተማሪዎች ማለፍ የሚቻለው በስራ መሆኑን ሲገነዘቡ ይሰተካከላል።

ትምህርት በአቋራጭና በስርቆት አልፋለው ብሎ በሚያስብ ተማሪና ማህበረሰብ ውስጥ አስተማሪዎችን ብታስተካክል የትም አትደርስም ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ እውነታ ከዚህ የተለየ አለመሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ ባለፈው ዓመት 5 ነጥብ 2 በመቶ ውጤት የተመዘገበ ሲሆን የተወሰነ ለውጥ መጥቷል፡፡

ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ተጨማሪ ሰዓት የድጋፍ ትምህርት መስጠት በመጀመራቸው የተወሰነ የውጤት መሻሻል ታይቷል፡፡ በስርዓት ማስተማር በመጀመራቸው ያለፈው አመት ውጤት መሻሻል ችሏል ብለዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ውጤት ዝቅተኛ የመሆን ምክንያቶችን አስመልክቶ ያጠናውን ጥናት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ማቅረቡ ይታወሳል።

በሞገስ ጸጋዬ

መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓም
👍7👏1
ፌደራል ፖሊስ ለዓባይ ግድብ ከ254 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ
***
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለዓባይ ግድብ ግንባታ ከ254 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን አሰታወቀ።

ፌደራል ፖሊስ ቃል-አቀባይ ረዳት ኮሚሽነር መጎስ ቸኮል እንደገለፁት፣ የታላቁን ሕዳሴ ግድብ ደህንነት ከመጠበቅ ባሻገር በቦንድ ግዥ ከ254 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ አሰባስበው ገቢ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ፌደራል ፖሊስ በዘመናዊ ጀልባ የታገዘ የተጠናከረ ጥበቃ ለማድረግ ፖስታል ጋርድ ፖሊስ አደራጅቶ ወደ ተግባር ለመግባት ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓም
👍84😁2
ኢትዮጵያና ኡጋንዳ በተለያዩ መስኮች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት አደረጉ
******
‎(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያና ኡጋንዳ በንግድ፣ በእንስሳትና አሳ ሀብት፣ በሲቪል አቪዬሽን፣ በአየር ትራንስፖርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በኢነርጂ፣ በውሃ ሀብት ልማትና አስተዳደርና በሌሎች ስምንት ዘርፎች በጋራ ለመስራት ተስማሙ።

4ኛው የኢትዮ-ዩጋንዳ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ።

‎በስምምነቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) እንደገለፁት፤ ስብሰባው በሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለሙያዎች ደረጃ ሲካሄድ ቆይቷል። የጋራ ጥቅምና ፍላጎት የሚያንጸባርቅ፤ በቀጣናው ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በሚያስችሉ በርካታ ጉዳዮች ላይ ምክክር መደረጉን ተናግረዋል።

‎በሁለቱ ሀገራት መካከል ከዚህ ቀደም የተደረጉ ስምምነቶች ያሉበት ደረጃ መገምገሙን ጠቁመው፤ በፖለቲካ፣ በፀጥታ፣ ኢኮኖሚ፣ ኢንቨስትመንት፣ አቪዬሽንና በሌሎችም ዘርፎች ከስምምነት መደረሱን ገልጸዋል።

‎ስምምነቱ በቀጣይም በሁለቱን ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር ነው ብለዋል።

‎የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጀነራል ኦዶንጎ ጄጄ አቡበከር በበኩላቸው፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከርና ስምምነቶችን ለመፈፀም ኡጋንዳ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

የስምምነቱን ተግባራዊነት እንደሚከታተሉ ጠቅሰው ስብሰባ እንዲሳካ የኢትዮጵያ መንግስት ላደረገው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርቧል።

5ኛው የኢትዮ-ዩጋንዳ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በኡጋንዳ ካምፓላ ከተማ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

‎በቃልኪዳን አሳዬ

መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓም
👍1
#ሐረር

የሹዋሊድ በዓል ከነገ ጀምሮ በሐረር በድምቀት ይከበራል

ሹዋሊድ የአብሮነት ዕሴት ጎልቶ የሚታይበት በዓል ነው። የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች በጋራ የሚያከብሩት በዓል ሲሆን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት በማይዳሰሱ ቅርስነት መመዝገቡ ይታወቃል።

መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓም
👍2
አቶ አደም ፋራህ ለሹዋሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
*****
(ኢ ፕ ድ)
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ለሹዋሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ አደም በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል ድልብ የሆኑ የማኅበራዊ እሴቶቻችንን በማጎልበት የማኅበራዊ ልማታችንን ማጠናከርና በሀገራችን ያሉ የቱሪዝም ፀጋዎችን በማልማት የብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ መገንባት ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።

በዚህ የለውጥ ዓመታት ጉዞ ውስጥ በበርካታ የአገራችን አካባቢዎች የሚገኙ የሕዝባችንን መልካም እሴቶች የሚያጠናክሩ ለመጪው ትውልድ የተሻለች ሀገር ለመገንባት የሚያስችሉ ባህሎቻችንና እሴቶቻችንን ለማጎልበት በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት በማይዳሰስ ቅርስነት በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የተመዘገበው የሸዋል ዒድ (ሹዋሊድ) ባህላዊ ክብረ በዓል አንዱ እንደሆነ ነው የገለጹት።

በመሆኑም ይህ በዓል በሐረሪ ክልል የቱሪዝም ዘርፉን ከማጎልበት አንፃር ጠቀሜታው የጎላ ነው። ሸዋሊድ ሐረር የምትታወቅበት የአብሮነትና የመቻቻል እሴትም ጎልቶ የሚታይበት የከተማዋ ነዋሪ የሆኑ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች በጋራ የሚሳተፉበት ባህላዊ ክብረ በዓል ነው ብለዋል።

በቀጣይ እንደ ብልፅግና ፓርቲ ባህላዊ ቅርሶቻችንና ሌሎች ድልብ ማኅበራዊ ሀብቶቻችን ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉና ለሀገራችን ተገቢውን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዲሰጡ ይበልጥ አበክረን መስራታችንን እንቀጥላለን ሲሉ አረጋግጠዋል።
👍42